አበበ ካሴ በእስር ቤት ድብደባ ተፈፀመበት
ነኅሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሽብር ወንጀል ተከሶ ቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኘው አበበ ካሴ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመበት ታወቀ አበበ ካሴ፣ በማእከላዊ እስር ቤት የሁሉም ጣቶቹ ጥፍሮች ተነቅለው፣ በዘር ፍሬው እና በመላ አካላቱ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞበት መረጃ ለማውጣት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ በመጨረሻ ቂሊንጦ እስር ቤት ከተወረወረ በሁዋላ፣ የደረሰበትን ችግር ሁሉ ዘርዝሮ …