ኢትዮጵያና ኬንያ ሶማሊያን ለመቀራመት መስማማታቸውን ዊኪሊክስ አጋለጠ
ሐምሌ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዊክሊክስ ባወጣው መረጃ ላይ የኢትዮያና የኬንያ ገዢዎች ሶማሊያን ለአራት ቦታ በመክፈል ለመቀራመት በሚስጥር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስነብቧል። ሶማሊያ ለም እና በማዕድን የበለጸገ ምድር ባለቤት በመሆንዋ የብዙ ሀገራትን ፍላጎትን ትስባለች።ዊክሊክስ ጅቡቲ ከሚገኘው የሳዑዲ አረቢያ ኤንባሲ መረጃውን እንዳገኘው ገልጿል።በአሁኑ ወቅት ብዙ አገራት በሶማሊያ ውስጥ ይገኛሉ፤የተወሰኑት በግፊት እንዲወጡ ተደርገዋል …