ሐምሌ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፍትህ ሚኒስቴር በሽብረተኝነት ክስ ለሚከሰሱ ጋዜጠኞችና የሃይማኖት መሪዎችና የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችና አባላት ጠበቃ በመሆን የሚታወቁትን አቶ ተማም አባ ቡልጉን የዲሲፒሊን ግደፈት ፈጽመዋል በሚል ለአንድ አመት ከ7 ወር አግዷቸዋል። መታገዳቸውን ከሚዲያ የሰሙ ጓደኞቻቸው እንደነገሩዋቸው የገለጹት አቶ ተማም፣ በህጉ ቢሆን ነሮ የእግድ ደብዳቤው ከሚዲያ በፊት ለእርሳቸው መድረስ ይገባው …

ሐምሌ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምንጮች እንደገለጹት የኢህአዴግ አባል የሆነችው ወ/ሮ አስቴር ስዩም የወረዳው የሴቶች ጉዳይ ሃላፊ፣ በቅርቡ ደግሞ በጎንደር ከተማ የጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅት ሃላፊ በመሆን ስትሰራ ቆይታለች። አስቴር የኢህአዴግ አባል ብትሆንም ከበላይ አካል የሚመጣውን ትእዛዝ ሁሉ እንደወረደ የማትቀበል እንደሆነችና በዚህም የተነሳ የተለያዩ ማስጠንቀቂያዎች ተሰጥቷት እንደነበር፣ ከስራም ታግዳ መቆየቷን እርሷን …

ሐምሌ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዘ ደይሊ ኔሽን የኢትዮጵያ ሰራዊት በታንክና በከባድ መሳሪያ ታግዞ በከተማዋ ውስጥ መታየቱን የአይን እማኞችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። ሰራዊቱ የተንቀሳቀሰው ከኢትዮጵያ መሆኑንም የገለጸው ጋዜጣው፣አልሸባብ የሚቆጣጠረውን የባርደሬ ግዛት ለማስለቀቅ ሳያቅድ እንዳልቀረ ገልጿል። የአፍሪካ ህብረት ከኢትዮጵያ ያገኘውን ጨምሮ ከ20 ሺ በላይ ሰራዊት በሶማሊያ ቢያሰማራም አልሸባብን ለመደምሰስ አልቻለም። ታጣቂ ሃይሉ …

ሐምሌ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሃኪንግ ቲም ለተባለ ኩባንያ 1 ሚሊዮን ዶላር በመክፈል የስለላ መሳሪያዎችን የገዛው በአብዛኛው በህወሃት አባላት የሚመራው የደህንነት መስሪያ ቤት፣ ከኩባንያው ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብቶ እንደነበርና ውዝግቡ ሳይፈታ መረጃው ይፋ መሆኑን ለህዝብ ይፋ ከሆነው መረጃ ለመረዳት ተችሎአል። ቢኒያም ተወልደ በተባለ የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ምሩቅ በኩል ግንኙነቱን የሚያደርገው የኢትዮጵያ የደህንነት …

ሐምሌ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጦር ሃይሎች ኢታማዦር ሹም ጄ/ል ሳሞራ የኑስ ፣ ጠ/ሚኒስትሩን ጨምሮ ከፍተኛ የኢህአዴግ የጦር አዛዦች በተገኙበት የወታደራዊ ጥቅል አቋማቸውን አቅርበዋል። በከፍተኛ ሚስጢር በተካሄደው ስብሰባ ላይ ፣ ጄ/ል ሳሞራ ” ጦራችን ከጊዜው ጋር እየዘመነ አይደለም፣ የታንኮቻችን አቅም ያረጀ ነው፣ ተዋጊ አውሮፕላኖቻችን ከገበያ የወጡ ናቸው፣ መቀየሪያ እቃዎቻቸው ( ስፔር …

ሐምሌ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከትናንት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የተጠናከረ ጥበቃ እያደረጉ ሲሆን፣ በርካታ ወጣቶችና የመንግስት ሰራተኞችም እየታፈሱ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በአዲስ አበባ የተቃዋሚ ሃይሎች ሰርገው ሳይገቡ ገብተዋል የሚል መረጃ ለደህንነት ክፍሉ እንደደረሰ የኢሳት ምንጮች ገልጸው፣ አሁኑ እንቅስቃሴም ከዚህ ጋር ሊያያዝ ይችላል ሲሉ ግምታቸውን …

ሐምሌ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን አማካሪ የሆኑት አቶ አንዱዓለም አዱኛ አሞኘ ከሀገር መኮብለላቸውን ሰንደቅ ጋዜጣ ዘግቧል። አቶ አንዱዓለም በ2007 ምርጫ በኢሕአዴግ ጽ/ቤት ለቅስቀሳ የሚሆኑ ሰነዶችን እንዲያዘጋጁ ከመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ተመድበው እንደነበር ጋዜጣው ዘግቧል። አቶ አንዱዓለም ከሀገር ከመኮብለላቸው በፊት ቀደም ብለው ባለቤታቸውንና ልጃቸውን ወደ አሜሪካ …

ሐምሌ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሰማያዊ ፓርቲ፣ የአንድነት እና የዓረና ትግራይ አመራሮች የሺዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታ፣ ሀብታሙ አያሌው እና ዳንኤል ሺበሽን ጨምሮ 10 ተከሳሾች ሐምሌ 1/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ ብይን ይሰጣል ተብሎ ቢጠበቅም፣ ብይኑን ሳይሰጥ ቀርቷል። ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህግ …

ሐምሌ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ወርሃዊ የዋጋ መረጃው በሰኔ ወር 2007 ዓ.ም የሸቀጦች ዋጋ ካለፈው ጋር ሲነጻጸር መጨመሩን ይፋ አደረገ፡፡ በኤጀንሲው መረጃ መሰረት በግንቦት ወር 9 ነጥብ 4 በመቶ የነበረው የዋጋ ግሽበት በሰኔ ወር ወደ 10 ነጥብ 4 በመቶ ከፍ ብሏል። በዚህም ምክንያት ኢህአዴግ መራሹ መንግስት የዋጋ ግሽበትን …

ሰኔ ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ ዛሬ ለፓርላማ አባሎች እንደተናገሩት የኤርትራ መንግስት አካባቢውን የማተራማስ አጀንዳውን ካላቆመ ፣ መንግስት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል ብለዋል። አቶ ሃይለማርያም ሻእቢያ ኢትዮጵያና ጅቡቲን ለማተራመስ እየሰራ ነው ሲሉ ከሰዋል። የኢትዮጵያን ህዝብ አስታውቀን እርምጃ እንወስዳለን ያሉት አቶ ሃይለማርያም፣ እስካሁንም ለደረሰብን ጥቃት ተመጣጣኝ እርምጃ ስንወስድ ቆይተናል ሲሉ አክለዋል። የአቶ …

ሰኔ ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊያ ፑትላንድ ራስ ገዝ ዋና ከተማ ጋሮው በከባድ መኪና ድንበር አቋርጠው ሲጓዙ የነበሩትን ሰማንያ ሁለት ሕገወጥ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችና የተሽከርካሪውን ሹፌር አብሮ መያዙን የፑትላንድ ፀጥታ ሹም ኃላፊ ተናግረዋል። በቅርብ ዓመታት ውስጥ ከአስር ሽህ በላይ አፍሪካዊያን ስደተኞች ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው አስተማማኝ ባልሆኑ ጀልባዎች በመሳፈር ባሕር አቋርጠው የተሻለ ኑሮ ፍለጋ …

ሰኔ ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዓለማቀፍ ታላላቅ የመገኛኛ ብዙሃን አውታሮች መነጋገሪያ ሆኖ የዘለቀው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን የመጐብኘት ውጥን አሜሪካ አምባገነን መንግስታትን ከመደገፍ የመነጨ በመሆኑ እምብዛም ትኩረት የሚሠጠው ጉዳይ አይደለም ብለዋል የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሣይንስ መምህር እና የመድረክ የፖለቲካ ማህበር አመራር ዶ/ር መረራ ጉዲና ´´አሜሪካ አምባገነኖችን የምትደግፍም …

ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፉት 3 ቀናት ወደ አረብ አገር እንወስዳችሁዋለን በሚል የተሰበሰቡ ወጣቶችን ወደ ወታደራዊ ካምፕ ለማጓጓዝ መሞከሩን ወጣቶች ተናግረዋል። ወጣቶች እንዳሉት ወደ አረብ አገራት ትሄዳላችሁ ተብለው ከተለያዩ ቦታዎች የተሰበሰቡ ወጣቶችን ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም እያጓጓዙ ሲሆን፣ አንዳንዶች መንገድ ላይ ጠፍተዋል። ካለፈው አመት ጀምሮ ወታደሮችን ለማሰልጠን ተደጋጋሚ ሙከራ ሲያደርግ …

ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኡስታዝ አቡበክር አህመድ የክስ መዝገብ የተከሰሱት 18 የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት በሙሉ ጥፋተኞች ሲባሉ የመጨረሻውን ውሳኔ ለመስጠት ፍርድ ቤት ለሃምሌ 27 ቀጠሮ ሰጠ። ከፍተኛው ፍርድ ቤት 4ኛው ወንጀል ችሎት በ አቶ አቡበከር አህመድ፣ አህመዲን ጀበል፣ ያሲን ኑሩ፣ ካሚል ሸምሱ፣ በድሩ ሁሴን፣ ሼህ መከተ ሙሄ መኮንን፣ …

ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘጋርድያን እንደዘገበው የተመድ የሰብአዊ መብቶች ካውንስል፣ ኢትዮጵያ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን፣ በአስቸኳይ አስፈላጊውን ካሳ በመክፈል እንድትለቃቸው ጠይቋል። የእስረኞችን ጉዳይ የሚከታተለው የተመድ የሰብአዊ መብት ካውንስል በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ በጭካኔ የተሞላ አካላዊ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንደተፈጸሙባቸው የሚያትቱ ተጨባጭ ማስረጃዎች እንዳሉት ለኢህአዴግ መንግስት በላከው 8 ገጽ ደብዳቤ ላይ ማስፈሩን …

ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በጋሞጎፋ ዞን ዘይሴ በሚባል ቀበሌ፣ ከ4 ቀናት በፊት አንድ ግለሰብ ከመሬት ጋር በተያያዘ በተፈጠረ አለመግባባት፣ የመሬት አስተዳደር ሃላፊውን ጨምሮ ሌሎች 3 የወረዳ ሹሞችን ገድሏል። ግለሰቡ በ2007 ምርጫ የተቃዋሚ አባሎችን ደግፈሃል በሚል የያዘውን መሬት እንዲለቅ የመሬት አስተዳዳር ሃላፊው በጠየቁት ጊዜ፣ ” ከአባቴ ያገኘሁትን የውርስ መሬት …

ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጣሊያን ውስጥ የሚገኘውና ሃኪንግ ቲም ” hacking team” በመባል የሚታወቀው ለደህንነትና ለስለላ የሚያስፈልጉ የኮምፒዩተር ሶፍት ዌሮችን የሚሸጠው ድርጅት፣ የራሱ መረጃዎች በሌሎች ሃይሎች የተዘረፈ ሲሆን፣ እስካሁን ይፋ በሆኑት መረጃዎችን ቢንያም ተወልደ የተባለ ኢትዮጵያዊ በብሄራዊ ስለላ ድርጅት ስም 1 ሚሊዮን ዶላር በአንድ ጊዜ መክፈሉን የወጣው ሰነድ ያመለክታል። ገንዘቡ …

ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ ግን ማስተባበያውን አጣጥለውታል። የፌዴራል ዋና ኦዲተር በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ ለፓርላማ ባቀረበው ሪፖርት፣ የማዕድን ሚኒስቴር የሼክ መሐመድ አል አሙዲ የወርቅ ልማት ኩባንያ ከሆነው ሚድሮክ ጐልድ በሕግ የተወሰነውን ገቢ ባለመሰብሰቡ፣ አገሪቱ ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ አጥታለች ማለቱ ይታወሳል። ዋና ኦዲተሩ አቶ ገመቹ …

ኢሳት ዜና (ሰኔ 28 2007  አም) የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን የአንድ አመት የእስር ቤት ቆይታ ሲከታተል የቆየው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የኢትዮጵያ መንግስት የካሳ ክፍያ በመፈጸም አቶ አንዳርጋቸውን በአስችኳይ እንዲፈታ ማሳሰቡን አለማቀፍ ሚዲያዎች ዘገቡ። ባለስምንት ገጽ ውሳኔውን በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን በኩል ለኢትዮጵያ ያቀረበው ድርጅቱ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በእስር ቤት ቆየታቸው ጭካኔ የተሞላበት ኢ-ሰባዊ ድርጊት እንደተፈጸመባቸው መግለጹን ዘ-ፋይናንሺያል ኤክስፕረስ …

ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአንድ ወር በላይ ተቋርጦ የነበረው የኢሳት ቴሌቪዥን አገልግሎት በአዲስ ሳተለይት ስራ ጀምሯል። ከኢህአዴግ መንግስት በሚደርስበት ከፍተኛ ጫና የተነሳ ስርጭቱ በተደጋጋሚ ሲቋረጥ የቆየው ኢሳት ቴሌቪዥን ኤ ኤም 44 በሚባል ሳተላይት የቴሌቪዥን ስርጭቱን ከትናንት ሰኔ 25፣ 2007 ዓም ጀምሮ እንደገና ጀምሯል። በአለማቀፍ የፕሬስ ድርጅቶች ሳይቀር ሃሳብን በማፈን የሚወነጀለው …

ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ የኢህአዴግ መንግስት የግል የጦር መሳሪያ የያዙ ዜጎች ህጋዊ ፈቃድ ከመንግስት በመውሰድ፣ የጦር መሳሪያቸውን እንደንብረት እንዲይዙ አዲስ መመሪያ በማውጣት፣ በተለያዩ አካባቢዎች ነዋሪዎች መሳሪያዎቻቸውን እያስመዘገቡ ፈቃድ ውሰደዋል። ይሁን እንጅ ገንዘብ እየከፈሉ ፈቃድ የወሰዱ ባለንብረቶች፣ በራሳቸው ገንዘብ የገዙትን መሳሪያ መሸጥ፣ መለወጥ ወይም ለሌላ ሰው ማውረስ እንደማይችሉ ተነግሯቸዋል። መሳሪያውን …

ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአንድ አመት በፊት የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት ወደ ስራ አሰማራችሁዋለሁ በሚል መንግስት ካሰበሰባቸው ከ2 ሺ 500 ያላነሱ ወጣቶች 1 ሺ 500 የሚሆኑት ስልጠናውን አጠናቀው በተለያዩ የመከላከያ ተቋማት ቢመደቡም፣ ቃል የተገባላቸው እና በተግባር የሚያዩት ነገር ባለመጣጣሙ ስራቸውን ጥለው መጥፋታቸውን ሰልጣኖች ተናግረዋል። አሚባራ በሚባለው አካባቢ የሚገኝ ጫካ መንጥረው ህንጻ …

ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት፣ የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም አደራጅ የሆነውን የወጣት ሳሙኤል አወቀን ገዳይ በ19 አመታት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል። ይሁን እንጅ ገዳይ ተብሎ የቀረበው አቶ ተቀበል ገዱ ለፍርድ ቤት የሰጠው ቃል እና ፖሊስ በወቅቱ የሰጠው መግለጫ ሊጣጣሙ አልቻሉም። ገዳይ ተብሎ የቀረበው ሰው ለፍርድ ቤቱ …

ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ሰበብ ታስራ ‹‹ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ በማወክ›› ወንጀል የተከሰሰችው ሜሮን አለማየሁ የ6 ወር እስር ተፈርዶባታል፡፡ ሜሮን አለማየሁ ሚያዝያ 14 በተጠራው ሰልፍ ላይ ‹‹ወያኔ ሌባ፣ መንግስት የለም፣ አትነሳም ወይ፣ የታረደው ወገን ያነተ አይደለም ወይ›› በሚል ሁከትና ብጥብጥ ፈጥራለች …

ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ የውጭ አገር ሥራ ስምሪት ረቂቅ አዋጅ ስምንተኛ ክፍል ያልደረሰ/ች ሠራተኛ ወደውጭ ሀገር መላክ የሚከለክል ሲሆን በሥራው የሚሰማሩ ኤጀንሲዎች ወደ 2 ሚሊየን ብር ወይም 100 ሺ ዶላር ለዋስትና ማስከበሪያ ካላስያዙ ወደስራ እንዳይገቡ ክልከላ አስቀመጠ፡፡ አሁን በስራ ላይ ያለውን አዋጅቁጥር 632/2001 ሙሉ በሙሉ የሚሰርዘው ይህ ረቂቅ አዋጅ …

ኢሳት ዜና (ሰኔ 26 2007) በቅርቡ በምስራቅ ጎጃም ዞን በወጣት እጩ የፓርላማ ተወዳዳሪ ላይ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ በርካታ ሰዎች በፖለቲካ አመለካከታቸው በመታሰር ላይ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጡ ። በዞኑ የሚገኙ አርሶ አደሮች ከ 15 አምት በፊት ያልከፈላቹት የማዳበሪያ እዳ አለባችሁ እየተባሉ በጅምላ መታሰራቸውን የተናገሩት እማኞች ገበሬዎቹ በሞት የተላዩዋቸውን ዘመዶች እዳ ጭምር እንዲከፍሉ መገደዳቸውም ታውቋል። …

ሰኔ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በአማራ ክልል ስፖርት ኮሚሽን በድንገት በተጠራው ስብሰባ ኮሚሽነር ያየህ አዲስ ፣ የብሄራዊ ሊጉ ጨዋታዎች በሚካሄዱበት ከተሞች ከምርጫ 2007 በኋላ የሚታዩ የስፖርታዊ “ጨዋነት ጉድለቶች” አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ተናግረዋል፡፡ ወቅቱ የምርጫ ውጤት ይፋ የሆነበት በመሆኑ በተለያዩ ስፖርታዊ ጨዋታዎች ላይ ልዩ ጥንቃቄ እንዲደረግም ተናግረዋል። ኮሚሽነር ያየህ ” …

ሰኔ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዶ/ር አዲሱ የምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ቢሆኑም ከህወሃት/ኢህአዴግ ቀጥተኛ መመሪያ በመቀበልና በማስፈጸም ረገድ ቁልፍ ሰው መሆናቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በተለይ ተቃዋሚዎች እንዲዳከሙና ትንንሽ ልዩነቶቻቸውን በማጦዝ ፓርቲዎች እንዲናጉና እንዲፈርሱ ከኢህአዴግ ጋር እየተናበቡ የሚሰሩ ሲሆን ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚያቀርቡትንም አቤቱታ በማድበስበስ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡ የቦርዱ ሰብሳቢ ፕ/ር …

ሰኔ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአቶ አቡበክር አህመድ የክስ መዝገብ የተከሰሱት የኮሚቴው አባላት የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል በሚል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙስሊም ኢትዮጵያዊ በችሎቱ ቢታደምም፣ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የማሰማቱን ሂደት በድጋሜ ወደ ሰኞ አራዝሟል። ችሎቱ የአቃቢ ህግ መስክሮችን ቃል አንብቦ ከጨረሰ በሁዋላ ተከሳሾች ለፖሊስ ሰጡት ያለውን ቃል በንባብ አሰምቷል። የፊታችን ሰኞ የመጨረሻው …

ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት በድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት ላይ ሊሰጥ የነበረውን ፍርድ ያራዘመ ሲሆን፣ ፍርዱ ለምን እንደተራዘመ ግን በግልጽ የታወቀ ነገር የለም። በአቶ አቡበከር አህመድ መዝገብ 18 የኮሚቴው አባላት በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው የመጨረሻውን ፍርድ ለመስማት ችሎት የተገኙ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ የክሱን …

ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመከላከያ ሰራዊት ያወጣው አዲስ የቅጥር ማስታወቂያ ተቀባይነት አለማግኘቱን ከተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። በሰሜን ሸዋ ከሁለት ሳምንት በፊት የወጣውን የቅጥር ማስታወቂያ ተከትሎ ተመዝጋቢ በመጥፋቱ፣ የአካባቢው ባለስልጣናት የሚያደርጉት ጠፍቷቸዋል። በአርባምንጭ ደግሞ የኢህአዴግ ካድሬዎች በመኪና እየዞሩ ወጣቱ ለመከላከያ አባልነት እንዲመዘገብ እየቀሰቀሱ ነው። ይሁን እንጅ ለጥሪው ወጣቱ የሚሰጠው ምላሽ …

ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢህአዴግ መንግስት ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ በማንኛውም መልኩ የህግ ትምህርት በግል ተቋማት እንዳይሰጥ የከለከለ ሲሆን፣ የአቶ ደመቀ ከፊል ንብረት የሆነው ሚሸከን ኮሌጅ ግን ተማሪዎችን እያሰተማረ እንደሚገኝ መረጃዎች አመልክተዋል። ተመሳሳይ ድርጊት የፈፀሙ ኮሌጆች ቢዘጉም፣ ለሚሽከን ኮሌጅ ግን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነት ጥራት ኤጀንሲ ከማሰጠንቀቂያ ያለፈ ውሳኔ አልሰጠውም። የሚሽከን ኮሌጅ …

ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰኔ 19 ቀን 2007 ዓም ከጧቱ 1 ሰአት ላይ መድሃኒአለም በሚባል አካባቢ ሁለት መኪኖች ኮንትሮባንድ እቃ ጭነዋል በሚል ምክንያት ሲከተሉዋቸው የነበሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት በድንገት ተኩስ በመክፈታቸው አንደኛው መኪና መስመሩን ስቶ ከወጣ በሁዋላ በመገልበጡ 7 ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ሰዎች ደግሞ ተጎድተው ሆስፒታል ገብተዋል። …

ሰኔ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ዲያስፖራውን በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች ለመያዝ ያደረገው ተደጋጋሚ ጥረት መክሸፉን ተከትሎ ፣ የዲያስፖራውን ቀልብ ሊስቡ ይችላሉ ያላቸውን አዳዲስ ዘዴዎች እያሰላሰለ ነው። በቅርቡ በኢትዮጵያ በሚካሄደው የዲያስፖራ ሳምንት ዝግጅት ዙሪያ አስመልክቶ ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዲያስፖራ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በክልልና በፌደራል ደረጃ ከሚገኙ የዲያስፖራ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ሃላፊዎች …

ሰኔ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ምድብ ወንጀል አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ለመኢአድ አባላት መከላከያ ምስክር መሆን መቻል አለመቻላቸው ላይ ነገ ሰኔ 24፣ 2007 ዓ.ም ብይን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ በግንቦት ሰባት አባልነት የተከሰሱት 5 የመኢአድ አባላት ‹‹በአንዳርጋቸው ፅጌ አሰልጣኝነት የሽብር ተግባር ለመፈፀም ተንቀሳቅሳችኋል፡፡›› በሚል ክስ …

ሰኔ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለሚቀጥለው አምስት አመታት ይተገበራል ተብሎ በተዘጋጀ የሁለተኛ ዙር የ5 አመታት እቅድ ላይ በተዘጋጀ የመወያያ ሰነድ እንደተመለከተው ባለፉት ሶስት አመታት 2 ሺ 995 ፕሮጀክቶች ወደ አገር ውስጥ ገብተው ስኬታማ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ተሰርዘዋል። በአማራ ክልል በባህርዳር እንዲሁም በኦሮምያ ክልል አዳማ የተደረገውን የምክክር ጉባኤ አስመልከቶ የተዘጋጀው ሰነድ እንደሚያሳየው፣ በዚህ …

ሰኔ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ከ2003 እስከ 2005 ዓ.ም ድረስ የሳምባ ምች በሽታ የመጀመሪያው ገዳይ በሽታ የነበረ ሲሆን፣ ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ኤች አይ ቪ ኤድስ አንደኛ የአእምሮ ጭንቀት ደግሞ የሁለተኛ ደረጃን ይዘዋል። ኤ አይ ቪ ኤድስ በኢትዮጵያ እየቀነሰ መምጣቱ ቢነገርም፣ በሽታው አሁንም ቀዳሚ ገዳይ በሽታ ተብሎአል። የአእምሮ ጭንቀት ሁለተኛ ገዳይ …

ኢሳት ዜና (ሰኔ 23 2007) ሰሞኑን ፍርድ ቤት ከእስር እንዲፈቱ ወስኖላቸው ፖሊስ በድጋሚ ለእስር በዳረጋቸው አራት የፓርቲ አባላት ላይ አቃቢ ህግ ይግባኝ ጠየቀ። ተከሳሾች የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ ጉዳያቸው ከውጭ ሆነው ለመከታተል ጥያቄን ቢያቀርቡም ከሳሽ አቃቢ ህግ ተቃውሞን እንዳቀረበ ከሀገር ቤት የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ጉዳዩን ለማየት የተሰየሙት ዳኛ ተከሳሾች እስካሁን ድረስ በእስር ቤት ስለመቆየታቸው የሚያውቁት ነገር …

ኢሳት ዜና (ሰኔ 22 2007 ዓም) በሚቀጥለው ወር በኢትዮጵያ ጉብኝት የሚያደርጉት የአሜሪካ ፕሬዘዳንትን ጉዞን በመቃወም የፊታችን አርብ በዚህ በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ ከተማ በሚገኘው “ ሁዋይት ሀውስ ‘’ የተቃውሞ ሰልፍ መጠራቱን አዘጋጆቹ ገለጹ ። በዋሺንግተን ከተማ ዙሪያ በሚገኘው የወጣቶች ግብረ ሀይል የተዘጋጀው የተቃውሞ ሰልፍ ፕሬዘዳንት ኦባማ የሚያደርጉትን ጉዞ እንዲያስቡበትና እንዲሰርዙት የሚጠይቅ መሆኑ ታውቋል። ፕሬዘዳንቱ በቀጣዩ ወር …

ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ብአዴን እያስተዳደርኩት ነው በሚለው የአማራ ክልል የጀመራቸው የተለያዩ ተቋማት ውጤት አልባ በመሆናቸው ብዙዎቹ እየፈረሱና ዜጎችን ለችግር እያደረጉ መሆኑን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል። የክልሉ ቴክኒክ እና ሙያ ኢንተርፕራይዝ እና የክልሉ ጥቃቅን እና አነሰተኛ ቢሮዎች በክልሉ የሚገኙ በሚልዮን የሚቆጠሩ ስራ አጦችን በተለያየ ሙያዎች በማሰልጠን የክልሉን የስራ አጥ ቁጥር …

ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስባ የሆነው መድረክ ባወጣው መግለጫ በ2007 ዓ ም በሀገራችን ተካሄደ የተባለው ምርጫ በሕግና ሥርዓት ያልተመራና በሕገ-መንግሥቱና በምርጫ ሕጎች የተደነገጉትን የነፃ፣ፍትሐዊና ታአማኒነት ያለው ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መርሖዎች በኃይል በተጣሱበት ሁኔታ የተፈጸመ በመሆኑ መድረክ የምርጫውን ሂደትም ሆነ ውጤት እንደማይቀበለው ገልጾ፣ ለዚህ አሁን ሀገራችን ለገባችበት አስቸጋሪ ሁኔታ …

ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግል ሠራተኞች የፕሮቪደንት ፈንድ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ ያለውን ገንዘብ ወደመንግስት በማስገባት ሠራተኞቹ በጡረታ እንዲታቀፉ በሚያስችል መልኩ የተደነገገው የግል ድርጅቶች የማህበራዊ ዋስትና አዋጅ ማሻሻያ በገጠመው ከባድ ተቃውሞ ምክንያት ለፓርላማው ሳይቀርብ በቋሚ ኮምቴዎች ውሳኔ እንዲሻሻል መደረጉን ዘጋቢያችን ገልጿል። የማሻሻያ ሕጉ ከአንድ ወር በፊት ለፓርላማ ሲቀርብ አሁን በስራ ላይ …

ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከዚህ ቀደም በ1997 ምርጫ ወቅት በቅንጅት መሪዎች፣ በጋዜጠኞችና በሲቪክ ተቋማት መሪዎች ላይ የቀረበው ክስ ፣ 24 ሰአታት አስቂኝ ፊልም የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ነበር። በፍርድ ቤቱ የነበረውን ሁኔታ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና የቃሊቲው መንግስት በሚል ርእስ ዘርዝሮ ማቅረቡ ይታወቃል። በቅርቡ አይ ኤስ ኤስ የተባለው አሸባሪ ድርጅት በ30 ኢትዮጵያውያን …

ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-“በኢትዮጵያ ያሉ ሚንስትር ድኤታዎች ድምፅ አልባ እና ተሳትፎ የሌላቸው ደካማዎች ናቸው” ሲል የኢህአዴግ ጽ/ቤት የአመራር ግንባታ የመለስ ዜናዊ የአመራር ግንባታ ክፍል ያወጣው ደብዳቤ አመለከተ። ደብዳቤው ዝቅተኛ እና መካከለኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ያላቸውን ሚኒስትር ድኤታዎች ዘርዝሮ አስቀምጧል። በአቶ አዲሱ ለገሰ የሚመራው እና ከፍተኛ የኢህአዴግ አባላትን ብቻ የሚያሰለጥነው …

ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምንጮች እንደገለጹት የሮመዳንን ጾም ተከትሎ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ተቃውሞ እንደገና ሊያገረሽ ይችላል በሚል ስጋት፣ 53 ሚሊየን ብር በጀት በመመደብ የመስጊድ ኢማሞችን በአክራሪነት ዙሪያ የማሰልጠን እና የማግባባት ስራውን እያከናወነ ነው፡፡ አንዴ ሞቅ ሌላ ጊዜ ቀዝቀዝ ሲል የሚታየው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አሁንም መንግስትን እንቅልፍ እንደነሳው ነው፡፡ በሁሉም ክልልች ለሚገኙ …

ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በብዙ መቶ ሚሊዮኖች ብር ወጪ ይሰራል የተባለውን የመለስ ፋውንዴሽን ለማስገንባት ህዝቡ በፈቃደኝነት ገንዘብ ያዋጣል ተብሎ ሲጠበቅ፣ የህዝቡ መልስ አስደንጋጭ መሆኑን የተረዳው በወ/ሮ አዜብ መስፍን የሚመራው ፋውንዴሽን፣ የመንግስት ስልጣንን በመጠቀም የመንግስት ደሞዝ ተከፋይ ሁሉ ገንዘብ እንዲያዋጣ ለማስገደድ ሞክረዋል። ግምገማ በመፍራትና በግዳጅ ገንዘብ እንዲያዋጡ ከተደረጉት መካከል የመከላከያ ሰራዊት …

ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወጣት ተመስገን ታፈሰ ተሰማ ዕድሜው 22 ዓመት ሲሆን በትምህርት ደረጃውም በማኔጅመንት የመጀመሪያ ድግሪ ያገኘ ወጣት ነው፡፡ ትውልዱና ዕድገቱ በደቡብ ክልላዊ መንግስት በቡርጂ ወረዳ ውስጥ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የኢማዴ-ደህአፓ/መድረክ አባል ሆኖ ለመታገል የወሰነና በመድረክ አባልነታቸው ምክንያት በሀገራቸው ሠርተው የመኖር የዜግነት መብታቸውን እየተነፈጉ አስተዳደራዊ ግፍ እየተፈጸመባቸው ካሉ …

ኢሳት ዜና (ሰኔ 18፥ 2007) በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ ባለው ዘረኝነትና አስተዳደራዊ በደል በመንገፍገፍ ከሰራቱ የሚለዩት የበረራ ባለሙያዎች ቁጥር እየጨመረ መገኘቱን እንዲሁም ሙስና በከፍተኛ ደረጃ መስፋፋቱን የአየር ሀይል ምንጮች ለኢሳት ገለጹ።  በህገ-ወጥ የሰው ዘውውር የአየር ሀይል አባላት የታሰሩ መሆናቸውንም  ለመረዳት ተችሏል። በ2007 አ/ም ብቻ አስር የበረራ ባለሙያዎች ስርአቱን በመክዳትና ወደ እስር ቤት በመጋዝ ከአየር ሀይሉ …

ሰኔ ፲፰ (አስራ ሰምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምንም አይነት መረጃ ወደ ውጭ እንዳይወጣ ከፍተኛ ቁጥጥርና ክትትል የሚደረግበት ከሰኔ አንድ ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን አዘጋጅነት የተጀመረው ግምገማ ፈታኝ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። ግምገማውን ተከትሎ አንዳንድ ፖሊሶች በደህንነቶች ተደብድበዋል። በጉለሌ ክፍለከተማ መምሪያ ስር የሚገኙ አንድ የሳጅን ማእረግ ያለውና አንድ ተራ ፖሊስ የአቶ …

ሰኔ ፲፰ (አስራ ሰምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ አንዳርጋቸው የህግ ድጋፍ በማያገኙበትና ይግባኝ ሊጠይቁ በማይችሉበት ሁኔታ በአስከፊ ሁኔታ መታሰራቸውን የእንግሊዝ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ፊሊፕ ሀሞንድ አውግዘዋል። የአቶ አንዳርጋቸው አያያዝ እና ደህንነት እንደሚያሳስበን በተደጋጋሚ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሃኖም ብንገልጽም ከቃል ያለፈ መልስ አለገኘንም፣ የምክር እና ራሳቸውን መከላከል የሚችሉበት መብትም አላገኙም ሲሉ የገለጹት …