እሥራኤልን ዐርባ ዓመት በበረሃ የመራ፣ ፈርዖንን ድል የነሣ፣ የኤርትራ ባሕርንም ለሁለት እንደ ድንጋይ የከፈለ ሰው ነው ሙሴ፡፡ እርሱን በተመለከተ አያሌ መጻሕፍትን ጽፈዋል፣ ፊልሞችን ደርሰዋል፣ ብዙዎችም በእርሱ ስም ተጠርተዋል፡፡ ሕዝብን ከባርነት የማውጣት፣ ለሕዝብ ብሎ የመከራከር፣ ለሕዝብ ብሎ ራስን የመሠዋት፣ ሕዝብን ከራሱ በፊት የማስቀደም፣ ሕዝብን በትዕግሥትና በጥበብ የመምራት፣ ለሕዝብ ብሎ ተከራክሮ ድል የማድረግ ተምሳሌት ነው – ሙሴ፡፡
ሙሴ ከወገኖቹ ጋር የኖረው ከተወለደ እስከ ሦስት ወር እድሜው ብቻ ነው፡፡ ያ ጊዜም ቢሆን ወገኖቹ በግብጻውያን እጅ ከባርነት በከፋ ስቃይ ውስጥ ገብተው የሚንገበገቡበት ጊዜ ነው፡፡ እንኳን ሌላውን ዓይነት ነጻነት ቀርቶ ልጅ ወልዶ የማሳደግ መብት እንኳን አልነበራቸውም፡፡ በተለይም ልጁ ወንድ ከሆነ፡፡ በምድርም ላይ እነርሱን ሊመለከት፣ ሊታደግና ሊራዳ የሚችል አንዳችም ኃይል አልነበረም፡፡ ዓለም እንደ ወስከንቢያ በላያቸው ላይ ተደፍታባቸው ነበር፡፡

ሙሴ ለዐርባ ዓመታት ያህል የኖረው በፈርዖን ቤተ መንግሥት ውስጥ የፈርዖን ልጅ ተብሎ፣ ግብጻዊነቱ እየተነገረው ነው፡፡ የተማረው የግብጽን ጥበብ፣ የበላው የግብጽን ምግብ፣ የሚያውቀው የግብጽን ቋንቋ፣ የኖረው ከግብጻውያን መኳንንትና መሳፍንት ጋር፣ የሚያየው የግብጻውያንን አማልክት፣ የተወዳጀው ከግብጻውያን ጠንቋዮችና አስማተኞች ጋር ነበር፡፡

ሙሴ የኖረበት የኑሮ ደረጃ ወገኖቹ ከነበሩበት የኑሮ ደረጃ እጅግ ከፍ ያለ ነበር፡፡ እርሱ በመኳንንት ወግ፣ በቤተ መንግሥት፣ ችግር የሚባል ነገር ሳይነካው፣ ግፍ የሚባል ነገር ሳይደርስበት፣ መብቱ በሚገባ ተጠብቆ፣ ከቅንጦትና ከድሎት አንዳች ሳይጎድልበት፣ የፈርዖን የልጅ ልጅ እየተባለ የኖረ ሰው ነበር፡፡ በተቃራኒው ወገኖቹ ደግሞ ሰው ሊደርስበት የሚችለውን የመጨረሻ መከራ እየተቀበሉ፤ ካሉት በታች ከሞቱት በላይ ሆነው ነበር የሚኖሩት፡፡ ህልውናቸው በሌሎች ፈቃድ እየተወሰነ፣ ፈንግል እንደያዘው ዶሮ ሞታቸው የሰዓታት ጉዳይ እየሆነ፣ መኖር ራሱ ቅጣት ሆኖባቸው ነበር የሚንገፈገፉት፡፡

ሙሴ እንዲህ በምቾትና በቅንጦት፣ ችግርን በጆሮው እንኳን ሳይሰማት አድጎ፣ የቤተ መንግሥቱን ቅምጥል አጣጥሞ፣ በፈርዖን ዕቅፍ ተቀምጦ – በዐርባ ዓመቱ ግን የወገኖቹ ነገር ያንገበግበው፣ ግፋቸው ይሰማው፣ መከራቸው ያመው፣ ስቃያቸው ያቃዠው፣ ሕመማቸው ያንቀጠቅጠው፣ ሞታቸው ዕረፍት ይነሣው ጀመር፡፡ እርሱ በቤተ መንግሥት ቢቀመጥም ልቡ ግን ከቤተ መንግሥቱ ወጥቶ ግፍ ከሚደርስባቸው ወገኖቹ ጋር ግፍ ይቀበል ጀመር፤ እርሱ ከፈርዖን ማዕድ ቢሰለፍም፣ ልቡ ግን ከወገኖቹ ጋር ይራብ ጀመር፡፡ እርሱ በሐር ልብስ ቢሞቀውም፣ ኅሊናው ግን ከወገኖቹ ጋር ተራቁቶ ይበርደው ነበር፤ እርሱ በሥልጣን ላይ ቢቀመጥም፤ ኅሊናው ግን ከወገኖቹ ጋር ለባርነት ተላልፎ ተሰጥቶ ይገረፍና ይታሠር ነበር፡፡ እርሱ ንጉሣዊ ሕይወትን ቢያጣጥምም፣ ልቡ ግን ከወገኖቹ ጋር ይሞት ነበር፡፡

ለዚህም ነበር አንድ ቀን ወደ ወገኖቹ ሲወጣ አጋዥ አልባ መሆናቸውን ያየ፣ ለግፍ ተላልፈው የተሰጡ መሆናቸውን ያጠና፣ የእነርሱ ሕይወት እንደ ጢንዚዛ ሕይወት ባለቤት የለውም ብሎ ያሰበ ግብጻዊ አንዱን ዕብራዊ ሲመታው ያየው፡፡ ለተመታው ዕብራዊ እርሱ አመመው፡፡ እርሱ የዚህ ግፍ የሚፈጸምበት ማኅበረሰብ አካል መሆኑን አመነ፡፡ ስለዚህም ታዳጊ ለሌለው ታዳጊ ለመሆን ወሰነና በራሱ ላይ ሞት ፈርዶ ያንን ግብጻዊ መታው፡፡ ልቡ ዐርባ ዓመት ከኖረበት ቤተ መንግሥት ሸፍቶ ሦስት ወር ወደኖረበት የእሥራኤላውያን የድህነት መንደር ገባ፡፡

እንዴት? ነው ጥያቄው፡፡ እንዴት?

ሙሴን ማን ነው ያስሸፈተው? ማንነቱን ሳይረሳ ዐርባ ዓመት በፈርዖን ቤተ መንግሥት ያኖረው ማነው? ከድሎቱ ይልቅ የወገኖቹን ስቃይ እንዲመርጥ ያደረገው ማነው? ሰዎች ለአንድ ዓመትና ለሁለት ዓመት ከሀገርና ከወገን ርቀው ባህላቸውንና ቋንቋቸውን ይረሳሉ፣ ማንነታቸውንም ይጥላሉ፡፡ እርሱ ግን ዐርባ ዓመት በፈርዖን ቤተ መንግሥት ሲኖር ለምን ማንነቱን ጠብቆ ኖረ? አንዳንድ ሰዎች ምቾትና ድሎትን ካገኙ፣ ከከበሩና ከተሾሙ ሀገራቸውን፣ ሕዝባቸውንና ወገናቸውን አሳልፈው ለመስጠት ዝግጁ ናቸው፡፡ ሙሴ ግን እምቢ አለ፡፡ እነርሱ ከበሉ ሕዝባቸው የበላ፣ እነርሱ ሲሾሙ ሕዝባቸው የተሾመ፣ እነርሱ ሲያገኙ ሕዝባቸው ያገኘ የሚመስላቸው ባለ ሥልጣናት ብዙ ናቸው፡፡ ሙሴ ግን ከወገኑ ተለይቶ ያገኘው ክብርና ምቾት፣ ሥልጣንና ሀብት ቆረቆረው እንጂ አልተስማማውም፤ ከእርሱ ድሎት ይልቅ የወገኑን መከራ መረጠ፡፡

መንግሥቱ ለማ፡-

የተለመደ ነው የመጣ ከጥንት

ከተጠቂው መራቅ አጥቂን መጠጋት

እንዳሉት የሀብታም፣ የባለ ሥልጣን፣ የታዋቂ ሰው፣ የባለ ጊዜ፣ የከበረ ወገን፣ የሚፈራና የሚከበር ሕዝብ ወገን ነኝ፣ ዘመድ ነኝ፣ አባል ነኝ ማለት ከጥንትም የነበረ ነው፡፡ የአጥቂው ወገን ሆኖ ከተጠቂው ጋር መቆም፣ የጨቋኝ ወገን ሆኖ ከተጨቋኝ ወገን መቆም፣ የክቡራን ወገን ሆኖ ከተዋረዱ ጋር መሰለፍ፣ የገፊዎች ዘመድ ሆኖ ከተገፊዎች ጋር መወገን፣ የሀብታሞች አካል ሆኖ ከድኆች ጋር መሰለፍ፤ የሹመኞች ቤት ሆኖ ለተራው ሕዝብ ዘብ መቆም ግን ብዙም የማይገኝ እንደ አልማዝ ብርቅ የሆነ ነገር ነው፡፡ ታድያ ሙሴ ይህንን ከየት አገኘው?

የሙሴ እናት ሙሴን በቤቷ ለመደበቅ የቻለችው ለሦስት ወራት ብቻ ነው፡፡ በዚያ ዘመን ሲወለድ ወንድ መሆኑ የታወቀ ዕብራዊ ሁሉ እንዲገደል በፈርዖን ዐዋጅ ወጥቶ ነበርና፡፡ የጨነቃት እናት መላ አታጣምና ዓባይ ወንዝ ወስዳ በሳጥን አድርጋ ጣለችው፡፡ የጣለችበት ቦታ የፈርዖን ሴት ልጅ ገላዋን የምትታጠብበት ቦታ ነበርና የፈርዖን ልጅ ሳጥኑን አየችው፡፡ ስትከፍተው የሚያምር ወንዝ ልጅ አገኘች፡፡ አምላክ የሰጠኝ ነው ብላ ወሰደችው፡፡ የሙሴ እናት ብልሃትና ጀግንነት ከዚህ ይጀምራል፡፡ እርሷ ባትኖር ኖሮ ሙሴ ከእነዚያ ሁሉ ሟች ሕጻናት ተለይቶ ባልተረፈ – በኋላም ታሪክ ባልሠራ ነበር፡፡

እናቱ ሙሴን ዓባይ ወንዝ ላይ ሰትጥለው እኅቱ መጨረሻውን እንድታይ ልካት ነበር፡፡ የፈርዖን ልጅ ሙሴን ከባሕር አውጥታ(‹ሙሴ› ማለት ከባሕር የወጣ ማለት ነው) ሞግዚት ስትፈልግ የሙሴ እኅት እናቱን ሞግዚት አድርጋ አመጣችላት፡፡ እናቱም ሞግዚት ሆና ሙሴን አሳደገችው፡፡ በፈርኦን ቤተ መንግሥት ውስጥ በእናቱ ሞግዚትነት ነበር ያደገው፡፡ ሁለተኛው ብልሃቷ ይሄ ነው፡፡ ሙሴ ሲያድግ እናቱ እውነቱን እየነገረችው ነው ያደገው፡፡ ‹‹አንተ በፈርዖን ቤተ መንግሥት ብትኖርም ግብጻዊ ግን አይደለህም፤ አንተ በምቾት ብትኖርም፣ የሚሰቃዩት የእሥራኤላውያን ወገን ነህ፤ አንተ የግብጽን ቋንቋ ብታጠናም ቋንቋህ ግን ዕብራይስጥ ነው፡፡ እዚህ ያገኘኸውን ልምድና ዕውቀት፣ሥልጣንና ክብር፣ ከሞት የመትረፍ ዕድል ወገኖችህን ነጻ ለማውጣት ተጠቀምበት፡፡ ይህ የምታየው ሕዝብ እንዲህ አልነበረም፡፡ ታላቅ ሕዝብ ነበር፣ ታላቅ ሕዝብም ነው፡፡ የአሁኑን መደኽየት፣ የአሁኑን መዋረድ፣ የአሁኑን መገፋት፣ የአሁኑን መጨቆን አትይ፡፡ ነገ ታሪክ ይለወጣል፡፡ አንተ ዛሬ ይህችን ክብርና ሥልጣን፣ ምቾትና ድሎት አገኘሁ ብለህ ከወገንህ ብትርቅ ታሪክ የተለወጠ ዕለት አንተም ስትረገም፣ ስትዋረድና ስትወቀስ ትኖራለህ፡፡ አንት ባታየው ዐጽምህ ይዋረዳል፡፡ ዛሬ ግን ከተገፉትና ከተዋረዱት ወገን ሆነህ ታሪክ ሲለውጥ አብረህ ብትሠራ ስምህ በወርቅ ቀለም ይጻፋል› – እያለች አስተማረችው፡፡

ሙሴ የእናቱ ውጤት ነው፡፡ ሰውነቱን ፈርዖን ሲያሳድገው ልቡን እናቱ ናት ያሳደገችው፤ ምግቡን ፈርዖን ሲሰጠው ጥበቡን እናቱ ናት የሰጠችው፡፡ አካን ቤተ መንግሥቱ ሲቀርጸው የሀገርና የወገን ፍቅር፣ ጽናትንና ብርታትን፣ ለወገን ሲሉ መሥዋዕት መሆንን የተማረው ከእናቱ ነው፡፡ የጥንቱን ታሪክ እየነገረች ልቡ በወገኑ ፍቅር እንዲቃጠል ያደረገችው እናቱ ናት፡፡ ያንን ታሪክ የመመለስ፣ ይህንን ሕዝብም ታላቅ የማድረግ ድርሻ ያንተ ነው ያለችው እናቱ ናት፡፡ ሙሴን ነጻ አውጭ እንዲሆን አድርጋ የሠራችው እናቱ ናት፡፡ በሙሴ ውስጥ ያለችው፣ ከፈርዖን ጋር የተከራከረችው፣ ቤተ መንግሥቱን ጥሎ ለወገኑ ሲል በረሃ እንዲንከራተት ያደረገችው፣ ባሕር እንዲክፍል ያበቃችው፣ የሕዝቡን ስድብ፣ ማጉረምረም፣ ሐሜትና ዐመጽ ችሎ ሕዝቡን እንዲመራ ያደረገችው እናቱ ናት፡፡ ‹ሕዝቤ ከሚጠፋ እኔን ከሕይወት መጽሐፍ ደምስሰኝ› ያሰኘችው እናቱ ነች፡፡

እንዲህ ያለች እናት በሌለችበት፣ እንዲህ ያለ ሙሴ መፈለግ ጉም መዝገን ይሆናል፡፡ እኛ የምንለፋው ሙሴን ለማግኘት ነው፡፡ የሚበጀን ግን ጀግናዋን የሙሴን እናት ማግኘት ነው፡፡

የሙሴ እናት የት ነው ያለሽው?

© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው

እሁድ ኖቨምበር 24 ቀን 2013 (እ.ኤ.አ.) በፍሎሪዳ ስቴትስ በምትገኘው ታምፓ ቤይ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት በሳዑዲ ዐረቢያ በሚገኙ የኢትዮጵያ ስደተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ኢሰብዓዊ በደል ከልብ እንዳስቆጣቸው ገልጠዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

PM Hailemariam Desalegn ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝግርማ ካሳ
በሕገ መንግሥቱ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰብሳቢ ናቸው። የጦር ኃይሎች ኤታ ማጆር ሹምን፣ ተቀዳሚ ጠቅላይ ሚኒስትርን፣ የሚኒስቴር ካቢኔዎችን፣ የፌደራል ፖሊስ አዛዦችን … የመሾምና የመሻር ሙሉ ሥልጣን አላቸው። ፓርላማውን በትነው አዲስ ምርጫ መጥራትም ይችላሉ። ፓርላማው በፈለገ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትሩን አውርዶ፣ ሌላ መሾም ይችላል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ተጠሪነታቸው ለፓርላማው ብቻ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ቅዱስ ዮሃንስ

ፀረ -ሽብርተኝነት ለአምባገነኖች ሁለት ጥቅም ያስገኝላቸዋል። አንደኛ በፀረ- ሽብርተኝነት ስም ከምዕራባውያን ኃያላን ጎን በአጋርነት በመቆማቸው በጥሬ ገንዘብም ሆነ በዓይነት (ለምሳሌ በመሣሪያ፣ በፖለቲካ ድጋፍ) ዳጎስ ያለ ጥቅም ያገኛሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት (የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር) Eng.Yilkal Getnet Chairman of Blue Party.ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
(የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር)

ሳውዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰች ያለውን ግፍና በደል በሰላማዊ ሰልፍ ለመቃወም ፓርቲያችን በወሰነው መሰረት ለሚመለከተው ክፍል አሳውቀን ነበር። መቼም ህዝባችን በጭቆና ውስጥ ስለኖረ በመብቱና በግዴታው መሀል ያለውን ድንበር በውል ካለመረዳቱ የተነሳ ሰልፉ እንዲደረግ ስለመፈቀዱ በተደጋጋሚ ስንጠየቅ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ህዳር ፲፯(አስራ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ ከሪያድ ወደ አዲስ አበባ ትሄዳላችሁ ተብለው በመኪኖች የተሳፈሩ ኢትዮጵያውያን እናቶችና ህጻናት በድንገት ጉዞዓቸው መሰረዙን ተከትሎ፣ በርካታ እናቶችና ህጻናት ለከፍተኛ የውሀ ጥም በመዳረጋቸው ህይወታቸው አደጋ ላይ ነው። እናቶች እና ህጻናት ተስፋ በቆረጠ ስሜት ያለቅሳሉ፤ ማለቃችን ነው ድረሱልን ሲሉ ይማጸናሉ። ህጻናቱና እናቶች አስፋልት ላይ ተበትነው በውሀ ጥም ማለቃቸው …

ህዳር ፲፯(አስራ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም ይህን የተናገሩት ” በክርስትና እና በእስልምና ሃይማኖት ሽፋን የሚካሄደው የፖለቲካ እንቅስቃሴ የመንግስት ቀጣዩ የምርጫ ፈተና” በሚል ርእስ ለኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ባቀረቡት ጽሁፍ ነው። ኢሳት የሚኒስትሩን  ሙሉ ንግግር የያዘ ሰነድ የደረሰው ሲሆን፣ በሰነዱ ግርጌ ላይ ” ለመደበኛ አባላት የማይነገር፣ ለከፍተኛ አመራሮች ብቻ” የሚል ተጽፎበት …

ህዳር ፲፯(አስራ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ጅጅጋ ከተማ ህዳር 29 ቀን 2006 ዓ/ም ለ8ኛ ጊዜ  የሚከበረውን የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች  በዓል  ጋር በተያያዘ የመንግስት ሥራ እና የዩኒቨርሲቲ ትምህርት እንዲቋረጥ ከመደረጉም በላይ በከተማዋ በየእለቱ ቤት ለቤትና በጎዳና ላይ ጥብቅ ፍተሻ እየተከናወነ ነው።  በጅጅጋ ከበዓሉ ጋር በተያያዘ ከ3ሺ500 በላይ እንግዶችን ታስተናግዳለች ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን እንግዶቹ ከሚያርፉባቸው ቦታዎች አንዱ የጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ማደሪያ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ሰሞኑን ለአንድ ወር ትምህርት …

ከሰሞኑ እየተመለሱ ወደ ትውልድ ሀገር ስለሚገቡትም በመነገር ላይ ነው። በሌላ በኩል በዚያ የሚገኙትን ግራ ያጋባ፤ ሆኖም ተጨባጭነት የሌለው የአውሮፓ መንግሥታት ተመላሾችን ለመቀበል እንደተዘጋጁ የሚናፈሰው ወሬ፤ በእርግጥ ተጨባጭነት የሌለው መሆኑም ታውቋል።

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መ ኢ አ ድ)በናዝሬት ከተማ ከ 33 የተቃውሞ ፓርቲዎች ጋር ከተደረገው የጋራ ስብሰባ በኋላ ፣ የራሱን አባላት በመጥራት የድጋፍ ፊርማ የማሰባሰብ ሥርዓት ማካሄዱ ተነገረ። በዚህ ሂደት በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ የወረዳ አስተዳደርና ፖሊስ ስብሰባየን አስተጓጎሉብኝ ሲል ወቀም ሆነ ስሞታ ማሰማቱም ታውቋል ።

ዓለማየሁ ዲባባ

የሳዑዲ ሕዝቦች በአንድ የታሪክ ዘመናቸው በኃይማኖት ልዩነት እርስ በእርሳቸው ተፋጅተው ወደ ኢትዮጵያ በተሰደዱ ወቅት ተቀብለናቸው አኑረናል፣ አስጠልለን መግበናል፣ አልብሰን አርዘናል። ከለላ እና ጥበቃ ሰጥተናቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የአውሮጳ ህብረት ለኢትዮጵያ ወደ 240 ሚልዮን ዩሮ የሚጠጋ የልማት ርዳታ እንደሚሰጥ አስታወቀ። ይህንኑ ርዳታ የሚመለከተው ስምምነት ትናንት በኢትዮጵያ መንግሥት እና ለጉብኝት አዲስ አበባ በገባው የአውሮጳ ህብረት የልዑካን ቡድን መሪ አንድሪስ ፒባልግስ መካከል ተፈርሞዋል።

ጥናቱ – እያንዳንዳቸው ከ50 – 122 ገጾች ያሏቸውን 15 የፖሊሲና ማኑዋል አርእስተ ጉዳዮችን ያካተተ መኾኑ ተገልጦአል፡፡ ከእነርሱም መካከል፡- የሰው ሀብት አስተዳደር፣ የሰው ኃይል ልማት፣ የፋይናንስ፣ የኦዲትና ኢንስፔክሽን፤ የዕቅድ፣ ክትትልና ግምገማ፤ የግዥ፣ ሽያጭና ንብረት አስተዳደር፤ የኢንቨስትመንትና ምግባረ ሠናይ፤ የቅርስና ቱሪዝም፤ የመንፈሳዊ ፍትሕ፣ የአስተዳደር እና የሥራ ክርክር ጉዳዮች ችሎቶችን የተመለከቱ ፖሊሲዎች፣ መመሪያዎችና ዝርዝር አሠራሮች ይገኙበታል፡፡ ዛሬ፣ ኅዳር …

ህዳር ፲፮(አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሪያድ የሚታየው ሁኔታ ተስፋ አስቆራጭ ነው ይላሉ ያነጋገርናቸው ኢትዮጵያውያን። እሁድ  2  ኢትዮጵያን ሴቶች መክረይመንታ ሸባቢያ በሚባል ቦታ ላይ በወታደራዊ ተሽከርካሪዎች መገደላቸውን በአይኔ ተመልክቻለሁ ያሉ የሪያድ ነዋሪ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ሌላ ኢትዮጵያዊት ደግሞ በአካባቢው ከተሰማሩት ወታደሮች ጋር ስትነጋገር በብረት ተመትታ መሞቷን እና አንዲት ኢትዮጵያዊትም እንዲሁ የቀኝ እጇ ተቆርጦ በአካባቢያቸው …

ህዳር ፲፮(አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአፍሪካ ፓርላማ  ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። በተቃውሞው ላይ የተገኘችው የኢሳት የደቡብ አፍሪካ ተባባሪ ዘጋቢ ዝናሽ ሀብታሙ እንደገለጸችው በሰልፉ ላይ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ኢትዮጵያውያን ታሰትፈዋል። ተቃውሞውን ያዘጋጀው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ምክትል ሊ/መንበር አቶ ንብረት ጌታሁንም ህዝቡ በተቃውሞው ላይ ተገኝቶ ስሜቱን በከፍተኛ ሁኔታ ገልጿል ብለዋል በተመሳሳይ …

ህዳር ፲፮(አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጋራ ትግል አስፈላጊ መሆኑን በፅኑ የሚያምኑት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር  እና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ  በሕዳር 13/2006 ዓ.ም በሁመራ ሉግዲ ከቀኑ    10፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1፡00 ለሶስት ሰዓት ያህል በወሰደው ውጊያ የመንግስት 24ኛ ክፍለ ጦር ድባቅ ተመቷል ብሎአል። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በ24ኛው …

ህዳር ፲፮(አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአፍሪካ ኅብረት በዓለም ዓቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ላይ የያዘውን አቋም እንዲደግፍ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ ጥያቄ አቀረቡ፡፡ ጥያቂያቸውን ለመቀበል አውንታዊ ምላሽ እንደገኙ በመግለጽ አፈጉባኤው ለጋዜጠኞች ቢናገሩም ጉዳዩ ተቀባነት ያገኘው ለውይይት እንጅ ለማጽደቅ አይደለም ተብሎአል። የአፍሪካ የካረቢያንና የፓስፊክ አገራት ፓርላማ 34ኛ መደበኛ ጉባዔ ትላንት በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን …

ህዳር ፲፮(አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ተማሪ አንተነህ አስፋው የተገደለው በዩኒቨርስቲው የጸጥታ ሀይሎች መሆኑ ታውቋል። ይህን ለመቃወም የወጡ በሺ በሚቆጠሩ ተማሪዎች ላይ የፌደራል ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ከ120 በላይ ተማሪዎች እንደታሰሩ ታውቋል። የተወሰኑ ተማሪዎች ከፉኛ በመደብደባቸው ሆስፒታል ገብተዋል፣ የአንድ ተማሪ ህይወትም በአሳሳቢ ሁኔታ ላኢ እንደሚገኝ ታውቋል።

ህዳር ፲፮(አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የታላቁ ሩጫ በከፍተኛ ወታደራዊ ጥበቃ ሥር ሆኖ እሁድ ህዳር 15 ቀን 2006 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡ መነሻውን ጃንሜዳ በማድረግ ፥ በ6 ኪሎ አደባባይ ፣ በምኒሊክ ሆስፒታል፣ በቀበና ፣በ አቧሬ ፣ በእንግሊዝ ኤምባሲ ፣ በመገናኛ አደባባይ በማደረግ ተመልሶ ጃንሜዳ የተጠናቀቀው ይህ ለ 13ኛ ጊዜ የተካሄደው ውድድር ከወትሮው በተለየ ጥበቃና የፖሊስ …

ፊልጶስ
የግፍ ጽዋው ሞልቶ፣ …
ሞልቶ፣ … ሞልቶ ፈሶ
ሰው መባል በሰው፣ ስዕብናችን አሶ
ከ’ጥናፍ – እስከ – አጥናፍ፣ ደማችን “‘ረክሶ”፤
ውቅያኖስ፣ ባህሩን፣ ወንዙን አደፍርሶ
እዩት ይ’ጣለላል፣ አስፋልቱን አልብሶ።
ግን እኮ፣ … እንኳ’ ደም
ውኃ ፈሶ፣ አይቀርም
ይዘገያል እንጂ፣ በሰፈሩት ቁና፣ መሰፈር አይቀርም።
“ዓለም የም’ጠፋው፣ ሰይጣናዊ ምግባር በሚፈጽሙ ሳይሆን፤ ምንም ሳያደርጉ ቀጭ ብለው በሚመለከቷቸው ሰዎች ነው።” /አልበርት አነስታይን/

ሙሉውን አስነብበኝ …

አበራ ሽፈራው ከጀርመን
በአረቡ ዓለም ከፍተኛ ተሰሚነትና የመላው ዓለም አይን ሁሉ በተለየ መልኩ በሚያያት ሳውዲአረቢያ በወገኖቻችን ላይ የደረሰው አሰቃቂ ግፍና መከራ ለትውልድ የማይረሳ ክፉ ታሪክ ጥሎብናል፤ ዛሬም ሰቆቃው ቀጥሏል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የእሥራኤል ሚንስትሮች ም/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር የገቡ ናቸው ያላቸውን አፍሪቃውያን ስደተኞች፤ በግዴታ እንዲመለሱ ማድረግ የሚቻልባቸውን የእርምጃ ዓይነቶች ትናንት ማጽደቁ ተነግሯል። እሥራኤል የገቡ 60,000 ያህል ስደተኞች ወደ መጡበት

ኢራን ድብቅ የኑክሌር ተቋም እንዳለት ከታወቀበት ከሁለት ሺሕ ሁለት ጀምሮ በቴሕራንና በምዕራባዉያን ሐገራት ፖለቲከኞችን መካከል የደራዉ ዉዝግብ ለመጀመሪያ ጊዜ-አንድ እልባት አግኝቷል። የእስራኤል-ምዕራባዉያን ልዩነት፥ የኢራን-እስራኤል ዉዝግብስ ነዉ?-የዛሬዉ ጥያቄ

ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)

የዚህ ፅሁፍ ማጠንጠኛ የፖለቲካ አመለካከትን መተቸት አይደለም፤ ከዋና ዋና  ገራዊ አ ንዳዎች ወረድ ያሉ የጉልበታሙን ስርዓት የሥራ አፈፃፀሞችን ማብጠልጠልም አይደለም፤ የተቀናቃኝ ፓርቲዎችን ስንክሳር መንቀስም… አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊ (አል- በሽ) መሆን ለፈተና፣ ለመከራ፣ ለሰቆቃ… መዳረጉ የወለደው ብሶት እንጂ፤ መመረር-ማምረር ነው፡፡ …ይህ የእኛ ዕጣ ፈንታ የሆነበትን ምስጢር መመርመር ነው፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

ኢያሱ ዓለማየሁ

የኢሕአፓ 41 ዓመት መራራና ረጅም ትግል ረጅም ትግስትን ጠይቋል። አያሌ ፈተናዎችን ተቋቁሞና አልፎ ዛሬም ህልውናውን ጠብቆ በትግሉ ሜዳ ላይ መገኘቱ በቅድሚያ የአባላቱታሪክን ገርተውና ጽፈዋት ያለፉትም ሆነ በሕይወት ያሉትን ጽናትና ቆራጥነትየሚመለከት ነው። ኢሕአፓን ለመመስረትና መስርቶም ለማታገል በተደረገው ትግል በታሪክ አጋጣሚ ዋና ተካፋይ ሆኜ በመቆየቴ የሚሰማኝ ደስታና ክብርም ወደር የለውም። ሀቁ ይህ ድርጅት ከቶም ባልተመሰረተ የሚሉት ጠላቶች እንደ ነበሩትና እንዳሉት ሁሉ (በአብዛኛው ከስርዓቶቹ ጋር የተያያዙ) ቤዛችን ነው፣ የወኔያችን መከሰቻ ነው፣ የሀገር አለኝታችን ነው ድርጅታችን ነው የሚሉ ደሞ ብዙዎች ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

SHARE:

ሳውዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰች ያለውን ግፍና በደል በሰላማዊ ሰልፍ ለመቃወም ፓርቲያችን በወሰነው መሰረት ለሚመለከተው ክፍል አሳውቀን ነበር፡፡መቸም ህዝባችን በጭቆና ውስጥ ስለኖረ በመብቱና በግዴታው መሀል ያለውን ድንበር በውል ካለመረዳቱ የተነሳ ሰልፉ እንዲደረግ ስለመፈቀዱ በተደጋጋሚ ስንጠየቅ ነበር፡፡ህጉ የሚለው ግን ማስፈቀድ ሳይሆን ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡በተቃራኒው መንግስት በተለያዩ ጉዳዮች ሳቢያ በእለቱ ለሰላማዊ ሰልፉ የደህንነት ከለላ መስጠት የማይችልበት ሁኔታ ከገጠመው ሰልፉን ለጠራው አካል ችግሩን ገልጾ ቀኑ እንዲተላለፍለት ይጠይቃል፡፡በመሆኑም ይህን መሰል ጥያቄ ከሚመለከተው መስሪያ ቤት ለፓርቲያችን ባለመቅረቡ በሙሉ ልብ ቅድመ-ዝግጅት ማድረጉን ተያያዝን፡፡
ሁሌም ቢሆን መንግስት ሰበብ ፈልጎ ሊወነጅለንና ከመስመር ሊያስወጣን እንደሚፈልግ በሚገባ እናውቃለንና በጥቃቅን ጉዳዮች ላይ ሳይቀር ጥንቃቄ እናደርጋለን፡፡ለሚመለከተው መስሪያ ቤት ባሳወቅን በአስራ ሁለት ሰአታት ውስጥ ምላሽ ስላልመጣ ሙሉ በሙሉ ህጋዊነታችንን አረጋግጠናል ማለት ነው፣እነሱ ደግሞ ጠብ-መንጃ በእጃቸው አለና የፈለጉትን ሁሉ ማድረግ ይችላል፡፡

አቶ ሽመልስ ከማል ለሚዲያወች የሰጡትን ፍጹም ከእውነት የራቀ ውንጀላና ሰበብ አዳምጨዋለው፡፡ “ሰላማዊ ሰልፉን ያገድንበት ምክንያት ጸረ-አረብ መፈክሮች ስለነበሩ ነው“ብለዋል፡፡መጀመሪያ ደረጃ ሰልፉ ገና ከግቢው ፈቅ ሳይል ነው ያፈኑት፣ሆኖም የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም አንድ በአንድ እየሆንን ወደ ሰላማዊ ሰልፉ መዳረሻ ለመሄድ ስንሞክር የተወሰኑ አመራሮችን አራት ኪሎ አካባቢ ያዙን፣እነሱ ቀድሞውኑ ሰልፉ እንዳይካሄድ ስለወሰኑ ነው እንጅ ትንሽ እንኳ ተንቀሳቅሶ የሰልፉን ባህሪ ለመገምገም ምንም እድል አልሰጡንም፡፡

ለምሳሌ ሰልፉን እንደምናደርግ ይፋ ባደረግን ማግስት ከራዲዮ ፋና ተደውሎ አንዳንድ ጥያቄዎች ተጠይቄ ነበር፡፡በቃለ-መጠይቁ ሰላማው ሰልፉ በዜጎቻችን ላይ የሚደርሰውን በደል በመቃወም እንደምናደርግ ተናግረናል፡፡ጋዜጠኛው ለሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች መልዕክት ካለ ብሎ በጠየቀኝ ወቅት የሳውዲ አረቢያ ሰንደቅ አላማ ላይ ያለው ምልክትና ጽሁፍ ሀይማኖትን የሚመለከት በመሆኑ ዜጎች በስሜታዊነት ባንዲራ እንዳያቃጥሉ፣እነሱ ቢያዋርዱንም እኛ ግን ክብር ያለን ዜጎች ስለሆንን ተቃውሟችንን ጨዋነት በተሞላበት ሁኔታ ማካሄድ እንዳለብን ተናግሬ ነበር፡፡ከሰላማዊ ሰልፉ በፊት በዚህና በተለያየ መንገድ በማያሻማ ሁኔታ መልዕክት ባስተላልፍም እነሱ ግን ይህን በመቁረጥ አላስተላለፉትም፡፡እነዚህና ሌሎች ምክንያቶች ሲደመሩ የአቶ ሽመልስ ከማል ንግግር ነጭ ውሸት መሆኑን ያስገነዝባል፡፡

ሁለተኛ የአንድ ሀገር መንግስት ዜጎቹ እየተደፈሩ፣በማጎሪያ ካምፕ በረሀብና በውሃ ጥም፣ሌላው ቢቀር መጸዳጃ ቤት እንኳ ተከልክለው ፍጹም ከሰውነት ክብራቸው ወርደው እየተበደሉ፣እየተገደሉ ባለበት ወቅት ገና ለገና ተቃዋሚ ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ በሚንጸባረቅ ጥላቻና ተቃውሞ የዲፕሎማሲ ግንኙነቴ ይበላሽብኛል ብለን መናገር እንችላለን?ሌላው ይቅር አንድ ክፉና ደጉን የለየ ሰው የሚያስበው ጤነኛ ሃሳብ ነው ማለትስ ይቻላል?

ከእገዳው ባሻገር የሚደንቀው ነገር ደግሞ በፓርቲያችን አመራሮችና አባላት ላይ የተደረገው ድብደባ ነው፣የሆነ ማስተላለፍ የፈለጉት ነገር ያለ ይመስላል፡፡የጭካኔያቸውን መጠን እንድናውቅ የሚደበድቡት አቅመ-ደካሞችን፣ሽማግሌወችንና ሴቶችን እየመረጡ በፍጹም አረመኔነት ነበር፡፡ይህን ተግባራቸውን ስመለከት የደረሱበትን የዝቅጠት ደረጃ መታዘብ ችያለው፡፡ከፖለቲካ ልዩነትም፣ከአምባገነንነትም በላይ ሰወቹ እንደታመሙ ነው ለመረዳት የቻልኩት፣ስር የሰደደ የቁስ ሰቀቀንና የስልጣን ጥም የተጣባቸው፣ለዚያ ሲሉም የትኛውንም አይነት ውርደት ለመቀበል የቆረጡና የሞራል ልዕልናቸውን ሙሉ በሙሉ ያጡ ሰዎች ናቸው፡፡ስነ-ልቦናቸው ክፉኛ ተቃውሷል እንጂ ሀገር እመራለው የሚል ቡድን እንዲህ ያለ ተግባር ይፈጽማል ለማለት እቸገራለው፡፡በአባላቶቻችን ላይ ክፍኛ ድብደባ ተፈጽሟል፣እስከዛሬም እግሮቻቸው መራመድ የማያስችላቸው፣የሚያነክሱ ሰዎች አሉ፡፡እውነት ለመናገር ይሄ እብደት ነው፡፡አንዲት እራሷን መከላከል የማትችል ሴትን ለሶስት መደብደብን ከዚህ በተሸለ ልገልጸው አልችልም፡፡

አንድ ማስገንዘብ የምፈልገው ነገር ለኛ ዋነው ጉዳይ የዜጎቹ ህጋዊነት ወይም ህጋዊ ያለመሆን ጉዳይ አይደለም፡፡በምንም አይነት መንገድ ሴቶች እየተደፈሩ፣ወንዶች በየስርቻው እንደ ውሻ ተቀጥቅጠው እየተገደሉ እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች ታጉረው ይህን ሁሉ መከራ መቀበላቸውን ልንታገሰው፣ወይም ከህጋዊነት አንጻር እየተራቀቅን ልንመለከተው አንችልም፣ስለ ህግም ከተወራ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ጭፍጨፋው ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ባላቸው ላይ ጭምር ሲፈጸም እንደነበር አምኗል፡፡

ባለንበት የግሎባላይዜሽን ዘመን የአንዱ ሀገር ዜጋ ካለ ሀገሩ መገኘት አገር ይያዝ የሚያስብል አይደለም፡፡መውጣት ካለባቸው ጊዜ በመስጠት፣ከመንግስታቸው ጋር በመነጋገር በዘዴ ነገሩን መከዎን እየተቻለ አንድ ሀገርና መንግስት በሰዎች ላይ እንዲህ የጭካኔ ጥግ የሆነን አቋም ይዘው መንቀሳቀሳቸው ፍጹም ኢ-ሰብአዊነት ነው፡፡
ለኢትዮጵያውያን እንዲህ ያለ አስከፊ ጊዜ የለም፣እውነቱን ለመናገር ለአገዛዙ ሰዎች የነበረኝ ጭላንጭል ተስፋም አፈር ተደፍቶባታል፣እንዲህ ግልጽ የሆነ ጭፍጨፋ እየደረሰብን እንኳ በድፍረት ለመናገር አልፈለጉም፡፡ስለ ኢትዮጵያውያን መገደል ለማውራት ሲፈልጉ ሌላ ሀገር ይጠቅሱና እነሱም እኮ እየተገደሉ ነው ይላሉ፣ወገን ከምንለው የማህበረሰባችን አካል ይሄን መስማቱ ከጥቃቱ ይበልጥ ያማል፡፡

ለምሳሌ ኢቲቪ ስጉዳዩ ሲያወራ ህገ ውጥ ሊባል የሚችል ድርጊት ተፈጽሟል በማለት ነው፡፡ተመልከቱ! እንዴት ያለ ባዕድነት ነው?ኢትዮጵያውያን በድህነትም ውስጥ እንኳ ለክብራችን የመሞት ባህሪ አለን፣ይሄ ከቀደሙት አንጡራ ኢትዮጵያውያን የወረስነውና ዛሬም ያለን ሀብታችን ነው፡፡

ትናንት ፍየል ጠባቂ የነበረ በረኸኛ ይህን ክብራችንን ገፍፎ እንደውሻ ቀጥቅጦ ስርቻ ሲጥለን ያልተቆጣ መንግስት ኢትዮጵያዊ ነው?ከዜጎቹ የወጣና ለህዝቡ የቆመ እውነተኛ መንግስት ከዚህ የበለጠ የሚቆጣበት ጉዳይ ከወዴት ይመጣል?
እውነተኛ መንግስት ቢሆን ኖሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሳውዲ ካምፓኒዎችን በሰአታት ውስጥ ማባረር፣ኢምባሲውን ዘግቶ አምባሳደሩን ማሰናበትን የመሳሰሉ ውሳኔዎችን ያሳልፉ ነበር፡፡የሆነው ግን በተቃራኒው ነው፣የድፕሎማሲ ግንኙነቴ ሊበላሽ ይችላል ብሎ እኛ ድምጻችን እንዳናሰማ ደበደበን፣አፈነን፡፡በግልጽ እንደሚታየው የጥቅም ትስስሩ ነው አፋቸውን ያዘጋቸው፣ይህች ጥቅማቸው እንዳትቋረጥ በዜጎች ህይዎት መደራደርን መርጠዋል፡፡

ስነ ልቦናቸው የተቃወሰ በመሆኑና ተራ ስስታሞች በመሆናቸው እንጂ ኢንቨስትመንትም ሆነ ዲፕሎማሲ ግብአትነታቸው ለሰው ልጅ ነው፣እንደ አህያ ሲያፈጋ ከርሞ ሬሳቸውን ለላከ መንግስት እንዴት ተመጣጣኝ ምላሽ ለመመለስ ይገዳል?እንዴት እንደ ኢትዮጵያ ያለች ታሪካዊትና ለአፍሪካ የነጻነትና የኩራት ተምሳሌት የሆነች ሀገርን እየመሩ እንዴት ትናንት የነዳጅ ዘይት ባቆማቸው እረኞች ስትዋረድ ዝም ይላሉ?!::
እንዴት!
በዜጎች ህይወት የተደራደረው አገዛዝ ማለፉ አይቀርም፣ለዚህ ጥርጥር የለኝም፡፡ታሪክ ለመጥቀስ ብዙ ርቀት መሄድ አያስፈልግኝም፡፡የቅርብ የሰሜን አፍሪካ አምባገነኖች የከፋ ፍጻሜ አለና፡፡ኢትዮጵያውያን ፍቅርም ጸብም እናውቃለን፣ሳውዲወችም የፈጸሙትን ግፍ ማወራረዳቸው አይቀርም፡፡በዚህ ክፉ ጊዜ ስለስብአዊ መብት ቆመናል የሚሉ አለም አቀፍ ተቋማት ዝምታን መምረጣቸው እውነተኝነታቸውን ለመመርመር ጥሩ እድል ይሰጠናል፡፡
መንግስት ቢኖረን ኖሮ ይሄ ሁሉ ውርደት ይፈጸምብን ነበር ብየ አላስብም፡፡በዚህ ሰአት ርዕሰ-መንግስት ብሆን ኖሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትልቅ ድርጅት እንደመሆኑ፣ወደየትኛውም ሀገር የሚደረገውን ጉዞ አቋርጨ ዜጎቸን ማስወጣትን አስቀድም ነበር፡፡ያሄ ጥቂት ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ሊያመጣብን ቢችልም ከከፋው የዜጎች ስቃይ ጋር ግን በአንድ ሚዛን ላይ አይቀመጥም፡፡የአደጋ መከላከያና ዝግጁነት ኮሚሽን የሚባል ድርጅት አለ፡፡በዜጎቻችን ላይ ጎርፍና ድርቅ ሲመጣ ብቻ ነው የሚንቀሳቀሰው? ይሄም ሰው ሰራሽ አደጋ ነው ሙሉ ሀይሉን ወደዚህ አዙሮ ሊንቀሳቀስ ይገባው ነበር፡፡

እርግጥ ነው ባቀድነው መሰረት ሰላማዊ ሰልፉ ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዳይሆን አድርገውታል፡፡ጩኸቱ ግን ይቀጥላል……ባለን አቅም ሁሉ አፈናውንም፣ወከባውንም ተቋቁመን ለዜጎቻችንና ለኢትዮጵያዊነት እንታገላለን፡፡
አገዛዙ ይሄን ሰላማዊ ሰልፍ ሲያፍን ለኢትዮጵያ ህዝብ እንድ መልእክት አስተላልፏል፣ይህን መልእክት እንዲያስትላልፍ ማስገደዳችንም ለኛ ትልቅ ስኬት ነው፡፡የሳውዲ መንግስት ያሻውን ያደርግ ዘንድ የፈቀድኩት እኔ ነኝ፣በመሆኑም እሱን በመቃወም ግንኙነቴን አታበላሹ ብሎ እርምጃ በመውሰዱ ህዝቡ የነገሩ ቁልፍ የት እንዳለ፣የአጥቂወቹ በራስ መተማመን ምን ላይ እንደቆመ በጠራ ሁኔታ ለመመልከት እንዲችል ሆኗል፡፡

ይሄ ሁሉ ነገር እየተፈጸመ የተስተዋለ አንድ ነገር አለ፡፡የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዝምታ እውነተኛ ማንነታቸው፣እውነተኛ በአገዛዙ ውስጥ ያላቸውን ቦታ ያሳየን ክስተት ነው፡፡እንደሚታወቀው እሳቸው በኢህአዲግ እንጂ በኢትዮጵያ ህዝብ የተመረጡ አይደሉም፡፡ኢህአዲግ የሚናገረው ከሌለ እርሳቸው የሚሉት አይኖርም፡፡እንደ አንድ ሀገርና ህዝብ መሪ ግን የመኮነንም ሆነ የማጽናናት ቃል ይጠበቅባቸው ነበር፡፡

ባሉበት ቦታ ያስቀመጣቸው ህወሀት ነው፤ድርጅቱ ደግሞ ይሄን አቋም አልወሰደም፡፡ስለዚህ እንደሚቆጣቸው ስለሚያውቁ ዝምታን መረጡ፣ቸልታንም አስበለጡ፡፡በሀገርም ሆነ በግለሰብ ደረጃ ከዚህ በላይ ሽንፈት ያለ አይመስለኝም፡፡

(ይህ ጽሁፍ በፋክት መጽሄት ተስተናግዷል፣ነገር ግን መጽሄቱ ላልደረሳቸው ሰዎች ይደርስ ዘንድ እዚህ ለማስተናገድ ወደድኩ፡፡)

የሥራ ተቋራጩ በ2 ዓመት ጊዜና በ3 ሚልዮን ብር ወጪ ግንባታውን አጠናቅቆ ማስረከብ ነበረበት፤ ይኹንና የሥራው መጠን ከ65 በመቶ በላይ ባልተራመደበትና ከውለታ ጊዜው ውጭ ለ6ኛ ዓመት በዘገየበት ኹኔታ አላግባብ በቀረበ የተቋራጩ የይገባኛል ጥያቄ ከብር 8 ሚልዮን በላይ ወጪ መከፈሉ ተጠቁሟል፡፡ ቋሚ ሲኖዶስ መስከረም ፰ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት÷ በ3 ሚልዮን ብር በ2 ዓመት ጊዜ […]