ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ከአንድ ሣምንት በኋላ ወደግብፅ የሚያደርጉት ጉዞ በህዳሴ ግድብ ላይ ከተፈጠረው ልዩነት ጋር የተያያዘ ያለመሆኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትረያርክ አቡነ ማትያስ አስታወቁ።

ግድቡን አስመልክቶ በኢትዮጵያ ያለው አስተሳሰብ ግልፅ እና አብረን እንጠቀም መሆኑን የተናገሩት አባ ማትያስ ርዕሱ ከተነሳ ምላሽ እንደሚሰጡ ከአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አስታውቀዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ኬንያ ውስጥ ሰሞኑን በስደተኞችና ፍልሰተኛ ነዋሪዎች ላይ እየካሄደ ያለው ፍተሻ፣ የቤት ለቤት አሰሳና የጅምላ እሥራት የፈጠረው የውጥረት ድባብ የሰብዓዊ መብቶች ጥያቄዎችን እያስነሣ ነው፡፡

ቪኦኤ ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተለና ዘገባዎችንም እያወጣ ነው፡፡

ከኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች መካከል እያነጋገርን ነው፡፡

የኬንያ ፖሊስ ያለህጋዊ ፈቃድ ሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የውጭ ሀገር ስደተኞችን ዒላማ ባደረገው ዘመቻችው ከአንድ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችን መርምረናል፥ ሁለት መቶ ሃያ አምስት ሰዎችን ልናስወጣ ነው ሲል አስታውቋል።

ለሰብዓዊ መብቶች የሚሟገቱ ቡድኖች እና ኬንያ ውስጥ ያሉ ሶማሌዎች ፖሊሶች ያዋክቡናል፥ ጉቦ ይጠይቁናል ፥ በጎሣችን ምክንያት የዘመቻው ዒላማ እየተደረግን ነው ሲሉ አማርረዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ማክሰኞ፤ ሚያዝያ 7/2006 ዓ.ም ጠዋት ላይ ያልታወቁ ታጣቂዎች፣ በቤኒሻንጉል-ጉምዝ ክልል 28 ሰዎች አሣፍሮ ይጓዝ በነበረ ከፍተኛ ተሽከርካሪ ላይ ተኩስ ከፍተው 9 ተሣፋሪዎችን ሲገድሉ በሰባቱ ላይ ደግሞ ከቀላል እስከ ከባድ የማቁሰል አደጋ አድርሰዋል።

ፖሊስ የጥቃቱን ምክንያት እያጠና መሆኑን ገልጿል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ – ኦፌኮ ባለፈው ዕሁድ አዲስ አበባ ላይ በጠራው ህዝባዊ ስብስባ ኦሮሚያ ውስጥ የሚገኙ ከተሞችን ከአዲስ አበባ አስተዳደር ጋር ለማስተሳሰር በወጣው ማስተር ፕላን ላይ ተቃውሞውን ገልጿል፡፡

ኦፌኮ ይህንን ያሳወቀው ያካሄደውን ምክክር ተከትሎ ባወጣው የአቋም መግለጫ የከተሞቹን ነዋሪዎች የሚጎዳ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ በመድረሱ መሆኑ ታውቋል፡፡

“የኦሮሞ ገበሬዎች  እየተነቀሉ ቦታቸው በሊዝ የሚሰጠው ለመሬት ቅርምት እንጂ ለልማት አይደለም” በማለት ኦፌኮ ተቃውሞውን አሰምቷል።

ዋና ፀሐፊው አቶ በቀለ ነጋ ለቪኦኤ የሰጡትን መግለጫ የያዘውን የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የደቡብ ሱዳን ፀረ-መንግሥት ኃይሎች የዩኒቲ ግዛት ዋና ከተማይቱን ቤንቲዩን መቆጣጠራቸውን የመንግሥቱ ኃይል የሆነው የሱዳን ሕዝብ አርነት ሠራዊት – ኤስፒኤልኤ ዛሬ አረጋግጧል፡፡

መንግሥቱ አክሎም ተቃዋሚዎቹ ምናልባት ድጋፍ ከኻርቱም አግኝተው ሊሆን እንደሚችል የሚጠቁም መልዕክት ቢያስተላልፉም አማፂያኑ ግን ይህንን የጁባን ውንጀላ ፈጥነው ሙሉ በሙሉ አስተባብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ቤንቲዩ ላይ ሁለቱም ወገኖች ገና እየተፋለሙ መሆናቸውን የደቡብ ሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስትር ተናግረዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያደምጡ፡፡

ኢትዮጵያ ከአምስት ዓመት ዕድሜ በታች ያሉ ህፃናትን ሞት ቁጥር በሁለት ሦስተኛ መቀነስ ብትችልም በሚሌኒየሙ የልማት ግቦች የሠፈረው ግብ ላይ እንዳልደረሰች ተገለፀ።

የእናቶችን ሞት ለመቀነስ አሁንም ብዙ እንደሚቀር ተገልጧል።
የአውሮፓ ኅብረት እነዚህን ግቦች ለመምታት ያግዝ ዘንድ አርባ ሚሊዮን ዶላር ለግሷል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካችው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ ልኮልናል።

(2007-2008 ዓ.ም)
የሚሌኒየሙ የልማት ግቦች

ሥር የሰደደ ድኅነትና ረሃብን ማጥፋት፤
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትን ለሁሉም ማዳረስ፤
የፆታዎች እኩል መሆንን ማስተማር እና የሴቶችን ውሣኔ ሰጭነት ማስፋት፤
የሕፃናት ሞትን መቀነስ፤
የእናቶች ጤናን ማሻሻል፤
ኤችአይቪ/ኤድስን፣ ወባንና ሌሎችም በሽታዎችን…

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የፌደራሉ አቃቢ ሕግ ከሁለት ወራት በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውን አይሮፕላን ወደ ጄኔቭ ከተማ በወሰደው ረዳት አብራራ ኃይለመድኅን አበራ ላይ ክሥ መሠረተ፡፡

አቃቢ ሕግ ኃይለመድኅንን የከሰሰው በማገት ወንጀል ነው፡፡

በመቶ ሺሆች ዩሮ የሚገመት ጉዳት መድረሱም በክሱ ላይ ተጠቅሷል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ የሚታዩ የተለያዩ ችግሮች በመንግሥቱ የተሣሣቱ ፖሊሲዎች ምክንያት የተፈጠሩ ናቸው ሲል ሰማያዊ ፓርቲ ክሥ አሰማ፡፡

ለችግሮቹም በአስቸኳይ መፍትኄ እንዲሰጥ፣ ካለበለዚያ ሥልጣኑን እንዲለቅቅ የሚጠይቅ ሰልፍ እጠራለሁም ብሏል፡፡

መንግሥት በበኩሉ “አሉ” ስለሚባሉት ችግሮች የሚቀርቡት ክሦች የተጋነኑ ናቸው ይላል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ ኃይሎች ነዳጅ ዘይት አምራቿን የዩኒቲ ግዛት ዋና ከተማ ቤንቲዩን መያዛቸውን አስታውቀዋል፡፡

ውጊያው ከተማይቱ ውስጥና በአካባቢዋ እንደቀጠለ መሆኑን የሃገሪቱ የጦር ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡

አንድ ማንነቱን መግለፅ ያልፈለገ የቤንቲዩ ነዋሪ የተፈጠረውን ሁኔታ ለቪኦኤ በስልክ አረጋግጧል፡፡

የተቃዋሚዎቹ መሪዎች የነዳጅ ዘይት ምርቱን የማቋረጥ ሃሣብ እንዳላቸው አመልክተዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

በሽብር ወንጀል ተከስሰው በክርክር ላይ የሚገኙት የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጥያቄዎች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትና ሌሎችም ተከሣሾች ለፍርድ ቤት ሲሰጡ የቆዩትን ቃል ዛሬ አጠቃልለዋል።

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ከሁለት ሣምንታት በኋላ አዲስ አበባ ላይ የሚያካሂዱት የእግር ጉዞ ዓላማ በተመሣሣይ ፆታ ግንኙነትና በሌሎችም “መጤ” ባሏቸው ልማዶች ወይም የባሕል ዘርፎች ላይ ግንዛቤ መፍጠር መሆኑን አዘጋጆቹ ማኅበራት አስታውቀዋል፡፡

ሁለቱ ማኅበራት ዛሬ በሰጡት መግለጫ የተመሣሣይ ፆታ ግንኙነት “ሊወገዝ የሚገባ ነው” ብለዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢና በአካባቢዋ በሚገኙ ስደተኞች ላይ በመንግሥቱ እየተፈፀመ ነው የሚሉት አፈሣና እሥራት በእጅጉ እያሣሰባቸው መሆኑን ስደተኞቹ እየገለፁ ነው፡፡

የኬንያ መንግሥት በሃገሪቱ ውስጥ እየደረሱ ያሉት ፍንዳታዎች ለፀጥታዬ አደጋና ሥጋት ደቅነዋል በሚል ስደተኞች ወደዚያ ሲገቡ ወደየተመደቡባቸው ሠፈሮቻቸው እንዲመለሱ በቅርቡ ማስታወቂያ አውጥቶ እንደነበረ ይታወሣል፡፡

ከዚያ ማስታወቂያ ወዲህ ባለፉት ከአምስት እስከ ሰባት በሚሆኑ ቀናት ብዙ ስደተኞች እየታፈሱና እየተንገላቱ መሆኑ ይሰማል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የደቡብ ሱዳን ገዥ ፓርቲ – የሱዳን ሕዝብ አርነት ንቅናቄ – ኤስፒኤልኤም ውስጣዊ ችግር ከተፈታ የሃገሪቱ ችግርም ሊፈታ ይችላል ሲሉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የኢህአዴግ ሊቀመንበር ኃይለማርያም ደሣለኝ ተናግረዋል፡፡

ፓርቲው ራሱን ለሚገመግምበትና ለሚያይበት ቀጣይ ስብሰባ መንገድ የሚጠርግ ውይይት አዲስ አበባ ላይ ተከፍቷል፡፡

ውይይቱን የሚያስተባብሩትና የሚመሩት የኢትየጵያው ገዥ ፓርቲ ኢህአዴግና የደቡብ አፍሪካው ገዥ ፓርቲ የአፍሪካ ብሔራዊ ምክር ቤት – ኤኤንሲ ሲሆኑ በኢትየጵያ በኩል የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ አማካሪ አቶ በረከት ስምዖን በዚሁ ኃላፊነት ተሰይመዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

ባለፉት አርባ ዓመታት አፍሪካ በካፒታል ሽሽት ምክንያት ከ103 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ማጣቷ ተገለፀ፡፡

አፍሪካ ይህንን ገንዘብ ማስቀረት ችላ ቢሆን ኖሮ የሚሌኒየሙን የልማት ግቦች ከማሳካት የበለጠ ብልፅግና ይኖራት ነበር ተብሏል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምፅን ዘገባ ያዳምጡ

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

በዛሬው የሙዚቃ ቃና ፕሮግራም በአሜሪካ የቢል ቦርድ ሰንጠረዥ ላይ ከመቶዎቹ ምርጥ ዜማዎች መካከል በዚህ ሳምንት ከአንድኛ እስከ አስረኛ ደረጃ የወጡትን ምርጥ ዜማዎች ያጠቃልላል::