መስከረም ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከፍተኛ ገንዘብ ወጥቶባቸው በተዝረከረከ የንብረት አስተዳደር ሥርዓት ምክንያት ለብክነት፣ ለምዝበራ እና ለብልሽት የተጋለጡ ንብረቶችን ለመታደግ ትክክለኛ የአሰራር ስርዓት መጥፋቱን፣ የመስሪያ ቤቱ ባለስልጣናትም ያለጠያቂ በሙስና መዘፈቃቸውን  የፌድራል የስነ ምግባር እና የጸረ ሙስና ኮሚሺን ገለጸ፡፡ በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ውስጥ የDCI እና የDN  የቧንቧ መገጣጠሚያዎች ቁመታቸው እና ውፍረታቸው …

መስከረም ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጋምቤላ ክልል ከ300 ሺ ሄክታር ያላነሰ መሬት በነጻ በሚባል ዋጋ የተረከበው የህንዱ የእርሻ ኩባንያ ካራቱሬ ፣ በተሰጠው መሬት ላይ የልማት ስራ አለማከናወኑንና የባንክና ሌሎች እዳዎችን ለመክፈል አለመቻሉን ሰንደቅ ጋዜጣ ዘግቧል። በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጠባባቂ የቢዝነስ ዴቭሎፕመንት የስራ ሒደት ባለቤት የሆኑት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ ለጋዜጣው  እንዳስረዱት ፣ ካራቱሪ …

መስከረም ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ቢሮው በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የአሸከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋማት ላይ ያደረገውን ግምገማ ውጤት ተከትሎ ማንኛውም የመንጃ ፈቃድ ሰልጣኝ ከጥቅምት1 ቀን 2006 በፊት በማናቸውም የአሸከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋማት ውስጥ ትምህርት እንዳይጀምሩ አስጠነቀቀ፡፡ ዛሬ ይፋ በተረደገው የጥናት ውጤት መሰረት ከ58 የማሰልጠኛ ተቋማት ዝቅተኛውን መስፈርት …

መስከረም ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቁጫ ከወራት በፊት የነተሳውን ተቃውሞ መርታችሁዋል በሚል 40 ሰዎች በአርባምንጭ እስር ቤት ታስረው ከቆዩ በሁዋላ ፍርድ ቤት እንዲፈቱ ቢያዝም ፖሊስ አልፈታም በማለቱ ሰዎቹ ለተጨማሪ ወራት ከታሰሩ በሁዋላ ከቀናት በፊት መፈታታቸው ይታወቃል። ይሁንና የመንግስት ሰራተኞች ወደ ስራ ገበታቸው ለመመለስ ወደ መስሪያ ቤታቸው ሲያቀኑ ለ14ቱ የስራ ስንብት ደብዳቤ ተሰጥቷቸዋል። …

መስከረም ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጸረ ሙስና ኮሚሽን  በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ውስጥ ስላለው የንብረት አስተዳደር አሰራር ስርዓት ጥናት አካሒዶ ከፍተኛ የገንዘብ ጉድለት መገኘቱን አረጋግጧል። በጥናቱ የተለየው የመጀመሪያው ችግር እቃዎች ተገዝተው ወደ ንብረት ክፍል ከመግባታቸው በፊት ንብረት ክፍሉን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደረግ የሚያስችለውና ወጥነት ያለው የማሳወቂያ ስርዓት አለመሰራት ነው፡፡ አብዛኛዎቹ ግዥዎች ከተፈጸሙ …

መስከረም ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በፕሮፌሰር ባደግ በቀለ የሚመራውና የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትን በተለይም የአመራር ሥልጠናዎችን በአገር ውስጥ በማስተማር የሚታወቀው ኢንተርናሽናል ሊደርሺፕ ኢንሰቲትዩት  በትምህርት ሚኒስቴር ስር ካለው የከፍተኛ ትምህርት አግባብነት ጥራት ኤጀንሲ ጋር ውዝግብ ውስጥ መግባቱ  ታውቋል። የሁለቱ አካላት ውዝግብ መነሻ ምክንያቱ ተቋሙ ሳይፈቀድለት በዶክትሬት ዲግሪ ከፍተኛ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር በመጀመሩ ነው፡፡ የከፍተኛ ትምህርት …

መስከረም ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር የሪፐብሊካን እና የዲሞክራቲክ ፓርቲ አባላት በአዲሱ በጀት ላይ ስምምነት ላይ ባለመድረሳቸው ሳቢያ  በርካታ መስሪያ ቤቶችና  ተቋማት በከፊል እየተዘጉ ነው።  ሪፐብሊካኑ የምክር ቤት አባላት በጀቱን ለማጽደቅ  የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ   የህክምና ፖሊሲ ማሻሻያ፤ በእግሊዝኛው አጠራር “ሄልዝ ኬር ሪፎርም” ሊዘገይ ይገባል  የሚል አቋምን እንደ ቅድመ-ሁኔታ አስቀምጠዋል። በዚህም ምክንያት …

መስከረም ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየአገሩ የተመደቡ የትኬት ሽያጭ ወኪሎች የተሸጡና ያልተሸጡ ቁጥሮችን በመለየት እስከ ኦክቶበር 8፣ በስልክ ወይም በኢሜል እንድታስታውቁ እንጠይቃለን። ትኬቱን እስካሁን ያልገዛችሁ ውድ የኢሳት ቤተሰቦችና ደጋፊዎች የቀሩትን ጥቂት ቀናት በመጠቀም ከአካባቢያችሁ ካሉ ወኪሎች ወይም በኦን ላይን ትኬቶችን መግዛት የምትችሉ መሆኑን ለማስታወስ እንደወዳለን። ትኬቶችን ሽጣችሁ የጨረሳችሁ ደግሞ በኢሳት አካውንት ገንዘቡን ገቢ …

መስከረም ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፓርቲው አመራሮች በዛሬው እለት ተሰብስበው ትናንት እሁድ ፓርቲው የጠራውን ሰለማዊ ሰልፍ ውጤት ገምግመዋል። መስቀል አደባባይ ብንሄድ ኖሮ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ሊገኝ እንደሚችል የተናገሩት አቶ ደንኤል፣ በከፍተኛ አፈና ውስጥ የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ከ80 ሺ በላይ በሆነ ህዝብ መካሄዱ የተሳካና ለሚቀጥለው ሰልፍ ፍንጭ የሰጠ፣ ህዝቡ ለውጥ ፈላጊ መሆኑንና ከፓርቲያቸው …

መስከረም ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ አንዳርጋቸው ይህንን የተናገሩት በኖርዌይ ከተካሄደው ደማቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በሁዋላ ነው። የግንቦት7 ዋና ጸሀፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው  የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቱ በአንድ በኩል በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል አባላት ላይ ከፍተኛ መነቃቃት የሚፈጥር በሌላ በኩል ደግሞ የተጣለብን ህዝባዊ አደራ ከፍተኛ መሆኑን የሚያስታውሰን ነው ብለዋል። በቅርቡ ከኢትዮጵያ አየር ሀይል ከድተው የሄዱት …

መስከረም ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዩጵያ አቆጣጠር በ2000 ዓ.ም በአውሮፓውያኑ በ2008  ወደ ገበያ የገቡት የባለ አምስት እና ባለ አንድ ብር የመገበያያ ኖቶች ከተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ በታች በሆነ ጊዜ ውስጥ ከገበያ መውጣታቸውን የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ ገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደሚለው ገንዘቦቹ የወደሙት የአገልግሎት ጊዚያቸው አብቅቶ በመቀደዳቸው ፣ በመቆረጣቸው፣  በመንተባቸው ወይም  በመታሸታቸው ነው። ብሮችን የሚቀብሩ …

መስከረም ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ ለኢሳት እንደገለጹት፣ ሊቀመንበሩን ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን ጨምሮ በርካታ የፓርቲው አመራሮች ቅስቀሳ በማድረግ ላይ እያሉ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው ለሰአታት ታግተው አርፍደዋል። ምንም እንኳ የአዲስ አበባ መስተዳደር  በመጪው እሁድ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርግ ለፓርቲው ፈቃድ ቢሰጥም ፣ ፖሊስ በበኩሉ ፓርቲው ቅስቀሳ ለማድረግ ከፈለገ …

መስከረም ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወራት በፊት በቁጫ ወረዳ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ታስረው የነበሩ 40 ሰዎች ተፈቱ። አስተባባሪ ናቸው በሚል የታሰሩት መቶ አለቃ ማሴቦ ማዳልጮ ግን ሳይፈቱ ቀርተዋል። ሰዎቹ ከ3 ወራት በፊት ፍርድ ቤት እንዲፈቱ ውሳኔ ቢያስተላልፍም ፖሊስ በራሱ ስልጣን አልፈታም ብሎ መቆየቱን በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል። ይሁን እንጅ እስረኞቹ በትናንትው እለት ተለቀው ከቤተሰቦቻቸው …

መስከረም ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አይን እማኞች እንደገለጹት ባለፉት 3 ቀናት ከ30 በላይ የሚሆኑ ታንኮችን እና የጦር መሳሪያዎችን የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ሰሜናዊ ክፍል አቅንተዋል። መንግስት የጦር መሳሪያዎችን ለማንቀሳቀስ ለምን እንደፈለገ የታወቀ ነገር የለም። አንዳንድ ወገኖች እንደሚገምቱት በትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ አማጽያን የሚፈጥሩትን ስጋት ለመቋቋም ተብሎ የተወሰደ እርምጃ ሊሆን ይችላል። በጉዳዩ ዙሪያ …

መስከረም ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከንቲባ ድሪባ ኩማ የሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የያዘውን የአምስት ዓመት ዕቅድ ሰሞኑን ባካሄደው ስብሰባ ወደሁለት ዓመት ካጠፈ በኋላ በሚቀጥሉት ሁለት አመታት የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ያረጋግጣል ያለውን መልሶ ማልማት ሥራ በሰፊው እንደሚያከናውን አስታውቆአል፡፡ በዚህ የመልሶ ማልማት ሥራ በመሃል ከተማ የሚገኙ በርካታ ቁልፍ ቦታዎች የሚፈርሱ ሲሆን ነዋሪዎችም የመፈናቀል አደጋ ተደቅኖባቸዋል፡፡ …

መስከረም ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ አርክቴክቸር፣ ሕንጻ ግንባታ እና ከተማ ልማት ኢንስቲትዩት ከጀርመኑ ባዉሃዉስ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ዊመር እና ከደቡብ ሱዳኑ ጁባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ከሶስቱም ዩኒቨርሲቲዎች በተውጣጡ ተማሪዎች አማካይነት በ10 ቀናት ውስጥ  የባለ አንድ ፎቅ ተገጣጣሚ ሕንጻ ገነባ፡፡ ይህ በዓይነቱ አዲስ የሆነውን ቴክኖሎጂ በነገው ዕለት ይፋ ለማድረግ ፕሮግራም ተይዞአል፡፡ …

መስከረም ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየአመቱ በኢትዮጵያውያን የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው ደመራ በአል በመላ አገሪቱ ተከብሮአል። በአዲስ አበባ የሀይማኖቱ አባቶች ፣ የመንግስት ባለስልጣናትና የውጭ አገር ዲፕሎማቶች በተገኙበት ተከብሮአል።

መስከረም ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ፣ “ኢህአዴግን የፈተነ ወሳኝ ክስተት” በማለት የገለጸውን የሙስሊሞች እንቅስቃሴ አልሻባብ፣ አልቃይዳ ፣ ግንቦት ሰባት ፣ እና የኤርትራ መንግስት እንደሚደግፉት በተደጋጋሚ በመገናኛ ብዙሀን ቢገልጽም፣ ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ ደግሞ የደህንነት ሀይሎች ቱጃሩን ሼክ ሙሀመድ ሁሴን አላሙዲንን ከእንቅስቃሴው ጀርባ እንዳሉበት የሚጠቁም መረጃ ለመንግስት ባለስልጣናት ማቅረቡ ታውቋል። በቅርቡ በወልድያ …

መስከረም ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ጎንደር ዞን ደልጊ አካባቢ  ከግጦሽ ሳር ጋር በተገናኘ በተነሳ ግጭት የአካባቢው ኗሪዎች በወሰዱት የመከላከል እርምጃ የፖሊስ አዛዡ ህይወት አልፏል፡፡ የፖሊስ አዛዡ  ነዋሪዎችን “  መሬት የመንግስት በመሆኑ በተከለከለ ቦታ ላይ ከብቶችን ማሰማራት እንደማይችሉ መናገሩን ተከትሎ ነዋሪዎቹ ” መሬት የኛ መሆኑን ነው የምናውቀው፣ መሬት የህዝብ እንጅ የመንግስት አለመሆኑን ነው …

መስከረም ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲሱ የኮምኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን ከቻይና ከህዝብ የፖለቲካ ምክክር መድረክ ምክትል ሊቀመንበር ጋር ባደረጉት ውይይት ኢትዮጵያና ቻይና የመገናኛ ብዙሀንን በተመለከተ ተቀራርበው መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል። ሁለቱም ልማታዊ መንግስታት በመሆናቸው በመገናኛ ብዙሀን ረገድ የሚሰሩት ብዙ ስራዎች አሉዋቸው ያሉት አቶ ሬዲዋን፣ የቻይናን ብሄራዊ ቴሌቪዥንና የዢኖዋን እንቅስቃሴ አድንቀዋል። ቻይና …

መስከረም ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ ባወጣው መግለጫ ዲቪ 2015 በፈረንጆች አቆጣጠር ኦክቶበር 1 ተጀምሮ ኖቬንበር 2 ይጠናቀቃል ብሎአል።

መስከረም ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመተከል ዞን በሚገኙ ከተሞች እንዲሁም በአዊ ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ካለፉት 3 ወራት ጀምሮ መብራት እንደተቋረጠባቸው ለዘጋቢያችን ገልጸዋል። በፓዊ የኤሊክትሪክ ሐይል መቆጣጠሪያ እና ማከፋፋያ ዲስትሪክት ስር የሚገኙት እና የቢኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ወረዳዎች፤ወንበራ ፤ ጉባ ፤ድባጢ ፤ ግልገል በለስ ፤ፓዊ ፤ ዳንጉር ፤ ማንኩሺ ፤ማንዱራ ፤ ማንቡክ፤ …

መስከረም ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዶ/ር ነጋሶ  ዛሬ ከቀኑ 9 ሰአት ላይ ሽሮ ሜዳ በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ እንዲታሰሩ መደረጉን  የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ  አቶ ዳንኤል ተፈራ ከገለጹ ከሰአታት በሁዋላ ፣ ሊቀመንበሩ ማምሻውን ተፈትተዋል። አንድ ግለሰብ “የፓርቲው የሰላማዊ ሰልፍ የቅስቀሳ ግብረሀይል አባላት ያለፍላጎቴ ፎቶግራፍ አንስተውኛል” በሚል ክስ መመስረቱን ተከትሎ ፣ የቅስቀሳ አባላቱ መያዛቸውንና …

መስከረም ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ካለፉት 8 ቀናት ጀምሮ ስብሰባ ላይ ሲሆኑ የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ ዋነኛው የመነጋገሪያ አጀንዳ መሆኑ ታውቋል። ከመቶ አለቃ በላይ ማእረግ ያላቸው ወታደራዊ መኮንኖች ስብሰባዎችን እያካሄዱ ያሉት የጄኔራሎች ስብሰባ ከወር በፊት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው። በጄኔራሎቹ ስብሰባ ላይ ለሰራዊቱ የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ ተነስቶ የነበረ ቢሆንም፣ …

መስከረም ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአቶ በረከት ስምኦን በተመራው የኢህአዴግ ማእከላዊ ኮሚቴ ውይይት ላይ ፣ የሀይማኖት አክራሪነት ከምርጫ 97 ቀጥሎ ከፍተኛ ፈታኝ አደጋ እንደሆነ ከተገለጸና ውይይት ከተካሄደ በሁዋላ የአገሪቱ ሲቪል ሰርቪስ የሀይማኖት ጉዳይን እንደ አንድ የእድገት መመዘኛ መስፈረት እንዲተገብር ስምምነት ላይ ተደርሷል። በጉባኤው ላይ የሐይማኖት አክራሪነት የመንግስትን ተቋም በማፈራረስ እና ተከታዮቹ ነፍጥ አንስተው …

መስከረም ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ምክርቤት ወይንም ፕሬስ ካውንሰል ለማቋቋም ኃላፊነቱን የተረከበው ጊዜያዊ ኮምቴ የካውንስሉን መስራች ጉባዔ መጥራት እንዳልቻለ ተጠቆመ፡፡ በኢህአዴግ  ደጋፊነት በሚታወቁት ወ/ሮ ሚሚ ስብሃቱ የሚመራው ጊዜያዊ መስራች ኮምቴ ፕሬስ ካውንስሉን እንዲመሰረት ኃላፊነት ቢሰጠውም አመራሩ እርስበርስ ባለመግባባቱና ከብዙሃኑ ጋዜጠኞች አዎንታዊ ምላሽ ባለማግኘቱ የምስረታውን ጉዳይ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ጥሎታል፡፡ ይህ …

መስከረም ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቅዳሜ  ከቀኑ 14 ሰዓት ጀምሮ  ሙሉ ሌሊቱን ጭምር  በደማቅ ሁኔታ በተከበረው የኢሳት 3ኛ ዓመት በዓል ላይ ‘ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በርካታ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል። በዝግጅቱ ኢሳት ከየት ተነስቶ የት ላይ እንደደረሰ በስፋት ያብራሩት የድርጅቱ ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ነዓምን ዘለቀ፤ኢሳት ለወደፊቱ መድረስ  ያለበትን ደረጃ አስመልክቶ  የተሰነቀውን ራዕይ ጠቁመዋል። ከፓናል ውይይቱ ተሳታፊዎች …

መስከረም ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ አየር ሃይል በመተው ሰሞኑን ግንቦት 7ትን  ከተቀላቀሉት አብራሪዎች እና የበረራ አስተማሪዎች መካከል የተዋጊ ሄሊኮፕተር ተዋጊና አዛዥ የሆኑት ካፒቴን አክሊሉ መዘነ ዛሬ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ በአንድ ወቅት በገናናነቱ የሚታወቀው የኢትዮጵያ አየር ሐይል አሁን ያለበት ደረጃ የሚያሳፍር መሆኑን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ ሰፍኖ አየር ሀይሉ ተመልሶ የሚገነባበት ጊዜ እንደሚመጣ …

መስከረም ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መስከረም 12 እና መስከረም 19 ሰማያዊ እና አንድነት ፓርቲዎች በተከታታይ የጠሩዋቸው ሰልፎች በመስቀል አደባባይ እንደማይካሄዱ የአዲስ አበባ መስተዳድር ህዝባዊ ስብሰባ ማስታወቂያ ክፍል አስታውቋል። ጽህፈት ቤቱ ይህን ያስታወቀው ከሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ጋር ውይይት ካደረገ በሁዋላ ነው። ይህንን ውሳኔ ተከትሎ ፓርቲው ባወጣው መግለጫ ” ህዝባዊ አገልግሎት የሚሰጥ ቦታ ለዜጎች ሁሉ …

መስከረም ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በቆላማና ከፊል  ቆላማ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ  አርብቶአደሮች ባለፉት 20 ዓመታት በአካባቢው በተደጋጋሚ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ለከፍተኛ ጉስቁልና መዳረጋቸው ታውቋል። በቦረና ዞን ብቻ በ2005 ዓ.ም 30 ሺህ 216  እንስሳት  በድርቅ  ሲያልቁ፣  በ2004 ዓ.ም ደግሞ 10 ሺህ 609 እንስሳት አልቀዋል፡፡ በማኅበራዊ ጥናት መድረክ የአካባቢ ጉዳዮች ተመራማሪ የሆኑት አቶ  አለባቸው …

መስከረም ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ሙርሲ ስልጣናቸውን በሀይል ከተነጠቁበት ጊዜ ጀምሮ ግብጽ ሰላም ማግኘት አልቻለችም። የአገሪቱ  መንግስት የፕሬዚዳንት ሙርሲን ደጋፊዎች ለማደን በሚያደርጉት ጥረት አንድ የፖሊስ ጀኔራል ተገድለዋል። መንግስት በርካታ የፕሬዚዳንቱን ደጋፊዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ሲያስታውቅ፣ ደጋፊዎቹ ግን ራሳቸውን መሰራያ በማስታጠቅ መንግስት ለመፋለም ቆርጠው መነሳታቸው ይነገርላቸዋል። መንግስት በያዘው አቋሙ ከገፋበት ግብጽ ዳግም ሶሪያ ልትሆን …

መስከረም ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ አራት አብራሪዎች ፣ የበረራ አስተማሪዎች ስርአቱን ከድተው ግንቦት7ትን መቀላቀላቸው ታውቋል። ከኢትዮጵያ አየር ሀይል በመለየት ግንቦት 7ትን መቀላቀላቸውን ለኢሳት ያረጋገጡት የበረራ ባለሙያዎች በአየር ሀይል ውስጥ የተንሰራፋውን ዘረኝነትና አድሮ ለርምጃው እንደገፋፋቸው አመልክተዋል። በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ ከዘረኝነትና አድሎው ባሻገር በሰራዊቱ ውስጥ የተስፋፋው ሙስና ተቋሙን …

መስከረም ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦህአዴድ፣ ብአዴን፣ ኢህዴንና ህወሀት ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ካለፈው እሁድ ጀምሮ በየክልሎቻቸው ተሰባስበው ግምገማ እያደረጉና ስልጠናም እየወሰዱ መሆኑን ከድርጅቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ለ10 ቀናት በሚቆየው ስልጠና አመራሮቹ እርስ በርስ ከመገማገም ባለፈ ስለ ልማት ሰራዊት አደረጃጀት፣ ስለ አንድ ለአምስት  አተገባበር ፣ አክራሪነትና ኪራይ ሰብሳቢነት እንዲሁም በመጪው አመት ስለሚካሄደው አገራቀፍ ምርጫ ስልጠናዎች …

መስከረም ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ሁለቱ ፓርቲዎች የጠሩዋቸውን ሰልፎች ተከትሎ በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የሚገኘው መንግስት በዛሬው እለት በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የሚገኙ ሊስትሮዎችን፣ በጎዳናዎች ላይ እቃዎችን የሚሸጡትን በጸጥታ ሀይሎቹ አማካኝነት  እንዲሰበሰቡና ወደ አልታወቀ ስፍራ እየወሰዱዋቸው ነው። የሚታፈሱት ሰዎች ወዴት እንደሚወስዱ ባይታወቅም ከአንዳንድ ሰዎች  ባገኘነው መረጃ ሰዎቹ ፓርቲዎቹ ያዘጋጁት ሰልፍ እሲከጠናቀቅ ታግተው ይቆያሉ። …

መስከረም ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-33ቱ ፔቲሽን ፈራሚ ፓርቲዎች ባወጡት መግለጫ ፣ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰላማዊ ትግላቸውን ለማስፋት በተጠናከረ መንገድ እየተንቀሳቀሱ ቢሆንም፣ መንግስት የህግ ጥበቃ ሊያደርግ ባለመቻሉ ከፍ ያለ ጉዳት እየደረሰባቸው ነው ብለዋል። አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ በወላይታ፣ በአርባ ምንጭ፣ በፍቼና፣ በጎባ ከተሞች በተንቀሳቀሰባቸው ወቅቶች አባሎቻቸው መደብደባቸውን፣ መታሰራቸውን፣ የሥራ መሣሪያዎቻቸውን መነጠቃቸውን፣  ለመኝታ ገንዘብ የከፈሉበት …

መስከረም ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጋዜጠኛ ርዕዮት ዐለሙን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን  እና አሜሪካዊው  ኤድዋርድ  ስኖውደንን ጨምሮ  ሰባት  ሰዎች የአውሮፓ ህብረት ለነፃነት ታጋዮች በየአመቱ ለሚያዘጋጀው የ “ሻካሮቭ ሽልማት” የ2013  ዕጩ ሆነው ተመረጡ። የአውሮፓህብረት የሻካሮቭ ሽልማት ኮሜቴ-ከህብረቱ የውጪ ጉዳይና ልማት ኮሚቴ እና ከሰብዓዊ መብት ንዑስ ኮሚቴ ጋር በመሆን ትናንት ሰኞ ይፋ እንዳደረጉት  ማላላ ዩሳፍዛይ ከፓኪስታን፣ ኤድዋርድ ስኖውደን …

መስከረም ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ8 ሺ 800 በላይ ሰዎች በመልሶ ማልማት የተነሳ እንደሚፈናቀሉ ከክልሉ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።  ተፈናቃዮች እንደሚሆኑ ያወቁ ነዋሪዎች በከፍተኛ የኑሮ ችግር ውስጥ ወድቀናል ሲሉ አማረዋል።በአማራ ክልል በሚገኙ በሶስቱ የክልሉ ሜትሮፖሊታን ከተሞች ማለትም በባህርዳር፣ደሴና ጎንደር በመልሶ ልማት የሚፈናቀሉ 5 ሳይቶች ተለይተው ተከልለዋል፡፡  በባህርዳር  በመጀመሪያው ዙር  431 የቀበሌ ቤት ተከራዮች ፣ 2 …

መስከረም ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከስድስት አመታት በፊት በኬንያ ከተደረገው ምርጫ ጋር በተያያዘ ለተገደሉት ሰዎች ተጠያቂ የተደረጉት የአገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ዘ ሄግ በሚገኘው አለማቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት በአካል ቀርበው የመጀመሪያዋን የጉዳቱ ሰለባን ቃል አዳምጠዋል። ማንነቷ በውል ያላታወቀችው መስካሪ በረብሻው ጊዜ የደረሰውን ግፍ በዝርዝር አስረድታለች፡፤ ም/ል ፕሬዚዳንቱ ክሱን ውድቅ ማድረጋቸው ታውቋል። ሌሎች 22 …

መስከረም ፮(ስድት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲስ ፓርቲው ባወጣው መግለጫ ምንም እንኳ የአዲስ አበባ መስተዳደር ለሰልፉ  በ12 ሰአታት ውስጥ መልስ የመስጠት ሀላፊነት የነበረበት ቢሆንም ይህን አላዳረገም።  ፓርቲው የሚጠበቅበትን ሁሉ ለሚመለከተዉ አካል የማሳወቅ ግዴታ በአግባቡ ስለተወጣና ለሰልፉም የሚያስፈልጉ ስራዎች እየተከናወኑ በመሆኑ መስከረም 12 ቀን 2006 ዓ.ም በታቀደው መሰረት ሰልፉ ይካሄዳል ብሎአል፡፡ በዚህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ የምናነሳቸው ጥያቄዎች …

መስከረም ፮(ስድት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲስ ከስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን የተገኝው መረጃ እንደሚያመለክተው ከተለያዩ የፌደራል መስሪያ ቤቶች 734 ሚሊዮን 6 መቶ ሺ ብር የመዘብሩ የስራ ሃፊዎች በተጣራ መረጃ ክስ ቢመሰረትባቸውም የውሳኔ ቅጣት እንዳልተላለፈባቸው ታውቋል። ለረጅም ጊዜ በተደረገ ምርመራ ተጣርቶና መስረጃ ተገኝቶባቸው ከ2004 ዓም ጀምሮ ክስ የተመሰረተባቸው የተለያዩ የሙስና ወንጀሎች የውሳኔ ሀሳብ እንዳልተላለፈባቸው ከመሰሪያ …

መስከረም ፮(ስድት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲስ በኢንዱስትሪ ዘርፍ ባለፈው ዓመት የተመዘገበው የወጪ ንግድ (ኤክስፖርት) አፈጻጸም እጅግ አነስተኛ እንደነበር ከኢንዱስትሪ ሚ/ር የተገኘ መረጃ አመለከተ፡፡ በ2005 የኢትዮጵያዊያን በጀት ዓመት ከጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ ከቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ከአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ ከፋርማሲዩቲካልስና ከኬሚካል የወጪ ንግድ 542 ሚሊዮን  4 መቶ ሺ ዶላር ለማግኘት ታቅዶ ማሳካት የተቻለው 281 ሚሊዮን  2 መቶ ሺ  ዶላር ወይንም 52 በመቶ …

መስከረም ፮(ስድት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲስ ከዓመት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ለ14 ወራት በቃሊቲ እስርቤት ከታሰሩ በኋላ  ተፈተው የወጡት ስዊድናውያን ጋዜጠኞች  ማርቲን ሺቢ እና ዩዋን ፐርሹን እንዲሁም ዓለምዓቀፍ የሰብዓዊና የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅቶች ተወካዮች፡ ጋዜጠኞችና በስዊድን የሚኖሩ በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እና ስዊድናውያን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባዘጋጀው ደብዳቤ ላይ ፊርማቸውን በማኖር  ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ  የታሰሩ ጋዜጠኞችን እንዲፈቱ ጠይቀዋል። ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ኢትዮጵያ ውስጥ …

መስከረም ፮(ስድት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አዲስ አበባ በተለምዶ አንበሳ ግቢ ተብሎ በሚጠራው የአንበሶች ማቆያ ማእከል ውስጥ ዛሬ ከጠዋቱ 1:30 ላይ  የአንበሶች መጋቢ የነበሩ ግለሰብ በ አንበሳ መበለታቸውን ራዲዮ ፋና ዘገበ። እንደራዲዮጣቢያውዘገባአደጋው የተከሰተው   በዛሬው እለት ተረኛ ተንከባካቢ የነበሩት እና አቶ  አበራ ሲሳይ የተባሉትየአንበሶቹ መጋቢ፥ የአንበሶቹን ማዳሪያ እያጸዱ ባሉበት ወቅት ነው። ከጥንቃቄ ጉድለት ባልተዘጋው በር የገባውና  መጋቢውን ለህልፈተ ህይወት የዳረጋቸው አንበሳ ስሙ-ቀነኒሳ እንደሆነም ራዲዮው ጨምሮ ዘግቧል። የግለሰቡን ህይወት ለማትረፍ በወቅቱ በስራ ላይ የነበሩ የግቢው ሰራተኞች ጥረት ቢያደርጉም-ሳይሳካ መቅረቱንም ለማወቅ ተችሏል። የሟች አስከሬን ከመንከባከቢያ ስፍራው ወጥቶ ወደ ምኒሊክ ሆስፒታል ተወስዷል። የዚህ አይነት አደጋ  በ19 89 ዓ.ም መከሰቱ የሚታወስ ነው።

መስከረም ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርቲው የምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካርያስ የማነብርሀን እንደገለጹት የአዲስ አበባ መስተዳድር ከተማሪዎች ትምህርት መጀመር እና ከተለያዩ የአዲስ አመት በአላት ጋር በማያያዝ ፓርቲው ሰልፉን በሁለት ሳምንት እንዲያራዝም በተጠየቀው መሰረት፣ ጥያቄውን ተቀብሎ ለማራዘም ፈቃደኛ ሆኗል። መስተዳድሩ ፓርቲው ተቃውሞውን መስከረም 19 ማካሄድ የሚችል መሆኑን ከመስተዳድሩ ወረቀት አግኝቷል። አቶ ዘካሪያስ መስተዳድሩ ሰላማዊ ሰልፉን …

መስከረም ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እውቋ የብእር ሰው፣ የነጻነት ታጋይ፣ የዩኒስኮና የኢንተርናሽናል ውሜንስ  ሚዲያ ፋውንዴሽን አሸናፊ ጸሀፊና መምህርት ርእዮት አለሙ ዛሬም በረሀብ አድማው ገፍታበታለች። እህቷ እስከዳር አለሙ እንደገለጸችው ዛሬ እርሷና የርእዮት እጮኛ የሆነው ስለሺ ሀጎስ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ቢሄዱም እንዳይገቡ ተከልክለዋል። እጮኛዋ ስለሺ ለሰአታት ታግቶ በማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች መደብደቡንም እስከዳር ተናግራለች  ርእዮት ከእናት፣ …

መስከረም ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ መንግስት በቀጣዩ ዓመት በሚጠናቀቀው የአምስት ዓመት  ዕቅዱ በስኳር ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለመገንባት ያቀደውን እንደማያሳካ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ። በህወሃት ነባር ታጋይ አቶ አባይ ጸሐዬ የሚመራው የስኳር ኮርፖሬሽን ከነባርና ዕውቀትና ልምዱ ካላቸው ባለሙያዎች ጋር ተግባብቶ መስራት ባለመቻሉ ብዙዎቹ ኮርፖሬሽኑንና በስሩ ከሚገኙ የስኳር ፋብሪካዎች ለቅቀዋል፡፡ ኮርፖሬሽን የገጠመውን የሰለጠነ የሰው ኃይል …

መስከረም ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአቶ መለስን ፋውንዴሽን ለመገንባት መንግስትና የመለስ ፋውንዴሽን በጋራ በመንቀሳቀስ ላይ ባሉበት በዚህ ጊዜ፣ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ልኡካን ለፋውንዴሽኑ ግንባታ የሚውል 50 ሺ ዶላር ለመለገስ ቃል መግባቱዋን የልኡካን ቡድኑ መሪ ሚስተር ዛሆ ገልጸዋል። አቶ መለስ በቻይናና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት እንዲጠናከር በማድረጋቸው  ልኢካኑ አመስግነዋቸዋል። ቻይና የኢትዮጵያን የአምስት አመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ …

መስከረም ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ  ከፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት የወጣውን መግለጫ በመጥቀስ እንደዘገበው፤  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማራዘም ያስፈለገው  ከአገሪቱ የ ደህንነት ሁኔታ ጋር በተያያዘ ነው። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተደነገገው ባለፈው ነሐሴ ወር  በመሀመድ ሙርሲ ደጋፊዎች ላይ የግብጽ ፖሊስና መከላከያ የሀይል እርምጃ መውሰዳቸውን ተከትሎ ነው። የፕሬዚዳንት መሀመድ ሙርሲን ከስልጣን መወገድ በተቃወሙ ደጋፊዎቻቸው ላይ በተወሰደው እርምጃ  …

መስከረም ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ምዕራብ ሩሲያ በሚገኝ በ አንዳ ሳይካተሪክ ሆስፒታል ውስጥ በተነሳ የ እሳት አደጋ 37 ሰዎች መሞታቸውን  ባለስልጣናት ገለጹ። “ኖቭጎሮድ” ተብሎ በሚጠራው ግዛት በ”ሉካ” መንደር ውስጥ ከእንጨት በተሠራው ሆስፒታል ውስጥ ወደ 60 ሰዎች እየታከሙ ነበር። የሩሲያ ብዙሀን መገናኛ ሪፖርቶችን በመጥቀስ ቢቢሲ እንዳለው፤ ህሙማኑን ትንከባከብ የነበረች አንዲት ነርስም ከሟቾቹ መካከል ትገኝበታለች። …