ጋዜጠኛ ርእዮት አለሙ በረሀብ አድማው ገፍታበታለች
መስከረም ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዩኒስኮና የ’ኢንተርናሽናል ዊመንስ ሚዲያ ፋውንዴሽን’ ሽልማቶች አሸናፊ የሆነቸው ታዋቂዋ ፀሀፊና መምህር ርእዮት አለሙ በእስር ቤት የጀመረቸውን የረሀብ አድማ የቀጠለች ሲሆን፣ በእስር ቤት የሚገኙ ሌሎች እስረኞች እያሰቃዩዋት መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል። በግፍ የታሰረቸው ርእዮት ይቅርታ ለመጠየቅ ፈቃደኛ ባለመሆኑዋ የሚደርስባት ስቃይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው። ሆን ተብሎ በተቀነባበረ ስልት ርእዮት ከእናትና …