ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ስማቸው እንደይጠቀስ የፈለጉ በኢትዮጵያ መብራት ሃይል ስር የሚሰሩ ሰራተኞች ለኢሳት እንደገለጹት በአዲስ አበባ የሚታየው የመብራት ሃይል መቆራረጥና መጥፋት ነዋሪውን ለስቃይ እየዳረገው ነው። እናቶች የአቦኩትን ሊጥ ለመጋገር ሲዘጋጁ መብራት ይጠፋና ሊጡ የሚደፋበት ጊዜ መኖሩን የሚናገሩት ሰራተኞች፣ ነዋሪዎች ምሬታቸውን ለመስሪያ ቤቱ በማቅርብ መልስ ሲያጡ የመብራት ሃይል ሰራተኞች ለጥገና ሲንቀሳቀሱ …

ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ረቂቅ አዋጁ ሁለቱ ሀገራት በወንጀል የጠረጠሩትን ዜጎች በመያዝ ለፈላጊው ሀገር አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችላቸው ነው፡፡ በረቂቅ አዋጁ ላይ እንደተመለከተው በዚህ ትብብር መሰረት መረጃው በሚፈለገው ሀገር አግባብነት ባለው ተቋም ህጋዊ መጠየቂያ ደብዳቤ መሰረት ለተጠያቂው ሀገር በመላክ ይከናወናል ይላል፡፡ ስምምነቱ በተጠርጣሪ ወንጀለኞች ጉዳይ ማስረጃዎችን የመሰብሰብ፣ ቃል የመቀበል፣ የሚያዙ ሰዎችን ወይንም …

ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅዱስ ላሊበላ ገዳም የሰው ሃይል አስተዳደር የሆኑት ቀኝ ጌታ በላይ አናውጥ ከልዩ ልዩ አካባቢ ለመጡ ጋዜጠኞችና ጎብኝዎች እንደ ገለጹት ገዳሙ በዝናብና ጸሃይ እየደረሰበት ያለው ጉዳት ቅርሶቹን በአስከፊ ደረጃ እያፈረሳቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ቅርሶቹን ከጸሐይና ዝናብ ይከላከላል ተብሎ ከለጋሽ ሃገሮች በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የተሰራው መጠለያም ምሰሶዎች ብረት የተተከሉት በቤተ …

ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግሪሳ ወፍ በሰብል ላይ ጉዳት ሳያደርስ ለመከላከልና ብሎም ለማጥፋት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የፌዴራል ግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ዛሬ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የሰጡት በፌዴራል ግብርና ሚኒስቴር ከፍተኛ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ከበደ ላቀው እንዳሉት በኦሮሚያ ክልል ዝዋይና መቄ አካባቢዎች 8 ሚሊዮን ሚጠጋ የግሪሳ ወፍ ተከስቷል፡፡ በአማራ …

ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የመንግስት ሃብትና ንብረትን ላለፉት ሶስት አመታት የህዝብን ሃብት በህገወጥ መንገድ በማባከን ሪኮርድ የሰበሩ መንግስታዊ ተቋማት እርምጃ እንዳልተወሰደባቸው ለተወካዮች ምክር ቤት ያዘጋጀው ሪፖርት ያመለክታል። የተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ ግምገማው ለኢትዮጵያ ህዝብ መቅረብ የለበትም ብለዋል። ባለፉት 3 አመታት ሂሳባቸውን በወቅቱ ያልዘጉ መ/ቤቶች …

ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት በአሚባራ በአፋርና በኢሳ መካከል የተነሳውን ግጭት  ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ አባላት በወሰዱት እርምጃ አንድ ሰው ገድለው ሌላ የአፋር ተወላጅን ደግሞ አቁስለዋል። በአካባቢው ውጥረቱ አሁንም መቀጠሉን ገልጸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ከትናንት ጀምሮ ገዋኔና ቡድመዳ ወረዳዎች በጎርፍ መጥለቅለቃቸው ታውቋል። የአካባቢው ነዋሪዎች መንግስት በቂ ድጋፍ እያደረገ አይደለም …

ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአቶ ሬድዋን ሁሴን የሚመራው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አሰልጥኖ በፌዴራል የመንግስት ተቋማት በህዝብ ግንኙነት ኃላፊነት ለመደባቸው ካድሬዎች የሁለት ቀናት የማህበራዊ ድረገጾች አጠቃቀም ስልጠና በመስጠት በተለይ በግንቦት ወር ከሚካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ እንዲሳካ የበኩላቸውን አዎንታዊ ሚና እንዲጫወቱ አደራ ተጥሎባቸዋል፡፡ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን እንደገለጸው የኮምኒኬሽን ጽ/ቤቱ በሚኒስትሮች ምክርቤት …

ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በቅርቡ በአዳማ ከተማ   ለጋዜጠኞች ባዘጋጀው ሴሚናር ከኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን ተወክለው በስብሰባው በመገኘት ንግግር ያደረጉት አቶ ናስር ለገሰ ባቀረቡት የኢትዮጵያ ሰፖርት ታሪክ ንግግራቸው የቀደሙት መንግስታትን ስራ በማጣጣል የገዢውን መንግስት ስራ በማግዘፍ ባቀረቡት ጽሁፍ ከጋዜጠኞች ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶባቸዋል፡፡ የገዢው መንግስት አሁን የሚያንቀሳቅሰው ከፍተኛ በጀት ስፖርቱ እንዲጎለብት ለማድረግ …

ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራል ፖሊስ በ2006 በጀት ዓመት በ36 መዝገቦች በኦነግ፣ በግንቦት ሰባት፣ በኦብነግ፣ በጋህነን፣ በቤህነን እንዲሁም በአልሻባብ ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎችን መክሰሱን በመጥቀስ የፌደራል ፖሊስ ሽብርን የመከላከል አቅሙ እንዳደገ በመግለጽ ራሱን አሞካሽቷል፡፡ ፌዴራል ፖሊስ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ ባለፈው ዓመት 36 የሽብር መዝገቦች መካከል በ27 ቱ ላይ ምርመራ ተጠናቆ …

ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የአካባቢው ወኪል እንደገለጸው በሸኮ መዠንገር ተወካዮችና በከፋ፣ ሸካ፣ ጋምቤላና ቤንች የዞን አመራሮች መካከል በሃይማኖት አባቶች አማካኝነት በቴፒ ውይይት እያደረጉ ነው። የአካባቢው ባለስልጣናትን በማናገር እንደዘገበው የንግግሩ ዋና አላማ ሸሽተው በየጫካው ውስጥ የሚገኙ የመዠንገርና የሸኮ ተወላጆች አሳምኖ ወደ ቀያቸው ለመመለስ ነው። ይሁን እንጅ ለድርድር የሄዱ አንዳንድ የመዠንገር ተወላጆች …

ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘጠኝ የኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጥቅምት 11/2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት የትብብር ስምምነት መፈራረማቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ፓርቲዎቹ ነጻ አሳታፊና ታአማኒ ምርጫ እንዲካሄድ በትብብር ለመስራት፣ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋትና የዜጎችን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ በጋራ ለመታገል መስማማታቸውን ትብብር ሰነዱ ላይ አስፍረዋል። ትብብሩን እንዲመሩ  ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ከሰማያዊ ፓርቲ …

ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወኪላችን እንደሚለው በከተማው የታየውን የስኳር እጥረት ተከትሎ፣ አንድ ኪሎ ስኳር እስከ 30 ብር በመሸጥ ላይ ነው። በተመሳሳይ መልኩ የሚታየው የዘይት እጥረት  የነዋሪውን ኑሮ አስከፊ እንዳደረገው ገልጿል። የስኳር እጥረቱ በደቡብ፣ በኦሮምያና በአማራ አካባቢዎችም በስፋት እየታየ ነው። መንግስት የስኳር ፋብሪካዎች ወደ ምርት ሲገቡ ስኳር ወደ ውጭ መላክ እንችላለን በማለት …

ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በክልሉ በሚገኙ የሰሜን ጎንደር ጠረፋማ ወረዳዎች፣ በአዊ፣ በዋግ ህምራ እና በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞኖች የሚገኙ መምህራን ወደ አጎራባች ክልሎች  በመፍለሳቸው  በትምህርቱ ጥራት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እያደረሰ መሆኑን  ባለሙያዎች ገልጸዋል፡፡ ክፍተቱን ለመሸፈን አስረኛ ክፍል ያጠናቀቁ እና በልዩ ልዩ ሙያ የተመረቁ ተማሪዎች እንዲቀጥሩ ለአራቱ ዞኖች ደብዳቤ  ስለደረሳቸው ይህንኑም እየተፈጸሙ …

ጥቅምት ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሰሞኑን አሻሽሎ ያዘጋጀውና የኢህአዴግ ምክር ቤት አባላት እንዲወያዩበት የተዘጋጀው  ሰነድ ለኢሳት የደረሰ ሲሆን፣ ሰነዱ የመንግስት የመረጃና የደህንነት መስሪያ ቤት ወይም ኢንሳ በኢሳት በአሜሪካ እና በጀርመን ድምጾች ላይ እርምጃ እንዲወስድ ከመማጸን ጀምሮ መንግስት በሴቶች፣ በወጣቶችና በምሁራን ስም የሃይማኖት ማህበራትን እንዲቋቋሙ እገዛ እንዲደርግ፣ በሰርተፍኬትና በዲግሪ ደረጃ የሃይማኖት …

ጥቅምት ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመንግስት የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ሬድዋን ሁሴን በተመራውና ሁሉም የክልል መንግስታት የኮሚኒኬሽንና የመገናኛ ብዙሃኖች የተሳተፉበት የኢህአዴግ የምርጫ ዘመቻ ፕሮፓጋንዳ ዝግጅት ባለፈው ቅዳሜ ሲጠናቀቅ ሁሉም የክልል ሚዲያዎች ቀጣዩን ምርጫ ሊያሳምን የሚችል አቀራረብ ፣ ዜና እና ፕሮግራም እንዲየቀርቡ እንዲሁም በምርጫው የኢህአዴግ አሸናፊት ቅኝት ውስጥ ስራዎችን እንዲሰሩ ታዘዋል። ብአዴን በምርጫው ዙሪያ ለከፍተኛ አመራሩ …

ጥቅምት ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምእራብ አርማጭሆ የመከላከያ ሰራዊትን የሚከዱ ወታደሮችን ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ፣ በአካባቢው የሚገኙት ወታደሮች በህዝቡ ላይ የአጸፋ እርምጃ እየወሰዱ ነው። የምእራብ አርማጭሆ ወረዳ ነዋሪዎች እሁድ እለት የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን፣ ለአሁኑ ሰልፍ ምክንያት የሆነው ጥቅምት 7 አንድ ወታደር መጥፋቱን ተከትሎ የአጎቱ ልጅ የሆነ የጤና ባለሙያ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶበት እንዲታሰር ከተደረገ …

ጥቅምት ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በኤርትራ ድንበር አካባቢ በጥበቃ ላይ የሚገኙ ወታደሮች በመረጃ ስህተት ለ33 ዲቃዎች በባዶ ሜዳ ላይ ሲተኩሱ የዋሉ ሲሆን፣ ለጦሩ የተሳሳተ መረጃ በመስጠት መከላከያን አወናብደዋል የተባሉ 5 ወታደሮች ተይዘው እንዲታሰሩ ተደርጓል። ከግንቦት ሰባት ተኩስ ተከፈተ ተብሎ ለማዕከላዊ የጦር ሃይል ሪፖርት የተደረገ ሲሆን ይህን ተከትሎ ከፍተኛ መደናገጥ ተገብቶ …

ጥቅምት ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ በረከት ስምኦን ” የኢሳት ዘጋቢዎችን መቆጣጠር አልተቻለም፣ በውስጣችን ያሉ ሃይሎች ጣሉን” ያሉ ሲሆን፣ ከሚኒስትሮች በስተቀር የደህንነት ሃይሎችም ሆኑ ጋዜጠኞች በፖለቲካ ስብሰባ ላይ ሞባይል ይዘው እንዳይገቡ እንደከለከሉ ትእዛዝ አስተላልፈዋል። አቶ በረከት ከዚህ ቀደም እርሳቸውንና ድርጅታቸውን የተመለከቱ መረጃዎች በኢሳት ተደጋግሞ መውጣት እንዳበሳጫው የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። የኢህአዴግን ምክር ቤት ስብሰባዎች …

ጥቅምት ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተቃዋሚ የፓርላማ አባል የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ ኢትዮጵያ በምግብ ራሱዋን ችላለች በሚል  በተደጋጋሚ ቢነገርም አሁንም ስንዴ ከውጭ እያስገባን ነው በማለት ላቀረቡት ጥያቄ ጠ/ሚንስትሩ “በምግብ ራሳችንን መቻላችንን” አለማቀፍ ተቋማት ሳይቀር ያረጋገጡት መሆኑን በመግለጽ፣ ኢትዮጵያ በአለፈው አመት 300 ሚሊዮን ኩንታል የግብርና ምርት ማምረት መቻሉዋን ገልጸዋል። ይሁን እንጅ የግንቦት20 በአል በሚከበርበት …

ጥቅምት ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጊዜ ሰሌዳ ላይ ለመወያየት ምርጫ ቦርድ በጊዮን ሆቴል የጠራውን ስብሰባ ‹‹ጥያቄዎቻችን የሚመልስ አይደለም›› በሚል ሰማያዊ ፓርቲ ፣ የመላው ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (መኢዴፓ) እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ (ኢብአፓ) ተወካዮች ረግጠው መውጣታቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ (ኢብአፓ) ዋና ጸኃፊ ወ/ት መሊሃ ጀሃድ  ምርጫ ቦርድ እነሱ ላነሱት …

ጥቅምት ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአስር ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ በውሃ ሙላት ህይወቱ ለአደጋ ተጋልጦ በሚገኝበት ወቅት ከመንግስት የሚቀርብላቸው ድጋፍ አነሳ መሆኑን ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ከውሃ ሙላቱ የተረፍነዎች በምግብ እጦት እየተሰቃየን በመሆኑ መንግስት በአፋጣኝ ይደረስልን ሲሉ አቤቱታ አቅርበዋል። አፋጣኝ መልስ ካልተሰጠም እስካሁን ከታየው በላይ አስከፊ የሆነ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል ተፈናቃዮች አስጠንቅቀዋል። ከአፋር ህዝብ እንደተወከሉ …

ጥቅምት ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ዳርፉር ኮርማ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የውሃ ጉድጓድ ሲጠብቁ ከነበሩ ኢትዮጵያውያን መካከል 2ቱ ወዲያውኑ ሲገደሉ አንደኛው በጽኑ ቆስሎ የነበረ ቢሆንም፣ ትንሽ ቆይቶ ህይወቱ አልፎአል። ጥቃቱን የፈጸሙት ታጣቂዎች እነማን እንደሆኑ በውል አልታወቁም።   የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ ግድያውን በጽኑ አውግዘው፣ ግድያውን የፈጸሙት አካላት አለማቀፍ ህግን መጣሳቸውን ማወቅ አለባቸው ብለዋል።

ጥቅምት ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ አፍሪካዊያን ወንድሞቻችንን እህቶቻችን ለመርዳት ፈቃደኛ የሆኑ ኢትዮጽያዊን የህክምና ባለሙያዎችን ከመከላከያ ሰራዊትና ከሌሎችም ተቋማት በሸታው ወደተስፋፋባቸው የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ለመላክ መወሰኑን አረጋግጠዋል፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ እንዳሉት «ኢትዮጽያ በአፍሪካ በሕዝብ ብዛት ሁለተኛዋ ሀገር እንደመሆንዋ መጠን አፍሪካዊያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን ለማገዝ የራሳችን ድርሻ መወጣት አለብን የሚል አቋም ተይዟል፡፡ መከላከያ ሠራዊት ውስጥ …

ጥቅምት ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለድርጅቱ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ለኢሳት እንደገለጹት የኢትዩጵ ያመንግስት ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰባቸውም በማለት እያቀረበ ያለውን ሪፖርት ነዋሪዎቹ አጥብቀው ተቃውመዋል። 87 ሰዎችን በእጃን  ቀብረናል ያሉት ኗሪዎች ዜናው የተነገረው ጉዳት ከደረሰ ከሳምንት በኃላ ሲሆን እርዳታ የመጣውም ብዙ ነገረ ከወደመ ከስድስት ቀናት በሁዋል መሆኑ ችግሩን የከፋ አደርጎታል ሲሉ አመልክተዋል። በድርጊቱ እጅግ …

ጥቅምት ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-99 በመቶ በላይ የኢህአዴግ አባላት በሞሉበት ፓርላማ ውስጥ ብቸኛ የሆኑት የአንድነት ፓርቲ ተመራጩ አቶ ግርማ ሰይፉ፣ በቅርቡ መንግስት ለዩኒቨርስቲ  መምህራን፣ ተማሪዎችና የመንግስት ሰራተኞች የሚሰጠውን የፖለቲካ ስልጠና አስመልክቶ ላቀረቡት ጥያቄ መልስ የሰጡት ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ ውይይቱን ማድረግ ያስፈለገው ትምክህተኞች፣ ጸረ ሰላም ሃይሎችና ጠባቦች የሚረጩት መርዝ ትክክል አለመሆኑን ለማሳየት ነው …

ጥቅምት ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ምንጮች  አቦቦ በሚባለው አካባቢ የተጀመረውን ግጭት ተከትሎ ወታደሮች የሚወስዱትን እርምጃ በመቃወም መንግስት ያስታጠቃቸው ከ15 በላይ ታጣቂዎች ስርአቱን አናገለግልም በማለት መጥፋታቸውንና የመከላከያ ሰራዊት አባላትም ታጣቂዎችን ለመያዝ አሰሳ መጀመራቸውን ገልጸዋል። የመንግስት ታጣቂዎች የነበሩ የጋምቤላ ተወላጆች ከመጥፋታቸው በፊት በመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ በመወሰዱት እርምጃ ከ2 ያላነሱ የመከላከያ አባላት መገደላቸውና የተወሰኑትም …

ጥቅምት ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲዎቹ በደብዳቤያቸው ከዚህ ቀደም ያቀረቡዋቸው ጥያቄዎች መልስ ባለማግኘታቸውና ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጭ እንዳይወጡ በመስጋታቸው ደብዳቤ ለመጻፍ መገደዳቸውን ገልጸዋል። ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው “የፖለቲካ አመራሮችን ማስፈራራት፣ የአካላዊ ጉዳት ማድረስ፣ በሃሰት ውንጀላና የፈጠራ ክስ ማሰር እየተጠናከረ መምጣት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከህዝብ ጋር እንዳይገናኙና አላማቸውን ፣ፕሮግራማቸውንና አማራጭ ፖሊሲዎቻቸውን ለህዝብ እንዳያቀርቡ ማድረግ፣ ገዢው ፓርቲ መንግስታዊ መዋቅርን …

ጥቅምት ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኖርዌይ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ በተጠራ ጉባኤ ላይ የተገኙትን የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በመቃወም የተጠራው ሰልፍ የአገሪቱን ዋነኛ የቴሌቪዥን ጣቢያ ኢነርኬን ሽፋን አግኝቷል። ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት በተጠራው ተቃውሞ፣ ኢትዮጵያውያን የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፣ ኖርዌይ የሰብአዊ መብት ጥሰት ከሚፈጽመው መንግስት ጋር የምታደርገውን ግንኙነት እንድታቆም ጠይቀዋል።በኢትዮጵያ ለሚታየው …

ጥቅምት ፭(አምት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በአዲስ አበባ ለሚገኙ ዜጎቹ ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ አልሸባብ በቦሌ አካባቢ ጥቃት ለመፈጸም እየተዘጋጀ መሆኑን አስተማማኝ መረጃ እንደደረሰው ገልጿል። ኤምባሲው አዲስ መግለጫ እስከሚወጣ ድረስ ዜጎቹ ከሆቴሎች፣ ምግብ ቤቶች፣ የማምለኪያ ቦታዎች፣ ከገበያ ቦታዎችና የመዝናኛ ቦታዎች እንዲርቁ መክሯል። ጥቃቱ የሚፈጸምበት  ትክክለኛ ቦታ ባይታወቅም ፣ የአሜሪካ ዜጎች …

ጥቅምት ፭(አምት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዞን 9 እየተባሉ የሚጠሩት ጸሃፊዎች እና ጋዜጠኞች ፍርድ ቤት ቢቀርቡም ፍርድ ቤት ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት አሰናብቷቸዋል። የተከሳሽ ጠበቆች ላቀረቡት የክስ መቃወሚያ አቃቢ ህግ ምላሽ የሰጠ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ መልስ ለመስጠት ለጥቅምት 25 ቀጠሮ ይዟል። ተከሳሾቹ  ነጭ ልብስ ለብሰው መቅረባቸውን፣ በጥሩ መንፈስና ጥንካሬ ላይ የሚገኙ መሆናቸውን ዘጋቢያችን …

ጥቅምት ፭(አምት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰንደቅ እንደዘገበው ማህበሩ ጥቅምት 1 ቀን 2007 ዓ.ም. በአድራሻ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በግልባጭ ደግሞ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ለኾኑት ለሁሉም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ባሰራጨው ደብዳቤ  ማህበሩ” በማያውቀው፣ ጥፋትም ካለ ተጠርቶ ባልተጠየቀበትና መልስ ባልሰጠበት ኹኔታ ፓትርያርኩ ባሉባቸውና በተለያዩ ጊዜያት …

ጥቅምት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ50 በላይ የመንግስት ፖሊሶች፣ ወታደሮችና ታጣቂዎች የተገደሉበት የደቡብ እና ጋምቤላ ድንበሮች አዋሳኝ በሆነው ጉራፈርዳ ወረዳ አካባቢ የተጀመረው ግጭት ወደ ጋምቤላ ከተማና አቦቦ ወረዳ መዛመቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። ትናንት ምሽት በጋምቤላ ከተማ በተነሳ ግጭት ከ3 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ ዛሬ ከተማዋ በመከላከያና ፖሊሶች ተወራለች። የመንግስት ስራና ትምህርትቤቶች ዝግ ሆነው …

ጥቅምት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ የተነሳ የአዋሽ ወንዝ በመሙላቱ በአሚባራና ዱላሳ ወረዳዎች ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች ገለጹ። ነዋሪዎች እንደሚሉት በአሚባራ አካባቢ ከ5 ሺ ሄክታር በላይ የታረሰ መሬት መውደሙን፣ የ7 ቀበሌ ሰዎች በውሃ መከበባቸውንና ንብረታቸው በውሃ መወሰዱን እንዲሁም አንድ የእርሻ ምርምር ማእከል በውሃ መወሰዱን ገልጸዋል። እስካሁን የሞቱ …

ጥቅምት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሳምንታት የችሎት መቋረጥ በሁዋላ ስራ የጀመረው ፍርድ ቤቱ፣ አንድ ምስክር እንካ በአግባቡ ሳያዳምጥ መብራት ሄደ በሚል ምክንያት እንዲቋረጥ መደረጉን ገልጿል። ሰኞ በነበረው ችሎት አቶ አህመድ ኡመር የተባሉ ምስክር እየተናገሩ ባለበት ጊዜ  ምስክርነታቸው ሳይጠናቀቅ መብራት በመሄዱ ለማክሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ቢሰጥም ዛሬ ማክሰኞ በተመሳሳይ ሁኔታ ችሎቱ ሳይካሄድ መቅረቱን ድምጻችን ይሰማ …

ጥቅምት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-“ህገመንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርአቱን በሃይል ለማፍረስ ” በሚል ወንጀል የተከሰሰው እውቁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ከተባለ በሁዋላ፣ ውሳኔውን በእስር ላይ ሆኖ እንዲሰማ ፍርድ ቤት ባዘዘው መሰረት ወደ እስር ቤት ተልኳል። ጋዜጠኛ ተመስገን የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በመሆን ሲሰራ ” ድህረ ምርጫ 1997 ዓምን ተከትሎ ህገመንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን …

ጥቅምት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ለ3 ወታደራዊ አዛዦች የሌተናል ጄኔራል ማእረግ ሲሰጥ ለቀሪዎቹ ደግሞ የሜጀር ጄኔራል መእረግ ሰጥቷል። ማእረጉ ከተሰጣቸው ጄኔራሎች ውስጥ 4ቱ የትግራይ አንዱ የአማራና አንዱ የኦሮሞ ተወላጅ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ መኮንኖቹ ባስመዘገቡት ውጤት ማእረግ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል። ግንቦት7 ከአራት አመት በፊት ያወጣውን የወታደራዊ መኮንኖች የብሄር ተዋጽኦ ጥናት ክለሳ መሰረት …

ጥቅምት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት  ባለፈው ቅዳሜና እሁድ የፌደራል ፖሊሶችን ልዩ ሃይልንና መከላከያን ባቀፈው የመንግስት ጦርና፣ መሳሪያ በታጠቁ የብሄረሰቡ ተወላጆች መካከል በተደረገው ውጊያ ከ40 በላይ የፌደራል ፖሊስ አባላትና ከ10 ያላነሱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ 4 ታጣቂ ሚሊሺያዎችና 3 የወረዳ ፖሊሶች ተገድለዋል። የሟቾቹ አስከሬን በሚዛን አማን ሆስፒታል እንዲገባ ከተደረገ በሁዋላ፣ ዘመድ ያላቸው …

ጥቅምት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊ ክልል በፕሬዚዳንቱና በ7 የስራ አስፈጻሚ አባላት መካከል ተፈጥሮ የቆየውን ውዝግብ ለመፍታት ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሁሉንም ወገኖች አዲስ አበባ ቢጋብዙም፣ ፕሬዚዳንቱ አቶ አብዲ ሙሃመድ የጠ/ሚሩን ጥሪ ውድቅ በማድረግ የራሳቸውን ጉባኤ በመጥራት አዲስ የስራ አስፈጻሚዎችን ሾመዋል። ባለፈው መስከረም 24 ቀን በፊቅ ከተማ በተደረገው ጉባኤ፣ ፕሬዚዳንቱ የራሳቸውን ደጋፊዎችና ዘመዶቻቸውን  በስራ …

ጥቅምት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሚሰጡት ደካማ አመራር ከፍተኛ ትችት ሲድርስባቸው የቆዩት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው ፣  ስልጣን በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ካሳወቁ በሁዋላ የብሄራዊ ምክር ቤት አባላት ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩትን አቶ በላይ ፈቃዱን ሊቀመንበር አድርጎ ሾሟል። ኢ/ር ግዛቸው በተመረጡ በወራት ውስጥ በርካታ የስራ አስፈጻሚ አባላት በመሪው አመራር ደስተኛ ባለመሆን ራሳቸውን ከሃላፊነት አግለለው …

ጥቅምት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአስተዳደሩ የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ጽ/ቤት ቅዳሜ ዕለት ይፋ ባደረገው የጨረታ ውጤት መሠረት በቦሌ ክፍለከተማ ለአንድ ካሬሜትር መሬት ቦታ አሸናፊ የሆነው ግለሰብ ለካሬሜትር 55ሺህ 597 ብር ከ65 ሳንቲም የሰጠ ሲሆን ግለሰቡ አሸናፊ የሆኑበት 403 ካሬሜትር ገንዘብ ሲሰላ 22 ሚሊየን 405ሺህ 852 ከ95 ሳንቲም ሆኗል፡፡ በዚሁ ክፍለከተማ ለጨረታ ከቀረቡት 38 …

ጥቅምት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና ወስደው የውሎ አበል ያልተከፈላቸው የመጀመሪያ አመትና ነባር ሶስተኛ ዙር ሰልጣኞች ‹‹የውሎ አበላችን ይሰጠን›› በሚል ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣታቸው በትናንትናው ዕለት በፌደራል ፖሊስ መደብደባቸውን ተማሪዎቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ሰላማዊ ሰልፉን አደራጅታችኋል የተባሉ በርከት ያሉ ተማሪዎች መታሰራቸውንም ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ስልጠናው አርብ መስከረም 30/2007 ዓ.ም የጨረሱት ተማሪዎች …

መስከረም ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በቴፒ አካባቢ በመዠንገር ብሄረሰብና ደገኛ በሚባሉት ነዋሪዎች መካከል የተፈጠረው ግጭት ተባብሶ በርካታ ህዝብ ካለቀ በሁዋላ የመከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢው ገብቶ ለጊዜያው ያበረደው ቢመስልም፣ ግጭቱ ወደ ጉራፈርዳ ወረዳ አቅጣጫ ተዛምቶ እስካሁን ከ20 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውና በርካቶችም በመሰደድ ላይ መሆናቸውን የአካባቢው የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ምንጮች እንደሚሉት ካለፉት ሶስት ቀናት …

መስከረም ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን ከኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ከየከተማው እና ከየወረዳው የተውጣጡ ከ300 በላይ አባላት በተሳተፉበት ግምገማ በአመራሩና በአባላት መካከል አለመግባባት ተከስቶ እርስ በርስ መዘላለፍ ደረጃ ደርሰው እንደነበር በስብሰባው የተሳተፉ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ግምገማው የተመራው በአዳማ ከተማ ከንቲባ ሲሆን፣ ከንቲባው ቀደም ብለው ያዘጋጁዋቸው አባላት በምክትሉ ከንቲባ በአቶ አህመድ የሱፍና በድርጅት ጉዳይ …

መስከረም ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መጪውን ምርጫ ተከትሎ የኢህአዴግ አባላት የሆኑ የመንግስት ሰራተኞች የ20 በ80 አሰራርን ተግባራዊ እንዲያድረጉ ታዘዋል። የኢሳት የኢህአዴግ ምንጮች እንደገለጹት የመንግስት ሰራተኞች 20 በመቶ ጊዜያቸውን ለመንግስት ስራ 80 በመቶ የሚሆነውን ደግሞ ከምርጫ ቅስቀሳ ጋር በተያያዘ ለሚሰሩዋቸው ስራዎች እንዲያውሉ ተነግሯቸዋል። 80 በመቶ የሚሆነው የሰው ጉልበት፣ ባጀት፣ ጊዜና የመሳሰሉት ነገሮች በሙሉ ለምርጫ …

መስከረም ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ የአሜሪካ መንግስት የአገሪቱን ሰንደቃላማ በአወረዱ  ተቃዋሚዎች ላይ ክስ ይመሰርታል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል። ቃል አቀባዩ ተቃዋሚዎቹ ከኤርትራ መንግስት እና ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት አላቸው ብለዋል። የአሜሪካ መንግስት የኢምባሲውን ደህንነት የመጠበቅ ሃላፊነቱን አለመወጣቱን የገለጡት ቃል አቀባዩ፣ ተቃዋሚዎቹን ለፍርድ ያቀርባል ብለው እየጠበቁ መሆኑንም አክለዋል። …

መስከረም ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠናን ለ11 ቀናት የወሰዱት የከተማ አውቶቡስ ድርጅት ሰራተኞች ስልጠናውን በደንብ አልተከታተላችሁም በሚል ተጨማሪ 8 ቀን እንዲሰለጥኑ ቅጣት ተጥሎባቸዋል ሲል የዘገበው ነገረ ኢትዮጵያ፣ ከመስከረም 19/2007 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 30/2007 ዓ.ም በተሰጠው ስልጠና 4 ሺ 100 የከተማ አውቶቡስ ድርጅት ሰራተኞች እንዲሰለጥኑ የተደረገ ሲሆን ሰራተኞቹ ግማሹን ቀን ሰልጥነው …

መስከረም ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጄነቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልክተኛ ፅ/ቤት ባለሙሉ ስልጣን በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አምባሳደር ሚኒሊክ አለሙ ጌታሁን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ ስራ ማግኘታቸውን ተከትሎ  ሃላፈነታቸውን መልቀቃቸውን  ከውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የደረሰን ዜና ያመለክታል። የኢህአዴግ ዋና ደጋፊ ናቸው የሚባልላቸው አምባሳደር ሚኒልክ ፣ ስርዓቱ የሚፈጽማቸውን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ሽንጣቸውን ገትረው ሲከራከሩ በመቆየታቸው ” …

መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ከሚፈስባቸው የመንግስት ክብረ በአላት መካከል አንዱ የሆነው የባንዲራ ቀን ዘንድሮም ጥቅምት 2 ቀን 2007 ዓም በአዲስአበባ ስታዲየም በድምቀት እንደሚከበር መንግስት አስታውቋል። “በሕዝቦች ተሳትፎና ትጋት ድህነትን ድል በመንሳት ብሔራዊ ክብሯን እና ሰንደቅ ዓላማዋን ከፍ ከፍ በማድረግ ላይ ያለች ሀገር!” በሚል መሪ ቃል  ለ7ኛ ጊዜ …

መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ረቡዕ እለት በአዋሳ ብሉ ናይል እየተባለ የሚጠራው ሆቴል ባለቤት የሆኑት አቶ ታምራት ፣ ድርጅታቸው እንዲሸጥ በፍርድ ቤት ውሳኔ ማተላለፉን ተከትሎ፣ ውሳኔው እንዲተላለፍ አድርጓል ባሉት ወጣት ጠበቃ ዳንኤል ላይ የግድያ ሙከራ አድርገው ተሰውረዋል። አቶ ታምራት ከአንድ ግለሰብ ጋር ባላቸው የገንዘብ ውዝግብ በመረታታቸው ሆቴላቸው እንዲሸጥ ምክንያት መሆኑን ምንጮች ሲገልጹ፣ …

መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጎንደር ዩኒቨርስቲ አመታዊ የተማሪዎች ምረቃ በዓል ብቅ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማርያም ደሳለኝ ህብረተሰቡ ምን ይለናል የሚለውን ለማዳማጥ ከሰሜን ጎንደር ከተሰባሰቡ የወረዳ አመራሮች ጋር ባደረጉት ድንገተኛ ስብሰባ የወረዳ አመራሮች በንባብ እንዲያሰሙት ከየዞን ሃላፊዎች የተሰጣቸውን ማስታወሻና አቅጣጫ ወደጎን በመተው መንግስት እንዲያስተካክላቸው በጠየቁዋቸው ጥያቄዎች ምክንያት ከስብሰባው በኋላ ወከባና ማስፈራሪያ እንደደረሰባቸው …