መስከረም ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በማዕከላዊ ምርመራ ታስሮ የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ  አቶ የሽዋስ አሰፋ የአራት ቀን የርሃብ አድማ ማድረጉን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። አቶ የሸዋስ ከጳጉሜ 4 ጀምሮ አዲሱን አመት በርሃብ አድማ ያሳለፈ ሲሆን ቅዳሜ መስከረም 3/2007 ዓ.ም ምግብ እንደቀመሰ ባለቤቱ ወይዘሮ ሙሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጻለች፡፡ አቶ የሽዋስ የርሃብ አድማ …

መስከረም ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሶስት ሳምንት በፊት ለአጭር ቀን ስልጠና ወደ አሜሪካ ለመብረር ዝግጅታቸውን ጨርሰው ቦሌ አየር ማረፊያ የተገኙት ምክትል ከንቲባው፣ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ በሚል ከአገር እንዳይወጡ ተደርጓል። ዋናው ከንቲባና አንድ ባለሙያ ስልጠናውን ተካፍለው መመለሳቸው ታውቋል። ምክትል ከንቲባው የእስልምና እምነት ተከታይ እና በኦነግ አባልነት እንደሚጠረጠሩ ምንጮች ገልጸዋል። በከንቲባውና በምክትሉ መካከል የተፈጠረው ልዩነት …

መስከረም ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሁለት አመት በኦሮምያና በሶማሊ ክልሎች የድንበር ከተሞች የተነሳውን ግጭት መርተዋል የተባሉና ቁጥራቸው በውል ላልታወቀ ዜጎች ሞትና ለንብረት መውደም ምክንያት ሆነዋል የተባሉ የሞያሌ ወረዳ አስተዳዳሪን ጨምሮ ሌሎች 29 ሰዎች እስከ 19 አመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል። 21 ተከሳሾች በሌሉበት ሲወሰንባቸው የሞያሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጉዩ ዋርየን በ14 …

መስከረም ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ2007ዓ.ም ለሚደረገው ሃገራዊና ክልላዊ ምርጫ ህብረተሰቡ ለተለያዩ ተቀናቃኝ ፓርቲዎች ድምፁን እንዳይሰጥ ለማፈን በሚያስችል ሁኔታ በክልሉ የሚገኙ ሚሊሻዎች ልዩ ተልዕኮ እንደተሰጣቸው ተገለጸ የአማራ ብሄራዊ ክልል መንግስት ሚሊሽያ ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ መኳንንት መልካሙ ሰሞኑን ለታማኝ አመራሮች በሰጡት ድርጅታዊ መግለጫ ላይ በያዝነው ዓመት በሚካሄደው ምርጫ ህዝቡ የተለያየ ፅንፍ በመያዝ …

መስከረም ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሁለት ሳምንት በፊት በጠ/ሚንስትር ጽ/ቤት የሶማሊ ክልል መሪዎች፣ የደህንነት ሃላፊዎችና በክልሉ የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች በተገኙበት በተደረገው ግምገማ በፕሬዚዳንቱ አብዲ ሙሃመድ ላይ በርካታ ወንጀሎች ተዘርዝረው ከቀረቡ በሁዋላ ፣ ፕሬዚዳንቱን ከስልጣን ለማውረድ በሚፈልጉት  የደህንነት ሹሙ አቶ ጌታቸው አሰፋና በክልሉ የመከላከያ ሹም ጄኔራል አብርሃ መካከል አለመግባባት ተፈጥሯል። ውሳኔ ለመስጠት የተቸገሩት …

መስከረም ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ጳጉሜ ወር የመከላከያ ሰራዊትን ጥለው የጠፉ ወታደሮች ለኢሳት እንደገለጹት፣ በጠጠናቀቀው አመት በርካታ ወታደሮች እየለቀቁ የተቃዋሚ ድርጀቶችን ከመልቀቅ ባሻገር ወደ ማሃል አገር እየሄዱ ኑሮአቸውን እየመሩ ነው። የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤት ትወስዳለህ ተብሎ ያለፍለጎቱ መከላከያን የተቀላቀለና ባለፈው ሳምንት መስሪያ ቤቱን በመልቀቅ የግል ኑሮውን ለመምራት የፈለገ ወታደር  እርሱ በነበረበት የሁመራ …

መስከረም ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመዠንገር ብሄረሰብ ተወላጆች ጎደሬና ሜጫ በሚባሉት አካባቢዎች እንደ አዲስ በጀመሩት ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውንና እስካሁን አስከሬኖች እንዳልተነሱ የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። ከጋምቤላ ብሄረሰብ ውጭ ያሉ የሌሎች አካባቢ ተወላጆች በሙሉ ይወጡ በሚል የተጀመረው ግጭት ፣ ደም አፋሳሽ ሆኖ ከመቀጠሉ ባሻጋር፣ በትናንትናው እላት ብቻ ከ1 ሺ ያላነሱ ሰዎች ተፈናቅለው ቴፒ ከተማ መግባታቸው ታውቋል። …

መስከረም ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ሆነው ለግንቦት7 የአርባ ምንጭና አካባቢው ወጣቶችን በመመልመል ወደ ኤርትራ ይልካሉ በሚል ጥርጣሬ ተይዘው ለሳምንታት በአርባ ምንጭ እስር ቤት ታስረው የቆዩት የፓርቲው የአርባ ማንጭ ምክትል ሰብሳቢ በፍቃዱ አበበ እንዲሁም የድርጅት ጉዳይ ሃላፊው ኢንጂነር ጌታሁን  ወደ ማእከላዊ እስር ቤት መወሰዳቸውን የፓርቲው ድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ ለኢሳት ገልጸዋል። …

መስከረም ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል አቃቢ ህግ በ17 የጅቡቲ፣ ህንድ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ ሲሪላንካና እና አሸራፍ አወል አብዲ  በሚባል ኢትዮጵያዊ ላይ በመሰረተው ክስ፣ ግለሰቦቹ ለኢትዮጵያውያን በተፈቀደው የንግድ ስራ ህገወጥ በሆነ መንገድ በመነገድ መንግስት ማግኘት የነበረበትን 700 ሚሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ እንዲያጣ አድርገዋል ብሎአል። በክሱ ዱባይ ኦቶ ጋላሪ ኤል ኤል ሲ እና ወርልድ ኢንተርናሽናል ፍሪዞን ኩባንያ …

መስከረም ፩(አንድ)ቀን ፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአሉ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እየተከበረ መሆኑን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። ኢትዮጵያውያን ስልክ በመደወል የመልካም ምኞት መግለጫ መልእክቶችም አስተላልፈዋል ከበአሉ ጋር በተያያዘ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች መከናወናቸውን  የደረሱን መረጃዎች ያሳያሉ። በበአሉ ዋዜማ ወቅት ከፍተኛ አደጋ የታየው በጋምቤላ ክልል በጎደሬ ዞን በጎሸም ቀበሌ ሲሆን፣ የመዠንገር ብሄረሰብ አባላት 9 ሰዎችን ገድለዋል። ግጭቱ አሁንም ድረስ …

ጳጉሜን ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከዚህ በፊት ባልተለመደ ሁኔታ በአንድ ወር ውስጥ ለ3ኛ ጊዜ የተካሄደው የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የአመራሩ ሚስጢሮች ተላልፈው የተሰጡበትና በአደገኛ ሃይሎች እጅ የወደቁበት ሁኔታ መከሰቱን ፣ አፋጣኝ እርምጃ ካልተወሰደ አደጋው የከፋ ሊሆን እንደሚችል ተወስቷል። 3ኛው አስቸኳይ ስብሰባ ትናንት ሲጠናቀቅ ብአዴንና ደኢህዴን በከፍተኛ ድክመት ውስጥ እንደሚገኙና ከዚህ ድክመታቸው በአስቸኳይ እንዲወጡ …

ጳጉሜን ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያሰብዓዊመብትኮምሽን «በጥበቃሥርያሉሰዎችመብትአከባበርበኢትዮጵያፖሊስ ጣቢያዎች» በሚልርዕስባካሄደውየዳሰሳጥናትጣቢያዎቹለእስረኞችእንደምግብ፣ውሃ፣ መኝታና፣ሕክምና  እና የመጸዳጃ  አገልግሎቶችበመንግስትወጪማሟላትየነበረባቸው ቢሆንምከፍተኛጉድለቶች በጥናቱማግኘቱን አስታውቋል፡፡ የዳሰሳጥናቱሰሞኑንበአዳማጀርመንሆቴልይፋበሆነበትወቅትእንደተጠቆመውየዳሰሳጥናቱ በሁሉምክልሎች በሁለትከተማአስተዳደሮችበአ/አእናድሬዳዋከሚገኙ 1ሺህ 81 ፖሊስ ጣቢያዎችውስጥበ170 ዎቹመካሄዱንጠቅሶግኝቱንአስቀምጧል፡፡ በዚሁመሠረትፖሊስጣቢያዎቹውስጥከሚገኙየተጠርጣሪእስረኞችመቆያክፍሎች አብዛኛዎቹደረጃቸውንያልጠበቁ፣እንደፍራሽናአልጋያሉመተኛዎችያልተሟሉላቸውናበእስረኞች የተጨናነቁ ናቸው፡፡የህክምናወጪበመንግስትየሚሸፈንላቸውበአዲስአበባእናበድሬደዋ በሚገኙፖሊስጣቢያዎች ለታሰሩት ብቻሲሆንበሌሎችክልሎችይህአገልግሎት አለመኖሩተመልክቷል፡፡ ጥናቱአያይዞምየእስረኞችቃልንበዛቻበማስፈራራትናአካላዊጥቃትበመፈጸምመቀበል በፖሊሶችናመርማሪዎችየተለመደአሰራርመሆኑንከማመልከቱምበላይበሕጉመሠረትበ48 ሰዓታትፍርድቤትየማይቀርቡእስረኞችመኖራቸውንምአጋልጧል፡፡ በተጨማሪምጥናቱየተካሄደባቸውየፖሊስጣቢያዎችበዘመናዊመረጃአያያዝበኩልችግር እንዳለባቸው፣የበጀት እጥረት፣የቁሳቁስናየሰውኃይልአለመሟላትአገልግሎትአሰጣጣቸው ላይአሉታዊተጽዕኖ ማሳረፉንጠቁሟል፡፡ ጥናቱእንደመፍትሔካስቀመጣቸውነጥቦችመካከልበጣቢያዎቹየሚመደበውበጀትናየሰው ኃይልማሻሻልእንደሚገባ ይመክራል፡፡በተጨማሪምሴቶች፣ከእናቶቻቸውጋርያሉሕጻናት፣ ወጣትተጠርጣሪዎች፣ የአእምሮወይንምየአካል ጉዳትያለባቸውተጠርጣሪዎችበቂድጋፍእንዲገያኙመደረግአለበትብሏል፡፡ የኢትዮጵያሰብዓዊመብትኮምሽንበሕገመንግስቱየሰፈሩመብቶችንናኢትዮጵያተቀብላ ያጸደቀቻቸውዓለምአቀፍ የሰብኣዊመብትድንጋጌዎችተፈጻሚመሆናቸውንእንደሚ ከታተልየተጠቀሰሲሆንየዚህን የዳሰሳጥናትውጤትጠቅላይ ሚኒስትሩንጨምሮለሚመለከታቸውአካላትናለዓለምአቀፍተቋማት  መላኩተጠቅሷል፡፡

ጳጉሜን ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በቦንኬ ወረዳ ላታ ቀበሌ  ከታሰሩት 9 አርሶደአሮች መካከል 3ቱ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸው በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ።  አዳነ አለማየሁ፣ አስኔ አለማየሁ፣ ክልክሌ አባ፣ ልልቱ ኮዳ፣ አይማ ዳዳ፣ ጋላሂ ጋሞ፣ ዳንኤል ጉዳ፣ አብሌ አለማየሁ እና አባተ እንዳለ የተባሉት አርሶአደሮች “ተጨማሪ ማዳበሪያ አንፈልግም ቀድሞ ለወሰድነውም እዳችንን ለመክፈል አልቻልንም” በማለታቸው መታሰራቸውን …

ጳጉሜን ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃድያ ዞን ሚሻ ወረዳ ሞርሲጦ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ አባይነህ ቁጥሩበውል ያልተወቀ ከፍተኛ ገንዘብ ይዘው መጥፋታቸውን የኢሳት አካባቢው ምንጮች ተናግረዋል። አቶ አባይነህ ገንዘቡን ይዘው እንደጠፉ ስልክ ሲደወልላቸው ” የድርሻየን ወስጃለሁ” የሚል መልስ መስጠታቸውንና ስልካቸውን ማጥፋታቸውን ለማወቅ ተችሎአል። ለወረዳው ስራ ማስኪያጃ የሚውለውን ገንዘብ ይዘው በመጥፋታቸው የወረዳውን ስራ ለማካሄድ ችግር መፍጠሩን …

ጳጉሜን ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ መንግስት በተከታታይ በሰብአዊነት ላይ የሚፈጽማቸውን ወንጀሎችለዓለምማህበረሰብየማጋለጥተግባርበተለያዩሃገሮችበተለይምየአቶአንዳርጋቸውጽጌንህገወጥእገታተከትሎተጠናክሮቀጥሏል።ሰላማዊሰልፎች አሁንምበበርካታከተሞችእየተደረገሲሆንበጀርመንየሚኖሩኢትዮጵያዊያንየኢትዮጵያውንገዢስርዓት ህገወጥተግባራትየሚያስረዱጽሁፎችንአዘጋጅተውለጀርመንነዋሪዎችእያዳረሱሲሆንየጀርመንመንግስት ለኢትዮጵያመንግስትየሚሰጠውንእርዳታከሰብዓዊመብትአኳያእንዲያጤንየሚጠይቅፊርማም እያሰባሰቡይገኛሉ። በሌላ ዜና ደግሞ ግንቦት7 በሜልቦርን ስብሰባ ማካሄዱን ዘጋቢያችን ኤልሳቤጥ ግዛው ከአውስትራሊያ ዘግባለች

ጳጉሜን ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ ኦሞድ ኦባንግ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ 400 ሰዎች የተገደሉበት የጋምቤላወኢ ጭፍጨፋ እንዴት እንደተከናወነ በዝርዝር አስረድተዋል። የህወሃት ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አቶ አባይ ጸሃየ ግድያውን በተመለከተ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። በክልሉ ስለሚፈጸመው ሙስናና የመሬት ወረራ የቀድሞው ባለስልጣን በዝርዝር ገልጸዋል። አቶ አዲሱ ለገሰ በቅርቡ ባወጡት ጽሁፍ በጋምቤላ ለኢህአዴግ ታማኝ የሆነ ሰው ለማግኘት …

ጳጉሜን ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ የኢህአዴግን ፖሊሲዎች ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ለዳኞችና አቃቢያን ህጎች፣ ለፖሊሶች እንዲሁም ለኢህአዴግ የተለያዩ ፎረም አባላት ሲሰጥ የቆየውን ስልጠና ለመንግስት ሰራተኛው በሙሉ ለመስጠት ማቀዱ ታውቋል። እስካሁን ድረስ በተካሄዱት ስልጠናዎች ኢህአዴግ ከአባላቱ ጭምር ሳይቀር ከፍተኛ የጥያቄ ናዳዎችን ሲያስተናግድ የቆየ ቢሆንም፣ ውይይቱን ከማቋረጥ ይልቅ ወደ መንግስት ሰራተኛው በማውረድ አስፋፍቶ ለመስጠት ማቀዱን …

ጳጉሜን ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመከላከያ ሰራዊት የከዱ 10 የሚደርሱ ወታደሮች ከሆሳእና ከተማ ባለስልጣናት ጋር የፈጠሩትን ውዝግብ ተከትሎ፣   አንድ የከተማው የምክር ቤት አባል በደረሰበት ድብደባ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን፣ ይህን ተከትሎ  አንደኛው ወታደር ሲያዝ ቀሪዎቹ አምልጠዋል። ይሁን እንጅ  ወታደሩ ነሃሴ 30 ቀን 2006 ዓም ታይዞ መታሰሩን የገለጹት ምንጮች፣ ያልተያዙት ወታደሮች በምሽት እስር ቤቱን በመስበር …

ጳጉሜን ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ፦ሂዩማን ራይትስ ዎችን በመጥቀስእንደሰገበውውሃእናህክምናፍለጋቀያቸውንለቀው  ወደሞቃዲሾየሰላምአስከባሪሀይሉወደሰፈረበትካምፕየሄዱየሶማሊያ ልጃገረዶችናሴቶችበህብረቱየሰላምአስከባሪሀይላትበሀይልተደፍረዋል። አንዲትየ 15 ዓመትሙስሊምወጣትልጅ  ከአንገቱዋበላይየተሸፋፈነች በትንልብስበሀይልእንድታወጣናእንድት ገላለጥከተደረገችበሁዋላ  መደፈሩዋንየሰብዓዊመብትተቁዋሙጠቅሱዋል። በሶማሊያ  አልሸባብንናአክራሪእስላሚስቶችንለመዋጋትወደ 22 ሺህጦርያሰፈረውየአፍሪካህብረትየሰብዓዊመብትተቁዋሙየመሰረተውን ክስአስመልክቶ  ማጣራትእንደሚያደርግአስታውቁዋል። የመንግስታቱድርጅትየስደተኞችጉዳይከፍተኛኮሚሽንሪፖርትእንደሚያመለክተው በ2012 ብቻ  ከቀያቸውበተፈናቀሉ 1700 የሶማሊያሴቶችላይየአስገድዶመድፈርወንጀልመፈጸሙተመስግቡዋል። ባለፈውዓመት  አንዲትየሶማሊያሴትበህብረቱሰላምአስከባሪናበሶማሊያ ጦርአባላትበጋራመደፈሩዋንተከትሎከፍተኛውስግብተነስቶእንደነበር ቢቢሲአስታውሱዋል። የመደፈርአደጋእያጋጠማቸውያሉትአብሳኞቹሴቶችበተለይከ2011 ጀምሮ እያየለበመጣውየእርስበርስግጭትና  በድርቅምክንያትከቀያቸውተፈናቅለው ወደተለያዩመጠለያካምፖች  የገቡናቸው። የአፍሪካህብረትየሶማሊያሰላምአስከባሪልኡክከእንግዲህእንዲህያለውንነገር አላየኹምብሎዓይኑንሊጨፍንአይችልም፤ይህንድርጊትማድበስበስ  በአካባቢው  በዋነኝነትየተሰለፈበትንሰላምየማስከበርአላማን  ዋጋያሳጣዋል” ብለዋል- የሂዩማንራይትስዎችየሴቶችጉዳይዳሬክተርሊየስልጌርንቶልትስ። ከ 12 ዓመትጀምሮያሉ 21 ሴቶችበተደረገላቸውቃለ-ምልልስአብሳኞቹበኡጋንዳናበብሩንዲወታደሮችእንደተደፈሩመናገራቸውን የቢቢሲሰገባያመለክታል።

ጳጉሜን ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአለፈው አንድ አመት ውስጥ ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ለፓርቲው የፖለቲካ ስራ የሚጠቅም ከመንግስት ባጀት ከ900 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ገንዘብ ማውጣቱን ምንጮች ገለጹ። ለብሄር ብሄረሰቦች ቀን፣ ለባንዲራ ቀን፣ ለመከላከያ ቀን፣ ለተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የፖለቲካ ስልጠና፣ ከ100 ሺ በላይ ለሚሆኑ የኢህአዴግ አባላት ስልጠና፣ ለፖሊስ ሰራዊት የተሰጠው ስልጠና፣ እንዲሁም በተለያዩ ታሃድሶ የሚል …

ጳጉሜን ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት በመግለጫ የከሰሳቸው ጋዜጠኞች አግር ጥለው ከወጡ በሁዋላ ጉዳያቸው በሌሉበት እየታየ ነው። ከሳምንት በፊት ጥሪ ተደርጎላቸው እኢነዲቀርቡ የታዘዙት የፋክት፣ አዲስ ጉዳይ እና ሎሚ መጽሄት አዘጋጆችና ባለቤቶች  ፍርድ ቤት ለመቅረብ ባለመቻላቸው 17ኛው ወንጀል ችሎት  ጉዳያቸውን በሌሉበት ለማየት ተጨማሪ ቀጠሮ ሰጥቷል። ተከሳሾቹ ህመንግስታዊ ስርዓቱን በአመጽ ለማፍረስ አስበዋል የሚል ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን፣ …

ጳጉሜን ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሊጠናቀቅአንድዓመትበቀረውየመንግሥትየአምስትዓመቱመርሃግብርመሠረት የሆልቲካቸርእናሰፋፊእርሻ ኢንቨስትመንትዕቅዶችየተለጠጡስለነበሩየተሳካአፈጻጸምእንዳልተመዘገበባቸውየግብርናሚኒስትሩ አቶተፈራደርበውለመጀመሪያጊዜአምነዋል፡፡ ሚኒስትሩከመንግስታዊውአዲስዘመንጋዜጣጋር  ባደረጉትቃለምልልስእንደተናገሩት በመርሃግብሩዘመንየሆልቲካልቸርበተለይምየአትክልትናፍራፍሬኢንቨስትመንትበማስፋፋትለሀገሪቱ ከአንድቢሊየንበላይየሚደርስ የውጭምንዛሪለማስገባትታቅዶእንደነበርአስታውሰውነገርግንዕቅዱከመነሻውየተለጠጠናየተለያዩችግሮችአጋጥመውስለነበር ያስብነውንያህልከዘርፉውጤትማግኘትአልቻልንምብለዋል፡፡ በዘርፉታይተዋልካሉዋቸውችግሮችመካከልየዕዝሰንሰለቱንየተከተለአሰራርአለመኖር፣ለአየርትራንስፖርትየቀረበመሬትአቅርቦት ችግር፣የሎጀስቲክአቅርቦትማነስተጠቅሰዋል፡፡ የሰፋፊእርሻኢንቨስትመንትንለማስፋፋትየተደረገውጥረትመሬትተረክበውበፍጥነት ወደሥራያለመግባትችግሮች ማጋጠማቸውንጠቁመውይህንችግርለመፍታትጥረቶችመደረጋቸውንጠቅሰዋል፡፡በአሁኑወቅት በዘርፉየቱርክ ባለሃብቶችበጥሩሁኔታእየተንቀሳቀሱመሆኑንሌሎችምከእነሱተሞክሮሊወስዱይገባልሲሉተናግረዋል፡፡ ሚኒስትሩእንደእነካራቱሪያሉየህንድባለሃብቶችየተረከቡትንመሬትተፈጥሮሃብትበማውደም፣ፈቃድያወጡበትን ኢንቨስትመንትስራባለመስራትእንዲሁምየባንክብድርበመውሰድስላደረሱትጥፋትናኪሳራምንምያሉትነገርየለም፡፡

ጳጉሜን ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲስ አበባ ውስጥ በየ ቤቱ እየዞሩ ዲሽ የሚገጥሙ ወጣቶች ‹‹ኢሳትን እየቀጠላችሁ ነው›› በሚል ወከባ እንደሚደርስባቸው መናገራቸውን ነገረ-ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡ጋዜጣው እንዳለው ወጣቶቹ ከኢሳት ውጭ ያሉ ጣቢያዎች የሚተላለፉበት ዲሽ  ጭምር በሚገጥሙበት ወቅትም ‹‹ኢሳትን እየቀጠላችሁ ነው፡፡ ህዝቡ ኢሳትን እንዲያይ ታደርጋላችሁ›› በሚል በደህንነቶች ወከባ እንደሚደርስባቸው ለጋዜጣው ዝግጅት ክፍል ተናግረዋል፡፡ ከወራት በፊት መርካቶ አካባቢ ዲሽ …

ጳጉሜን ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአሉ ቅዳሜ መስከረም 6 ቀን 2014 ዓ.ም የድርጅቱ አባላትና ደጋፊዎች በተገኙበት በድምቀት መከበሩን ከስፍራው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል። የዕለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት አቶ አበረ አዳሙ የግንቦት ሰባት ምክር ቤት አባል ስለ ወቅቱ ተጨባጭ ሁኔታና የግንቦት ሰባት የሥራ እንቅስቃሴ ሰፊ ንግግር አድርገዋል። በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የሕይወት ታሪክ ላይ የተዘጋጀ ዶክመንታሪ ቪድዮ …

ነሃሴ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመላው አውሮፓ የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን የተገኙበት ይህ የተቃውሞ ሰልፍ እጅግ ደማቅ መሆኑን ወንድማገኝ ጋሹ በስልክ ገልጿል። የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ  በየመን የጸጥታ ሃይሎች ተይዘው  ተላልፈው ከተሰጡበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግስት ሰብአዊ መብታቸውን በመግፈፍ በኢትዮጵያውያን እንዳይጎበኙ ከልክሏል። አብዛኛውን ስራቸውን እንዳጠናቀቁ በተደጋጋሚ ሲናገሩ የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ወደተለያዩ ቦታዎች በሌሊት እየተዘዋወሩ ምርምራ እየተደረገባቸው መሆኑን …

ነሃሴ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ በተለያዩ ሊጎች ወይም ፎረሞች ለሰበሰባቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የሚሰጠው የፖለቲካ ስልጠና ባልጠበቀው አቅጣጫ እየሄደበት መሆኑን ተከትሎ ሰዎችን ከመከፋፈል ጀምሮ እስከ ማባረር መድረሱን ምንጮች ገልጹ። በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የመሰብሰቢያ ቦታዎች በሚደረጉት ስልጠናዎች ላይ ለገዢው ፓርቲ ፈታኝ የሆኑ ጥያቄዎችን የሚያቀርቡ ወጣቶች እና የፖለቲካ ንቃት አላቸው የሚባሉ ነዋሪዎች ፣ ከቀሪ …

ነሃሴ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለገጣፎ ውስጥ በሶስት ጎጦች የሚኖሩ ዜጎች በ10 ቀን ውስጥ ቤታቸውን እንዲያፈርሱ መታዘዛቸውን ጋዜጣው የትእዛዝ ወረቀቱን በማያያዝ ያሰፈረው ዜና ያማለክታል፡፡ጎራጎጭ፣ዳሌናድሬበተባሉትሶስትጎጦችእስከ 23 ሺህህዝብእንደሚኖርባቸው ነዋሪዎቹ ለጋዜጣው ዘጋቢ ተናግረዋል። “የሰንዳፋወረዳሰራተኛናማህበራዊጉዳይጽ/ቤት ማህተም አስቀርጾ የመረዳጃ እድር ማቋቋሙን፣ ለመብራትኃይልአንድሚሊዮንያህልገንዘብከፍለውትራንስፎርመርለማስተከልእየተጠባበቁመሆናቸውንና፣የውሃናሌሎችተቋማት ህጋዊለሆነአካልየሚሰጡትንአገልግሎትከፍለውእያገኙእንደቆዩበመግለጽየሚኖሩበትአካባቢህገወጥአለመሆኑንበመግለጽ እየተከራከሩ ቆይተዋል። እንደጋዜጣው ዘገባ  ነሃሴ 26 ተጻፈየተባለናከፊንፊኔልዩዙሪያ  በረህወረዳ   የመሬትአስተዳደርጽ/ቤትእንደሆነ የሚገልጽፊርማየሌለውደብዳቤ  ማምነታቸው በውል ያልተለየ ሰዎች ነሃሴ 30 …

ነሃሴ ፳፱(ሃያዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ1997 ምርጫ ወቅት ለ200 ሰዎች ሞት እና በመቶዎች ለሚቀጠሩት ቁስለኞች ተጠያቂ በሆኑ 13 ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ወታደራዊ  አዛዦች ላይ ለፖሊስ የክስ አቤቱታ አስገቡት በስዊድን ታዋቂ የሆኑት ጠበቃ ስቴላ ጋርደ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፣ በቅርቡ ለፖሊስ ከገባው አቤቱታ በተጨማሪ የኢትዮጵያ መንግስት በግፍ ለተገደሉት፣ ለቆሰሉት ፣ ለታሰሩት፣ ከስራ ለተፈናቀሉት አስፈላጊውን …

ነሃሴ ፳፱(ሃያዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለከተሞች በመካሄድ ላይ ባለው የኢህአዴግ አባላት ስብሰባ ፣ አባላቱ ዛሬም በርካታ ጥያቄዎችን ሲጠይቁ መዋላቸውን ከውስጥ ምንጮች የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ዛሬ ከሰዓት በኋላ በአባላቱ ከተነሱት ጥያቄዎች  መካከል፡- ” የኢትዮጵና የኤርትራ ህዝቦች የማይነጣጠሉ የአንድ ሃገር ዜጎች ሆነው ሳለ በመሪዎች አለመግባባትና ሽኩቻ በመለያየታቸው እስከዛሬ ድረስ እየተላቀሱ ይገኛሉ፤ ይህም የሆነው …

ነሃሴ ፳፱(ሃያዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው  ነሃሴ 29/2006 ዓ.ምበአራዳችሎትየቀረበው የአረና ፓርቲ የአመራር አባልና ታዋቂ ጸሃፊ መምህር አብርሃደስታ ፣ ፖሊስ ‹‹ተጨማሪሰነድለማሰባሰብናምስክሮችለማቅረብ” የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው በመጠየቁ ፣ ፍርድ ቤቱ ለመስከረም 22 ቀጠሮ ሰጥቷል። የኢምባሲናሌሎችተወካዮችንጨምሮበርከትያለህዝብየተገኘሲሆንአብርሃደስታከማዕከላዊወደችሎቱበሚመጣበት ጊዜህዝቡደመቅባለ ጭበጭባእንደተቀበለው ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡ህዝቡለአብርሃያደረገውንጭብጨባተከትሎምፖሊስህዝቡከግቢውእንዲወጣቢያስገድድምህዝቡ ሳይወጣ መቅረቱንም አክሎ ዘግባል። የአብርሃደስታጠበቃ  የሆኑት አቶ ተማምአባቡልጉከደንበኛቸውጋርበ28 ቀናትውስጥአንድቀንብቻ እንዳገኙት የነገረ ኢትዮጵያ ዘገባ ያመለክታል። ሀብታሙ አያሌው፣ …

ነሃሴ ፳፰(ሃያስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ በአዲስ አበባ የሚገኙ መላ አባላቱን ለስልጠና ምቹ የሆኑ አዳራሾች ባሉዋቸው ትምህርት ቤቶች እና የመንግስት ተቋማት ከትናንት ጀምሮ በፕላዝማ የታጀበ ስልጠና እየሰጠ ነው። ስልጠናው በመላው አገሪቱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ያነሱዋቸው አፍራሽ የተባሉ ጥያቄዎች እና አመለካከቶች ወደ ህዝቡ ወርደው አደጋ ከመፍጠራቸው በፊት የኢህአዴግ አባላት እንዴት እንደሚከላከሉዋቸው ስልጠና ለመስጠት ያለመ ቢሆንም፣ የድርጅቱ …

ነሃሴ ፳፰(ሃያስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፊታችን ቅዳሜ የሚከበረውን የአርባምንጭ የ50ኛ አመት የምስረታ በአልን የማጠቃለያ ዝግጅት ለመካፈል ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ እና ሌሎች የመንግስት ባለስልጣናት የተገኙ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎ በከተማዋ ረብሻ ሊያስነሱ ይችላሉ የተባሉ ወጣቶች እየታደኑ ነው። ዘጋቢያችን እንደገለጸው፣ ከ3 ቀናት በፊት እናቶች በየቀበሌው እየተጠሩ ልጆቻቸውን እንዲሰበስቡ ተነግሮአቸው ነበር። ማንኛውም ወጣት በምሽት ከተማ ውስጥ መዘዋወር፣ ሰብሰብ …

ነሃሴ ፳፰(ሃያስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጅቱ ለኢሳት በላከው መግለጫ ላይ  “ኮ/ል አለበል አማረ የድርጅቱ መስራችና ሊቀመንበር ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸውን፣ ውጭ አገር ከሄዱም በሁዋላ ድርጀቱን በማጠናከር ከፍተኛ ሚና መጫወታቸውን” ካወሳ በሁዋላ፣ ድርጅቱ መስዋትነት እየከፈለበት ያለው የነጻነት ትግል በቶሎ ግቡን እንዲመታ መሬት ላይ ወርዶ መታገሉ የበለጠ ውጤታማ ያደርገዋል ተብሎ ስላሚታመን  በተደጋጋሚ እንዲመጡ ቢነገራቸው ሊመጡ ባለመቻላቸውና አሁን …

ነሃሴ ፳፰(ሃያስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጳጉሜ 1 ቀን 2006 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ሊያካሂደው የነበረው የኪነጥበብ ሽልማት  አርቲስቶች ከፍተኛ ቅሬታ ከማቅረባቸው ጋር ተያይዞ እንዲሰረዝ መወሰኑ ተሰማ፡፡ ሚኒስቴሩ ኪነጥበብን ለማበረታታት በሚል በሥነጹሁፍ፣ በሥዕል፣በሙዚቃ እና በፊልም ዘርፎች ብቻ የየዘርፎቹ ማህበራት መርጠው የላኩዋቸውን 10፣ በድምሩ 40 ዕጩዎች በማወዳደር ከየዘርፉ የተሻለ ውጤት ያገኘውን ለመሸለም አቅዶ …

ነሃሴ ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ሃብታሙ አያሌው፣ የድርጅቱ ም/ል የድርጅት ጉዳይ ሃለፊ ዳንኤል ሽበሺ፣ እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት/ምክትል ሰብሳቢ የሺዋስ አሰፋ ከሰአት በሁዋላ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበረ ቢሆንም፣ ፖሊስ ተጨማሪ መረጃ ለማሰባሰብ በሚል የጊዜ ቀጠሮ በመጠየቁ ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ 28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ፈቅዷል። የእስረኞችን ጉዳይ የሚከታተሉት …

ነሃሴ ፳፯(ሃያሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለሁለት ሣምንታት ለዩኒቨርሲቲ አዲስና ነባር ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረው የመጀመሪያ ዙር አስገዳጅ ሥልጠና የፊታችን ቅዳሜ የሚጠናቀቅ ሲሆን ሁለተኛው ዙር ሥልጠና ወዲያውኑ ለመቀጠል ትምህርት ሚኒስቴር መዘጋጀቱን መረጃዎች ጠቁመዋል። ተማሪዎችተገድደውበገቡበትበዚሁየሥልጠናቆይታቸውደስተኛያለመሆናቸውንበመናገርላይናቸው፡፡ በዋነኛነት የመንግሥት ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን ለተማሪዎች ለማስተዋወቅ በሚል በመንግሥት ከፍተኛ በጀት ከ33 በላይ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በሚሰጠው በዚሁ ሥልጠና ላይ የኢህአዴግ ዋና ዋና ካድሬዎች …

ነሃሴ ፳፯(ሃያሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መጪውን የትምህርት ዘመን ለመጀመር የሚያስችል ምዝገባ ለማካሄድ በትምህርት ቤቶች የተገኙ ተማሪዎች ለአባይ ግድብ ገንዘብ የማያዋጡ ከሆነ እንደማይመዘገቡ ተገልጸላቸዋል። ተማሪዎቹ በነፍስ ወከፍ 120 ብር የማይከፍሉ ከሆነ ምዝገባ እንደማያካሂዱ እንደተነገራቸው ለኢሳት እንደተነገራቸው ገልጸዋል። ሁለት እና ከዚያ በላይ  ልጆች ያላቸው ወላጆች በቤተሰብ ደረጃ ሳይሆን በእያንዳንዱ ልጅ ስም የመክፈል ግዴታ ተጥሎባቸዋል። አንዳንድ ተማሪዎች …

ነሃሴ ፳፯(ሃያሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአማራ ገጠር መንገዶች ባለስልጣን  ኪራይ ሰብሳቢዎች በባለሃብቱ እና በመስሪያ ቤቱ መካከል በመግባት ከፍተኛ ብዝበዛ እየፈጠሩ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡ ሰኞ ነሃሴ 19/2006 ዓ.ም የመስሪያ ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ስማቸው ንጋቱ በሰጡት መግለጫ የመስሪያቤቱ ወሳኝ ሰራተኞች ከደላሎች ጋር በፈጠሩት የረዢም ጊዜ ቁርኝት እያንዳንዱ ጨረታ ህጉን በተከተለ መንገድ ለመስራት አስቸግሮ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ …

ነሃሴ ፳፯(ሃያሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርብ ተሰርተው ከተጠናቀቁት የኮንዶሚኒዮም ቤቶች መካከል ገሚሱን ለመከላከያየጦርመኮንኖችለመስጠትማቀዱንእናበቅርቡቤቶቹንእንደሚያስተላልፍከኢትዮጵያንግድባንክሰራተኞች የተገኘው  መረጃ አመልክቷል። የኮንዶሚኒየም ቤቶችን የሚያገኙ መኮንኖች በምን መስፈረት እንደተመረጡ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም። መንግስት ሰሞኑን በተለያዩ የአዲስ አበባ ክ/ከተሞች ለሚሰለጥኑ ፖሊሶች የኮንዶሚኒየም ቤቶችን እንደሚያድል ቃል መግባቱን መግለጻችን ይታወሳል።

ነሃሴ ፳፮(ሃያስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ ከተለያዩ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጋር ያደረገው የመጀመሪያ ዙር ውይይት የተፈለገውን ውጤት አስገኝቶለታል ብለው እንደማያስቡ ኢሳት ያነጋገራቸው ተማሪዎች ገልጸዋል። መጪውም ምርጫ አስታኮ የተሰጠው የፖለቲካ ስልጠና በተማሪዎች እና በኢህአዴግ ባለስልጣናት መካከል ያለውን አለመግባባት ያሳየና ተማሪዎች በስርአቱ ላይ አመኔታ እንደሌላቸው የሚያመለክት መሆኑነ ተማሪዎች ግልጸዋል። በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያው ዙር ስልጠና መጠናቀቁን በማስመልከት ጥያቄ …

ነሃሴ ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጸረ ሽብር አዋጁን ተገን በማድረግ በጋዜጠኞች ላይ የተከፈተውን ዘመቻ ተከትሎ፣ አገር ጥለው የሚወጡ የነጻው ፕሬስ አባላት ቁጥር መጨመሩን መረጃዎች አመልክተዋል። ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከ12 ያላነሱ ጋዜጠኞች ከደህንነት ሃይሎች በደረሰባቸው ጫና ምክንያት አገራቸውን ጥለው የተሰደዱ ሲሆን፣ ብዙዎቹ በስደት በሚኖሩባቸው አገሮች ለችግር ተዳርገዋል። የኢትዮጵያ የደህንነት ሃይሎች ያለ ተቆጣጣሪ ገብተው በሚወጡባት …

ነሃሴ ፳፮(ሃያስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በኢትዮጵያ የደህንነት ሃይሎች ታፍኖ መወሰድ ተከትሎ ንቅናቄው በተለያዩ አገራት የጠራው ህዝባዊ ስብሰባ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ዘጋቢዎቻችን ገልጸዋል፡ በኖርዌይ በተካሄደው ስብሰባ 250 ሺ የሚጠጋ ክሮነር ሲዋጣ፣ ዝግጀቱም በደመቀ ሁኔታ መጠናቀቁን ባልደረባችን አበበ ደመቀ ተናግሯል። በስብሰባው ላይ እንግዳ የነበሩት የንቅናቄው የህዝባዊ እምቢተንነት ሊ/መንበር አቶ …

ነሃሴ ፳፮(ሃያስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሱዳኑፕሬዘዳንት ጄኔራል አልበሸር  ከግብጹፕሬዘዳንት አብደልፋታህ አልሲሲ በተደረገላቸው ግብዣ መሰረት በጥቂት ቀናት ውስጥ ግብጽን እንደሚጎበኙ ታውቋል :: በካይሮ የሚገኙት የሱዳን አምባሳደር አብደልሃሊም አብደልሞሃመድ እንዳስታወቁት የጉብኝቱ ቀዳሚ አጀንዳ ኢትዮጵያ ስለምትሰራው  የግድብ ስራ ሲሆን ሱዳንም የግብጽን ችግር ለመረዳት ያስችላታልብለዋል:: ግብጽ በተደጋጋሚ እንዳስታወቀችው ኢትዮጵያ የምትሰራውግድብወደአገርዋየሚገባውንየውሃመጠንይቀንሳልበማለትክስእያሰማችትገኛለች:: አምባሳደር አብዱል በበኩላቸውእንደተናገሩት  ግድቡላይየሚነሳውአቤቱታየሚፈታው  በሶስትዮሽስምምነትብቻ ነውብለዋል:: ሶስቱ አገሮች …

ነሃሴ ፳፫(ሃያሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ አገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ነጋዴዎች ለኢሳት እንደገለጹት መንግስት በሰበብ አስባቡ ከገበያ እያስወጣቸው ነው።አንዳንድ ነጋዴዎች አድሎአዊ በሆነ ሁኔታ ከሚጣለው ግብር በተጨማሪ ፣ በአስተዳደራዊ በደሎች እየተማረሩ ነው። በአዋሳ ነዋሪ የሆኑ አንድ ነጋዴ እንደተናገሩት፣ ኢፍትሃዊ በሆነ መንገድ በተጣለባቸው ግብር ድርጅታቸውን ሸጠው ስደት ለመምረጥ እየተገደዱ ነው በሚዛን ተፈሪ ነዋሪ የሆኑ ሌላ አስተያየት ሰጪ …

ነሃሴ ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በለንደን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት በየሳምንቱ የሚካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ዛሬም በጠነከረ ሁኔታ ተካሂዷል። የተቃውሞ ሰልፉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሄዱን በስፍራው የምትገኘው መታሰቢያ ቀጸላ ገልጻለች። አቶ አንዳርጋቸው ባለቤት ወ/ሮ የምስራች ሃ/ማርያምም በተቃውሞ ሰልፉ እና በእንግሊዞች አቋም ዙሪያ ተናግረዋል።

ነሃሴ ፳፫(ሃያሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ከተማ በኢንቨስትምንት ስራ ላይ ከተሰማሩት በውጪ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጽያዊን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ወይንም የዲያስፖራ አባላት መካከል በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማሩት 7 በመቶ ብቻ መሆናቸው አሳሳቢመሆኑን አንድጥናትአመለከተ፡፡ የዲያስፖራው አባላት 93 በመቶ ያህል የተሰማሩባቸው ሥራዎች የአገልግሎት ዘርፎች ማለትም በሆቴል እና በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ መሆናቸውን ያመለከተው ጥናቱ አባላቱ በቴክኖሎጂ …

ነሃሴ ፳፫(ሃያሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኮሌጁ የሚማሩ ከ1 ሺ በላይ የክረምት ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው ለመውጣት የተገደዱት የትምህርቱ ጊዜ በመራዘሙ ነው። የኮሌጁ አስተዳደር ቀደም ብሎ ለ4 አመት ይሰጥ የነበረው ትምህርት ወደ 6 አመት እንደሚራዘም የገለጸላቸው ሲሆን፣ ተማሪዎቹ የኮሌጁን ውሳኔ ተቃውመዋል። “ብትፈልጉ ተማሩ ወይም ግቢውን ልቀቁ መባላቸውን” የገለጹት ተማሪዎች፣ በዚህም የተነሳ ግቢውን ለቀው ወደ መጡበት መመለሳቸውና …

ነሃሴ ፳፪(ሃያሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምርጫ 97 ለተገደሉት እና ለቆሰሉት ፍትህ ለመጠየቅ የተቋቋመው ግብረሃይል ስራውን አጠናቆ ዛሬ የ13 ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትንና የመከላከያ ሰራዊት አዛዦችን ስም ዝርዝር የያዘ የክስ ማመልከቻ ለስዊድን አለማቀፍ የጦር ወንጀል መርማሪ ፖሊስ አስረክቧል። አርከበ እቁባይ፣ በረከት ስምኦን፣ አባ ዱላ ገመዳ፣ ሳሞራ የኑስ፣ አባይ ጸሃየ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ሌ/ጄ ታደሰ ወረደ፣ ሃሰን ሺፋ፣ …

ነሃሴ ፳፪(ሃያሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ መንግስት በፋክት፣ አዲስ ጉዳይ፣ ሎሚ፣ እንቁ፣ ጃኖ መጽሄቶችና አፍሮ ታይምስ ጋዜጣ ላይ ፍትህ ሚኒስትር ክስ መመስረቱን ተከትሎ ሚዲያዎቹ ከህትመት በመውጣታቸው ምክንያት ስራ ሊያቆሙ መሆኑን የጋዜጣ አዙዋሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በአራት ኪሎ፣ ፒያሳ፣ መርካቶ፣ ሳሪስ፣ ቦሌና ካሳንቺስ የሚገኙ የጋዜጣ አዙዋሪዎች በርካታ አንባቢ የነበራቸው መጽሄቶችና ጋዜጦች ከገበያ በመውጣታቸው፣ ሌሎቹን ጋዜጦችና …

ነሃሴ ፳፪(ሃያሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግብጽ ጋዜጦች እንደዘገቡት ኢትዮጵያ ለወራት ውድቅ ስታደርገው የነበረውን ስምምነት ከግብጽ ጋር ተፈራርማለች። አዲሱ ስምምነት የአባይ ግድብ ግንባታ በውጭ አገር ገለልተኛ አጥኚዎች እንዲጠናና ኢትዮጵያም የጥናቱን ውጤት እንድታከብር የሚያስገድድ ነው። በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ሲደራደሩ የቆዩት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ አለማየሁ ተገኑ ከወራት በፊት ሱዳን ላይ ተካሂዶ በነበረው የሰላም ስምምነት ላይ ግብጽ …