ኀዳር ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ግሎባል ፋይንሻል ኢንተግሪቲ ባወጣው ዘገባ በዚህ ሳምንት የቡድን 20 አገራት በአውስትራሊያ በሚያደርጉት ስብሰባ በህገወጥ መንገድ ገንዘብ በሚያዘዋውሩ ኩባንያዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቋል። ተቀማጭነቱ አሜሪካ የሆነው ድርጅት በዋጣው ዘገባ፣ ኩባንያዎች ሽያጮቻቸውን፣ ታክሶቻቸውን፣ ትርፋቸውና ኪሳራቻውን ግልጽ እንዲያደርጉ መመሪያ ሊወጣላቸው ይገባል ብሎአል። ታዳጊ አገሮች በእነዚህ ኩባንያዎች የተነሳ በእየአመቱ 1 ትርሊዮን …

ኀዳር ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- “የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኢህአዴግ የምርጫ ድል የልማት ሰራዊት ግንባታ አደረጃጀት ማንዋል ለምርጫ 2007″ በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ሰነድ በጥቅምት ወር በአዋሳ እንዲቀርብ ተብሎ የተዘጋጀ ቢሆንም፣  የሰነዱ ጥራት የወረደና በሰነዱ የተካተቱት ነጥቦች ከልማት ሰራዊቱ ኢህአዴግ ሙሉ በሙሉ መጠቀሙን  አያረጋግጥም በሚል  በኢህአዴግ ጽ/ቤት በመተቸቱ እንዲሻሻል ከተደረገ በሁዋላ እንደገና ህዳር 1 …

ኀዳር ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአማራ ክልል የአስተዳደር እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሴ አሰሜ እንደተናገሩት በምዕራብ ጎጃም ዞን ሜጫ ወረዳ ፤ ሰሜን እና ደቡብ አቸፈር ስራ አጥ ወጣቶች በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ግንቦት ሰባት እና አርበኞች ግንባር እየተቀላቀሉ ነው። የወረዳው ወጣቶችን ያወያዩት ሃላፊው ወጣት አርሶ አደሩ ተምሮ ስራ ካላገኘ ፤ ወይ የሚያርሰው …

ኀዳር ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሰሜኑ የአገሪቱ ክፍሎች የታፈኑ  የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ወደ ማዕከላዊ መዛወራቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡ በሰሜን ጎንደር ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አግባው ሰጠኝ ፣ የምእራብ አርማጭሆ  የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ  ሰብሳቢ አቶ አንጋው ተገኝ  ትናንት  ወደ ማዕከላዊ መወሰዳቸውን ጋዜጣው ዘግቧል። ሌሎች የተቃዋሚ አመራሮች ወደ ማእከላዊ ይወሰዱ አይወሰዱ …

ኀዳር ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ገልፍ ኒውስ ባወጣው ዘገባ 4 ወንዶች አንዲት ኢትዮጵያዊትን አአስገድደው መኪና ላይ ከጫኑዋት በሁዋላ በየተራ ደጋግመው በመድፈርና በመኪናቸው ገጭተው በመግደል በላዩ ላይ ድንጋይ በማስቀመጥ ለማምለጥ ሞክረዋል። ግለሰቦቹ ተይዘው ፍርድ ቤት ከቀረቡ በሁዋላ የጄራጂ ፍርድ ቤት በግለሰቦቹ ላይ የሞት ፍርድ ለማስተላለፍ በሂደት ላይ ነበር። ይሁን እንጅ ዳኛ አብዱላህ የሱፍ …

ጥቅምት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ››በሚል መርህ ትብብር  የመሰረቱት 9 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቀደም ብለው ባሳወቁት የአንድ ወር መርሃ ግብር መሰረት የጀመሪያውን ጥሪ ለሃይማኖት ተቋማት አድርገዋል። ፓርቲዎቹ አገራችንና ህዝቧ በተፈጥሮ ሚዛን መዛባት በሚከሰትበትም ጊዜ ሆነ በአገዛዝ ሥርዓቶች ምክንያት በችግር ውስጥ በሚወድቁበት ጊዜ የኃይማኖት  ተቋማትና ምዕመናን ሚና ከፍተኛ እንደነበር አውስተው፣ ዛሬ ላይ እነዚህ …

ጥቅምት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-‹በተለይ ባሳለፍነው አንድ ሳምንት ጊዜያት ውስጥ መቆራረጡ በወሳኝ ሰዓታት ጭምር ማለትም በምሽት እና በጠዋቱ ጊዜያት ተጠናክሮ መቀጠሉን የገለጹት ነዋሪዎች በዚህ ምክንያት ለከፍተኛ ኪሳራና ወጪ እየተዳረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ባለስልጣናት «የኃይል እጥረት የለም፣ እንዲያውም ተርፎን ለጎረቤት ሀገራት ኤክስፖርት እያደረግን ነው» በሚሉበት በዚህ ወቅት በተለይ የአፍሪካ ርዕሰ መዲና መሆንዋ በሚነገርላት አዲስአበባ …

ጥቅምት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-‹በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ከገቢያቸው ጋር በማይመጣጠን የግብር  እዳ እየተሰቃዩ  ነው። የገዢው ፓርቲ ባለስልጣኖች አድሎአዊ በሆነ መልኩ በሚጥሉት ግብር ነጋዴዎች ድርጅታቸውን እየዘጉ ነው። በእነብሴ ሳር ምድር   ወረዳ አሰፋ ሁነኛው፣ ኢሳየ ቸኮል፣ የንጉስ ዋለና  መሰሉ የሚባሉት ነጋዲዎች በጋራ ለቤት መስሪያ በባንክ ከስያዙት  ገንዘብ ላይ ያለፍላጎተቻው …

ጥቅምት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ታማኝ የሆኑ የደህንነቶች ሰራተኞች ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የጦር መሳሪያ እና ሌሎች እቃዎችን ጭነው ሲጓዙ የነበሩ 4 መኪኖችን አስቁመዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴቨን ዱጃሪክ እንደገለጹት የደህንነት ሰራተኞች መሳሪያዎቹ ለአንድ ተቃዋሚ ሃይል ሊሰጥ ነው በሚል እንደያዙትና በሹፌሮቹ ላይ ጉዳት እንዳደረሱባቸው ገልጸዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት …

ጥቅምት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየስብሰባዎቹ የተሳተፉ ምንጮች ለዘጋቢያችን እንደተናገሩት በየመድረኩ የጋዜጠኞች መታሰር፣ የሃይማኖት እኩልነትና ነጻነት አለመከበር፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መባባስ፣የሙስናና ብልሹ አሠራር መንሰራፋት፣ የህወሃት የበላይነት መኖር፣ የድህነት መንሰራፋትና የዋጋ ግሽበት አለመቀረፍ፣ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ ወከባና እስር መጠናከር በተደጋሚሚ የሚነሱና ኢህአዴግ በቂ ምላሽ ሊሰጥባቸው ያልቻለባቸው አበይት ጉዳዮች መሆናቸው ታውቆአል፡፡ ጥያቄዎቹ በተለይ …

ጥቅምት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የድረገጹ አዘጋጆች ለኢሳት በላኩት መግለጫ እንደጠቀሱት ድረገጹ በኢትዮጵያ ውስጥ ወንጀሎችን ያቀዱ፣ ለወንጀሎቹ ውሳኔ የሰጡ፣ ወሳኔዎችን ያስፈጸሙ፣ የመሩና ያቀነባበሩትን በሰሜን አሜሪካ፣ በአውሮፓ እንዲሁም በየትኛውም የምእራብ ሀገሮች እንደ የሀገሮቹ የህግ አግባብ መሰረት ክስ ለመመሥረት የሚያስችሉ ልዩ ልዩ መረጃዎችንና ምስክሮችን ማሰባሰብ እና ማጠናቀር አላማ አድርጓል። ወንጀል በፈጸሙት ላይ በቂ …

ጥቅምት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአባይ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት እቅድ እንደሚያሳየው ግድቡ ሲጠናቀቅ 1600 ኪሎሜትር ስኩየር  መሬት የሚሸፍን ውሃ የሚተኛበት ሲሆን፣ የዚህ መሬት አካል 90 በመቶው በደን የተሸፈነነ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ አንጻራዊ በሆነ መልኩ የተሻለ የደን ሽፋን አለው የሚባለው ግድቡ የሚሰራበት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቢሆንም፣ ከ200 ኪሎ ሜትር ያላነሰ ስፋት ያለው …

ጥቅምት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን ተጠናክሮ የቀጠለው የገዢው ፓርቲ አፈና መንግስት ራሱ ያስታጠቃቸውን ታጣቂዎች ትጥቅ እስከማስፈታት መድረሱን ምንጮች ገለጹ በትግራይና በአማራ ክልሎች ባለፉት ሶስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው አፈና ቀጥሎ ጥቅምት 26 ቀን 2007 ኣም የሰላም ታጋይ እየጠባለ የሚታወቅ ወጣት ሽሻይ አዘናው በመቀሌ ከተማ በትግራይ ክልል የፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ገ/ህይወት ካህሳይ …

ጥቅምት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ በኢትዮጵያ እና በአረብ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት እንዲሁም መንግስት ወደ አረብ አገራት በሚላኩ ዜጎች ጉዳይ ሊፈጽመው ያሰበው ስምምነት ምን ደረጃ ላይ  እንደደረሰ ግምገማ ተካሂዶ ነበር። መንግስት ተጓዝ ሰራተኞችን በሚመለከተ ያወጣው ህግ በአረብ መንግስታት እውቅና የተነፈገው ሲሆን፣ የአረብ አገራት ባለስልጣናት ኢትዮጵያውያን …

ጥቅምት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዩኒቨርስቲው ውስጥ በሚታየው ተደጋጋሚ የሃይል መቆራረጥና የውሃ እጥረት ተማሪዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ ለመከታተል አልቻሉም። ከውሃ እጥረት ጋር በተያያዘ ከጽዳት ጋር ለተያያዙ በሽታዎች ሊደራጉ እንደሚችሉ ተማሪዎች ፍርሃታቸውን ገልጸዋል።

ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባዔ  የአሁኑ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ( ሰመጉ) ባወጣው 132ኛ ልዩ መግለጫ በክልሉ በመንገሽና ጎደሬ ወረዳዎች ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የተገደሉ የ60 ሰዎች ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል። በሪፖርቱ እንደቀረበው 27 የአማራ፣ 27 የመዠንገር፣ 2 የከፋና 4 የኦሮሞ ተወላጆች ተገድለዋል። እንዲሁም 16 የአማራና 6 የመዠንገር ተወላጆች …

ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፉት ሁለት ቀናት ጀምሮ መንግስት በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ የተቃዋሚ አመራሮችን በመያዝ እያሰረ ነው::  በትግራይ ክልል በምዕራባዊያን ዞን ቃፍታ ሁመራ ወረዳ ዳንሻ ከተማ የአረና ፓርቲ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ዘነበ ሲሳይ ጥቅምት 25፣ 2007 ዓም ከቤታቸው ተነጥለው በመወሰድ ሲታሰሩ፣  በተመሳሳይ ቀን በሁመራ የአረና የቁጥጥር ኮሚቴ አባል የሆኑት …

ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ክስ በመሰረተባቸው አቶ ዘላለም ወርቅነህ፣  ሃብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታ ፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ የሽዋስ አሰፋና በሌሎች 5 ተካሳሾች ላይ ዋስትናን በተመለከተ ሊሰጥ የነበረውን ውሳኔ አራዘመ። ፍርድ ቤቱ የሁሉም ጠበቆች ተዘጋጅተው ባለመቅረባቸው ውሳኔውን ለህዳር 2 ፣ 2007 ማራዘሙን አስታውቋል። እስረኞቹ በሽብር …

ጥቅምት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአዲስ አበባ የተላኩ የፌደራል ፖሊስ አባላትና ደህንነቶች፣ ወደ ፓርቲው መሪዎች ቤት ከንጋቱ አስራ አንድ ሰአት ላይ በመሄድ፣ መኖሪያ ቤቶቻቸውን ሰብረው በመግባትና አንዳንዶችንም ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በመደብደብ አፍነው ወዳልታወቀ ቦታ ወስደዋቸዋል። የመተማ ወረዳ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ በላይነህ ሲሳይ፣ የምእራብ አርማጭሆ ወረዳ ሰብሳቢ አቶ አንጋው ተገኝ እንዲሁም የስራ አስፈጻሚ …

ጥቅምት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ትብብር የመሰረቱ 9 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል ለአንድ ወር የሚቆይ የመጀመሪያ ዙር የህዝባዊ ትግል ፕሮግራሙን ጥቅምት 25/2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ይፋ አድርገዋል። ‹‹ነጻነት በሌለበት ፍትሃዊ ምርጫ የማይታሰብ በመሆኑ የተዘጋውን በር ለመክፈት የ‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ› በሚል የዝግጅት መርሃ ግብር አዘጋጅቷል። ‹‹ምርጫ ቦርድ ለገዥው ፓርቲ …

ጥቅምት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቅማንት ተወላጆች ያነሱትን ጥያቄ ተከትሎ በተጠራ የስራ ማቆም አድማ በዞኑ የሚገኙ ከ80 በላይ ትምህርት ቤቶች ካለፈው አርብ ጀምሮ የተዘጉ ሲሆን፣ መንግስት እስከ መስከረም 30 መልስ የማይሰጥ ከሆነ፣ ተቃውሞው ግብር ባለመክፈል እንደሚቀጥል አስተባባሪዎቹ ለኢሳት ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም በርካታ አስተባባሪዎች ተይዘው የታሰሩ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን መንግስት ለጥያቄው እስከ መስከረም …

ጥቅምት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ፍርድ ቤቱ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ ተይዘው በነበሩት ተማሪዎች ላይ ከ1 እስከ 5 በሚደርስ እስር እንዲቀጡ ውሳኔ አሳልፏል። በሌላ ዜና ደግሞ በአዳማ ቤታቸው የሚፈርስባቸው ሰዎች ባስነሱት ተቃውሞ ፖሊሶች ተጎዱ። የአከባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት  ከከተማ አስተዳደሩ ቤት አፍራሽ ግብረ ሀይል  ህገወጥ የተባሉ ቤቶችን ለማፍረስ ወደ ስፍራው …

ጥቅምት ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መጪውን ምርጫ ተንተርሶ በሚመስል መልኩ በምስራቅና ምእራብ ጎጃም አመራሮችና አባላት መታሰራቸውን ድርጅቱ አስታወቀ በተመሳሳይ ዜና ደግሞ የወላይታ ዞን የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ ማሞ ገሞ እና የዞኑ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ወኖ በዳሳ ጥቅምት 22 ቀን 2007 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ በአንድ ሆቴል ውስጥ እያሉ በከተማው የፖሊስ አዛዥ …

ጥቅምት ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሆለታ ገነት የሚገኘው የሼከ አላሙዲ ንብረት የሆነው “ኢትዮ ድሪም” የአበባ እና የእንጆሪ ሰራተኞች ጥቅምት 21 እና  22 ከፍያ ተፈጽሞላቸዋል። ሰራተኞች ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው ለኢሳት ባስተዋቁ በቀናት ውስጥ እንደተከፈላቸው ቢገልጹም፣ አሁንም ከሰራተኞች ማመላለሻ መኪናና ከጤና ጋር የተያያዙ ችግሮችን እያነሱ ነው።  ድርጀቱ ለሰራተኛ ማመላለሻ  /ሰርቪስ/ እና ለምርት ማጓጓዣ የተከራያቸው መኪኖች …

ጥቅምት ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መጤ አረሙ ከሸፈነው መሬት ሁለት ሺህ ሄክታር በሩዝ ማሳ ላይ ሲሆን ቀሪው በኃይቁና በዙሪያው በሚገኙ ውሃ አዘል መሬት ላይ መሆኑን ተገልጿል፡፡ አረሙ በደንቢያ፣ በጎንደር ዙሪያ፣ በሊቦ ከምከም፣ በፎገራና በደራ ወረዳ በሚገኙ 16 ቀበሌዎች በፍጥነት እየተዛመተ እንደሆነም ታውቋል።አረሙን ለማጥፋት ሲሞከርም በሦስት ሳምንታት ራሱን መልሶ የሚተካ መሆኑና በውሃው ላይ …

ጥቅምት ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጀቱ እሁድ እለት በሮም ባካሄደው ስበሰባ ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተገኝተው ድርጅቱን ወክለው ከተገኙት ከአቶ አበበ ቦጋለ ጋር ውይይት አድርገዋል። የፖለቲካ ድርጅቶች በጣሊያን ስብሰባ ሲያደርጉ ባይታይም፣ ግንቦት7 ያካሄደው ስብሰባ ግን የተሳካ እንደነበር ያዘጋጅ ኮሚቴው ሰብሳቢ ሮዛ ተስፋየ ለኢሳት ተናግራለች። በውይይቱ ላይ የተገኙት አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ግንቦት7 ከኤርትራ ጋር ስላለው …

ጥቅምት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል አቃቢ ህግ በ10 ተከሳሾች ላይ የሽብርተኝነት ወንጀል ክስ የመሰረተባቸው ሲሆን አብዛኞቹ ተከሳሾች ከግንቦት7 እና ከደሚት ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለዋል። የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት  ጥቅምት 21/2007 ዓ.ም  ሲሰየም ተከሳሾች በመቶዎች የሚቆጠሩ ገጾች ያሉዋቸው ክሶች ደርሷቸዋል። የግንቦት7 አመራር ነው የተባለው ዘላለም ውርቅአገኘሁ፣ አንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት …

ጥቅምት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሃረርና የድሬዳዋ ወኪሎች እንደዘገቡት ከጥቅምት 17 ጀምሮ ከአዲስ አበባ የመጡ የፌደራል የጸረ ሽብር ግብረ ሃይል አባላት መሆናቸውን የገለጹ እንዲሁም የፌደራል ፖሊሶች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የኢንትርኔት ቤት ባለቤቶችን ይዘው በማሰር ወደ ማእከላዊ እስር ቤት ወስደዋቸዋል። ድርጅቶቻቸውና ቤቶቻቸው የተፈተሹባቸው ሲሆን፣ ንብረቶቻቸውም ተጭነው ተወስደዋል። በሀረር በገሊል ህንጻ ላይ የሚገኘው የአሜን ፕሮዳክሽን …

ጥቅምት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እንግሊዝ አገር የሚታተሙ ጋዜጠኞች ከዚህ ቀደም ለኢትዮጵያ በቂ ሽፋን አይሰጡም በሚል ሲተቹ ቢቆይም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ በማንሳት እንግሊዝ በኢትዮጵያ የምትከተለውን ፖሊሲ የሚነቅፉ ዘገባዎችን እያወጡ ነው። ዘ ቴሌግራፍ ” እርዳታችን ለተበላሹ እጆች” በሚል ርእስ ባወጣው ሃተታ፣ በቅርቡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በኦሮሞ ህዝብ ላይ …

ጥቅምት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስአበባ የመኖሪያ ቤቶችን እጥረትን ለመፍታት ዳግም በተደረገው ምዝገባ ከ993 ሺ በላይ ቤት ፈላጊዎች መመዝገባቸውንና ይህን የቤት ፍላጎት ለማርካት በመንግስት በኩል እየተካሄዱ ያሉ ግንባታዎች አፈጻጸም ደካማ መሆኑን ከኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት የተገኘ መረጃ ጠቁሟል። እንደመረጃው ከሆነ የአዲስአበባ ቤቶች ግንባታ ለማየት በተካሄደው የመስክ ግምገማ የአዲስአበባ የቤቶች ግንባታ አፈጻጸም በዝቅተኛ …

ጥቅምት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለ27 አመታት አገሪቱን የመሩት ብሌስ ካምፓወሬ፣ እንደገና ለመመረጥ የነበራቸውን ፍላጎት ተቃውሞ መነሳቱን ተከትሎ መተዋቸውን ካስታወቁ በሁዋላ፣ የሽግግር መንግስት ፕሬዚዳንት በመሆን ለማገልገል መፈለጋቸውን ገልጸው ነበር። ይሁን እንጅ ተቃዋሚዎች ፕሬዚዳንቱ ከስልጣን ካልተባረሩ ተቃውሞአችንን አንተውም በማለታቸው፣ ፕሬዚዳንቱ ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን አስታውቀዋል። ተቃውሞቸውን ሲያሰሙ የነበሩት ሁሉ የመሪውን መውረድ እንደሰሙ ደስታቸውን ገልጸዋል። የአገሪቱ …

ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በርካታ ቁጥር ያላቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት በቴፒ ከተማ በብዛት መታየታቸውን ተከትሎ መንግስት   የከተማውን ህዝብ አርብ ጥቅምት 20፣ በትልቁ አዳራሽ በመሰብሰብ፣ በአካባቢው የሚታየውን ችግር በጋራ እንፍታ በማለት ጥሪ አቅርቧል። ለግማሽ ቀን በተካሄደው ስብሰባ ነዋሪዎችና የመንግስት ባለስልጣናት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሲወዛገቡ አርፍደው ሳይግባቡ መለያየታቸውን በስብሰባው የተሳተፈው ወኪላችን ገልጿል። …

ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ለአንድ ሳምንት ያክል በታሰረበት ክፍል ውስጥ እንዲጸዳዳ መደረጉን፣ ለ3 ቀናት በጨላ ክፍል ውስጥ ታስሮ የበቀል እርምጃ እንደተወሰደበት ፓርቲው በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። ምክትል የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ የሆነው አቶ ዳንኤል ሽበሺ ደግሞ በታፈነ ክፍል ውስጥ እንዲቀመጥ መደረጉን፣ በተቅማጥና በሌሎች በሽታዎች እየተሰቃየ …

ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-  በምዕራብ ሸዋ በሆለታ ገነት የሚገኘው የሼክ ሙሃመድ አላሙዲጅ ንብረት በሆነው ” ኢትዮ ድሪም” ድሪም የአበባ እርሻ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ላለፉት ሁለት ወራት ደሞዝ ያልተከፈላቸው በመሆኑ እነሱና ቤተሰቦቻቸው ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል። ሰራተኞች አቤቱታቸውን ለድርጅቱ ሃላፊዎች ቢያቀርቡም መልስ ማጣታቸውን ገልጸዋል። አብዛኛው ሰራተኛ 600 ብር እንደሚከፈለው የሚናገሩት ሰራተኞች፣ ከዚህ …

ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሪክ ማቻር የሚመራው የተቃዋሚ ቡድን ቤንቲዩና ሮቡክና የተባሉ ቦታዎችን መቆጣጠሩን መረጃዎች አመለክተዋል። ሁለቱን ተፋላሚ ሃይሎች ለማስታረቅ በኢትዮጵያ በኩል ሲደረግ የነበረው ድርድር ውጤት አለማምጣቱን ታዛቢዎች ይናገራሉ። የሪክ ማቻር ሃይሎች ሃይላቸውን እያጠናከሩ በመሆናቸው ሌሎች ከተሞችንም ለመያዝ ተከታታይ ጥቃት ሊፈጽሙ ይችላሉ ሲሉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ገልጸዋል።

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ዋና ኦዲተር፣ አባካኝ የመንግስት ተቋማት በሚል ለጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት እና ለተወካዮች ም/ክር ቤት አፈ ጉባኤ ያቀረበው ሪፖርት ለህዝብ ይፋ ይሁን አይሁን የሚለው ጉዳይ  ሚኒስትሮችን አወዛግቧል። አቶ አባዱላ ገመዳ፣ አቶ ደመቀ መኮንን፣ አቶ አዲሱ ለገሰና አቶ ጸጋየ በርሄ፣ የፌደራል ኦዲተሩ ሪፖርት ለህዝብ በፍጹም ሪፖርት መደረግ የለበትም ብለው …

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው ባወጣው መግለጫ የሀገራችን አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሱና እየከፉ የመምጣታቸውን ያህል ገዢው ፓርቲ ቆም ብሎ ከማሰብ ይልቅ ወደ ማይወጣው አዘቅት ውስጥ ሀገሪቷን ጭምር እያንደረደራት ይገኛል ብሎአል። ኢህአዲግከዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደት ፍፁም በማይጣጣም መለኩ ዜጎችን ለአንድ ሀሳብ ብቻ እንዲገዙ አስገዳጅ መንገዶችን ጭምር በመጠቀም አፋኝ መዋቅሩን …

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ለ 90 ቀናት በተከታታይ በወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ እና የመረጃ እና ደህንነት ትምህርቶች ያሰለጠናቸውን ታጋዮች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የተለያዩ የተቃዋሚ ድርጅቶች ተወካዮች በተገኙበት በደመቀ  ሁኔታ ባስመረቀበት ወቅት የህዝባዊ ሃይሉ ስልጠና በግንቦት ሰባት ስም ከሚደረጉት ስልጠናዎች የመጨረሻው መሆኑ ተመልክቷል። የህዝባዊ ሃይሉ ዋና አዛዥ ኮማንደር አሰፋ …

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከትናንት በስቲያ በጨርቆስ አካባቢ አንድ ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሎ መገኘቱን እና ሌሊት ላይ በቦሌ አካባቢ የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን የሚያስተጋቡ ወረቀቶች በየግድግዳውና የኤሌክትሪክ ፖሉ ላይ ተለጥፈው መገኘታቸውን ተከትሎ በከተማዋ ውጥረት መንገሱን ነገረ ኢትዮጵያ በዘገባው አመልክቷል። ‹‹አንድ የጨርቆስ አካባቢ ነዋሪ ተገድሎ መገኘቱን ተከትሎ ‹የጨርቆስ ወጣቶች› ተሰባስበው ይህን ድርጊት ይፈጽሙ …

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለቤታቸውን በድንገተኛ ሞት ከማጣታቸው በፊት የፓርላማ አባል የነበሩት ወ/ሮ አዜብ መስፍን በራሳቸው ፍቃድ ፓርላማውን ከመልቀቃቸውም በተጨማሪ በድርጅታዊ ስራዎች ላይ የሚያደርጉት ተሳትፎ እየተዳከመ መምጣቱን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ወ/ሮ አዜብ ባለፈው አንድ ዓመት በፓርላማው መቀመጫቸው ላይ ታይተው የማያውቁ ሲሆን ለፓርላማው ቅርበት ያላቸው ምንጮች ወይዘሮዋ  በራሳቸው ፈቃድ ከፓርላማ አባልነታቸው መሰናበታቸውን ገልጸዋል፡፡ …

ጥቅምት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ታዋቂው አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅት በፈረንጆች አቆጣጠር ከ2011 እስካሁን ያለውን ሁኔታ አጥንቶ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ፣ ከ5 ሺ ያላነሱ ኦሮሞች በእስር ላይ ይገኛሉ። ጥናቱን ያጠኑት የአምነስቲ የኢትዮጵያ ክፍል ሃላፊ ክሌር ቤስተን መንግስት አገሪቱን ለአለማቀፍ የመገናኛ ብዙሃን፣ ለአለማቀፍ የሰብአዊ  መብት ድርጅቶች እንዲሁም ለአገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ክፍት ቢያደርግ …

ጥቅምት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ፖሊሶች ሰኞ እለት አሸባሪዎች በከተማዋ ገብተዋል በማለት በቦሌ አካባቢ ፍትሻ ባደረጉ ምሽት መንግስት ሙስሊሙ ማህበረሰብ ያነሳውን ጥያቄ እንዲመልስ የሚጠይቁ መፍክሮች  በቦሌ ወሎ ሰፈርና በደንበል አካባቢዎች ተጽፈው አደረዋል።  መብትን መጠየቅ ሽብር አይደለም፣ ድምጻችን ይሰማ፣ በመንግስታዊ ጥቁር ሽብር ተስፋ አንቆርጥም የሚሉ መፈክሮች በየመንገዱ ተለጥፈው ታይተዋል። ተመሳሳይ መልእክት የያዙ …

ጥቅምት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያ የሚገኙት የአለም ባንክ ፕሬዚዳንት ጂም ዮንግ ኪም በምእራብ አፍሪካ የሚታየውን የኢቦላ ወረርሽን ለመዋጋት ቢያንስ 5 ሺ ዶክተሮች የሚያስፈልጉ በመሆኑ ፣ ዶክተሮች ና የጤና ባለሙያዎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃዳቸውን እንዲገልጹ ተማጽነዋል። ” በአሁኑ ሰአት ይህን ሁሉ ቁጥር ያለው የህክምና ዶክተር ከየት እንደምናገኝ ሳስብ እጨነቃለሁ” ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ …

ጥቅምት ፲፮(አስራ ሥድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመስተዳድሩ ኃላፊዎች በፖለቲካ ስልጠና እና በግምገማ መወጠራቸው ውሳኔ በወቅቱና በአግባቡ የሚሰጥ አካል በመጥፋቱ ነዋሪዎች አገልግሎት ለማግኘት ተቸግረዋል። በእያንዳንዱ የሴክተር መስሪያ ቤት ውስጥ የሚገኙጥ ኃላፊዎች የሉም ያለው ዘጋቢያችን፣ ውሳኔዎችን የሚሰጥ በመጥፋቱ የውጪም ሆነ የውስጥ አግልገሎት ቆሟል። ኦህዴድ በአዲስ አበባ ያሉትን ከፍተኛ የአመራር አካላት ወደ አዳማ በመጥራት ለ14 ቀናት …

ጥቅምት ፲፮(አስራ ሥድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጋምቤላና በደቡብ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች በሚኖሩ በመዠንገርና በመንግስት ታጣቂ ሃይሎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ፣ ቁጥራቸው 50 የሚጠጋ የፌደራል ፖሊስ፣ የመከላከያና የአካባቢው ሚሊሺያዎች ከተገደሉ በሁዋላ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመከላከያ ሰራዊት አሁንም በአካባቢው እንቅስቃሴ እያደረገ ነው። ወኪላችን እንደሚለው ጦርነት ይነሳል በሚል ካለፈው ሳምንት አጋማሽ ጀምሮ ከፍተኛ ስጋት የነበረ ሲሆን፣ …

ጥቅምት ፲፮(አስራ ሥድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው እውቁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ህዝብን ለአመጽ በማነሳሳት፣ ግዙፍ ባልሆነ ማሰናዳትና የመንግስትን ስም በማጥፋት ወንጀል ተከሶ ሲከራከር ከቆየ በሁዋላ፣ የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 9ኛ ወንጀል ችሎት በ3 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል። ጋዜጣውን ሲያሳትም የነበረው ማስተዋል የህትመትና ማስታወቂያ ስራ ድርጅት ደግሞ በ10 ሺ …

ጥቅምት ፲፮(አስራ ሥድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ፖሊስ አባላት አሸባሪዎች ገብተዋል በማለት የሚያደርጉት ተደጋጋሚ ፍተሻ እንዳስመረራቸው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚታየው የተጠናከረ ፍተሻ ሰኞ እለት ተጠናክሮ መቀጠሉን የተናገሩት በቦሌ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ ግለሰቦች፣ አሸባሪዎች ገብተዋልና አጋልጡ በሚል መኪኖች ሲፈተሹ መዋላቸውን፣ መንገደኞች እየቆሙ መፈተሻቸውን እንዲሁም የቤት ለቤት አሰሳ መደረጉን ለሰአታት ታግተው የቆዩ …

ጥቅምት ፲፫(አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ለ3ኛ ጊዜ በተዘጋጀው የፖለቲካ ስልጠና መድረክ ከወረዳ ጽ/ቤት እስከ ማዕከል ቢሮዎች የሚገኙ ሰራተኞች እና የፌደራል መ/ቤት ሰራተኞች ከማክሰኞ ጥቅምት 3 ቀን እስከ ቅዳሜ ጥቅምት 14/2007 ዓ.ም ለተከታታይ 11 ቀን የፖለቲካ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን፣  በዚህ መድረክ እስካሁን ከታዩት በላይ በሰልጣኖችና በኢህአዴግ አመራሮች መካከል ፍጥጫ ታይቷል። ጠንካራ …

ጥቅምት ፲፫(አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያ በፈረንጆች አቆጣጠር ከ2008 እስከ 2013 በነበረው ጊዜ ከፖሊዮ ነጻ አገር ተብላ የተወደሰች ቢሆንም፣ ካለፉት 2 አመታት ጀምሮ በሽታው እንደገና መታየቱን ዩኒሴፍ አስታውቋል። ባለፈው አመት 10 የፖሊዮ ተጠቂዎች መታየታቸውን የገለጸው ዩኒሴፍ፣ የበሽታው እንደገና መከሰት ለአገሪቱ ፣ ለቤተሰቦችና ለህጻናቱ እጅግ አደገኛ ክስተት ነው ብሎአል። ኢትዮጵያ በሽታውን ለመከላከል ተጨማሪ …

ጥቅምት ፲፫(አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያኑ በህገወጥ መንገድ መግባታቸውን የገለጸው የኬንያ ፖሊስ፣  54ቱ ኢትዮጵያውያን በአንድ ቤት ውስጥ ታጭቀው ተገኝተዋል ብሎአል። ሰዎቹን ወደ ኬንያ ያመታው ግለሰብ መጥፋቱንም ፖሊስ ገልጿል። ኢትዮጵያውያንን ወደ ደቡብ አፍሪካ ማሻገር ትልቁ የገቢ ምንጭ እየሆነ መምጣቱን ፖሊስ ገልጿል። ወደ ደቡብ አፍሪካ እንጓዛለን በማለት ሙከራ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን፣ በ ዝምባብዌ፣ ታንዛኒያ፣ ኬንያና …