ጥር ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ትብብሩ ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ ፤ገዥው ፓርቲ  በአንድነት የውስጥ ጉዳይ ገብቶ የሚፈፅመውን ደባ ለመቃወም ሰልፍ በወጡ የአንድነት አመራሮች፣ አባላት፣ ደጋፊዎችና በፓርቲው ጽህፈትቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ቤተ ክርስትያን አካባቢ በነበሩ አዛውንቶቸ ላይ  ሳይቀር ድብደባ በመፈጸም ፤ጭካኔውን ዳግመኛ አሳይቶናል ብሏል። ትብብሩ ጠርቶት በነበረው የአዳር ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተወሰደውን ዘግናኝ እርምጃ …

ጥር ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአበበ ቢቂላ፣ የማሞ ወልዴና የዋሚ ቢራቱ ልጆች በአረቢያን ባህረ ሰላጤ ዳርቻ ጀግንነታቸውን አስመሰከሩ። ወበቃማውን  የዱባይ አየርና አናት የምትበሳውን ጸሀይ በመቋቋም በደማቅ ቀለም ልዩ ታሪክ ጻፉ። የዝናም ውሀ በተጠማው የዱባይ ምድር አረንጓዴ ጎርፍ ፈሰሰ። ዛሬ ማርፈጃውን  የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባዘጋጀው የዱባይ ማራቶን  በወንዶች 1ኛ ኢትዮጰያ 2ኛ ኢትዮጰያ………………….12ኛ ኢትዮጵያ በመሆን …

ጥር ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር የተባረሩት አብዮታዊ ዲሞክራሲን መቀበል ያልቻሉ ናቸው ብለዋል። በአሁኑ ወቅት በመላ ሀገሪቱ ፖሊሶችና ሚሊሻዎች ከምርጫው ጋር በተያያዘ ሊነሱ ይችላሉ የተባሉ ህዝባዊ አመጾችን ለማክሸፍ ያስችላል የተባለ የተኩስ ልምምድ እያደረጉ እንደሚገኙ ከየክልሎቹ የመጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። ከፍተኛ በጀት ተመድቦለት በፌድራል ፖሊስ  አድማ ብተና አደረጃጀት  በየክልሉ የሚካሄደውን  ይህን  …

ጥር ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከቀናት በፊት በፖሊሶች ከፍተኛ ድብደ ተፈጽሞባቸው ወዳልታወቀ ስፍራ ስለመወሰዳቸው የተዘገበው የመላው ኢትዮጰያ አንድነት ድርጅት ምክትል ፕሬዚዳንት  አቶ ዘመነምህረት አዘዞ በሚገኘው መከላከያ ካምፕ መታየታቸውን ፓርቲያቸው ገለጸ። መኢአድ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የድርጅቱ  ምክትል ፕሬዝደንት እና የሰሜን ቀጠና ኃላፊ የሆኑት አቶ ዘመነ ምህረት የድርጅታቸውን ጠቅላላ ጉባኤ አድርገው ወደ መኖሪያቸው ጎንደር …

ጥር ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቲቪ(ኢቢሲ) ፣ራዲዮ ፋና እና ሌሎች የመንግስት ሚዲያዎች በምርጫው ዙሪያ ጠንካራ ስራ አልሰሩም ሲል የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር ተቸ። የመንግስትና የድርጅት ሚዲያዎች  ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ  ለተፎካሪ ፓርቲዎች በተሰጣቸው አጀንዳ ዙሪያ ብልጫ ያለው ስራ  አልሰሩም ሲል የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር -የኢትዩጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬትን ወቀሰ። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ -ለኢቢሲ  ባስተላለፈው የደብዳቤ …

ጥር ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የባህርዳር፣የአዲስ አበባ፣ የአምቦ፣ የጅማ፣የድብረማርቆስ እና የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ለኢሳት ወኪሎች እንደተናገሩት  በየቤቱ እየዞሩ  የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ በሚቀሰቅሱ ካድሬዎች ከመረበሻቸውም በላይ  የምርጫ ካርድ ካላወጡ ስለሚጠብቃቸው ቅጣት  ዛቻና ማስፈራሪያ እየተፈጸመባቸው ይገኛል። ሲጀመር ምርጫ መኖሩ በየቀኑ በራዲዮና በቴሌቪዥን እየተለፈፈ ባለበት ሁኔታ  በር እያንኳኩ ምርጫ ካርድ ውሰዱ ብሎ መቀስቀሱ አስፈላጊ አልነበረም …

ጥር ፲፬(አስራ አራት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቀደም ሲል የኢህአዴግ መንግስት ፤ በስዊድን-ስቶኮሆልም  አዘጋጅቶት የነበረው የቦንድ ሽያጭ ዝግጅት ላይ ኢትዮጰያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ ማሰማታቸው ይታወቃል። <<ከአባይ በፊት ዘረኝነት ይገደብ>> በሚል መርህ ተቃውሞውን ያደረጉት ኢትዮጰያውያን፤  ዜጎች ያለፍርድ እየታሰሩና እየተገደሉ ባለበት ሁኔታ  ገንዘብ ለመሰብሰብ መሯሯጥ፤ በሀገርና በህዝብ ላይ መቀለድ እንደሆነ በመናገር  ነበር- ተቃውሟቸውን  ጫማና እንቁላል በመወርወር …

ጥር ፲፬(አስራ አራት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፖሊሶች ልብሳቸውን በመቀየር በእግራቸው ወደ ጅንካ ከተማ እየሸሹ ነው። የፖሊስ ግጭት ወቅታዊ መረጃን በመጥቀስ የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ባወጣው መግለጫ እንደተመለከተው፤ ሐመሮች በወሰዱት የመልሶ ማጥቃት እርምጃ የዞኑን የፖሊስ አዛዥ ሻምበል ለማ አሸናፊን ጨምሮ ሰባት ፖሊሶች ሲገደሉ፤ ስድስት  ፖሊሶች ደግሞ ቁስለኛ ሆነዋል። ከፖሊሶቹ በተጨማሪ ሁለት ሲቪሎችም መገደላቸውና …

ጥር ፲፬(አስራ አራት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የድርጅቱ ምንጮች ለኢሳት እንደጠቆሙት፤ በመጀመሪያው ዙር ፈሰስ የተደረገው ይህ ገንዘብ ለቲሸርት ፤ ለኮፍያ ፤ እና ለበራሪ ወረቀቶች ህትመት  የሚውል ነው ተብሏል፡፡ ለፕሮሞሺን ስራ አገልግሎት የሚውል ተብሎ በብሄር ለተደራጁ ድርጅቶች ፈሰስ  ከተደረገው ከዚህ ገንዘብ ባሻገር ለአራቱ የኢህአዴግ ድርጅቶች ማለትም ለህወሀት፣ ለብአዴን፣ለኦህዴድ እና ለደኢህዴግ  5 ሚሊዮን  87 ሺህ …

ጥር ፲፬(አስራ አራት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አደጋው የደረሰው ሳሪስ አቦ ማዞሪያ ትንሽ ከፍ ብሎ በሚገኘውና የሀዲድ ንጣፍ ስራ እየተካሄደበት ባለ ቦታ ላይ ነው። በአደጋው የደረሰውን ጉዳት ለጊዜው ማወቅ   ባይቻልም፤አምቡላንሶች የተጎዱ ተማሪዎችን  ወደ ሆስፒታል ሲያመላልሱ  መዋላቸውን ሪፖርተራችን ከስፍራው ዘግቧል።

ጥር ፲፬(አስራ አራት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግና ምርጫ ቦርድ አንድነት ፓርቲ ለሁለት እንደተሰነጠቀ በማስመሰል ያቀነባበሩት ሴራ መጋለጡን እና መክሸፉን ከፓርቲው ጽሕፈት ቤት  የደረሰን ዜና ያመለክታል። ምርጫ ቦርድ “የአንድነትን ጠቅላላ ጉባኤ ጠርተዋል” ሲላቸው  የነበሩት አቶ አየለ ስሜነህ፤ በዛሬው እለት “አንድነት አንድ ነው፤ እናት ፓርቲዬን ለማዳን ተመልሻለሁ” በማለት በአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በአንድነት …

ጥር ፲፫(አስራ ሦስት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሀገሪቱ የምትመራበትን  ፖሊሲ ከመጠምዘዝ ጀምሮ ድርጊቱ በሀገርና በህዝብ ላይ የከፋ ተጽእኖ እንዳለው የተገነዘቡ ኢትዮጰያውያን በዩኒቨርሲቲው ላይ  የተቃውሞ ዘመቻ እያስተባበሩ ነው። አዲስ አበባ የሚገኘው ኢንተርናሽናል ሊደር ሺፕ ኢንስቲትዩት አማካይነት የሚቀርቡለትን ባለስልጣናት በአጭር ቀናት ኮርስ በማስተርስ ዲግሪ እያንሸበሸ ያለው ፤በእንግሊዝ ሀገር የሚገኘው የግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ ነው። በአይ ኤል አይ ድረገጽ …

ጥር ፲፫(አስራ ሦስት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምርጫ ቦርድ የውስጥ ጠቅላላ ጉባዔ ጠርታችሁ የውስጥ ችግራችሁን ካልፈታችሁ በመጪው ምርጫ አትሳተፉም የሚል  ውሳኔ በ አንድነትና በመ ኢአድ ፓርቲዎች ላይ ማሳለፉን ተከትሎ አንድነት ፓርቲ  የቦርዱን ውሳኔ ለማሟላት ከሳምንት በፊት  በአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ  ማካሄዱ ይታወሳል።   ይሁንና በወቅቱ ድርጅቱ  በጠራው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ተጋብዞ  ተወካዩን ለመላክ ፈቃደኛ …

ጥር ፲፫(አስራ ሦስት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዜጎች የምርጫ ካርድ እንዲያወጡ ጥሪ  ያቀረበው የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር፤ <<ምህዳሩ ካልተስተካከለ  ምርጫው አንድ ቀን ሲቀረውም ቢሆን ከምርጫ ልንወጣ እንችላለን›› ሲል አስታወቀ። ትብብሩ ፡<<ነፃነትን የማስመለስ ትግሉን አጠናክረን እንቀጥላለን>> በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ፤ ኢህአዴግና ምርጫ ቦርድ አፈና እና ጫና እያደረጉ ቢሆኑም ነፃነትን ለማስመለስ የያዘውን ግብ ለማሳካት ወደኋላ እንደማይል …

ጥር ፲፫(አስራ ሦስት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል  የመላው ኢትዮጰያ አንድነት ድርጅት  አባላት በብዛት እየታሰሩ መሆናቸውን ከስፍራው  አንድ የመኢአድ  አመራር ገለጹ። የድርጅቱ የ አዲስ አበባ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አወቀ አባተ  ለኢሳት እንደገለጹት፤በምራብ ጎጃም ዞን  በዳንግላ ወረዳ ጫራ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት የመኢአድ አባላት ወጣት ታጀለ አለኸኝ እና ወጣት የዋንስ ገደቡ፣ እንዲሁም የቡሬ …

ጥር ፲፪(አስራ ሁለት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመጪው ግንቦት ከሚካሄደው ምርጫ ጋር በተያያዘ በመላ ትግራይ ክልል  <<ምርጫ አስፈጻሚ>>የተባሉ ተኳሽ ሚሊሻዎች ከፍተኛ የተኩስ ልምምድ እያደረጉ እንደሚገኙ በለክልሉ ያሉ ወኪሎቻችን ዘግበዋል። ይህ የሚሊሻዎች ስልጠናው ፤ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በሗላ  በዓይነቱም ሆነ በሰልጣኞቸ ብዛት ለየት ያለ ሲሆን፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የህወሓት ኣባላት ብቻ  የተሳተፉበት መሆኑ ታውቋል። ሚሊሻዎቹ በኣፅቢ …

ጥር ፲፪(አስራ ሁለት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ልጅ በሆኑት  በዶክተር አሉላ ፓንክረስ የሚመራው  <፣ያንግ ላይቭስ>> ሰሞኑን ይፋ ባደረገው ጥናት  ኢትዮጵያ ውስጥ  የትምህርት ደረጃና ጥራት ከክልል-ክልል እንደሚለያይ ጠቁሟል። ትምህርት ከጀመሩ ተማሪዎች መካከል  17 በመቶ ያህሉ በተለያዩ  ችግሮች እንደሚያቆሙ  ያመለከተው ጥናቱ፤ ከሚማሩት መካከልም 24 በመቶዎቹ  ወደተከታዩ ክፍል ማለፍ እየተሳናቸው እንደሚደግሙ  ይጠቁማል። ዋና …

ጥር ፲፪(አስራ ሁለት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሮፌሰር መስፍን ይህን ያሉት ሰማያዊ ፓርቱ እና በሰሜን አሜሪካ የሰማያዊ ፓርቲ ድጋፍ ኮሚቴ በመተባበር ያዘጋጁትን ውይይት ሲከፍቱ ነው። <<ሁላችንም ስንለወጥ ነው ለውጥ የሚመጣው ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን፤ ከጣሊያን ጊዜ አንስቶ አሁን እስካለንበት ጊዜ ድረስ ባንዳው፣ፖሊሱ፣ባለስልጣኑ ሁሉ በመሸጦነት ማለፋቸውን በማውሳት፤ አንድ ትውልድ ይህን የመሸጦነት ባህል እየተባበረ ከሄደ ለውጥ …

ጥር ፲፪(አስራ ሁለት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሐውልቱ  ስራ  አስተባባሪዎች መካከል  የጃኖ  ባንድ መስራች የሆነው አርቲስት አዲስ ገሰሰ  ለታዲያስ  አዲስ እንደገለጸው፤  የቦብ  ማርሌይ  ሐውልት  ከሶስት  ሳምንት  በሁዋላ  በገርጂ  ኢምፔሪያል ሆቴል ፊት ለፊት ይቆማል። በምርጫ 97 ዋዜማ የቦብ ማርለይ 60ኛ አመት በመስቀል አደባባይ  ሲከበር፤ በወቅቱ  የመዲናዋ  ከንቲባ  የነበሩት አቶ አርከበ  እቁባይ  በበአሉ የተገኙትን የቦብ …

ጥር ፲፪(አስራ ሁለት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ደብረጽዮን- ከአርቲስቶች ጋር  ባደረጉት ዝግ ስበሰባ የተናገሩት ነገር ተቀርጾ  በይፋ  በማህበራዊ  ሚዲያዎች የተለቀቀ ሲሆን፤ በንግግራቸው አርቲስቶችን ሲመክሩና፣ ሲያባብሉ እና  ሲገስጹ ተሰምተዋል። <<በፌስ ቡክ የሚነገረንን ነገር እንሰማለን፤አርቲስቶች ሆዳሞች እንደምትባሉ እናውቃለን!>> ያሉት ዶክተር ደብረጽዮን፤ <<መለስን ሳይቀር የሚሳደቡ አሉ፤ መለስን ብቻ ሳይሆን ሁላችንንም ሲሰድቡን አይተናል>> …

ጥር ፲፩(አስራ አንድ ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጎንደር በፋሲል ግንብ አጠገብ በተከበረው በዓለ-ጥምቀት ከትናን የከተራ እለት ጀምሮ በርካታ ቱሪስቶች መገኝታቸውን ወኪላችን ከስፍራው ዘግቧል። በዓሉ በአዲሰ አበባ ጃን ሜዳም – እንደ ወትሮው ሁሉ እጅግ በደመቀ ሁኔታ መከበሩ ታውቋል። በላሊበላ እጅግ በርካታ ቀሳውስት ተገኝተው በወረብና በዝማሬ ማክበራቸውንም በስፍራው ያለችው ወኪላችን የላከችው መረጃ ያመለክታል። እንዲሁም በተለያዩ የውጪ …

ጥር ፲፩(አስራ አንድ ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወይዘሮ የምስራች በተለይ ለኢሳት  ሲናገሩ፤ አቶ አንዳርጋቸው ካልታወቀ እስር ቤት ሆነው ልጆቻቸውንና የቤተሰቡን አባላት ድንገት ሲያናግሩ ደንግጠው እንደነበር በመጥቀስ፤ ድንገት የተደወለውን ስልክ ሲያነሱ በድምጻቸው ወዲያው እንደለዩዋቸው ግልጸዋል። ሰላምታ ከተለዋወጡ በሁዋላ ጤንነታቸውን በተመለከተ እንደተጠያየቁና   አቶ አንዳርጋቸው በደህና ጤንነት ላይ መሆናቸውን እንደገለጹላቸውም ወዘይሮ የምስራች ተናግረዋል። <<ድምጹን ሥንሰማው  ደስታም፣ድንጋጤም …

ጥር ፲፩(አስራ አንድ ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በባህር ዳር ከተማ  ለከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች  መምህራን ሲካሄድ የቆየው ስብሰባ የታሰበለትን ዓላማ ሳያሳካ መጠናቀቁን በስፍራው የሚገኘው የኢሳት ወኪል ያጠናቀረው መረጃ ያመለክታል። መንግስት  ሰሞኑን ትምህርት ቤቶችን ለአንድ ሳምንት በመዝጋት ለግልና ለመንግስት መምህራን ሲሰጠው የቆየው ስልጠና በሚጠናቀቅበት ጊዜ መምህራን  በተሰጡት በሁሉም ርዕሶች ላይ ስምምነት ላይ …

ጥር ፲፩(አስራ አንድ ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጎንደር ዙሪያ ወረዳ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) አስተባባሪ  የሆነው ወጣት ዘመነ ምረተአብ ትናንት ጥር 10 ቀን  11:00  አካባቢ  በማክሰኝት ከከተራ በዓል ላይ ባልታወቁ ሰዎች ተወስዷል። አፋኞቹ ዘመነ ምረተአብን ወዴት እንደወሰዱትና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ እስካሁን አልታወቀም። ቀደም ሲል የታሰሩት  የመኢአድ የቀድሞ  ዋና ጸሃፊ አቶ ተስፋየ ታሪኩ፣ የድርጅቱ …

ጥር ፲፩(አስራ አንድ ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካራቱሪ በበኩሉ መንግስት አስፈላጊውን ነገር አላመቻቸልኝም ባይ ነው። የህንዱ ግዙፍ ኩባንያ <<ካሩቱሪ ግሎባል ሊሚትድ>> በኢትዮጵያ ሲያደርግ በቆየው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ መንግሥት እምነት እንዳጣበት መግለጹን ሪፖርተር ዘግቧል። አቶ አበራ ሙላት ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ፣ ኩባንያው ይጠበቅበት የነበረውን ሥራ ማከናወን ሳይችል ቀርቷል፡፡ በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ኢንቨስትመንትና መሬት አስተዳደር …

ጥር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፖሊሶቹ በበኩላቸው – <<እኛን ህዝብ ጋር አታጣሉን>> ሲሉ ለአዛዦቻቸው ትእዛዝ ምላሽ ሰጥተዋል። የክልሎ ፖሊሶች  ከመቼውም በላይ ለእርምጃ እረንዲዘጋጁ  የተነገራቸው፤የማረሚያ ቤቶችንና የትራፊክ ፖሊሶችን ጨምሮ ላለፉት ስድስት ቀናት በአማራ ክልል ለሚገኙ ፖሊሶች በሚሉ ሲሰጥ በነበረው ስልጠና  ላይ ነው። እስከ ትናንት ሐሙስ  ድረስ በቆየው በዚሁ ስልጠና ላይ ከምርጫው  እና ከጥምቀት በዓል …

ጥር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዝዋይ ወህኒ ቤት የሚገኘውን ወንድሙን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ለመጠየቅ ትናንት ማለዳ ወህኒ ቤቱ በራፍ ላይ የደረሰው ታሪኩ ደሳለኝ በወህኒ ቤቱ ሀላፊና ስምንት በሚደርሱ ወታደሮች ድብደባ እንደደረሰበት በፌስ ቡክ ገጹ ታሪኩ አስታውቋል፡፡ለተመስገን ይዞ የመጣውን ምግብ ወታደሮቹ መሬት ላይ ከመድፋታቸውም በላይ በኪሱ የያዘውን ገንዘብ ወስደውበታል፡፡ታሪኩ ከደረሰበት ድብደባ በላይ ወንድሙን ሳይጠይቅና …

ጥር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ፣የደሴ፣ የሀዋሳ፣የአርባምንጪ፣ የሀረር፣ የሚዛን ተፈሪ፣የሰበታ፣ የባህርዳር፣ የወልቂጤና የሌሎችም ከተሞች ነዋሪዎች  ለኢሳት እንደገለጹት፣በካድሬዎች አማካይነት ህዝቡ የምርጫ ካርድ በግዳጅ እንዲወስድ እና ድምጹን ለኢህአዴግ እንዲሰጥ እየተደረገበት ያለው ግፊት ከመቼውም ጊዜ በላይ እየከፋ መጥቷል። ከካድሬዎቹ ማስፈራሪያዎች መካከል፦<<የምርጫ ካርድ ካልወሰዳችሁ የቀበሌ መታወቂያና ሌሎችንም አስተዳደራዊ አገልግሎቶች አታገኙም፣ በምርጫው ኢህአዴግን ካልመረጣችሁ ሁዋላ ላይ ተጣርቶ …

ጥር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ኦሞ ዞን አመር ወረዳ- ላላ ቀበሌ ነዋሪ በሆኑ አርብቶ አደሮችና- በፖሊስ መካከል ግጭት ተቀስቅሶ የሰው ነፍስ መጥፋቱን ነገረ ኢትዮጰያ ዘገበ፡፡ ጋዜጣው ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ትናንት ጥር 7/2007 ዓ.ም  <<አርብቶ አደሮች ማጎ ፓርክ ገብተው አውሬ ገድለዋል>> በማለት  ፖሊስ- አርብቶ አደሮቹ ገዳዩን አሳልፈው እንዲሰጡት በጠየቀበት ወቅት ነው ግጭቱ የተነሳው። …

ጥር ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ንቅናቄው  በግንቦት 7 እና በ አርበኞች ግንባር መካከል የተደረገውን ውህደት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ << እኛ መዋሃድ መወሰናችንን  ስንገልጽ፤ በተናጠል ከሚደረጉት – በጋራ የሚደረጉ የትግል ጥረቶች ውጤታማ ይሆናሉ በሚል ብቻ ሳይሆን፣፡”የተቃዋሚ ድርጅቶች፣ በምንም ዓይነት ሁኔታ በሀገርና በሕዝብ ደረጃ ትርጉም ያለው ሥራ በጋራ መስራት አይቻሉም’ የሚለውን፣ አስከፊ ተመክሮና አመለካካት ለመስበርም …

ጥር ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ ጥር 7/2007 ዓ.ም የዓመቱን የሥላሴ በዓል ለማክበር አራት ኪሎ የሚገኘው ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን የተገኙ ወጣቶች ሰማያዊ ቲሸርት በመልበሳቸው በፖሊስ መባረራቸውን ነገረ- ኢትዮጰያ ዘግቧል፡፡ ፖሊስ፤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅስ የተጻፈበት  ሰማያዊ ቲሸርት የለበሱትን ወጣቶች ቲሸርቱን እንዲያወልቁ ሲጠይቅ ወጣቶቹ አናወልቅም በማለታቸው ከበዓሉ እንዳባረራቸው የዐይን እማኞች ገልጸዋል፡፡  ከተባረሩት ወጣቶች መካከል …

ጥር ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ልኳንዳ  ተብሎ በሚጠራው አካባቢ  የሚገኘውንና ከጥንት ጀምሮ  የአባት ጦረኞችና የአርበኞች መኖሪያ የሆነውን የወታደር ካምፕ  ቦታው ተከልሎላቸው የሰሩት  ራሳቸው   አርበኞቹ  መሆናቸው ተመልክቷል። ፈጽሞ ባላሰቡበትና ባልተዘጋጁበት ሁኔታ መኖሪያ ካምፓቸው ያለ ምንም ተለዋጪ ማረፊያ  መሳሪያ በታጠቁ ወታደሮች እንዲፈርስ መደረጉ እንዳስደነገጣቸው የሚናገሩት ነዋሪዎቹ፤ ውሳኔውን በመቃወም እስከ ፍትህ ሚኒስቴር ድረስ አቤት ቢሉም ሰሚ …

ጥር ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከትግራይ ሕዝብ ዲሚክራሲያዊ ድርጅት ‹‹ደሚህት››  ጋር ግንኙነት  ተብሎ የሽብርተኝነት ክስ የተመሰረተበት የአንድነት የመቀሌ ዞን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ፤ ወጣት ሺሻይ አዛናው በትናንትናው ፍርድ ቤት ቀርቦ ተጨማሪ ቀጠሮ ተጠየቀበት። ወጣት ሲሳይ  ቀደም ሲል በተጠየቀበት የሃያ ስምንት ቀናት ቀነ-ቀጠሮ መሰረት ትናንት በአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት   ቢቀርብም፣ ፖሊስ ማስረጃዬን ሰብስቤ አልጨረስኩም …

ጥር ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፎርቹን ሳምንታዊ ጋዜጣ እንደዘገበው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ -የአእምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤትን በጀነራል ዳይሬክተርነት እረየመሩ ያሉትን አቶ ብርሀኑ ያዴሎን   ካለፈው ታህሳስ 27 ቀን ጀምሮ ከስልጣን አንስተዋቸዋል። ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተጻፈ ደብዳቤ  ከዚያው እለት ጀምሮ በአስቸኳይ አቶ ብርሀኑ ያዴሎ ከስልጣናቸው መነሳታቸውንና በምትካቸው በቢሮው የፓተንት ዳይሬክተር የሆኑት  አቶ ግርማ በጅጋ መተካታቸውን …

ጥር ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሶስት ዓመት ህጻንን ጨምሮ ከሶስት ህጻናት ልጆች ጋር ለእህቷ ስርግ ወደ ኢትዮጰያ አቅንታ የነበረችውና ላለፉት 20 ቀናት በአዲስ አበባ የቆየችው ወይዘሮ አበባ፤ ከነ ልጆቿ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ታስራ እንድታድር ከተደረገች በሁዋላ ነው ከሀገር የተባረረችው። በእህቷ ሰርግ ላይ በርካታ ደህንነቶች ሲከታተሏት እንደነበረ የገለጸችው ወይዘሮ አበባ፤ በማግስቱ በቤተሰቦቿ ቤት ሳለች  …

ጥር ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግብጽ የመስኖ ሚኒስትር -በኢትዮጰያ እየተሰራ ያለው ግድብ የሚይዘው የውሀ መጠን በግብጽ  የውሀ ድርሻ ላይ ጉዳት ስለሚያስከትል  እንደሚቃወመው አስታወቀ። አህራም  ኦንላይን “ሜና”የተሰኘውን የ አገሪቱን የዜና አገልግሎት ጠቅሶ  እንደዘገበው በመስኖ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ  የአባይ ግድብ ቃል አቀባይ የሆኑትን ሚስተር አላን ያሲን  በአሁኑ ወቅት ኢየተሰራ ያለውና 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ …

ጥር ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፍኖተ ነጻነት የፓርቲውን የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ አቶ ተክሌ በቀለን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ  ታህሳስ 25 ቀን 2007 ኣመተ ምህረት ባደረገው ስብሰባ  መጪውን ምርጫና ከምርጫው ጋር ተያይዘው ስለሚመጡ ጉዳዮች፤ እንዲሁም ከምርጫው በሁዋላ ፓርቲዎች ሊኖራቸው ስለሚገባው ትብብርና ውህደት የሚያመቻች ኮሚቴ ተቋቁሟል። በስብሰባው፣ ፓርቲዎች በትብብርና በውህደት …

ጥር ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ትናንት እሁድ ጥር 3-2007 ማለዳ ላይ ነበር በ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ሰመናዊ ሆቴል የሆነው ታሪካዊው ጣይቱ ሆቴል በእሳት የወደመው። የዓይን ምስክሮች በወቅቱ እንደተናገሩት፤የእሳት አደጋ ብርጌድ መስሪያ ቤት በሆቴሉ አቅራቢያ ሆኖ ሳለ እሳቱ ከተነሳ በትንሹ ለአንድ ሰኣት ያህል አንድም የ እሳት አደጋ መኪና አለመታዬቱ፣ሰግይተውም ከመጡት ሶስት መኪኖች መካከል አንድኛው ወሃ …

ጥር ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትራፊክና የማረሚያ ቤት ፖሊሶችን ጨምሮ የባህር ዳር ከተማ  ፖሊሶች በሙሉ ከእሁድ እለት ጀምሮ  ስልጠና  ላይ ናቸው። አባይ ማዶ በሚገኘው የምክር ቤት አዳራሽ እሁድ እለት በተጀመረውና እስከ ፊታችን አርብ በሚቆየው ስብሰባ  በጠቅላላ ፖሊሶች በመግባታቸው፤ በከተማዋ ም ሆነ በማረሚያ ቤቶች የሚታይ አንድም ፖሊስ የለም።

ጥር ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ታህሣሥ 28/2007 ዓ.ም ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ህገ-ወጥ ተግባራት›› እየፈጸመ እንደሆነ በመግለጽ ይቅርታ እንዲጠይቅ ለጻፈው ደብዳቤ፣ ሰማያዊ ፓርቲ በፃፈው መልስ ምርጫ ቦርድ ያቀረባቸው ውንጀላቸው ህገ-ወጥ በመሆናቸው ቦርዱ ከውንጀላዎች  እንዲቆጠብ ጠይቋል፡ << ሰማያዊ ፓርቲ ህጋዊ እውቅና ሳያገኝ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፣ ቦርዱ ያዘጋጃቸውን ስብሰባዎች ረግጦ ወጥቷል፣ ከቦርዱ እውቅና ውጭ …

ጥር ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቦርዱ  -አንድነት በአራት ቀናት ዉስጥ አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ አመራሮችን በምስጢር አሰጣጥ መምረጥ እንዳለበት ሲያሳስብና ሲያስጠነቅቅ መቆየቱ ይታወሳል። ሆኖም፤  ይህን የቦርዱን ማስጥንቀቂያ ተከትሎ  አንድነት ከትናንት አርብ  ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤና  የአመራር ምርጫ  ታዛቢ እንዲልክ በደብዳቤ የተጠየቀው ምርጫ ቦርድ፤  “አየለ የሚባል ሰው ሌላ የአንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ይደረጋል የሚል ደብዳቤ ስላሰገባ፣ …

ጥር ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መኢአድ መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን፤ ሲል አንድነት ፦” ኢህአዴግን በምንም መልኩ አንፋታውም እያለ ነው። ባሳለፍነው ሳምንት መግቢያ የምርጫ ቦርድ  ምክትል ሰብሳቢ  <<አንድነትና-መኢአድ በውስጠ ድንባቸው መሰረት ያልፈቷቸው ችግሮች አሉ፤ችግሮቻቸውን ካልፈቱ በምርጫው ላይሳተፉ ይችላሉ>> ማለታቸው ነው  የውዝግቡ መነሻ። በወቅቱ በውስጠ-ደንቡ መሰረት ምንም ያልፈታው ችግር እንደሌለ የገለጸው አንድነት ፓርቲ፤ ምርጫ ቦርድ  …

ጥር ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቲሸርቶቹ ላይ የሚያሳትሟቸውን ሀይማኖታዊ  ጥቅሶችም  በራሳቸው መምረጥ እንደማይችሉ ተነገሩ። ድርጊቱ  የግል የማመን መብታችንን የሚጋፋ ከመገሆኑም በላይ ሀይማኖታችንንም መድፈር ነው ያሉ ወጣቶች ቁጣቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ። ፖሊሶች ከትናት ታህሳስ 1 ቀን ጀምሮ በ አዲስ አበባ የተለያዩ ሰፈሮች በመንቀሳቀስ ወጣቶች  ለመጪው የከተራ እና የጥምቀት በዓል ሰማያዊ-ቲሸርት መልበስ እንደማይችሉ፣ እንዲሁም በቲሸርቶቻቸው ላይ …

ጥር ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ስኞ  እለት ታህሳስ 27 ቀን 2007 ዓመተ ምህረት ታንኮችን የጫኑ የመከላከያ ሰራዊት ተሽከርካሪዎች  ባህር ዳር ከተማ መግባታቸውን የዓይን ምስክሮች ተናግረዋል። የከተማው ነዋሪዎች ለኢሳት እንዳሉት፤ ከየት አቅጣጫ እንደመጡ ያልታወቁ የጦር ተሸከርካሪዎች  ሰኞ ምሽቱን ባህርዳር ወደሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ድርጅት(መኮድ) ካምፕ ገብተው ካደሩ በሁዋላ  በማግስቱ ጧት ወደ ጎንደር አቅጣጫ ተጓጉዘዋል። ተሸከርካሪዎቹ …

ታኀሳስ ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት በትናንት በዘገባው እንዳስታወቀው ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን እና ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም  ወደ ኤርትራ ያቀኑት  በኤርትራ ድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የ ኢት ጰያ ተቃዋሚዎች እያደረጉት ያለውን እንቅስቃሴ በዓይን አይቶ ለመዘገብ፤እንዲሁም  ከተሳካላቸው በወደፊቱ የኢትዮጰያና የኤርትራ ግንኙነት ዙሪያ  የኤርትራ ባለስልጣናትን ቃለ ምልልስ ለማድረግ ነው። ይህን ተከትሎ  እጅግ በርካታ ኢትዮጰያውያን ለጋዜጠኞቹ ያላቸውን አክብሮትና …

ታኀሳስ ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሀገራዊው ምርጫ ጥቂት ወራት በቀሩበት በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ መምህራንና የመንግስት ሰራተኞች ማሰተማራቸውንና ስራቸውን በማቆም ስልጠና እንዲገቡ መታዘዛቸውን ለኢሳት ደረሱት መረጃዎች ያመለክታሉ። በዚህም መሰረት በባህር ዳር የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ መምህራን ከፊታችን ማክሰኞ ጀምሮ ማስተማራቸውን በማቁዋረጥ ወደ ስልጠና እንዲገቡ ታዘዋል። እንዲሁም በጋሙጎፋ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች …

ታኀሳስ ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶበት የሶስት ዓመት እስር የተበየነበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ደህንነቱ አደጋ ላይ መውደቁን  ቤተሰቦቹ ገለፁ፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን፣ በዝዋይ ወህኒ ቤት፤ ኮማንደር ቢኒያም ተብሎ በሚጠራው የወህኒ ቤቱ አስተዳዳሪ ጠዋትና ማታ ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰበት ከመሆኑም በላይ በቀን ለአምስት ጊዜ ያህል ሌሊትን ጨምሮ በሰበብ አስባቡ ከክፍሉ እየተጠራ …

ታኀሳስ ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሳምንት ታጣቂዎች በከባድ መሳሪያዎች በመታጀብ በጎንደር አርማጭሆ ውስጥ <<ሶረቃ>> የሚባለውን አካባቢ ወደ ትግራይ ለማካለል በወሰዱት እርምጃ የተነሳው ግጭት እስካሁን ሊበርድ እንዳልቻለ  በስፍራው የሚገኘው የኢሳት ወኪል ያጠናቀረው ሪፖርት ያመለክታል። ወኪላችን እንዳለው ታጣቂዎቹ፤ አርሶ አደሮችን በኃይልና በማን አለብኝነት አስነስተው ቦታውን ለማካለል ያደረጉትን ጥረት የአካባቢው ህዝብ  ከዳር እስከዳር በመንቀሳቀስና ውጊያ …

ታኀሳስ ፳፱(ሃያ ዘጠኖ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግንቦት 7 <<ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌን እንሁን!!!>> በሚል ርእስ ዛሬ ታህሳስ 29 ቀን ባስነበበው ርእሰ-አንቀጽ፤በህወሓት ሙሉ ቁጥጥር ስር የሚገኘው የፌደራል ፖሊስ እሁድ እለት በቴሌቪዥን ፕሮግራሙ በግፍ እስር ላይ የሚገኘውን የግንቦት 7 ዋና ፀሐፊን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለ 10 ደቂቃ አቅርቦት እንደነበር በማውሳት፤ይህ የ10 ደቂቃዎች ምስል ለቁጥር በሚያታክት ሁኔታ …

ታኀሳስ ፳፱(ሃያ ዘጠኖ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የውጥረቱ  መካረር ምክንያት የምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር አዲሱ ገብረ እግዚአብሔር  ከቦርዱ ውሳኔ ቀድመው ወደ ድርጅት ሚዲያ በመሄድ ” አንድነትና መኢአድ የውስጥ ችግራቸውን ካልፈቱ በምርጫ ላይሳተፉ ይችላሉ” የሚል መግለጫ መስጠታቸው ነው። ዶክተር አዲሱ፤ ሁለቱ ፓርቲዎች  በህገ- ደንባቸው መሰረት ውስጣዊ ችግራቸውን እንዲፈቱ  በቦርዱ ቢነገራቸውም ችግራቸውን አለመፍታታቸውን በመጥቀስ፤  አሁን …