የካቲት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወኪላችን እንደዘገበው በሰቆታ አካባቢ የተከሰተውን ከፍተኛ ድርቅ ተከትሎ አርሶደአሮቹ  ወደ ምእራብ ጎጃምና ሌሎች የአማራ ክልል አካባቢዎች በመሰደድ ላይ ናቸው። ተፈናቃዮቹ ከክልሉ ባለስልጣናትም ይሁን ከፌደራል መንግስቱ ምንም አይነት እርዳታ አለማግኘታቸውን ገልጸዋል። ብዙዎቹ ተፋናቃዮች ወጣት ወንዶችና ሴቶች ሲሆኑ፣ በሰፈሩባቸው አካባቢዎች ስራ ሰርተው ራሳቸውን እንዲያስተዳድሩ እየጠየቁ ነው። ተፈናቃዮቹ በዝናብ እጥረት ምክንያት …

የካቲት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን እንዳዲስ ተጠናክሮ በቀጠለው ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን የማሰር ዘመቻውን በመቃወም ድምጻችን ይሰማ የጠራው ስልክን ለ12 ሰአታት የማጥፋት ዘመቻ በተሳካ ሁኔታ መካሄዱን ዘጋቢያችን ገልጿል፡፡ በርካታ ሙስሊሞች ስልኮቻቸውን አጥፍተው የዋሉ ሲሆን፣ በማህበራዊ የመገናኛ ብዙሃን የሚያደርጉትን እንቅስቃሴም አቁመው ውለዋል። በርካታ ክርስቲያኖችም ጥሪውን ደግፈው ስልካቸውን ዘግተው ውለዋል። እርምጃ የመንግስት ዋነኛ የገቢ ምንጭ በሆነው …

የካቲት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በክልሉ ኢንዱስትሪና  ከተማ ልማት ቢሮ እና የተለያዩ ቢሮዎች  በየእለቱ ጉዳያቸውን ለማስፈጸም የሚመላለሱ ባለጉዳዮች በተለያየ ሰበብ ፈጻሚ በማጣት መቸገራቸውን ድርጅቱ ባዘጋጀው የአስተያየት መስጫ መዝገብ ላይ ማስፈራቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ  ያሳያል። ከተለያዩ አካባቢዎች ጉዳይ ለማስፈጸም እንደመጡ የገለጹት ቅሬታ አቅራቢዎች  በተለይ በስብሰባ ሰበብ ለረዢም ጊዜ መጉላላታቸውን ባሰፈሩት የሃሳብ መስጫ ደብተር ላይ ለማንበብ ይቻላል። አስተያየት ሰጪዎች …

የካቲት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ጋዜጠኞች አብዛኞቹ የኢህአዴግ አባላት መሆናቸውን ኢሳት በደረሰው የአባላት ስም ዝርዝርና የስራ ድርሻ ሰነድ ለማረጋገጥ ችሎአል። በቀድሞው ኢቲቪ በአዲሱ አጠራሩ ኢቢሲ እና በኢትዮጵያ ሬዲዮ  ስር የሚሰሩ ዳይሬክተሮች፣ የዜና አዘጋጆች፣ የወቅታዊ ዘገባ አቀናባሪዎች፣ የስፖርት ጋዜጠኞች ፣ የካሜራ ባለሙያዎች፣ ቴክኒሻኖችና የተለያዩ የድጋፍ ሰራተኞች የህወሃት፣ …

የካቲት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በትግራይ ክልል በብዙ መቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር በማውጣት ከአንድ ወር በላይ ሲያከብር የቆየውን የ40ኛ ኣመት የምስረታ በዓሉን የፊታችን እሁድ በአዲስአበባ ሚሌኒየም አዳራሽ በሚያካሂደው ድግስ ለማጠቃለል መዘጋጀቱ ታውቋል፡፡ በዚህ ዝግጅት ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ አምባሳደሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የሚገኙ ሲሆን የዕለቱን የፌሽታ  በዓል …

የካቲት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጃፓን መንግስት የሚደገፈው የግልግል ዳኝነት ይፋ ባደረገው ጥናታዊ ጽሁፍ በአማራ ክልል የማረሚያ ቤቶች በህግ ታራሚዎች አያያዝ እና አስተዳዳር ከፍተኛ ችግሮች አሉባቸው ብሎአል። 31 እስር ቤቶች በእስረኞች  ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያስከትሉም ተገልጿል። ለሰው ልጆች አደገኛ ተብለው ከተለዩት እስር ቤቶች መካከል ደብረ ታቦር፣ ጋይንት፣ አዲስ ዘመን፣ ሃይቅ፣ ደብረ-ብርሃን፣ መሃል …

የካቲት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሁለቱ ፓርቲዎች የድጋፍ ኮሚቴ አስተባባሪዎች በጋራ በመስራት ሰማያዊ ፓርቲና ሌሎች በሃገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን በጋራ ድጋፍ ለመስጠት ውሳኔ ማሳለፋቸውን ያስታወቁት፣ አንድነት ፓርቲ መንግስት በሚቆጣጠረው ምርጫ ቦርድ አማካኝነት እንዲፈርስ ከተደረገና አባሎቹም ሰማያዊ ፓርቲን ከተቀላቀሉ በሁዋላ ነው። በሌላ ዜና ደግሞ በተለያዩ ክልሎች ቀድሞ የአንድነት አሁን የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሆኑ …

የካቲት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በህገወጥ መንገድ ወደ ደቡብ ሱዳን ሊሄዱ ሲሉ ተያዙ የተባሉት 101 ኢትዮጵያውያን ኬንያ ፍርድ ቤት ቀርበው 50 ሺ የኬንያ ሸልንግ መቀጣታቸውን፣ ቅጣታቸውን ካልከፈሉ ደግሞ በአንድ አመት እስር ተቀጠው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተወስኖባቸዋል። ኢትዮጵያውያኑ በምግብ እጥረት የተነሳ በከፍተኛ ሁኔታ ተጎሳቁለው ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተዘግቧል። መንግስት ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ማግኘቱን …

የካቲት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህወሀትን 40ኛ ዓመት አክብረው ሲመለሱ  እግረ መንገዳቸውን  በ አማራ ክልል የተለያዩ  አካባቢዎችን እየጎበኙ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ  ፤የካቲተ 16 ቀን በወልቃይት ሊያደርጉት የነበረውን ጉብኝት የህዝቡን ተቃውሞ በመፍራት መሰረዛቸው ነዋሪውን ክፉኛ አስቆጥቷል። የወልቃይት ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የካቲት 16 ቀን ወልቃይትን እንዲጎበኙ በአካባቢው ሹመኞች መነገሩን ተከትሎ  …

የካቲት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የሚታየው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ፋብሪካዎች ስራቸውን በተገቢው መንገድ እንዳያከናውኑ እንቅፋት ፈጥሮባቸዋል። ከዚህ ቀደም ከደንበኞቻቸው ጋር የተለያዩ የስራ ውሎችን ተዋውለው በጊዜው ማድረስ ያልቻሉ ፋብሪካዎች፣ ለደንበኞቻቸው ” በአገራችን በሚታየው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት በሰአቱ ማድረስ አልቻልንም” በማለት የይቅርታ ደብዳቤዎችን በመጻፍ ላይ ናቸው። በማኑካንቸሪንግና በኮንስትራክሽን ዘርፍ እንዲሁም በአስመጪነት …

የካቲት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲዎቹ ምርጫ ቦርድ የአባል ፓርቲዎችን ዕጩዎች ያለ አግባብ በመሰረዙና እስከዛሬ ድረስ ዕጩዎቻቸውን በዝርዝር ባለማሳወቁ ምክንያት ለየካቲት 22/2007 ዓ.ም በ15 ከተሞች ሊያደርጉ አስበው የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ ማስተላለፋቸውን የትብብሩን ጸሃፊ አቶ አቶ ግርማ በቀለን ጠቅሶ ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። አቶ ግርማ በቀለ ‹‹ምርጫ ቦርድ ዕጩዎችን እመዘግብበታለሁ ባለበት የጊዜ …

የካቲት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ ” የአገራችን ህዳሴና የሲቪል ሰርቪስ ሚና” በሚል ርዕስ ለከፍተኛ አመራሩ ስልጠና ባዘጋጀው ሰነድ ላይ፣ በመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ የሚገኘው የተማረው ክፍል በኢህአዴግ የመጨረሻው የማይታመነው ክፍል ነው ሲል ገልጾታል። “ይህ የተማረው ሃይል” ይላል ሰነዱ ” አመፅየመምራት፤ኢሳትና ቪኦኤን ከመሳሰሉ አፍራሽ ሚዲያዎች ጋር በመተባበር የቀለም አብዮት ለመምራት ፣ …

የካቲት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ አባይ ጸሃየ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በሃይል እንደሚተገበር በድብቅ ሲናገሩ  መደመጣቸው ፣ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ አመጽን የሚጋብዝ ብቻ ሳይሆን ፣ ከዚህ ቀደም የደረሰው ደም መፋሰስ ሳይበቃ ተጨማሪ ደም መፋሰስ እንዲኖር የሚጋብዝና የሰው ህይወት እንዲጠፋ የሚያደርግ ነው ሲል የሰብአዊ መብት ሊጉ ባወጣው መግለቻ ጠቅሷል። የባለስልጣኑ እብሪት …

የካቲት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የገዳሙ ምንጮች ለኢሳት እንደገለጹት ከወልቃይት ተነስቶ በዋልድባ አብረንታት ገዳም አድርጎ ወደ ማይፀብሪ የሚሰራው መንገድ በ2004ዓ/ም በገዳሙ ፣በአካባቢው ሕብረተሰብ እና  በውጭ በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጠንካራ ተቃውሞ የተነሳ ተቋርጦ ቆይቷል። መንግስት ወደ ገዳሙ የሚገባው ለአፈር ምርምር እንጂ መንገድ ለመስራት አይደለም በሚል የመንግስት ካድሬዎችና አንዳንድ መነኮሳትና የቤተክነት ሃላፊዎች …

የካቲት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኬንያ የወንጀል ምርመራ ልዩ ክፍል ሃላፊ ኖሃህ ካቱሞ  100 ኢትዮጵያውያን ኬንያን እንደመሸጋገሪያ በማድረግ በህገወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማቅናት ሲሉ መያዛቸውን ገልጸዋል። ኢትዮጵያውያኑ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም አማርኛ የሚያስተረጉም በመጥፋቱ በማግስቱ መቀጠራቸውን የኬንያ ጋዜጦች ዘግበዋል። አምና በተመሳሳይ መንገድ 95 ኢትዮጵያውያን ተይዘው ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር። አገራቸውን እየለቀቁ ወደ …

የካቲት ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አለማቀፉ የሰብአዊ መብት ድርጅት ሂውማን ራይትስ ወች ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ  በአለም ባንክ ድጋፍ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ፣ የባንኩን ፖሊሲ የሚጻረሩ ሆነው መገኘታቸውን የአለም ባንክ የውስጥ የምርመራ ክፍል ማሳወቁን ገልጿል። ይሁን እንጅ የባንኩ ማኔጅመንት በባንኩ የውስጥ የምርመራ ቡድን የቀረበውን ሪፖርት የሚቃረንና ባንኩን ከተጠያቂነት የሚያድን ሌላ ሪፖርት አቅርቧል። …

የካቲት ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሕዝበ ሙስሊሙ ፍላጎት ውጪ በ2005 ዓ.ም የተመረጡት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) አመራሮች የመንግስትን ፍላጎት ማርካት  ባለመቻላቸውና በአመራሮቹ ላይ እምነት በመጥፋቱ በአስቸኩዋይ ስልጣናቸውን እንዲያስረክቡ በማድረግ በምትካቸው ሌሎች ተመርጠዋል። በአሁኑ ወቅት በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ሼህ ኪያር መሐመድ ኢማንን …

የካቲት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በጌዲዮ ዞን በኮቾሬ ወረዳ ጨለለቅቱ ከተማ ሃሙስ የካቲት 12 ቀን 2007 ኣም ከቀኑ 11 ሰአት ላይ በተነሳው ግጭት አንድ ሰው ሲሞት ከ10 በላይ የሆኑ ደግሞ ቆስለው ዲላ ሆስፒታል በመታከም ላይ ናቸው። በከተማዋ ያሉ በርካታ ሱቆች ተዘርፈዋል፣ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎም ተነስቷል። የፌደራልና የዞኑ ፖሊስ ወደ …

የካቲት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪ ልማት ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ሃይሌ ከስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን አጣሪ ቡድን ጋር ባደረጉት ውይይት ከመንገድ ስራ ፣ ከባቡር መስመር ዝርጋታና፣ ከቤቶች ልማት ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እየተዘረፈ መሆኑን አምነዋል። የፀረ ሙስና ኮሚሽን ባካሄደው ጥናት በባቡር መስመር ግንባታ 2.3 ኪሜ የባቡር …

የካቲት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከ2 ሺ 700 በላይ የተማሪዎች ማደሪያ አልጋዎች ለተመላላሽ ተማሪዎችና ለማይታወቁ ሰዎች እየተከራዩ መሆኑ ታውቓል። በቅርቡ በአክሱም ከተማ በተካሄደው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማዊ ለውጥ ምክርቤት ጉባዔ ላይ ጉዳዩ በይፋ የተነሳ ሲሆን በአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ከ750 በላይ የተማሪዎች ማደሪያ ክፍሎች ውስጥ የሚገኙ ከ2ሺ 700 በላይ አልጋዎች በድብቅ …

የካቲት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ አሰተዳደር እና ፀጥታ ቢሮ መረጃ እንደሚያሳየው በክልሉ በሚካሄደው ትጥቅ የማስፈታት ሂደት በሰሜን ጎንደርና በምእራብ ጎጃም ዞኖች ብቻ 2 ሚሊዮን 13 ሺ 497 ልዩ ልዩ የጦር መሳሪያዎችና ጥይቶች ለክልሉ ሚሊሺያ ጽ/ቤት ገቢ ተደርጓል። የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ጉዳዩች መምሪያ ኃላፊው አቶ ደጀኔ ሽባባው በጽ/ቤቱ የ2ዐዐ7 …

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የወራሪው  የጣሊያን  ሰራዊት  በጦር  አዛዡ  ፊልድ  ማርሻል  ሮዶልፎ  ግራዚያኒ  አማካኝነት 30  ሺህ  ኢትዮጰያውያንን  በግፍ  የጨፈጨፈበት  78ኛ  ዓመት  ዛሬ  በመላው  ኢትዮጰያውያን  ዘንድ  በመተሳብ  ላይ  ነው። በኢትዮጵያና  ከኢትዮጵያ  ውጭ  የሚኖሩ  ዜጎች ፣ የጣሊያን  ወራሪ  ሃይል  በንጹሃን  ኢትዮጵያውያን ላይ  የፈጸመውን  አስከፊ  ጭፍጨፋ የሚያስታውሱ  ጽሁፎችን  በመልቀቅ  እለቱን  ዘክረውታል።

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቤተመንግስት ትንሹ አዳራሽ ውስጥ የተካሄደውን የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ግምገማ የሚቃኘው መረጃ እንደሚያሳየው የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አባይ ወልዱ የህወሃት ክንፍ እንዲፈጠር ከመከላከያ ኢታማጆር ሹም ሳሞራ የኑስ ጋር ማሴራቸው በሌሎች የኢህአዴግ አባላት ሂስ ቀርቦባቸዋል። አቶ አባይ ወልዱ የቀረበባቸውን ሂስ በደፈናው ተቀብያለሁ፣ አርማለሁ በማለት መመለሳቸውን ሰነዱ ያስረዳል። አቶ አባይ …

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ  የአገሪቱ ክፍሎች ከ200 በላይ ዕጩዎቹ በምርጫ ቦርድ ትዕዛዝ የተሰረዙበት መሆኑን የገለጸው ፓርቲው፣ የካቲት 22  ከትብብሩ ፓርቲዎች ጋር በ15 ከተሞች የሚያደርገው የተቃውሞ ሰልፍ  የነጻነት ትግል አካል ነው ብሎአል። የድርጅቱ ሊ/መንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ  እንደገለጹት ሰማያዊ ፓርቲ በመላ አገሪቱ በተለይም በደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በወላይታ፣ …

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በህገወጥ መንገድ በታገደው የአንድነት ለፍትሕና ለዲሞክራሲ  አመራሮች ላይ  ደህንነቶች ዛቻ፣ማስፈራሪያና ማዋከብ እየፈጸሙ ነው። የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበሩት አቶ አስራት አብርሀ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ  ባለፈው እሁድ ማታ መናኛ አለባበስ የለበሱ ሁለት ወጣቶች የተከራዩበት ቤት ድረስ በመሄድ  “እንፈልገሃለን”  እንዳሏቸው በመጥቀስ፤ “በዚህ ሰዓት የምትፈልጉኝ እናንተ ደግሞ …

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው በእንጦጦ ማርያም ሙዚየም የወርቅ መስቀሎች ጠፍተዋል መባሉ በምእመናን ዘንድ  ተቃውሞ አስነስቷል። ለርዕሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን፣ ከተለያዩ ምዕመናን በስለትና በስጦታ የተሰጡና እስከ አራት ኪሎ ግራም ሊመዝኑ ይችላሉ የተባሉ ሁለት የወርቅ መስቀሎችና አንድ የወርቅ ሐብል፣ በቅርስነት ከተቀመጡበት ሙዚየም ውሰጥ መጥፋታቸውን …

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግምገማው የተካሄደው እንደተለመደው ባለስልጧናቱ በየተራ አስቀድመው ችግራቸውን እንዲናገሩ በማድረግና የራሱን ችግር በተናገረው አመራር ላይ ሌሎቹ ያላቸውን ተጨማሪ ትችት እንዲያቀርቡ በማድረግ ነው። በአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ መሪነት በተካሄደው በዚህ ግምገማ  ከ አዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ  የተገመገሙት አፈ-ጉባኤ አባዱላ ገመዳ፣”የሀሰት የስራ አፈጻጽመ ታቀርቢያለሽ” የተባሉት የሴቶችና የወጣቶች ሚኒስትር …

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አባ ዱላ-ገመዳ ከኦሮሚያ ክልል  ፕሬዚዳንት- ከአቶ ሙክታር ከድር ጋር እንደማይግባቡ የተናገሩት፤ የኢህአዴግ ምክር ቤት ከፍተኛ አመራር አባላት በቃኘው ጥልቅ ግምገማ ላይ ነው አፈ-ጉባኤው በግምገማው”የኦሮምያ አባላትን በተለየ ትህትና ታሰተናግዳለህ፣የአፈ ጉባኤነቱን ቦታ በደስታ አልተቀበልከውም፣ በአዲስ አበባ አዲስ ማሰተር ፕላን ጋር ተያይዞ ተል እኮ የማስፈጸም ችግር አለብህ፣ ከማስተር ፕላኑ …

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፍትሕ ራዲዮ እንደዘገበው፤በአዲስ አበባ ብቻ ከ800 -1000 የሚደርሱ ሰዎችን ለማሰር ታቅዷል፡፡ የሙስሊሙን ማህበረሰብ አካላት  በምክንያት ለማሰር በከፍተኛ የኢትዬጲያ መንግስት የደህንነት ሃይሎች የሚመራ ዘመቻ  መከፈቱን ፍትህ ራዲዬ ዘግቧል። ራዲዮው ምንጮቹን በመጥቀስ እንደዘገበው፤ዘመቻው ያነጣጠረው፤ ከመጪው  ሃገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ በህዝበ-ሙስሊሙ መካከል ትልቅ ንቅናቄ ይፈጥሩ ይሆናል የሚል ስጋት ባሳደሩ …

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሦስቱ ጋዜጠኞችና ስድስቱ ጦማሪያን ዛሬ በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ምድብ ችሎት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን፤ ሁሉም በተከሰሱባቸው ክሶች <<ጥፋተኞች አይደለንም>> ብለዋል። የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ያደመጠው ፍርድ ቤትም፤ ለፊታችን መጋቢት 21 ቀጠሮ በመስጠት የእለቱን ችሎት  አጠናቋል፡፡ ተከሳሾቹ እጃቸው ከተያዘበት ከሚያዚያ ወር 2006 ዓመተ ምህረት …

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሐት) ውስጥ ፖለቲካዊ ጠባብነትና ትምክህት የሚያራምዱ ወገኖች መኖራቸውንና ሕገመንግስቱም በተሟላ ሁኔታ እየተተገበረ አለመሆኑን አቶ ስብሃት ነጋ የቀድሞ የህወሃት ሊቀመንበር እማኝነታቸውን ሰጡ፡፡ አቶ ስብሃት ነጋ የካቲት 9 እና 10/2007 ዓ.ም ከወጣው አዲስዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ በህወሃት ውስጥ ፖለቲካዊ ጠባብነትና ትምክህት መኖሩን አምነዋል፡፡ …

የካቲት ፲ (አስር) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-‹‹ነጻነትለፍትሃዊምርጫ›› በሚልመርህ የሚካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ የካቲት 22 ቀን 2007 ዓም በ15 ከተሞች እንደሚካሄድ ትብብሩ አስታውቋል። የሙስሊም ማህበረሰቡ ታህሳስ 10፣ 2007 ዓም  በኑር መስጂድ ፣ የካቲት 6፣ 2007 ዓም ደግሞ በአንዋር መስኪድ ያደረገው ተቃውሞ  እንዲሁም የባህርዳር ከተማ ህዝብ ታህሳስ 10፣ 2007 ዓም ያሳየው ህዝባዊ እምቢተኝነት ትግል በሃይል ሊዳፈን ቢችልም እንደማይጠፋ ትምህርት ሰጥቷል …

የካቲት ፲ (አስር) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ  (ህወሃት) የትጥቅ ትግል የጀመረበት 40ኛ ኣመት በዓል በስኬት ላይ ብቻ የተመሠረተና ከበሮ ድለቃ የበዛበት የህወሃትን ጉድፎች የተደበቁበት ሆኖ እየተከበረ መሆኑ አሳዛኝ ነው ሲሉ የቀድሞ የድርጅቱታጋይገለጹ፡፡ ስማቸውእንዲገለጽያልፈለጉትየድርጅሩ የቀድሞታጋዮች ለኢሳት በላኩት መልእክትህወሃትየደርግአገዛዝበትጥቅትግል ለማሸነፍከሌሎችየትግልሃይሎችጋርበጣምራናበተናጠልሲታገልመቆየቱናአስከፊውንስርኣትመገርሰሱመልካም ነገር መሆኑ ባይካድም፣  ድርጅቱበሺየሚቆጠሩታጋዮቹን ለሞት ዳርጎ መንግስታዊስልጣን ከተቆናጠጠበሃላየታገለለትዓላማበመርሳትጥቂትሹማምንትራሳቸውንናቤተሰቦቻቸውንየሚያበለጽጉበት፣ቡድናዊ ወገንተኝነትበመመስረትብዙሃኑንያገለለስርዓትእንዲፈጠርአስተዋጽኦአድርጎአልብለዋል፡፡ ህወሃትመንግስታዊስልጣንላይበቆየባቸውባለፉት 23 ኣመታትዴሞክራሲ፣የህግየበላይነትእናየሰብዓዊመብት ጥበቃለማክበርናለማስከበርመታገሉንበመርሳትደጋግሞከሚረግመውየደርግስርዓትባልተናነሰአፋኝስርዓት እየገነባመምጣቱየፓርቲውንመክሸፍቁልጭአድርጎያሳያልሲሉ እነዚሁ ታጋዮች …

የካቲት ፲ (አስር) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-በኮምቦልቻ ከተማ በቡራሮ አዳራሽ ጥሪ የተደረገላቸው የተመላሽ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ለመንግስት ደግፋቸውንና ታማኝነታቸውን እንዲገለጹ በተጠየቁበት ወቅት እስካዘሬ የት እንደወደቅን ሳትጠይቁን፣ አሁን ምን ስለተገኘ ነው በማለት ውድቅ አድርገዋል። ያለፈው አልፏል ለወደፊቱ እንደጋገፍ በሚል ካድሬዎች የማግባባት ስራ ቢሰሩም ፣ የተመላሽ ሰራዊት አባላት ሳይቀበሉት ቀርተዋል። አቶ መለስ ጽፈውታል የተባለውን ማንዋል  ለማስተማር በሚዘጋጁበት ወቅት ፣ …

የካቲት ፱ (ዘጠኝ) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-በስልጣን ላይ ያለውን የህወሃት /ኢህአዴግ መንግስት በሃይል ለመጣል የሚንቀሳቀሱት ሶስቱ የአፋር ድርጅቶች ማለትም አርዱፍ፣ ጋድሌና የአፍዴራ ታጋዮች የካቲት 8 ቀን 2007 ዓም የጋራ ግንባር ፈጥረዋል። የአርዱፍ ሊቀመንበር አቶ  ኢብራሂም ሙሳ ለኢሳት እንደገለጹት ሶስቱም የአፋር ድርጅቶች በተናጠል ሆነው መዋጋታቸው ለስርአቱ እድሜ መርዘም አስተዋጽኦ በማድረጉ በቅድሚያ ድርጅቶቹ የጋራ ግንባር ፈጥረው በጋራ ለመዋጋት አስፈላጊ …

የካቲት ፱ (ዘጠኝ) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-ካድሬዎቹ በደቡብክልል በሲዳማ ዞን በቡርሳ ወረዳ  ስለዕጩዎች ምዝገባና ቀጣይ ድርጅታዊ ሥራዎች ላይ ለመወያየት በወረዳው በሚገኘው የሲአንጽ/ቤት ተሰበስበው በነበሩ የሲአን/መድረክ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ፣በወረዳው የመድረክ ዕጩ ተወዳዳሪዎችና ሌሎች አባላት ላይ የወረዳው የፖሊሰ ኃይልን በመጠቀም ድብደባ ፈጽመውባቸው እንዲበተኑ ማድረጋቸውን መድረክ ገልጿል፡፡ የቡርሳ ከተማከንቲባበሆኑትበአቶአለማየሁፉንአቴትዕዛዝበተፈጸመውበዚሁድብደባበጽ/ቤቱተሰብስበውበነበሩት 20የሲአንመድረክአባላትላይአካላዊጉዳትእንደደረሰባቸውአስታውቋል፡፡ በዚሁዞን  *በወንሾወረዳበዱባምርጫክልል* የመድረክየክልልምክርቤትዕጩተወዳዳሪየሆኑት አቶበሾላገቢሶበመድረክዕጩነትመቅረባቸውእንደታወቀለብዙጊዜያትሲያርሱየኖሩትንናበአሁኑወቅትምየቡናና የእንሰትተክሎችበብዛትየሚገኙበትንየእርሻመሬትለደንእንፈልገዋለንብለውበመከለልናምልክትበማድረግከዕጩነታቸው እንዲለቁማስፈራሪያእየተደረገባቸውእንደሆነመድረክ ገልጿል።

የካቲት ፱ (ዘጠኝ) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-በኖርዌ የነበረውን ስነስርአት በተመለከተ ከአቶአበበ ደመቀ ጋር አጭር ቆይታ አድርገናል። በአውስትራሊያሜልበርንከተማ  እሁድ  ፈብራሪ 15፣ 2015 ዓ .ምበደማቅሁኔታተከብሯል። ፕሮግራሙ በህሊና ጸሎት ከተጀመረ በኋላ አቶ አንዳርጋቸውን የሚያስታውሱ በቪዲዮ የተቀነባበሩ ስነ ግጥሞች ፣መዝሙሮች እና  ዘጋቢ ፊልሞች ቀርበዋል። የፕሮግራሙአስተባባሪዎች፦  <<የአቶ አንዳርጋቸውን 60ኛ አመት የልደት በአልየምና ከብረው፤  አቶ አንዳርጋቸው የከፈሉትን ዋጋ በመዘከር ፣እርሳቸው እየተሰዉለት ያለውን አላማ …

የካቲት ፱ (ዘጠኝ) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-የጠ/ሚኒስትሩ አማካሪና የህወሃት ነባር ታጋይ አባይ ጸሃየ አወዛጋቢው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በሃይል ተግባራዊ እንደሚደረግ አዋሳ ውስጥ በተደረገ ስብሰባ ላይ መናገራቸውን የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ገልጿል። አቶ አባይ ጸሃየ የኦሮምያ ልዩ ዞን ሃላፊዎችን በቅድሚያ የወቀሱ ሲሆን፣ ክልሉም እነዚህን ልክ ባለማስገባቱ ሌላው ተጠያቂ መሆኑን ገልጸዋል። የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እንደወጣ በርካታ የኦሮሞ ተወላጆች  …

የካቲት ፱ (ዘጠኝ) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-እጅግ አስደንጋጭ የሆነ የመሬት ሊዝ ዋጋ ንረት እየታየበት የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰሞኑን ባወጣው 13ኛው  የሊዝጨረታ በአዲስ አበባ፤በቦሌእና  በአቃቂቃሊቲ ክፍለ ከተሞች በድምሩ 238 ቦታዎችን በሊዝለማስተላለፍ አቅርቧል። መንግሥት የመሬትችርቻሮውስጥከመግባቱጋርተያይዞየአንድካሬሜትርባዶቦታዋጋከ 150 እስከ 305 ሺብር  መሰቀሉ መንግሥትን በከፍተኛ ደረጃ ካስተቸው ወዲህ እንዲህ በብዛት ቦታዎች ለጨረታ ሲያቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡ በዚህጨረታበቦሌክፍለ ከተማ 116 ቦታዎችለጨረታየቀረቡሲሆንየአንድካሬሜትርመነሻዋጋ …

የካቲት ፱ (ዘጠኝ) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-በዓለም ባንክ አዲስ መረጃ መሰረት ፤ ከአስሩ የዓለማችን የመጨረሻ ሀገሮች መካከል አንዷ ኢትዮጵያነች ። በጥናቱ በድህነት ከ 1 እስከ 10 የተመዘገቡት እንደ ቅደምተከተላቸው ማላዊ ፣ ቡሩንዲ ፣ቻድ ፣ ኒጀር ፣ ላይቤሪያ ፣ ማዳካስካር ፣ ኮንጎ ፣ጋምቢያ ፣ኢትዮጵያና ጊኒናቸው። እንደተለመደው ሁሉ  በዘንድሮውም ጥናት በድህነት ተርታ የተመደቡት አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገሮች ሲሆኑ ፤ ከነኚህ …

የካቲት ፮(ስድስት) ቀን፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ባለፈው የክረምት ወር ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሰጠውን የፖለቲካ ስልጠና ለከምባ ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች ሲሰጥ ቢቆይም፣ ሰራተኞች ለጠየቅናቸው ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ አልተሰጠንም በሚል ፣ በስብሰባው ማጠቃለያ ላይ አስተያየት አንስጠም በማለታቸው ስብሰባው መተናቀቁን በስብሰባው የተገኙ ተስብሳቢዎች ተናግረዋል። “በደቡብና በጋምቤላ ክልሎች መካከል ያለው የእርሻ ቦታ  ለኢህአዴግ አባላት ኢንቨስተሮች ለምን ተሰጠ? ኢትዮጵያ እየተበደረቸው ያለው …

የካቲት ፮(ስድስት) ቀን፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊመንበር አቶ ታምሩ አበበ ለኢሳት እንደገለጹት አንዳንድ ነዋሪዎች በውጭ አገራት ነዋሪዎች ላይ በወሰዱት እርምጃ 6 ኢትዮጵያውያን መገደላቸውንና ከ300 ያላነሱት ደግሞ ንብረታቸውን መዘረፋቸውን ተናግረዋል። ድርጊቱን ለማውገዝ የደቡብ አፍሪካ ሰራተኞች ማህበርና የተለያዩ የኮሚኒቲ አባላት ድርጊቱን አውግዘዋል።

የካቲት ፮(ስድስት) ቀን፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በምእራብ ሸዋ ዞን በአቡነ ግንደበረት ወረዳ በመንዲዳ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ባልቻ፣ በፌደራል ፖሊሶች በግፍ የተገደለባቸውን ደሜ ባልቻ የተባለውን ልጃቸውን የሙት አመት በመዘከራቸው፣ ለምን ይህን አደረጉ በሚል እርሳቸውና ሌሎች 10 ወጣቶች ባለፈው ሰኞ ተይዘው መታሰራቸው ታውቋል። አቶ ባልቻ የልጃቸው ገዳዮች እንዲያዙ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ቢቆዩም አልተሳካላቸውም። የልጃቸውን ፎቶ …

የካቲት ፮(ስድስት) ቀን፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከቅርብ ጊዜ ወዲህ  እረገብብሎ የነበረው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ከጁማ ጸሎት በሁዋላ በአንዋር መስጊድ ተካሂዷል። ኢትዮጵያውያኑ በቅርቡ መንግስት በመጅሊስ ውስጥ ያካሄደውን ሹም ሽር ተከትሎ ነጻ መጅሊስ እንዲኖር ጠይቀዋል። ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የተለያዩ መፈክሮችን የያዙ ፊኛዎችን አሳይተዋል። የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት ህዝበ ሙስሊሙ ያነሳውን የነጻ መጅሊስ ጥያቄ መርታችሁዋል በሚል ታስረው እንደሚገኙ ይታወቃል።

የካቲት ፮(ስድስት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-ጥር 7 በባህርዳር በሚካሄደው የመከላከያ ቀን ላይ ነዋሪው በስፋት እንዲወጣ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ቤት ለቤት እየዞሩ የነዋሪዎችን ስም እየመዘገቡና በበአሉ ላይ ካልተገኙ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው እያስፈራሩ መሆኑን የከልሉ ዘጋቢያችን ገልጻለች። ሰሞኑን በየመንገዱ ላይ የተለያየ የሙዚቃ ትርኢት በማሳየት ህብረተሰቡን ለመቀስቀስ ቢሞክሩም የህዝቡን ትኩረት ለማግኘት ያልቻሉት የመከላከያ አመራሮች፣  መንገዱን በየ50 ሜትር በታጠቁ ወታደሮችና የፌደራል ፖሊሶች …

የካቲት ፮(ስድስት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-ተርኪሽ ፕሬስ እንዳለው፤ የሶስቱ ሀገራት ባለስልጣናት  ስብሰባቸውን ያደረጉት ባለፈው ረቡእ  በአዲስ አበባ ውስጥ ነው። የሀገራቱ ባለስልጣናት  ድንገተኛ ስብሰባ ለጋዜጠኞች ዝግ እንደነበርም  የአናሎዱ የዜና አገልግሎት ወኪል ዘግቧል። በስብሰባው   የግብጹ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር  ሳሜህ ሾርኪ፣ የግብጽ የመስኖ ሚኒስትር  ሆሳም ሞጋሲ፣ የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም፣ የሱዳን የመስኖ ሚኒስትር  ሞታሳ ሙሳ እና  ከሶስቱም …

የካቲት ፭(አምስት) ቀን፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራና  በትግራይ  ድንበር  አካባቢ  የሚኖሩ  ነዋሪዎች  የትግራይ  ክልል  ህገወጥ በሆነ  መልኩ  ባደራጃቸው  ታጣቂ  ሚሊሺያዎች  አማካኝነት ፣ ሰፋፊ  የእርሻ  መሬቶችን  በጉልበት  እየቀማ  ነው  በሚል  ያስነሱትን  ተቃውሞ ለመፍታት  ከሁለቱም  ክልሎች  የተውጣጡ  ባለስልጣኖችና  ከ300  ያላነሱ  የህዝብ  ተወካዮች  ከሳምንታት  በፊት  ተሰብስበው  መግባባት  ባለመድረሳቸው  ለየካቲት  4  በድጋሜ  ቀጠሮ  ከተያዘ  በሁዋላ ፣ ትናንት  ሊካሄድ  የነበረው  ስብሰባ …

የካቲት ፭(አምስት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-ከማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በቁጫ  ወረዳ  የተነሳውን  ህዝባዊ  ተቃውሞ ተከትሎ  ከአመት  በላይ  ለሆነ  ጊዜ  በአርባምንጭ  እስር  ቤት  ታስረው  የሚገኙት  ዜጎች ፣ ፍትህ አጥተው  አሁንም ስቃይ ላይ  መሆናቸውን  የአካባቢው ምንጮች  ገልጸዋል። ባለፉት 3 ቀናት ደግሞ ሌሎች ተጨማሪ 5 ሰዎች ተይዘው መታሰራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት እርምጃ ተቃውሞውን ለማዳፈን ሙከራ ቢያደርጉም፣ መጪውን …

  የካቲት ፭(አምስት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-መድረክ የተሰኘው የአራት ፓርቲዎች ግንባር እና  ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ለፌዴራል ፓርላማጠንካራዕጩዎቻቸውንያስመዘገቡ ሲሆን፣  በተለይ በአዲስ አበባ ኢህአዴግ ያቀረባቸው ዕጩዎችእም ብዛም የማይታወቁ፣ በ1997 ምርጫ የተሸነፉና በሕዝብ ዘንድ ያላቸው ድጋፍ አነስተኛ የሆኑ አመራሮቹን መሆኑ በራሱ አባላትና ካድሬዎች ሳይቀር ጥያቄ እየተነሳበት ይገኛል፡፡ አንድበአዲስአበባየሚገኝወረዳአመራርለዘጋቢያችንእንደገለጹትነጋጠባሕዝቡንአልያዛችሁትም፣ህዝቡጋርአልደረሳችሁምበሚልበሚካሄድተደጋጋሚግምገማመሰላቸታቸውን፣በአንጻሩከደጋፊናአባሉበስተቀርአብዛኛውሕዝብደግሞምንምነገርመስማትየማይፈልግመሆኑአጣብቂኝውስጥከቷቸዋል። ለጉዳዩቅርበትያላቸውምንጮችእንደተናገሩትእነዚህየኢህአዴግዕጩዎችአሸንፈውመውጣትይችላሉወይየሚለውጥያቄያስጨነቀውኢህአዴግ ፣ ሕዝቡንለመያዝሲባልበአዲስአበባበየካቲትእናበመጋቢትወራትለሁለትጊዜያትየኮንዶሚኒየምቤቶችን፣የ40 በ60 እናየ10 በ90 ቤቶችንበተከታታይለመስጠትእናበቀጣይምብዙቤቶችለመስራትቃልበመግባትየሕዝቡንድጋፍለማግኘትአቅዶአል፡፡ ከዚህቀደምየኮንዶሚኒየምቤቶችዕጣከወጣበሃላ ለባለዕድለኞችለማስተላለፍየማጠናቀቂያስራዎችንለመስራትበሚልከሁለትኣመትበላይይፈጅየነበረውጊዜ …

የካቲት ፭(አምስት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ) የጎንደር ሰብሳቢና የመኢአድ መስራች የሆኑት መምህር ጥጋቡ ሃብቴ ለሳምንታት ማስፈራሪያ ሲደርሳቸውና ክትትል ሲደረግባቸው ከቆዩ በሁዋላ የካቲት 4/2007 ዓም ደህነቶች ሌሊት ወደ ቤታቸው በመግባት ፍተሻ ካካሄዱ በሁዋላ ወደ አልታወቀ ቦታ አፍነው ወስደዋቸዋል። የቀድሞው የመኢአድ አዲስ አበባ ህዝብ ግንኑነት ሃለፊ አቶ አወቀ አባተ ለኢሳት እንደገለጸው ፣ መምህር ጥጋቡ …