መጋቢት ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በየመን የሚካሄደውን የእርስ በርስ ጦርነት ተጋፍጠው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ቢሆንም፣ ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚፈልጉትን ከ2 ሺ ያላነሱ ፈቃደኛ ኢትዮጵያውያንንን ለመመለስ እንቅስቃሴ እየታየ አይደለም ሲሉ የመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አስታውቀዋል። ኢትዮጵያውያኑ ኢምባሲው ባቀረበው ጥሪ መሰረት ምዝገባ አካሄዱ ቢሆንም ፣ መቼና እንዴት እንደሚሄዱ የሚያውቁት ነገር …

መጋቢት ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህር ዳር ከተማ በሁሉም ክፍለ ከተማዎችና ሙሉዓለም አዳራሽ የተደረገው ስብሰባ የተፈለገውን ግብ ሳይመታ መጠናቀቁን የስብሰባው ተሳታፊዎች ተናገሩ፡፡ ቅዳሜ መጋቢት 26/2007 ዓ.ም በተደረገው ስብሰባ የብአዴን አባላትን በጥሪ ወረቀት የከተማ ነዋሪዎችን ቤት ለቤት በመዞር በስብሰባው እንዲገኙ በመመዝገብና የተለመደውን ማስፈራሪያ በመጠቀም እስከ ቀኑ 6 ሰዓት በተደረገው ስብሰባ ተሳታፊዎች የተለያዩ …

መጋቢት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰማያዊ ፓርቲ ሊ/መንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ወደ አሜሪካ ሊያደርጉት የነበረው ጉዞ በደህንነት ሰዎች እንዲሰረዝ ከተደረገ በሁዋላ፣ እስካሁን ድረስ ምክንያቱን የሚነግራቸው አካል መጥፋቱን ሊ/መንበሩ ለነገረ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። የኢሜግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ መስሪያ ቤት ‹‹ፓስፖርቱ እኛ ጋር አልደረሰም፡፡ ቆይተው ደውለው ይጠይቁ››  ብለው ስልክ እንደሰጧቸው የገለጹት ኢ/ር ይልቃል፣ ይህም ሆን ተብሎ …

መጋቢት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከፍተኛውን ድርሻ የሸፈኑት የመንግስት ሰራተኞች መሆናቸውም ተገልጿል። በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአባይ ግድብ ህዝባዊ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ፀሀፊና የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ሰሞኑን ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ፣  በአራት አመቱ ውስጥ በክልሉ የተሰበሰበው ገንዘብ ስድስት መቶ ሚሊዮን ብር አካባቢ መሆኑን ገልጸው፤ ከዚህ ውስጥ …

መጋቢት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ከታማኝ ምንጮች እንዳረጋገጠው በቦሌ አየር ማረፊያ  በሚስጢር ስም የተመዘገቡና ባለቤታቸው ተለይቶ ያልተመዘገቡ  ድርጅቶች ካለፉት 10 አመታት ጀምሮ የኮንትራት ጊዜያቸውን ሳያድሱ እና የቤት ኪራይ ክፍያቸውን ለመንግስት ገቢ ሳያደርጉ በመነገድ  ላይ ናቸው። በእነዚህ ድርጅቶች ጀርባ የከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እጅ እንዳለበትም ምንጮች ጠቁመዋል። የኤርፖርቶች ድርጅት ፣ተከራዮችንና ሌሎች የሚመለከታቸውን የህብረተሰብ …

መጋቢት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በስራ አፈፃፀማቸው ብልጫ አመጥተዋል እንዲሁም የመቆያ ጊዜያቸውን ሸፍነዋል ለተባሉ  የአንድ አካባቢ ተወላጅ ከፍተኛ መኮንኖች፣መሰረታዊ መኮንኖችና ለባለ ሌላ ማዕረግተኞች  የማእረግ እድገት ተሰጥቷል። መጋቢት 15 ቀን 2007 ዓ.ም በምድቡ ወታደራዊ መዝናኛ ክበብ በተዘጋጀው የማዕረግ አሰጣጥ ስነ-ስርዓት የምድቡ ታማኝ ሰዎች ብቻ የተገኙ ሲሆን ፣ ስነስርዓቱ ለሁሉም የሚዲያ ሰዎች ዝግ እንዲሆን …

መጋቢት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ መንግስት ሁሉንም ኃይሎች ያሳተፈ ብሔራዊ መግባባት መፍጠር ባለመቻሉ ለአባይ ግድብ ፕሮጀክት ሕዝቡ በቂ ድጋፍ እንዳያደርግ ተጽኖ አድርጎበታል ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። የግድቡ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበት 4ኛ ዓመት በዓል በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግድቡ ባለበት ጉባ ከተማ በመከበር ላይ ሲሆን ባለፉት 4 ዓመታት  ሕዝብን በማንቀሳቀስ ለግድቡ ግንባታ የተሰባሰበው …

መጋቢት ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፉት ሶስት አመታት በደቡብ ክልል በቤንች ማጂ ዞን በጉራ ፈርዳ ወረዳ ይኖሩ በነበሩ በአማራ ተወላጆች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲፈጸም ትእዛዝ ያስተላለፉት ከፍተኛ ባለስልጣናት ፍርድ ቤት ባልቀረበቡበት ሁኔታ፣  በወረዳ እና በቀበሌ ደረጃ ያሉ ሹማምንት ባለስልጣናት ሰኞ መጋቢት 21 ቀን 2007 ዓም ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ተደርጓል። አቃቢ ህግ …

መጋቢት ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፍርድ ቤቱ በሰጠው ውሳኔ ክሱን ያቀረቡት ወገኖች የአንድነት ፓርቲን በመወከል ክስ ሊያቀርቡ አይችሉም ብሎአል። ምርጫ ቦርድ ቀደም ብሎ ህወሃት ኢህአዴግ የሰጠውን የፖለቲካ ውሳኔ ማስፈጸሙን የገለጹት የፓርቲው የቀድሞ አመራር አቶ አስራት ጣሴ፣  የዛሬው የፍርድ ቤት ውሳኔም ህግና ደንብን የጣሰ ነው ብለዋል። የፓርቲው የስራ አስፈጻሚ አባላት አሁንም እንዳሉ የገለጹት …

መጋቢት ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድምጻችን ይሰማ ይጠራው የሳንቲም ማጠራቀም የተቃውሞ ሰልፍ በቀላልና በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ዘጋቢያችን ገልጿል። በአዲስ አበባ የተለያዩ የእስልምና እምነት ተከታዮችን አነጋግሮ እንደዘገበው በርካታ ሙስሊሞች ሳንቲሞችን በማጠራቀም ተቃውሞአቸውን እየገለጹ ነው። አንድ መርካቶ አካባቢ የንግድ ድርጅት ያለው ግለሰብ  ” ንጹህ የሆኑ የሙስሊሙ መሪዎች ፍትህ አጥተው በእስር በሚማቅቁበት ወቅት፣ እኔ …

መጋቢት ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፉት 8 ወራት ጀምሮ በማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ የታሰሩት እስረኞች አብዛኞቹ አርበኞች ግንቦት7 ትን ሊቀላቀሉ ሲሉ ተይዘዋል የሚል ክስ ሲመሰረትባቸው እስካሁን ድረስ ክስ ያልተመሰረተባቸው በርካታ እስረኞች እንደሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል። የሰማያዊ ፓርቲ የአመራር አባላት ከሆኑት ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ ፍቅረማርያም አስማማውና እየሩሳሌም ተስፋው እንዲሁም የቀድሞው የአንድነት አመራር አባል የነበረው …

መጋቢት ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በግድግዳዎች ላይ ተጽፈው የሚገኙ የተለያዩ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ጽሁፎች በአስቸኳይ እንዲጠፉ  የደህንነትና ድርጅት ጉዳይ ጽ/ቤት ለአዲስ አበባ ፖሊስ ትእዛዝ ሰጥቷል። ፖሊሶቹ በግድግዳ ላይ የተጻፉ የነፃነትና የፍትህ ጥያቄዎችን  የሚያቀርቡ የግድግዳ ላይ ጽሁፎችን እግር በእግር ተከታትለው ማጥፋት እንዳለባቸው ተነግሯቸዋል፡፡ ትእዛዙን ተከትሎም የአዲስ አበባ ፖሊሶች በየቀጣናው …

መጋቢት ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመጪውን ምርጫ መቃረብ ተከትሎ በአዲስአበባ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ 32ሺ ያህል ብዛት ያለው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ከሳምንት በፊት ቢወጣም ቅድሚያ ክፍያው የዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች አቅም በላይ ሆኗል። የኮንዶሚኒየም  ቤቶች ዋጋ ካለፈው ዘጠነኛ ዙር ጋር ሲነጻጸር እስከ 20 በመቶ የዋጋ ጭማሪ እንዳሳየ ራሱ አስተዳደሩ …

መጋቢት ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የንቅናቄው መስራችና አደራጅ   ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት የህዝባዊ ወያን ሃርነት ትግራይ መንግስት በአካባቢው ያለውን መሬት ሙሉ በሙሉ ጠቅልሎ ለመውሰድ ባለው ፍላጎት በአኝዋኮችና በኑወር ብሄረሰቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ነው። ኑወሮችን በጦር መሳሪያ ከማስታጠቅ ጀምሮ ከደቡብ ሱዳን የሚፈናቀሉ ኑዌሮች በአኝዋኮች፣ መዠንገሮችና ሌሎች ብሄረሰቦች መካከል እንዲሰፍሩ በማድረግ እስከዛሬ …

መጋቢት ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር -ኦብነግ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ፣ የኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስትር በበሁለት አመት ውስጥ ኦጋዴን  ያለውን የተፈጥሮ ጋዝ ለውጭ ገበያ እናቀርባለን በማለት የሰጡት መግለጫ፣  ያልተጨበጠና የማይሆን ነው ብሎአል። መንግስት በኦጋዴን ውሰጥ ህዝቡን በጅምላ ኢላማ በማድረግ የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸሙን የገለጸው መግለጫው፣ የቻይና ኩባንያ ይህን እያወቀ ለመንግስት ሰራዊትና …

መጋቢት ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በቁጥጥር ስር የዋሉትእና በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ በእስር ላይ የሚገኙት ብርሃኑ ተክለ ያሬድ፣ ፍቅረማሪያም አስማማውና እየሩሳሌም ተስፋው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ፍርድ ችሎት ቀርበው ተጨማሪ የ28 ቀናት ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ችሎት ከመግባታቸው በፊት በፈገግታ በፍርድ ቤት ቅጥር ግቢ የነበሩትን ቤተሰቦቻቸውን፣ ጓደኞቻቸውንና ወዳጆቻቸውን ሰላም ሲሉ መታየታቸውን ጋዜጠኛ …

መጋቢት ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአገራችን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ጋር በተያያዘ በርገን የኢሳት የድጋፍ ኮሚቴ አማካኝነት የተሰራው የሳውል ፍሬዎች በፈረንጆች አቆጣጠር ማርች 28 በበርገን ኖርዌይ ከተማ ተመርቋል። በአይንሸት ገበያው  ተደርሶ በጋዜጠኛ ገሊላ መኮንን አርታኢነትና አዘጋጅነት በተሰራው ፊልም ፣ በበርገን እና አካባቢዋ የሚኖሩ 11 ኢትዮጵያውያን ተሳትፈውበታል። በበርገን በተካሄደው ዝግጅት ለተሳታፊዎች የምሰክር ወረቀትና አበባ …

መጋቢት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በ9 የፖለቲካ ድርጅቶች ትብብር መጋቢት 20 በአዲስ አበባና በ15 የክልል ከተሞች የተጠራው የተቃውሞ ሰልፍ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን የትብብሩና የሰማያዊ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ለኢሳት ተናግረዋል። ኢ/ር ይልቃል በግብርናና ገጠር ልማት ዙሪያ በሚደረገው የምርጫ ክርክርም እንዳይሰታፉ መከልከላቸውን ገልጸዋል። 

መጋቢት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ወደ ማእቀብ እና ትብብር የመንፈግ  ሂደት መሸጋገሩን ድምጻችን ይሰማ ካስታወቀ በሁዋላ፣ አርብ መጋቢት 20 የሳንቲም መሰብሰቡ ሂደት ተጀምሯል። ምን ያክል ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጥሪውን ተቀብለው ተግባራዊ እያደረጉት መሆኑን ለማወቅ አስቸጋሪ ቢሆንም ሙስሊሙ ከዚህ በፊት ይተላለፉ የነበሩ የድምጻችን ይሰማን መመሪያዎች ሲተገብር በመቆየቱ፣ አዲሱን መመሪያም ተግባራዊ …

መጋቢት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኬንያው  ዘ ደይሊ ኔሽን እንደዘገበው ኢትዮጵያውያኑ ወደ አገሪቱ በህገወጥ መንገድ በመግባታቸው እያንዳንዳቸው 2 መቶ ሺ ሽልንግ እንዲከፍሉ የኢሲዮሎ ፍርድ ቤት ወስኖባቸዋል። ሁሉ ም ስደተኞች ባለፈው ሰኞ ሳምቡሩ በተባለው ስፍራ ላይ የተያዙ ሲሆን፣ ተከሳሾች ያለፈቃድ ወደ ኬንያ መግባት እንደማይቻል ባለማወቃቸው ምህረት እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል። ይሁን እንጅ ፍርድ ቤቱ …

መጋቢት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች እንደሚሉት ከማሃል ወደ አዋሽ በሚወስደው መንገድ ላይ ያሉ አካባቢዎች ውሃ ካጡ ረጅም ጊዜ አስቆጥረዋል። ውሃ ጀሪካን በጋሪ ላይ ጭኖ መሄድ ወይም ለውሃ ወረፋ ረጃጅም ሰልፎችን መጠበቅ የእለት ተእለት ክስተት መሆኑን ነዋሪዎች ይገልጻሉ። በተመሳሳይም በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀሌ የሚታየው የውሃ ችግር ሊቀንስ አልቻለም። …

መጋቢት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪነት የተሰባሰቡትና ምርጫ ቦርድ ዕውቅና አልሰጠሁም በሚል ትብብራቸውን እንዲያቆሙ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ የሰጣቸው ዘጠኝ ፓርቲዎች በትብብር የጠሩት ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ የፊታችን እሁድ የአዲስአበባ እና የድሬዳዋ ከተሞችን ጨምሮ በአስራአምስት ዋና ዋና ከተሞች ይካሄዳል፡፡ ሆኖም አዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ከወዲሁ ሰልፉ በመንግስት በኩል ያልተፈቀደ ነው በሚል ለማጨናገፍ እየተንቀሳቀሰ …

መጋቢት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በመቶ ሚሊየን በሚገመት ወጪ በታላቅ ፌሽታ እያከበረ የሚገኘው የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) አመራር በአንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች ትምህርት ቤቶችን እስከማዘጋት የደረሰውን የመጠጥ ውሃ ችግር ሊታደግ ያልቻለ መሆኑን መረጃዎች ጠቆሙ፡፡ ከግብርና ሚኒስቴር የወጣ አዲስ መረጃ እንደሚያሳየው፣ በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተው የመጠጥ ውሃ …

መጋቢት ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድምጻችን ይሰማ ባለፉት 3 ዓመታት የተካሄደው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ወደ ማእቀብ እና ትብብር የመንፈግ  ሂደት መሸጋገሩን ካስታወቀ በሁዋላ፣  ከመጋቢት 18፣2007 ዓም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ላልተወሰነ ጊዜ  ሳንቲምበመሰብሰብናበማጠራቀምራስላይየመቆጠብእቀባይፋ አድርጓል። በቅርቡ በቴሌላይተቃውሞ መደረጉን የገለጸው ድምጻችን ይሰማ፣  በሂደትም ከዚህ ከፍ ያሉ የትብብር መንፈግስልቶችንቀስበቀስወደመላመዱእናወደመተግበሩ፣ቀስበቀስምወደማሳደጉ መግባትተገቢሆኖእንዳገኘው ገልጿል። ድምጻችን ይሰማ ሳንቲም የመሰብሰብ እንቅስቃሴው …

መጋቢት ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የባለሰልጣኑ የኦዲት ሪፖርት እንደሚያሳየው በአማራ ክልል የባህርዳር ከተማ፣በምዕራብ ጎጃም ዞን የባህርዳር ዙሪያና የይልማና ዴንሳ ወረዳዎች የጣና- በለስ-ባህርዳር 400 ኪሎቮልት እና የባህርዳር- ደብረማርቆስ 400 ኪ.ቮ. የኃይልማስተላለፊያ ፕሮጀክቶች፣በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን የምስቃን ወረዳ፣በሀዲያ ዞን የሌሞ ወረዳ የወላይታ ሶዶ- አዲስ አበባ 400 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ ፕሮጀክት በካሳ ግምት ስም …

መጋቢት ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን መጋቢት 16/2007 ዓ.ም ለፓርቲው በላከው ደብዳቤ፣ ከተላኩት የቅስቀሳ መልክቶች መካከል ” የመከላከያ ሰራዊቱ ሌሎችም የአገሪቱ ቁልፍ ተቋማት ከገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ውጪ አልሆነም፣ በተለይም በገዛ ሃገራቸው ከስራ ይባረራሉ ፣ ተቋማቱን እውቀት የሌላቸው ካድሬዎች እንዲመሩት ተደርጓል፣ ገዢው ፓርቲ ፖሊስን፣ ሚዲያውን፣ መከላከያ ሰራዊቱን፣ ደህንነቱን ሰማያዊንና ሌሎች ተቃዋሚዎችን …

መጋቢት ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሊጉ ም/ል ሊቀመንበር በመሆን ለአመታት ያገለገለችው ወ/ት እየሩሳሌም  አበረ  ከኢሳት ጋር ባደረገችው ቃለምልልስ “የአዲስ አበባ ህዝብ እንደሚገነፍል ድስት እፍ እፍ እየተባለ  ቢያዝም፣ አሁንም በርካታ የዲሞክራሲ እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን እያነሳ ነው” ብላለች። የታፈነ የመልካም አስተዳደር እና የዲሞክራሲ ጩኸት አለ የምትለው ወ/ት እየሩሳሌም፣ ገዢው ፓርቲም ህዝቡ በከፍተኛ ብሶት …

መጋቢት ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በጋራ የፈረሙት አዲሱ ስምምነት ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ በሙሉ ነጻነት የምትሰራውን ስራ እንደሚገድብ ከአረብኛ ወደ እንግሊዝኛ የተተረጎመው  ሰነድ አመልክቷል። ሰነዱ ኢትዮጵያ ግድቡን ለመገንባት በምታደርገው ማንኛውም እንቅስቃሴና በየትኛውም የግንባታ ደረጃ ላይ አለማቀፉ አጥኝ ቡድን ለሚሰጠው አስተያየት ተገዢ በመሆን እንድትተገብር ይገልጻል። አጥኝ ኮሚቴው የግድቡ ግንባታ የግብጽንና ሱዳንን …

መጋቢት ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በአዲስ አበባ በተወሰኑ ክፍሎች የሚገኙ የፌደራል ፖሊሶች ተቃዋሚዎችን ይደግፋሉ በሚል መነሻ ጠንካራ ግምገማ እየተካሄደባቸው ነው። የፌደራል ፖሊሶች ፌስ ቡክ እና ሌሎች የመገናኛ ዘዴዎችን እየተጠቀሙ በተለይ በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ይገናኛሉ በሚል የእጅ ስልካቸውን ተነጥቀው ፍተሻ ተደርጎባቸዋል። ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው እስካሁን በተካሄደው ፍተሻ ቁጥራቸው …

መጋቢት ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ምንጮች እንደሚሉት 8 የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ካለፈው ሳምንት ረቡዕ ጀምሮ በእስር ላይ ናቸው። ሰዎቹ ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውንና ዘመዶቻቸው ለፖሊስ አባላት ሄደው በሚያመለክቱበት ወቅት የእነሱ ጉዳይ ከባድ ነው ጠብቁ የሚል መልስ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል። በነጻነት መንቀሳቀስ አልቻልንም የሚሉት ሌሎች አባሎች፣ በገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት ከፍተኛ በደል እየደረሰባቸው መሆኑን ይናገራሉ። …

መጋቢት ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅዳሜው የሐውልት ምረቃው ላይ ያልተገኙት ጠ/ሚኒስትሩ፣  በማግስቱ በጅማ ከተማ በተካሄደው የስታዲየም ሰልፍ ላይ ተገኝተው ኦህዴድን የሚያወድስ ንግግር ቢያደርጉም እርሳቸውም ሆኑ የህወሃት ባለስልጣናት በሃውልቱ ምርቃት ላይ አልተገኙም። የህወሃት ከፍተኛ አዛዦች በሐውልት ምረቃው ላይ ያልተገኙት “ኦህዴድን  የፈጠርነው እኛ ነን” ከሚለው የህወሃቶች ትምክህት ወይም  ኦህዴድ ሰማዕታት አሉኝ በማለት የሚናገረውን ላለመቀበልና …

መጋቢት ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በባህርዳር ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው 2ኛው የትምህርት ቤቶች ውድድር ተገኙት ተወዳዳሪዎች እንደተናገሩት በውድድሩ በርካታ አዳዲስ ተተኪ ወጣቶች ለማፍራት የሚያስችል  ቢሆንም ወቅቱን የጠበቀ አለመሆኑ በትምህርታቸው  ላይ ጉዳት እንደሚያደርስባቸው ተናግረዋል፡፡ ከመጀመሪያው መንፈቅ አመት ፈተና በኋላ በቀጥታ ወደ ስፖርት ውድድር ልምምድ በመግባታቸው፣  ከትምህር ገበታቸው ላይ ለሁለት ወር ያህል መለየታቸውንና …

መጋቢት ፲፬(አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለኢህአዴግ መንግስት ቅርበት ያላቸው የመገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያ አየር ሃይል ኤርትራ ውስጥ የሚገኘውን ቢሻ የማእድን ማውጫ ኩባንያን መደብደቡን ቢዘግቡም፣  በኤርትራም ሆነ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል በይፋ የተሰጠ ማረጋጋጫም ሆነ ማስተባበያ አልተገኘም። ይሁን እንጅ የኩባንያው 60 በመቶ የአክሲዮን ባለቤት የሆነው ተቀማጭነቱ ካናዳ የሆነው ኩባንያ ፣ በማእድን ማውጫው ላይ  ባለፈው ሳምንት …

መጋቢት ፲፬(አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ሰሞኑን በሰሜን ጎንደር አካባቢ የታየውን የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ የአገሪቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ካለፈው ሃሙስ ቀን ጀምሮ በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ታዛዋል። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የአየር ሃይል አባላት ካለፈው ሃሙስ ጀምሮ ከግቢ እንዳይወጡ ሲታዘዙ የተወሰኑት ደግሞ ከደብረዘይት እና ድሬዳዋ አየር ሃይል  ወደ መቀሌ አምርተዋል። ብዛት ያለው የእግረኛ …

መጋቢት ፲፬(አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሶስቱ ሀገራት የፈረሙት ስምምነት በተለይ ባለፉት አራት ዓመታት በግድቡ ምክንያት በግብጽና በ ኢትዮጵያ መካከል  የነበረውን ውጥረት የሚያስቀር ነው ብሏል-አህራም። “የዓባይ ወንዝ ለሺህዎች ዓመታት በእግዚአብሔር ትእዛዝ ሲፈስ ኑሯል”ብለዋል የግብጹ ፕሬዚዳንት አል ሲ ሲ -ስምምነቱን ለመስማት በካርቱም ለተሰባሰቡ የተፋሰሱ ሀገራት ልኡካን ባደረጉት ንግግር። አል ሲሲ አክለውም፦”በመተባበር ትልቅ ነገር መፈጸም …

መጋቢት ፲፬(አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ፣ የተቋረጠውን የሰላም ድርድር በኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ ለማስጀመር የነበረው እቅድ ሳይሳቃ በመቅረቱ የልኡካን ቡድኑ ከኢትዮጵያ ለቆ ወጥቷል። እንደ ድርጅቱ መግለጫ ላለፉት 2 አመታት ሲደረግ የነበረው ጥረት፣ ለወደፊቱም ይቀጥላል። ኢትዮጵያ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች የሚለው መግለጫው፣ የአገሪቱን ችግር ፈትቶ ወደ ሰላምና ዲሞክራሲ ለመውሰድ ገዢው ፓርቲ የተለየ …

መጋቢት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የጎንደር ከተማ የሚሊያሻዎች ሃላፊ ኮማንደር መጋቢት 11 ቀን 2015 ዓም ቀበሌ 15 ወይም ፋሲለደስ ትምህርት ቤት አካባቢ ከምሽቱ 2 ሰአት አካባቢ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድሏል። ገዳዮቹም መሳሪያውን ማርከው ከእነ ትጥቃቸው ወደ አርማጭሆ ጫካ መግባታቸው ታውቋል። የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊው ግንባሩ አካባቢ በጥይት የተመታ ሲሆን …

መጋቢት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞ መንግስት ወታደሮች የነበሩ ግለሰቦችን በማሳባሳብ በህወሃት አማካይነት የተመሰረተው የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ለ25ኛ ኣመት የምስረታ በዓሉን ያሰራውን የሰማእታት ሃውልት ቅዳሜ መጋቢት 12 ቀን 2007 ዓ.ም በጨለንቆ ከተማ ያስመርቃል። ህወሃት እንደ ኦነግ ካሉ ድርጅቶች ጋር ግንባር ለመፍጠር የነበረው ፍላጎት ከከሸፈ በሃላ በ1982 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ …

መጋቢት ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምእራብ አርማጭሆ ወረዳ በአብርሃ ጅራ ከተማ ተቃዋሚ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩት ሁሉ እየተያዙ በመታሰር ላይ ናቸው። ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ እየተካሄደ ባለው ጥብቅ ፍተሻ በርካታ የኢህአዴግ አባላትና የጸጥታ ሃይሎች ተይዘው ሲታሰሩ፣ ቁጥራቸው በውል ያልተወቀ ነዋሪዎች ደግሞ አፈሳውን በመፍራት እያመለጡ የትጥቅ ትግል የሚያደርጉ ተቃዋሚዎችን በመቀላቀል ላይ ናቸው። እስካሁን በተደረገው አፈሳ …

መጋቢት ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዘላለም ወርቅአገኘሁ መዝገብ የተከሰሱ የቀድሞው የአንድነት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው፣  ምክትል የድርጅት ጉዳይ ሃላፊው አቶ ዳንኤል ሽበሺ፣ የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ የሽዋስ አሰፋ እንዲሁም የአረና ፓርቲ አመራር መምህር አብራሃ ደስታ ከሌሎች 6 ተከሳሾች ጋር መጋቢት 10 ቀን 2007 ዓም ፍርድ ቤት ቀርበው …

መጋቢት ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምእራብ  አርማጭሆ በአብርሃጅራሃ ከተማ ፀጉረ ልውጥ ሽፍቶችን አስገብተዋል በተባሉ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ፍተሻ እየተደረገ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ተናግረዋል። የከተማው ሕዝብና የአካባቢው ገበሬ በከፍተኛ ሥጋት ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ በሆቴሎች በዋና ዋና መንገዶችና መተላለፊያዎች ላይ  ፍትሻ እየተካሄ ነው። ነዋሪዎች ደግሞ በሚሄዱበት አካባቢ ሁሉ መታወቂያቸውን እየተጠየቁ ነው። እስካሁን ድረስ በቁጥጥር …

መጋቢት ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ ልዩ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል በሚል ክልሎችን ህወሃት፣ ብአዴንና ኦህዴድ እንዲያስተዳድሩዋቸው ካከፋፈለ በሁዋላ፣ የክልሎችን የመጀመሪያ ሪፖርት ሰሞኑን ተቀብሎአል፡ ኢሳት ቀደም ብሎ በሰራው ዘገባ የሶማሊ ክልል በህወሃት፣ ሃረሪ በኦህዴድና ህወሃት፣ አፋር በህወሃት፣ ቤንሻንጉል በብአዴን እንዲሁም  ጋምቤላ በህወሃት እንዲተዳደሩ መወሰኑን ዘግቦ ነበር። እነዚህ አዳጊ የተባሉ ክልሎች ማንኛውንም የስራ እንቅስቃሴያቸውንና እቅዶቻቸውን  ለእነዚህ …

መጋቢት ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች እንደገለጹት በመጪው ግንቦት ወር ምርጫ የምርጫ ካርድ ያልያዙ ሰዎች ስኳርና ዘይት እንደማያገኙ እንደተነገራቸው ለኢሳት ተናግረዋል። አንዳንድ ቀበሌዎች የምርጫ ካርድ ዘይትና ስኳር ለመሸጥ የምርጫ ካርድ አብረው የሚጠይቁ ሲሆን፣ ካርድ ላልወሰዱት እንዲወስዱ እየጠየቁ ነው። መራጮች የመምረጥም ሆነ ያለ መምረጥ መብት ቢኖራቸውም ፣ ገዢው ፓርቲ ከስኳርና ዘይት …

መጋቢት ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-3 የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መታሰራቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመለከተ። ወጣት ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ ወጣት ፍቅረማርያም አስማማውና እየሩሳሌም ተስፋው ካለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ በማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ እንደሚገኙ ኢሳት አረጋግጧል። ወጣቶቹ በምን ምክንያት እንደታሰሩ ለማወቅ አልተቻለም። መንግስትም እስካሁን የሰጠው ይፋ መግለጫ የለም። በሌላ በኩል ደግሞ የፓርቲው ሊ/መንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት …

መጋቢት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በአንድ ኢትዮጵያዊ ከፍተኛ ተቃውሞ ያገጠማቸው አቶ አብዲ ሙሃመድ ተቃውሞውን ያቀነባበሩት ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ የደህንነት ሹሙ ጌታቸው አሰፋ፣ ኢሳት ፣ ግንቦት7 እና የኤራትራ መንግስት በጋራ በመሆን ነው ሲሉ አካራ ኒውስ በተባለው የግል ዌብሳይታቸው ላይ በሶማልኛ ባወጡት ረጅም ጽሁፍ ገልጸዋል። ፕሬዚዳንቱ ተቃውሞውን ሲያሰማ የነበረውን መኮንን የተባለውን ሰው …

መጋቢት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ውስጥ ለሚሰራው የቀላል የባቡር መንገድ የኤሌክትሪክ ሃይል መስመር ዝርጋታ ርክክብን በተመለከተ በኢትዮጵያ መብራት ሃይል ኮርፖሬሽንና እና በመከላከያ ኢንጂነሪንግ የስራ አስፈፃሚ አመራሮች መካከል ከፍተኛ ውዝግብ መነሳቱን የውስጥ ምንጮች አመለከቱ፡፡ በመጀመሪያ መንግስት ለባቡሩ የሚያስፈልገውን  የኤሌክትሪክ አቅርቦት ግንባታ ለማስጀመር ከአንድ የግብጽ ኩባንያ ጋር ለመዋዋል በእንቅስቃሴ የነበረ ቢሆንም፣  ም/ል ጠቅላይ …

መጋቢት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለኢሳት የሚደርሱት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የንጹህ የመጠጥ ውሃ ችግር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ከትግራይ እስደ ደቡብ ክልል የውሃ ጀሪካኖችን በምንጮችና በውሃ መስጪያ ባንቧዎች ተሰልፈው ማየት የተለመደ ነገር ሆኗል። በዋና ከተማዋ አዲስ አበባም እንዲሁ በተለያዩ ቦታዎች የውሃ እጥረት ማጋጠሙን የየክልሉ ሪፖርተሮች ከሚልኩት እለታዊ መረጃ ለመረዳት ይቻላል።

መጋቢት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግብጽ፣ ሱዳንና ኢትዮጵያ በሚስጢር ሲያደርጉት የቆዩት ድርድር ከተጠናቀቀ በሁዋላ፣ የሶስቱ አገር መሪዎች በተገኙበት በካርቱም እንደሚፈረም መረጃዎች አመልክተዋል። የፊርማ ስነስርአቱ የፊታችን ሰኞ በካርቱም የሚካሄድ ሲሆን፣ ዝርዝር ይዘቱ ለህዝብ ይፋ እንዳይሆን ተደርጓል። የአባይ ግድብ  ከህዝብ በውዴታና በግዴታ በሚዋጣ ገንዘብ እየተገነባ መሆኑ እየታወቀ፣ ስምምነቱን ገንዘቡን ለሚያዋጣው ህዝብ ይፋ ለማድረግ ለምን እንዳልተፈለገ …

መጋቢት ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኦህዴድ የ25ኛ አመት በአሉን በትግራይ ክልል ውስጥ ለማክበር የነበረው ፍላጎት ከተደናቀፈ በሁዋላ፣ በደራ ወረዳ ጉንዶመስቀል ከተማ ለማክበር ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ ሲሆን፣ የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተዘግተው ሰራተኞች የገጠሩን ህዝብ እንዲቀሰቅሱ ተሰማርተዋል። መጋቢት 10 የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጉንዶመስቀል ይገባሉ ተብሎ በመጠበቁ እጅግ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላትና የደህንነት ሰራተኞች ወደ …

መጋቢት ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢህአዴግ ካድሬዎችን የሚያሰለጥነው አካዳሚ ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ አዲሱ ለገሰ ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ  በመለስ ዜናዊ ስም የተሰየመው  የአመራር አካዳሚ በመንግስት በጀት ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በአምስት ዙሮች 2ሺ 500 ያህል ከፍተኛ አመራሮችን፣ ከ30ሺ በላይ መካከለኛ አመራሮችን አሰልጥኗል፡፡ አካዳሚው ያለአንዳች ፈቃድ ከ2003 ዓ.ም እስከ 2006 ዓ.ም ሲሰራ ከቆየ በሃላ በ2006 ዓ.ም …