ሚያዝያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በግንቦት አጋማሽ ሊደረግ በታሰበው  ምርጫ ላይ  ገዢው ፓርቲ በቡድን ድምጽ የሚሰጡ ዜጎችን በማደራጀት ላይ መሆኑን በተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰቡ መረጃዎች አመልክተዋል። ዜጎች ድምጽ እንዲሰጡ የሚደረገው ገዢው ፓርቲ አንድ ለአምስት እያለ በሚጠራው የአፈና ስርአት ውስጥ ሆነው ነው። የኢህአዴግ ካድሬዎች በድምጽ መስጫው ቀን በአንድ ለአምስት የተደራጁትን ሰዎች በአንድ ላይ …

ሚያዝያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተእስራኤላውያን ዘረኝነትን በመቃወም ካለፈው ሃሙስ ጀምሮ የጀመሩት የተቃውሞ ሰልፍ እሁድ ተጠናክሮ ከቀጠለ በሁዋላ፣ የአገሪቱ ጠ/ሚኒስትር ቤንጃሚን ናታኒያሁ ፣ የተቃውሞው መነሻ የሆነውን ወታደር ደማስ ፈቃደን አነጋግረውታል። ወታደር ደማስ በእስራኤል ፖሊሶች መደብደቡ በአገሪቱ የሚኖሩትን በተእስረኤላውያንን በእጅጉ አበሳጭቶ ለተቃውሞ አደባባይ አስወጥቶአቸዋል። ቤተእስረኤላውያኑ በአገሪቱ ውስጥ ያለውን ዘረኝነት እጥብቀው …

ሚያዝያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሀገሪቱካሉት 879 በላይ  የጤናተቋማትውስጥመሰረተልማቶችየተሟሉላቸው 105 ብቻሲሆኑ፣ ከእርግዝናና ከወሊድ ጋር በተያያዘ በየቀኑ 68 ሴቶች በየሰዓቱ ደግሞ 3 እናቶች ህይወታቸው እንደሚያልፍ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የአብዛኛው እናቶች ሞት የሚከሰተው በደም መፍሰስ፣ በተራዘመ ምጥና በከፍተኛ የደም ግፊት ነው። በአዲስ አበባ ብቻ ከአንድ መቶ ሺ እናቶች መካከል 420ዎቹ ከወሊድ ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን …

ሚያዝያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው በዚህ ሳምንት ብቻ 9 ሺ 405 ወጣቶች ድንበር አቋርጠው ወደ ሱዳን ሲጓዙ በድንበር ጠባቂ ፖሊሶች ተይዘዋል። ፋሲል የኔአለም ዝርዝሩን ያቀርበዋልበሰሜን ጎንደር ዞን ቆላማ ወረዳዎች በተደረጉ 2 የዳሰሳ ጥናቶች በቀን  ከ150-250  በዓመት ደግሞ ከ 54,000 እስከ 90,00 ኢትዮጵያውያን   ወደ  ሱዳን ይሻገራሉ፡፡ …

ሚያዝያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሪፖርቱ ኢህአዴግ ምርጫውን ለማሸነፍ መልካም እድል መኖሩን ጠቅሷል። ኢህአዴግ መንግስት መሆኑና የመንግስትን ንበረቶችና ጽህፈት ቤቶች መጠቀሙ እንዲሁም   በቅስቀሳ ወቅት አንድ  ለአምስት  በሚል  አሠራር  በተጠቀመበት  የቅስቀሳና  የማሳመን አሠራር    በርካታ  ድምፆችን ለመውሰድ የሚያስችል እድል መፍጠሩን በ2002 ቱ ምርጫ ወቅት መታየቱን አቶ ሬድዋን ሁሴን ለሚኒስትሮች ባቀረቡት ሪፖርት ገልጸዋል። በቅድመ …

ሚያዝያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ነጻ ፕሬሱን በማዋከብ፣ በማሳደድ፣ በማሰር ከሚያደርገው ቀጥተኛ ጥቃት በተጨማሪ ስልታዊ ጥቃትን በተጠናከረ መልኩ ስራ ላይ እያዋለ ነው። በነገው ዕለት የሚከበረው የዓለም የፕሬስ ቀን በኢትዮጵያ ታስቦ የሚውለው የፕሬሱ ስልታዊ አፈና በተጠናከረበት ወቅት መሆኑም ያነጋገርናቸው ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ምንም ዓይነት ትችትና የተለየ …

ሚያዝያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአቶ ሬድዋን ሁሴን የሚመራው የኮምኒኬሽን ምክር ቤት  የኢሳት አባሎችን እና ቁልፍ የግንቦት ሰባት አመራሮችን የግል ላፕቶፓቸውን እና ለመረጃ መሰብሰብ የሚጠቀሙባቸውን ስልኮች ለማግኘት የሚያስችል እቅድ ማውጣቱ ታውቋል። በግምገማው ወቅት ኢሳት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠነከረ መሆኑ ተገልጿል። ኢሳት በመንግስት ላይ እየሰነዘረ ያለው ጥቃት ጉልህ ለውጥ የማምጣት አቅም …

ሚያዝያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሚያዝያ 20/2007 ዓ.ም አንዲት ምጥ የተያዙ እናት በአቅራቢያቸው በሚገኝ የጎምበራ የጤና ጣቢያ በሄዱበት ወቅት ‹‹ከአቅማችን በላይ ነው!›› ተብለው ወደ ሆሳና ሪፈራል ሆስፒታል ሄደው እንዲታከሙ ሪፈር ቢጻፍላቸውም በትራንስፖርት ችግር ነፍሳቸው ማለፉን ጋዜጣው ዘግቧል፡፡ ለጎምበራ ጤና ጣቢያ የተመደበችው አምቡላንስ በጎምበራ ወረዳ ኦሌ ቀበሌ ለገዥው ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ በመውጣቷ …

ሚያዝያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቤተእስራኤላዊያኑ የተቃውሞውን ሰልፍ ያደረጉት ደማስ ፈቃደ የተባለ ቤተእስራኤላዊ  ወታደር በፖሊሶች መደብደቡን ተከትሎ ነው። አንድ ፖሊስ ወታደር ደማስን መደብደቡን የሚያሳይ በሚስጢር የተቀረጸ ቪዲዮበማህበራዊ ሚዲያዎች ይፋ ከሆነ በሁዋላ ፣ ቤተ እስራኤላውያኑ ቁጫቸውን በአደባባይ ገልጸዋል። ሰልፈኞቹ ከፖሊስ ጋር ግጭት ፈጥረው እንደነበር የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የእስራኤል መንግስት ድርጊቱን የፈጸመውን ፖሊስ …

ሚያዝያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ፣ የማረሚያ ቤቱ ሹሞች ፖሊሶችን ለአስቸኳይ ስብሰባ እንደሚፈልጓቸው ከገለጹላቸው በሁዋላ፣ በስብሰባው ላይ የተገኙትን ፖሊሶች የሞባይል ስልኮች ተቀብለው ፍተሻ አድርገዋል። በፍተሻው ወቅት 18 ፖሊሶች ከኢንተርኔት የተለያዩ ፎቶዎች፣ ጽሁፎችንና ቀስቃሽ ዘፈኖችን በማውረድ በስልኮቻቸው ላይ አስቀምጠው የተገኘ ሲሆን፣ ፖሊሶቹም ወዲያዉኑ እንዲባረሩ ተደርጓል። በተለይ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ …

ሚያዝያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያኑ በጀኔቫ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፊት ለፊት  ባደረጉት ሰልፍ በሊቢያና የመን በችግር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ጥያቄያቸውን በተወካዮች አማካኝነት ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣኖች ያቀረቡ ሲሆን፣ የፖለቲካ ችግር ያለባቸው ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በአፋጣኝ ወደ ሶስተኛ አገር እንዲሸጋገሩ፣ ሌሎችም እንዲሁ አሁን ካሉበት አገር ወጥተው በሶስተኛ አገር …

ሚያዝያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከደህንነት ምንጮች የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ሚያዚያ 30 ፣ 2007 ዓም ከፍተኛው ፍርድ ቤት በእነ አቶ አቡበክር አህመድ በተከሰሱት ላይ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ቢጠበቅም፣ ከደህንነት መስሪያ ቤት በተሰጠትእዛዝ፣ ውሳኔው ከምርጫው በፊት አይሰጥም። ኢሳያስ ወልደጊዮርጊስ የተባሉት የደህንነት ባለስልጣን ይህንኑ አቋም በቅርቡ ተደርጎ በነበረው የኢህአዴግ የምክር ቤት ስብሰባ ላይ …

ሚያዝያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ  አለም ባንክ አካባቢ የሚገኙ ቤታቸው የፈረሰባቸው ከ3 ሺ በላይ አባወራዎች ያለፉትን 11 ወራት በስቃይ ቢያሳልፉም ፣ እስካሁን መፍትሄ ሊያገኙ አልቻሉም። የመንግስት ባለስልጣናት ከዚህ ጊዜ በሁዋላ ለምርጫ ቅስቀሳ መምጣታቸውን የገለጹት ነዋሪዎች፣ አሁን ያሉበት ህይወት ከሞቱት በታች መሆኑን በምሬት ገልጸዋል። ቤታቸው ከፈረሰባቸው …

ሚያዝያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመተማ ዮሃንስ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የቀበሌ አስተዳዳሪዎች እና የከተማዋ ፍትህና ጸጥታ ጉዳይ አመራሮች የመሳሪያ ፈቃድ የሚያወጡትን ነዋሪዎች፣ ለመሳሪያ ፈቃድ 260 ብር ፣ ለግዳጅ ቦንድ ግዢ 1 ሺህ ብር እንዲሁም ለቀበሌ መታወቂያ 300 ብር በማስከፈል ላይ መሆናቸውን ህዝቡን ምሬት ላይ ጥሎታል። በሱዳኗ የጠረፍ ገበያ ማዕከል በሆነችው የገላባት …

ሚያዝያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ከምሁራንና ከዲሞክራሲ አቀንቃኞች ጋር በጋራ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ፣ ተጋባዥ እንግዶች በኢትዮጵያ ወቅታዊ ፖለቲካ ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ወረቀቶችን ያቀርባሉ። ምሁራኑ ኢትዮጵያ የገጠሙዋትን ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች በማንሳት ተጨባጭ የመፍትሄ ሃሳቦችንም ያመላክታሉ ተብሎ ይጠበቃል። በውይይቱ ላይ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ምሁራን፣ የዲሞክራሲ አቀንቃኞችና የውጭ አገር ዜጎች ይገኛሉ ተብሎ …

ሚያዝያ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን አሰቃቂ  አደጋ ተከትሎ ለተቃውሞ የወጡ ኢትዮጵያውያን በፌደራል ፖሊሶች ተደብድበው እንዲታሰሩ በተደረገ ማግስት፣ የኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለከተሞች የሚገኙ ወጣቶችን በምሽት በማፈን ወደ እስር ቤት እያጋዙ ነው። የከተማዋ ነዋሪዎች እንደተናገሩት ባለፉት ሶስት ቀናት ብቻ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች …

ሚያዝያ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው አርብ ባሃድያ ዞን በሶሮ ወረዳ በጊምቢቾ ከተማ የፊዚክስ መምህር የነበረው ጌታቸው አብራሃም ፣  በወረዳው አስተዳደር  ግቢ ውስጥ ቤንዚን አርከፍክፎ ራሱን አቃጥሎ ገድሏል። የመድረክ አባል የነበረው መምህር ጌታቸው ከምርጫው ጋር በተያያዘ የምርጫ ቅስቀሳ ያደርግ ነበር። የተቃዋሚ አባል በመሆኑ ብቻ የ3 ወር ደሞዙን እንዳያገኝ የተከለከለው መምህር፣ አቤቱታውን …

ሚያዝያ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢችል ቀሬ እና ብርሃኑ ታየ የተባሉ ወጣቶች መጋቢት 29 ቀን 2007 ዓም በፌደራል ፖሊሶች ታፍነው ከተወሰዱ በሁዋላ የደረሱበት አልታወቀም። ወጣቶቹ በምን ምክንያት ታፍነው እንደተወሰዱም ሆነ  ታፍነው ከተወሰዱ በሁዋላ በህይወት ይኑሩ አይኑሩ  እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።

ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በመላው አገሪቱ በሚታየው የሕዝብ ቁጣ ስጋት ላይ የወደቀው ኢህአዴግ መራሹ መንግስት፣ በምርጫ ቦርድ አማካይነት ግንቦት 16 ቀን ሚካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ በሠላም ስለሚጠናቀቅበት ለመምከር የአንድ ቀን ስብሰባ ጠርቷል፡፡ በሒልተን ሆቴል በሚካሄደው ስብሰባ ላይ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች እንዲገኙ ተጋብዘዋል፡፡ በተቃዋሚዎች ሁልጊዜም ቅሬታ የሚቀርብበት …

ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሊቢያ ቤንጋዚ የሚኖር አንድ ሙስሊም  ኢትዮጵያዊ በጦርነት መሃል አልፎ ከ3 ወር ልጇ ጋር ለሶስት ቀናት ቤት ዘግታ የተቀመጠቸውን ኢትዮጵያዊት ማዳኑን ኢሳት በልዩ ዘገባ ካቀረበ በሁዋላ፣ ባልየው ከ4 ቀን በሁዋላ ከእስር ቤት አምልጦ ከቤተሰቡ ጋር ተቀላቅሏል። በቀሌ አስፋው የተባለው ኢትዮጵያ ወደ ሊቢያ የሄደው በቅርብ ሲሆን፣ የሊቢያ ፖሊሶች መንገድ …

ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በማምረቻ ወይንም በማኒፋክቸሪንግ ዘርፍ መንግስት በያዘው የአምስት ዓመት የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ መሰረት መከናወን ካለባቸው ትልልቅ ፕሮጀክቶች መካከል ከሲሚንቶ በስተቀር አለመሳካቱን አንድ ሰነድ አመልክቷል፡፡ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተገኘ ሰነድ እንዳመለከተው በሰኔ ወር 2007 ዓ.ም በሚጠናቀቀው የአምስት ኣመት እድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ ከተካተቱት መካከል ጥቅም ላይ የዋሉ ወረቀቶችና ከነባር ፋብሪካዎች …

ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ የነበረው እና በአሁኑ ወቅት የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው አቶ ስንታየሁ ቸኮል  ሚያዝያ 20/2007 ዓ.ም በደህንነቶች ታፍኖ ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዱን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ አራት ሲቪል የለበሱ ደህንነቶች ‹‹ትፈለጋለህ!›› በማለት በመኪና አፍነው ወዳልታወቀ ቦታ …

ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአሜሪካ የግብርና ዲፓርትመንት ባወጣው ጥናት በፈረንጆች አቆጣጠር በ2030 ወይም ከ15 አመታት በሁዋላ የኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ ገቢ 820 ዶላር ይደርሳል። ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ በቅርቡ ኢትዮጵያን መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ እንደሚያሰልፋት በተደጋጋሚ ቢናገርም፣ የጥናት ውጤቱ እንደሚያሳየው በ2030 ኢትዮጵያ ፣ የመካከለኛ ገቢ ዝቅተኛ መነሻ ከሆነው 1 ሺ ዶላር ለመድረስ …

ሚያዝያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባሳለፍነው ሳምንት በሊቢያ፣ በደቡብ አፍሪካና በየመን በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ግፍ የሚቃወሙ ሰልፎች፣ የሻማ ማብራት ስነስርአቶችና ጸሎቶች በአውሮፓ፣ በአሜሪካና በእስያና በአውስትራሊያ ተካሂዷል። በለንደን ሰኞ ሚያዚያ 19 ቀን 2007 ዓም በተካሄደው ከፍተኛ ተቃውሞ ኢትዮጵያውያን በወገኖቻቸው ላይ የደረሱትን በደሎች አጥብቀው ኮንነዋል። ጋዜጠኛ ወንድማገኝ ጋሹ በስፍራው ተገኝቶ እንዳለው …

ሚያዝያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህወሃት የልማት ድርጅት ፣ ኢፈርት ንብረት የሆነው መሶቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ላለፉት ሶስት አመተት  ያለተቀናቃኝ በከፍተኛ ዋጋ ለአባይ ግድብ ስሚንቶ ሲያቀርብ ከቆየ በሁዋላ ፣ ስራውን አቋርጧል። የአባይ ግድብ ግንባታ የኢኮኖሚ አዋጭነት ጥናት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ይፋ ከተደረገ በኃላ በባለስልጣናት መካከል ውዝግብ መነሳቱ ታውቋል። ጉባ የሚገኘው  የስሚንቶ ማምረቻ …

ሚያዝያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፒተር ስዋይዘር የተባሉ ጸሃፊ በቅርቡ በሚያሳትሙት መጽሃፍ ላይ ሼክ አላሙዲን ለክሊንተን ፋውንዴሽን 20 ሚሊዮን ዶላር እኤአ በ2006 መስጠታቸውን አጋልጠዋል። የሼክ አላሙዲን ድርጅት ለክሊንተን ፋውንዴሽን በጻፈው ደብዳቤ፣ እርዳታው የተሰጠው በኢትዮጵያ መንግስት ስም ሲሆን፣ የቡሽ አስተዳደር የውጭ ፖሊስ በክሊንተን አስተዳደር ጊዜም  እንዲቀጥል ያስስባል። በባለቤታቸው ስም ገንዘብ የተቀበሉት ሂላሪ …

ሚያዝያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከጎንደር ከተማ አስተዳደር የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው አቶ ቀናው ክንዴ የተባሉ የከተማው ነዋሪ  ሚያዚያ 6/2007 ዓም ከጧቱ ሁለት ሰአት ላይ የብአዴን ኢህአዴግን የምርጫ ምልክት ቀደዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። ግለሰቡ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊ በመሆናቸው ብቻ የሃሰት ክስ እንደተመሰረተባቸው ቢናገሩም የጎንደር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በማግስቱ ሚያዚያ 7/2007 ዓም …

ሚያዝያ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሊቢያ በረሃና  በደቡብ አፍሪካ በ አሰቃቂ ሁኔታ  የተገደሉትን ኢትዮጵያዊያንን ለማሰብ ረቡዕ ሚያዚያ 15 ቀን 2007 ዓም መንግስት የጠራው ሰልፍ ወደ  ሕዝባዊ ተቃውሞ በመለወጡ በብዙ መቶወች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በፖሊሶች ተደብድበው ሆስፒታል ከገቡ በሁዋላ፣ በቦታው ላይ የተያዙ፣ ማሽት ላይ በየቤቱ እየተለቀሙ የተያዙ እንዲሁም ዛሬ ሃሙስ ጧት የተያዙ በየክፍለ ከተማው …

ሚያዝያ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ህብረቱ የተለያዩ የፖለቲካ እና ሲቪክ ማህበራት መሪዎችን በመጋበዝ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ከ4 ሰአት በላይ ውይይት አድርጓል። የአውሮፓ ህብረት የእንግሊዝ ተወካይ፣ ወ/ሮ ጁሊ ዋርድ፣ በህብረቱ የፖርቱጋል ተወካይ ወ/ሮ አና ጎሜዝ፣ የስዊድኖቹ፣ ሶራያ ፖስትና ቦዲል ሲቢሎስ እንዲሁም የስፔን ተወካይ ሚ/ር ጆርዲ ሴባሲቲያ  እና ሌሎችም የህብረቱ ባለስልጣናት በውይይቱ ላይ …

ሚያዝያ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ማንነታቸው ያልታወቁት ሟቾች አስከሬን ማልታ ውስጥ በክብር እንዲያርፍ ተደርጓል። የኢትዮጵያ፣ የሶማሊ፣ የኤርትራና ሌሎችም አፍሪካውያን በቀብር ስነስርአቱ ላይ ተገኝተው ሀዘናቸውን ገልጸዋል። የሟቾቹ ዜግነት በውል ባይታወቅም፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው መረጃ ኤርትራውያን፣ ኢትዮጵያውያን፣ ሶማሊያውያንና ሌሎች አፍሪካውያን ይገኙበታል።

ሚያዝያ ፲፫(አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሊቢያ በአሸባሪዎች ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ለተገደሉት ወጣቶች ኢያሱ ይኩኖአምላክና ባልቻ በለጠ ቤተሰቦች ሀዘናቸውን ለመግለጽ ከተለያዩ አቅጣጫዎች  በማምራት ላይ የነበሩ ወጣቶች ስሜታቸውን መቆጣጠር ተስኖአቸው ተቃውሞአቸውን ሲያሰሙ ውለዋል። በሺ የሚቆጠሩ ወጣቶች መንግስትን የሚያወግዙ መፈክሮችን እያሰሙ ወደ ቤተመንግስት በማቅናት ላይ እያሉ ሂልተን ሆቴል አካባቢ በብዛት የተሰባሰቡት የፌደራል ፖሊሶች አስቁመዋቸዋል። ወጣቶች …

ሚያዝያ ፲፫(አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድምጻችን ይሰማ፦”ኢ–ሰብአዊነትንና ሽብርን ደግመን እናውግዝ! ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን እንታደግ!”በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ በደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያውያን እና ሌሎችም አፍሪካውያን ዜጎች ላይ አሰቃቂ የግድያ ወንጀል እየተፈጸመባቸው እንደሚገኝ በመጥቀስ፤ ሰቅጣጩ የጭካኔ ምግባር አፍሪካዊያን ላይ በአፍሪካዊያን የሚፈፀም መሆኑ ደግሞ ይበልጥ አሳዛኝ ያደርገዋል ብሏል። ከአስርት ዓመታት በፊት ምእራባዊያን ደቡብ አፍሪካዊያን የሚያደርጉትን የፀረ-አፓርታይድ ትግልና …

ሚያዝያ ፲፫(አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ የአለማቀፍ የስደተኞች ኮምሽነር ቃል አቀባይን  ጠቅሶ እንደዘገበው ሰሞኑን በሜዲትራኒያን ባህር በሰጠመችው ጀልባ ከነበሩ ከ800 በላይ የተለያዩ አገር ዜጎች መካከል 350 ኤርትራውያን ናቸው ተብሎ እንደሚገመት ገልጾ፣ ቀሪዎቹ ደግሞ ከኢትዮጵያ፣ ሶሪያ፣ ሶማሊያ፣ ሴራሊዮን፣ ማሊ፣ ሴኔጋል፣ ጋምቢያ፣ አይቮሪኮስት እና ባንግላዲሽ የመጡ መሆናቸውን ዘግቧል። አይ ኦ ኤም የተባለው አለማቀፍ የስደተኞች …

ሚያዝያ ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያን ሳምንቱን በሀዘን ተውጠው አሳልፈዋል። በየመን የተጀመረው የኢትዮጵያውያን የድረሱልኝ ጩኸት በደቡብ አፍሪካ እና በሊቢያ ተሰምቷል። 30 ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን በአሰቃቂ ሁኔታ በአይ ኤስ ወታደሮች የተገደሉበት ዜና መላውን አለም እያነጋገረ ነው። ኢትዮጵያውያን ሀዘናቸውን ከመግለጽ በተጨማሪ ምን እናድርግ እያሉ በመጠየቅ ላይ ናቸው። በፌስቡክ እና በማህበራዊ ድረገጾች የፖለቲካ እምነታቸውም ሆነ ሃይማኖታዊ …

ሚያዝያ ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ ሚያዚያ 12 ፣ 2007ዓም ኡራኤል አካባቢ አንድ ኢትዮጵያዊ ቤንዚን በራሱ ላይ አርከፍክፎ የተወሰነ የሰውነት ክፍሉ ከተቃጠለ በሁዋላ በህዝብና በፖሊስ እርዳታ ሊተርፍ ችሎአል። የአይን እማኞች ግለሰቡ ሙሉ ልብስ የለበሰ እና ጥሩ የሰውነት ቁመና  ያለው መሆኑን ተናግረዋል።  ፖሊሶችም ግለሰቡን ወደ ስድሰተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወስደውታል ዘግይቶ በመጣው መረጃ ደግሞ …

ሚያዝያ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፍሪደም ሀውስ  ይህን ያለው-በዩናይትድ ስቴትስ  ምክትል የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ  ወንዲ ሸርማን ስለ ኢትዮጵያ ምርጫ አስመልክተው ለተናገሩት ንግግር በሰጠው ምላሽ ነው። ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሀገር እንደኾነች የጠቀሱት ወንዲ ሸርማን  ሀገሪቱ በመጪው ግንቦት  የምታደርገው ምርጫ  ነጻ፣ፍተሀዊና ተዓማኒ እንደሚሆን  በእርግጠኝነት  ተናግረዋል። “ወንዲ ሸርማን የተናገሩት ነገር መሉ በሙሉ በመረጃ …

ሚያዝያ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ዶክተርን ኮሳዛና ድላሚኒ  የተፈጸመው ጥቃት በፍጹም ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በመጥቀስ፤ በጥቃቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ሀዘናቸውን ገልጸዋል። “ምንም ዓይነት ችግር ቢጋረጥብንም፣ ሟቾቹ የሀገሬው ሰው ይሁኑ አልያም የውጪ ሀገር ዜጋ፤ በህዝብ ላይ የሚፈጸምን ጥቃት በምንም ዓይነት ምክንያት ማስተባበል አይቻልም” ብለዋል- ሊቀመንበሯ። የደቡብ አፍሪካ መንግስትና  የኩዋ ዙሉ  አካባቢ …

ሚያዝያ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፓርቲው ፦«ከራሳችን ውጪ ለችግራችን ደራሽ መንግስት የለንም!»በሚል ርእስ በየመንና በደቡብ አፍሪካ በሚገኚ ኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈጸመ ያለውን ጥቃት አስመልክቶ ባወጣው ወቅታዊ መግለጫ ፣የኢትዮጵያውያን የውርደት ዘመን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ሰሞኑን ከተከሰተው እጅግ አስከፊ ሁኔታ ላይ አድርሶናል ብሏል። “የመን ውስጥ በተከሰተው ጦርነት ተጎጂ የሆኑትን የውጭ ዜጎች መንግስታቶቻቸው ቀድመው ሲያስወጡ …

ሚያዝያ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከዛሬ ሚያዝያ 9/2007 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀን በሚከበረው ‹‹የመምህራን ቀን›› የኢህአዴግ አባል የሆኑ መምህራን ብቻ መሸለማቸውን ነገረ ኢትዮጵያ በዝግጅቱላይ የነበሩ መምህራንን ዋቢ  አድርጎ ዘገበ፡፡ በተማሪዎች ዘንድ ብቃት የላቸውም ተብለው ቅሬታ የሚነሳባቸው መምህራን የገዥው ፓርቲ አባል በመሆናቸው ብቻ ‹‹ምርጥ መምህራን›› ተብለው እንደተሸለሙ የገለጹት መምህራኑ ‹‹ከመቶው 90፣ 80…. አግኝተዋል ተብለው ከመሸለማቸውውጭ መስፈርቱም ግልጽነት የጎደለውና ወገንተኛ እንደሆነ በግልጽ ተገንዝበናል›› ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በታህሳስ ወር 2007 ዓ.ም በፈጠራ ውጤታማ የሆኑትን መምህራን ሸልመው እንደነበር ያስታወሱት መምህራን ‹‹በአገር ደረጃ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በፈጠራ ሙያቸው የተሸለሙት መምህራን አሁን በከተማደረጃ ለተደረገው ሽልማት እንደማይበቁ ተደርጎ ከሽልማቱ መገለላቸው መምህራኑን አነጋግሯል›› ብለዋል፡፡ ዛሬ በተከበረው በዓል በአገር አቀፍ ደረጃ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሸለሙት እንዳይካተቱ የተደረገበት ዋነኛ ምክንያት የኢህአዴግ አባል ባለመሆናቸው እንደሆነ፣ በሌላ በኩል የኢህአዴግ አባል የሆኑትና በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም የተሸለሙትአሁንም መሸለማቸው የድርጅቱ አባል ያልሆኑትን መምህራን ሆን ተብሎ ለማግለል ያለመ ነው ብለዋል፡

ሚያዝያ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ አፍሪካ የውጪ ሀገር  ዜጎች ላይ የተፈጸመው ጥቃት  ያስቆጣቸው በርካታ ደቡብ አፍሪካውያን  ደርጊቱን  ለማውገዝ  በደርባን  ታላቅ ሰልፍ  ማድረጋቸውን የአገሪቱ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ደቡብ አፍሪካውያን እና የውጭ አገር ዜጎች በሰልፉ ላይ  ተገኝተዋል። “የውጪ ሀገር ዜጎችን ማጥቃትና ማሳድድ ይቁም!” የሚል መፈክር ያነገቡት የደርባን ነዋሪዎች፤ በጥቃት ፈጻሚዎቹ ላይ …

ሚያዝያ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የከተማዋ የኢሳት የመረጃ ምንጮች እንደገለጹት ከትናንት ሰኞ ምሽት ጀምሮ እስከ ዛሬ ማክሰኞ እኩለቀን ድረስ ከተማዋ በተኩስ ስትናወጥ ውላለች። አንዳንድ ነዋሪዎች እንደሚሉት የተኩሱ ልውውጡ የተካሄደው በመከላከያ ሰራዊት አባላት እና በሶማሊ ክልል ልዩ ሚሊሺያዎች መካከል ነው፡፡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት አንድ የክልል 5 ጠባቂ መግደላቸውን ተከትሎ፣ የክልሉ ልዩ  ሃይል ሚሊሺያዎች …

መጋቢት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለስልጣኖቹ በባህርዳር ከተማ በሁሉም አካባቢዎች የሚገኙ የተመላሽ ሰራዊት አባላትን ሰብስበው ስርአቱ አደጋ ውስጥ በመግባቱ እንዲታደጉት ጥሪ ቀርቦላቸዋል። ከምርጫው ጋር ተያይዞ ልማቱን ለማስቀጠል አደጋ ውስጥ ገብተናል ያሉት ባለስልጣናቱ፣ የተቀናሽ ሰራዊት አባላት በምርጫው ንቁ ተሳተፎ በማድረግ ስርአቱን እንዲታደጉ ተማጽነዋል። የሰራዊቱ አባላት “የቦታ ባለቤት እናደርጋችሁዋለን” ተብሎ ቃል የተገባላቸው ሲሆን፣ የፊታችን ቅዳሜ  …

መጋቢት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ9 ፓርቲዎች ትብብር ስር የሚንቀሳቀሰው የከምባታ ህዝቦች ኮንግረስ  ሊ/መንበር አቶ ኤርጫፎ ኤርዴሎ የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ ወደ ትውልድ ቀያቸው አንገቻ ወረዳ ቢያቀኑም፣ የወረዳው አመራሮች ከፍተኛ ችግር እንደፈጠሩባቸው ለኢሳት ተናግረዋል። ወደ ወረዳው በመሄድ የምርጫ ፖስተሮችን ሲለጥፉ እንደተቀደደባቸው፣ የተከራዩትን ቤት እንዲለቁ መገደዳቸውን የገለጹት አቶ ኤርጫፎ ይባስ ብሎ ከተማው ውስጥ ሆቴል ለመያዝ …

የየመንን ዋና ከተማ ሰንአን በመቆጣጠር ሁለተኛዋን ታላቋን ከተማ ኤደንን ለመቆጣጠር ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በመፋለም ላይ የሚገኙት የሃውቲ ሚሊሺያዎች፣ ከሳውድ አረቢያ የሚደርስባቸውን የአየር ጥቃት ተቋቁመው ከተማዋን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር መቃረባቸውን መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ነው። አማጽያኑ በሚደርስባቸው የአየር ጥቃት ሳይበገሩ፣ የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ታማኝ ወታደሮች በመፋለም ላይ ናቸው።አሜሪካ ለሳውድ አረቢያ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን በማቅረብ ላይ መሆኗን ገልጻለች። ኢራን በበኩሉዋ …

መጋቢት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመድረክ አባል የሆነው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊ/መንበር አቶ በቀለ  እንደተናገሩት በመጪው ምርጫ ለመሳተፍ ድርጅታቸው በኦሮምያ የተለያዩ አካባቢዎች እጩዎችን ቢያሰማራም፣ እጩዎቹ እየታሰሩና እየተደበደቡ በመሆናቸው መድረክ ቀጣዩን ሂደት ለመወሰን እየተነጋገረ ነው። አቶ በቀለ በሆድሩ ጉድሮ አባሎቻቸው ቅስቀሳ እንዳያደርጉ መከልከላቸውን፣ በሜታ ሮቢ  ከ50 ያላነሱ ወጣቶች መታሰራቸውን፣ በግንደበረት የወረዳው አስተዳደር ሽጉጥ …

መጋቢት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት _IOM ባወጣው ዘገባ ህይወታቸው በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 131 ኢትዮጵያውያንን ከጅቡቲ ወደ አገራቸው መልሷቸዋል። ከተመላሾቹ መካከል 100 ያህሉ ኢትዮጵያውያ ወደ የመን ለመጓዝ በዝግጅት ላይ እንደነበሩ ድርጅቱ አስታውቋል። 28 ኢትዮጵያውያን ደግሞ ከየመን ወደ ጅቡቲ በባህር ላይ ጉዞ አድርገው የደረሱ ናቸው። በሰላም ወደ አገራቸው ከተመሰሉት መካከል …

መጋቢት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ዞን በአለፋ ጣቁሳ ወረዳ በሻውራ ከተማ የከተማዋ ነዋሪዎች ካለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ ውሃ በማጣታቸው መቸገራቸውን ለኢሳት ገልጸዋል። አንድ ጀሪካን ውሃ እስከ 20 ብር ለመግዛት ተገደናል የሚሉት ነዋሪዎች ምክንያቱም ሙስና ነው ይላሉ። የወረዳው መስተዳደር 300 ሺ ብር የተገዛውን ጄኔረተር 800 ሺ ብር እንደተገዛ አድርጎ ማቅረቡን የሚናገሩት …

መጋቢት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሱዳን ትሪቢውን የግንባሩን ሊቀመንበር ተዋት ፖል ቻይን ጠቅሶ እንደዘገበው ፣ የደቡብ ሱዳን አማጽያን፣ የሳልቫኪር መንግስት ለኢትዮጵያ አርበኞች አንድነት ግንባር ወታደራዊ ስልጠና፣ የገንዘብ እንዲሁም የሎጅስቲክ ድጋፍ ያገኛል በሚል ያቀረበው ወቀሳ ተቀባይነት የሌለው ነው። አማጽያኑ የፖል ቻይ ጦር ወደ ጋምቤላ በመግባት ጥቃት ለመፈጸም አስቧል በማለት ክስ አሰምተው ነበር። ፖል …

መጋቢት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እንድ ራዲዮው ዘገባ  ትናንትና አንዲት ወጣት አይነስውር ድልድዩን ስትሻገር ገደል ውስጥ ገብታ ህይወቷ አልፏል። ይህ  ቀጭኔ መድህኒ ዓለም አካባቢ ያለው ድልድይ በቀኝና በግራ በኩል አደጋ መከላከያ ድጋፍ የሌለው በመኾኑ ለሰዎች መጥፋት ምክንያት እየሆነ መምወጣቱን የ አካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። አካል ጉዳተኞችን ለአደጋ የሚያጋልጡ ከደረጃ በታች የሆኑ ድልድዮች  በከተማው …

መጋቢት ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኤጀንሲው በአዳማ ስብስባ እንደሚያካሂድና አንድ የድርጅቱ ከፍተኛ የሥራ መሪ እንዲገኝ በስልክ በተነገራቸው መሠረት በአዳማ መገኘታቸውን የተናገሩት አንድ የስብሰባው ተሳታፊ ፣ በዚህ ስብሰባ ላይ ምግባረሰናይ ድርጅቶችን አላሰራ ባሉት ሕጎችና አሰራሮች ዙሪያ ምክክር ይደረጋል የሚል ሃሳብ ይዘው በቦታው ቢገኙም የገጠማቸው ግን ፈጽሞ ያላሰቡት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዚሁ ስብሰባ ላይ …