የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን ለጠ/ሚኒስቴር ለኃ/ማሪያም ደሳለኝ ሁለት ጊዜ ደብዳቤ መፃፋቸውን ተዘገበ::

በመጋቢት ወር አጋማሽ ላይ በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደርጋሉ ተብለው የሚጠበቁት የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳይ ያላቸውን ስጋት በመግለፅ ለጠ/ሚኒስቴር ለኃ/ማሪያም ደሳለኝ ሁለት ጊዜ ደብዳቤ መፃፋቸውን በዝ ፊድ ኒውስ የተሰኘ ጋዜጣ ዘገበ ።
የሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሲያደርግ የቆየው ጥረት ውጤት አለማምጣቱን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤውን እንደጻፉ በዝ ፊድ ኒውስ የተሰኘ ጋዜጣ በዘገባው አስፍሯል። የጠቅላ ሚኒስትሩ ዴቪድ ካሜሮን የኢትዮጵያ ጉብኝት የነበረው በቅርቡ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና ከተለያየ አካላት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲፈቱ ግፊት እንደያደርጉ የቀረበላቸውን ከ130ሺ በላይ ፊርማ ተከትሎ መሆኑም ተገልጿል።
የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ወደ ሃገራቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ ለማመቻቸት በርካታ ጥረቶችን ሲያደርግ ቢቆይም የተፈለገው ውጤት ሊገኝ አለመቻሉን ሬፕሪቭ የተሰኘ የብሪታኒያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በድረ-ገጹ ዘግቧል። የጥረቱን አለመሳካት ተከትሎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ያላቸውን ስጋት በመግለጽ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ሃይለማሪያም ደሳለን ሁለት ጊዜ ደብዳቤ መጻፋቸውን ጋዜጣው የሃገሪቱን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።
የእንግሊዝ ጠ/ሚኒስቴር ዴቪድ ካሜሮን ለጠ/ ሚኒስቴር ለአቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በፃፉት ደብዳቤ ሁለቱ ሃገራት ካላቸው የጠበቀ ግንኙነት አንፃር በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ዙሪያ ሲደረገ የቆየው ውይይት ፍሬ አለማፍራቱ ቅሬታን እንደፈጠረባቸው በደብዳቤያቸው ገልጸዋል።
የብሪታኒያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተለያዩ አካላት የቀረበባቸውን ግፊት ግምት ውስጥ በማስገባት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫናን እንዲያደርጉ በማሳሰብ ላይ መሆናቸውም ተዘግቧል። ሪፕሪቭ የተሰኘውን የብሪታኒያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ጨምሮ በርካታ አካላት ሀገሪቱ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የደህንነትና የጸጥታ ድጋፍ እንድትቋረጥ ሲያሳስቡ መቆየታቸውም የሚታወቅ ነው።
MeTfo sreat miwodq bemeTfonetu new.
Hulum slemiqawemew amro taglo ygeressewal.
Andargachew tasro tgrai woyanie liwedq zarie nege qertotal.
Baschequay andargachew yfeta.
Don’t expect something posotive from Pm David Cameruen,as his country is the most enemy of Ethiopia.
What a joke. If cameron likes within an Hour can do it.Please don’t fool us! Don’t you know ,the idiot tplf &eplf are the Child of Britain and still didn’t accomplisch their mission?
Don’t expect something posetive from Pm David Cameruen,as his country is the most enemy of Ethiopia.
ወይ እንግሊዝ፥ አንዳርጋቸው ኦሪጂናል እንግሊዛዊ ስላልሆነ እንጂ ነጭ ቢሆን ኖሮ እውነት በወያኔ አስር ቤት ውስጥ ይህን ያህል ጊዜ እንዲቆይ ታደርግ ነበር? በ19ኛው ክ/ዘመን ዓፄ ቴዎድሮስ አሠሯቸው ያሏቸውን ዜጐቻቸውን ለማስፈታት ጦርነት ያካሄዱ፤ ዛሬም ጥቅማቸውንና ክብራቸውን የሚነካ ነገር ከተፈጠረ ምንም ከማድረግ ወደኋላ የማይሉ እንደ እንግሊዝ ያሉ ምዕራባውያን በነሱ ላይ የዲፕሎማሲና የእርዳታ ጥገኛ የሆነውን መንግሥት በማስገድድ ጭምር ዜጋቸውን ማስፈታት ያዳግታቸዋል ብሎ ማመን ይከብዳል። በፖለቲካ ጉልበትና በጦረኝነት ተፅዕኖዋ እምብዛም የማትታወቀው ስዊድን እንኳን በህገወጥ መንገድ ወደአገሪቱ በመግባታቸው ረጅም ዓመት እስር የተፈረደባቸው ዜጐቿን በዚያ በዚህም ብላ በአጭር ጊዜ ውስጥ ማስፈታት መቻሏ ለዚህ ለእንግሊዝ ድክመት ጥሩ ማሳያ ይመስለኛል።
እኔ ስለ እናንተ ደከምኩ እንዴት ነው ነገሩ? እምንሠራዉን የምናውቀው አይመስልም ኤሪትሪያ በረሐ ስትገቡ እንግሊዝ ወይም አሜሪካን በማንኛውም መንገድ ብያዝ እነሱ ያስፈቱናል ብላችሁ ከሆነ ትልቅ ስሕተት ነው።ጦር ሜዳ ቢሞት ኖሮስ?ማፈሪያዎች ጀግና የሆነ በራሱ በሕዝቡ ተማምኖ ታሠረብኝ የሚለውን ሲያስፈታ ነው።ፕሮፌሠር ብርሃኑ ሳይደገም ምክር ለግሡት አለበለዚያ ነገ ደግሞ ለእርሡ ሠልፍ እንዳትጠሩን።ግን እናን የደርግ ሰልፍ ናፋቂዎች ተዉን።ባለ 5 ኮከብ ሆቴል ሆኖ እንደመዋጋት ይቆጠራል የተባለላት ኤርትራ ያለው ትግል ምን ደረሠ? ለነገሩ ማን ሞኝ አለ ያንን የመሠለ ሆቴል ማን ይለቃል ብሬም እኮ ሊቭ ኦፍ አብሰንት ሞልታ የሄደችው ሪሠርች ልትሠራ ነው።ጉድ ጃብ ፕሮፌሰር።በዚህ ሒደት ፶ዓመት እሠጣለሁ ለዉጥ አታመጡም።ለአዳራሽ ለስብሰባ ወደኤርትራ ካዝና የሚገባው ገንዘብ ያሣዝነኛል።ጎበዝ ከሆናችሁ እንደ ፈርኦን ልጆች ኑሐገር እንግባ መስቀል አደባባይ እንቁም ለመግደል ሳይሆን ለመሞት መተናል ሕዝባችን ፍትህ አቷል ርሀብ ድንቁርና በዝቷል ስልጣን ለሕዝቡ ስጥ እንበል እዚህ እስታርባክስ ቁጭ ብሎ መፎከር ጥቅም የለውም።ለመሞት ከኤርትራ እዛው ሐገር አይሻልም?ብርሃኑ ነጋ በእርሱ መርህ ስንት ወጣት አስፈጅቶ ወደ አሜሪካ ሸሽቶ የመጣው?ማፈሪያዎች።በእናን ስግብግብነት፣ስልጣን ጥም የሐገሬን ሕዘብ ለነፍሠበላዉ ወያኔና ኦነግ እንዲሁም ሻዕቢያ ቀንበር እንዲጫንበት አደረጋችሁ።ምንካሽ ሐገሬ አንድ በላይ ዘለቀ፣አንድ አሉላ አባነጋ፣አንድ አብቹ፣አንድ አብዲሣ አጋ፣ አንድ ምኒሊክ፣አንድ ዮሐንስ፣ እንድ ቴዎድሮስ፣አንድ ጦና፣አንድ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ጴጥሮስ፣አንድ…ብቻ ነዉ እንዴ አፍርተሽ ያቆምሺዉ?ምን ነካህ አን ትግሬ?ያን ሁሉ ወጣት ሙት እና አካል ዳተኛ የሆኑት እነዚህ ባንዳ የባንዳ የባንዳ ልጆች በሐገርህ ላይ ሲጨፍሩ ዝምበለሕ አታ ወዲ ጀግና ትልአል ኢትዮጵያ እያለቀሠች ነዉ አንተ አማራ ምነው ሸዋ ምነዉጎንደሬ ምነው ጎጃሜ ምነዉ ወሎዬ ተነሣ እንደ በላይ ዘለቀ ዱር ግባ አንተ ኦሮሞ ምነዉ ኦሮሞ የታለ አብቹ?የታለ አብዲሣ።አንቺ ኢትዮጵያ የታሉ ልጆሽ ባንዳ የባንዳልጅ አረገሽ መቀለጂያ።ከፕሮፌሠር ብርሃኑ እስከ ፅንፈኛዉ ጁሐር መሐመድ እጃችሁን ከሕቤ ላይ አንሱ
Who is the guy who wrote this article in Amharic ?
An MI6 or CIA agent perhaps ?
Better not to tolerate this kind of “parroting” of ferenji written propaganda and lies without the Ethiopian author adding his own comments.
The Ethiopian author should not have simply repeated the press release of the UK government, which is almost 100% lie, without adding his comment.
He didn’t for example remind readers that USA and UK control TPLF, it is their puppet. That UK tried to get him released but failed so far should not have been written without questioning its truthfulness. The Ethiopian author should have also questioned the seriousness of the UK demand to get the prisoner released.
If you ask me,
i really suspect this particular prisoner issue. It could be an MI6 operation, which aim could be to get a UK friendly leader at the helm of power in Ethiopia after TPLF.
ለምን 1001 ጊዜ አይፅፉም