በኢደል አደሀ ( በአረፋ በዓል) ላይ ፊዳከ የሚል ቲሸርት ለብሳችሗል በሚል ክስ የተመሰረተባቸው 15 ወጣት ሙስሊሞች በነፃ እንዲሰናበቱ መደረጉ ተሰማ
በኢደል አደሀ ( በአረፋ በዓል) ላይ ፊዳከ የሚል ቲሸርት ለብሳችሗል በሚል ክስ የተመሰረተባቸው 15 ወጣት ሙስሊሞች በነፃ እንዲሰናበቱ መደረጉ ተሰማ

በነ አድናን ኑሩ አብደላ የክስ መዝገብ የተካተቱት 15 የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች ባለፈው መስከረም 13/1/2008 በተመሰረተባቸው ሃሰተኛ ክስ ፊዳከ የሚል ቲሸርት ለብሳችሗል ፣ ድምፃችን ይሰማ አሏሁ አክበር ኮሚቴው ይፈታ ብላችሗል በሚል ተከሰው ፍርድ ቤት ቀርበው ላለፉት ከ3 ወራቶች በላይ ክርክር ሲያደርጉ ቆይተው በዛሬው እለት ያቀረቡት የመከላከያ ምስክር በቂ ነው በማለት የካንጋሮው ፍርድ ቤት በነፃ እንዲሰናበቱ ሲል ወስኗል