ወያኔ ፈሪ ነው::የጊዜ ጀግና እንጂ የሰው ጀግና ያሌለው ሙልጭ ያለ ፈሪ አገዛዝ ..

ወያኔ ፈሪ ነው::የጊዜ ጀግና እንጂ የሰው ጀግና ያሌለው ሙልጭ ያለ ፈሪ አገዛዝ ..

እንደ ወያኔ አይነት ውርጃ ፈሪ አገዛዝ ንጹሃንን ያልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎችን ይገላል – ያስራል::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Change‬ ‪#‎Freedom‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ወያኔ ፈሪ ነው::የጊዜ ጀግና እንጂ የሰው ጀግና ያሌለው ሙልጭ ያለ ፈሪ አገዛዝ .. ወንድ እና ጀግና እኮ ሰላምን እና ሰላማዊ ጥያቄን ያከብራል::በመሃል ክፍላተሃገራት የተነሳውን የተማሪዎች ንቅናቄ ተከትሎ የወያኔው አገዛዝ ከግድያ ጀምሮ እስከ እስር እና ዛቻ ድረስ ቀጥሎበታል:: ወያኔ ጀግኖችን ይፈራል ወያኔ እውነትን ይፈራል ስለሚፈራ ደግሞ በመሳሪያ ሃይል ስር ተደብቆ ምንም ያሌላቸውን ንጹሃንን ያጠቃል::ወያኔ ደፋር እና ጀግና ቢሆን እኮ አደባባይ የወጣን ያልታጠቀ ሕዝብ ላይ የጥይት ውርጅብኝ አያወርድም::በስለጠነ አለም ላይ ላይ በባዶ እጃቸው አደባባይ ወጥተው ጥያቄ የጠየቁ ይሁኑ በተባ ብእራቸው ተቃውሞ ያሰሙ ሕዝቦችን መግደልና ማሰር የአገዛዙን ፍርሃት እና ውርጃነት ወለል አድርጎ ያሳያል::

የግድያው እና ከተቃውሞ ሰልፎች ላይ የታፈሱት ሲገርመ በየቤቱ እና በየመንገዱ እየጠበቁ በማፍያ ስራ በተካኑ ደህንነቶች የፖለቲካ አመራሮችን እና አክቲቭስቶችን ማፈንን አጥብቀን እንቃወማለን::አገዛዙ አገር መምራት ስላልቻለ ስልጣኑን ለቆ ለሕዝብ ማስረከብ ሲገባው ሰላማዊ ዜጎችን እያሳደዱ ማሰር እና መግደል ነገ ከተጠያቂነት እንደማያስመልጥ በድጋሚ ለመናገር እፈልጋለሁ::የጊዜ ጉዳይ እንጂ እንኳን ሕዝባዊ መሰረት ያጣው ወያኔ አይደለም ሕዝብን አፍኖ ከአፍሪካ ግዙፍ ሰራዊት የገነባው ደርግ በሕዝብ ተጋድሎ በኢትዮጵያ ውስጥ መንኮታኮቱን መዘንጋት የለብንም::ስለዚህ የወያኔ አገዛዝም ተንኮታኩቶ ተረት ተረት የሚሆንበት የዘረፉት ንብረትም በሕዝባዊ መንግስት የሚወረስበት በስተርጅና የወያኔ ጉጅሌዎችም እስር ቤት የሚጃጁበት ከሃገር የወጥውም ፍርዱን የሚያገኝበት ጊዜ ቅርብ ነው:;ወያኔ የጊዜ ጀግና እንጂ የሰው ጀግና አይደለም:: መፍትሄው አንድ እና አንድ ብቻ ነው::በጋራ ተባብረን በመታገል ወያኔን መደምሰስ አራት ነጥብ ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬