የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞና የወለዳቸው የፍትህ እና መልካም አስተዳደር ጥያቄ ድምጾች መሰማታቸው ቀጥለዋል::
የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞና የወለዳቸው የፍትህ እና መልካም አስተዳደር ጥያቄ ድምጾች መሰማታቸው ቀጥለዋል:: #Ethiopia #OromoProtests #AddisAbabaMasterplan
የወያኔ አገዛዝ የፌዴራል ፖሊሶች ኮማንድ ፖስት ለጥፋት በሁለት አቅጣጫ በምእራብ ሸዋ እና ደቡብ ምእራብ ሸዋ መሰማራታቸው ከዚህ ምስል ታይቷል::

Minilik Salsawi በተለያዩ ክፍላተ ሃገራት ተማሪዎች ገበሬዎች እና የአከባቢው ነዋሪዎች በመቀናጀት የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም የጀመሩት ሰልፍ የቀጠለ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘ የመብትና ነጻነት የፍትህ እና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በመስተጋባት ላይ ናቸው::
በምአራብ ሸዋ ባኮ በዶዶላ አርሲ በምስራቅ ሃረርጌ ቆቦ በቆሬ አርሲ በቡራዩ ከተማ ተማሪዎች ገበሬዎች እና የአከባቢው ነዋሪዎች ማስተር ፕላኑን በመቃወም ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ላይ ይገኛሉ::በሲቡ ስሬ ከተማ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ተቋውሟቸውን በማሰማት ላይ ሲሆኑ አግኣዚ ጦር በመሳሪያ ሀይል በመጠቀም ወንጀል በመስራት ላይ ይገኛል:: #MinilikSalsawi
