በእንደርታ ወረዳ ለሚገኙ በድርቅ ለተጎዱ ተብሎ የመጣው የእርዳታ እህል እየተዘረፈ ነው።

በእንደርታ ወረዳ ለሚገኙ በድርቅ ለተጎዱ ተብሎ የመጣው ኣንድ እስካንያ መከኒ ከነተጎታቹ የእርዳታ እህል በወረዳው ባለስልጣናትና ነገዴዎች በመመሳጠር የተራገፈ ኣስመስለው በሌላ መኪና ገልብጠው ጭነው ሲወስዱ የኲሓ ህዝብ እጀ ከፈንጅ ይዞ ለፖሊስ ኣስረክበዋል።

እነዚ የወረዳ ባለ ስልጣናትና የኲሓ ነጋዴዎች የዘረፉት በኣራት መኪኖች ጭነው ወደ ነጋዴዎቹ መጋዘንና በራሕለ ወደተባለችው የዓፋር ከተማ ሲያጓጉዙት ተይዘው መቐለ ወኽኒቤት እንዲታሰሩ ተደርገዋል።

በሌላ ዜና ደግሞ እንደርታ ወረዳ ዓራቶ ቀበሌ የእርዳታ እህሉ እየዘረፉ የተገኙት የቀየሌ ኣመራሮች ህዝቡ እጀከፈንጅ ይዞ ፖሊስ ጣብያ ኣድርሰዋል።

በመላ ትግራይ በድርቅ ለተጠቁ ወገኖች የመጣው የእርዳታ እህሉ ዘረፋ በእጅጉ ተጣጥፎ ቀጥለዋል።

በደቡባዊ ዞን እንዳመኾኒ ወረዳ ችንኮማጆ ቀበሌ ኑዋሪ ህዝብ ለሴፍትነት የመጣው እህል እየዘረፉ ያገኛቸው የወረዳና ቀበሌ ኣመራሮች ይዞ ወደ ፖሊስ ጣብያ በመውሰዱ ከፍተኛ ውጥረት ነግሰዋል።

በእንዳመኾኒ ወረዳ ጎለውሳ ቀበሌ የሚገኙ ኣመራሮች የሴፍትነት እህል የመዳባርያ፣ የማህበራት፣ የኣባይ፣ የመፅሄት ወዘተ እያሉ ያለ ደረሰኝ እየቆረጡለት እንደሚገኙ ታውቀዋል።

በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች እየመጣ ያለው የእርዳታ እህል እየተዘረፈ መሆኑ ወይዘሮ ያለም ፀጋይ የምስራቃዊ ዞን ኣስተዳዳሪ እንደመሰከሩ የሚታወቅ ነው።

ይሄ ዝርፍያ ከፍተኛ የክልል ባለ ስልጣናት ጀምሮ የወረዳና የቀበሌ ኣመራሮች እየተሳተፉበት ይገኛሉ።

ህዝቡ በተቻለው መጠን ሌቦች ይዞና ኣጋልጦ ወደ ፖሊስ ጣብያ እያደረሰ ቢሆንም ከሁለት ቀን እስራት ተመልሰው የማስወጣት ተግባር የጠቆመባቸው ህዝብ እያሰቃዩት ይገኛሉ።

የዓረና ኣባላት ሙሉ በሙሉ ከድርቅ እርዳታው ውጭ ተደርገዋል።

Amdom Gebreslasie's photo.

6 Comments on “በእንደርታ ወረዳ ለሚገኙ በድርቅ ለተጎዱ ተብሎ የመጣው የእርዳታ እህል እየተዘረፈ ነው።”

  1. እናቱ የሞተችበት ልጅና እናቱ ውሃ ልትቀዳ የሄደችበት ልጅ ሁለቱም እኩል ያለቅሳሉ ! ! ! ! የኦሮሞውና የአማራው ሕፃናት እናታቼው በወያኔ ጥይት ተገድላባቼው ያለቅሳሉ።የወያኔው ሕፃን ግን እናቱ ከወንዝ ውሃውን ይዛለት እስከምትደርስ ያለቅሳል።የቅንጦት ለውሶ ! ! ! ! የእርዳታ ስንዴ ተሰረቀ ተብሎ መዘገብ አሁን ለኦሮሞና ለአማራው ሕዝብ የቅንጦት ዜና ነው።የልጆቻችንና የእናቶቻችን ሕይወት በወያኔ ጥይት እየተቀጠፈ ባለበት ጊዜ ስለእርዳታ ስንዴ መዘረፍ ማውራት ለእኛ ለኦሮሞና ለአማራ ሕዝቦች ቅንጦት ነው።

  2. temelkach…..er kemechie new egna amhara…oromo malet yejemerachihu….kkkk deron siyataliluat alu…..lemanignawum oromo bileh bemetratik ….temesgen new….

    ante gin yetigrayu dirk minim gid yesetek atimesilem….lik ende h/slassie…lik ende derge…ende abatik…

    mechiem bihon gin oromo …ke Amhara gar andinet yifetral bilek endatasib….NEFTEGNA…gena ..gena …yaletewerarede eda alebet…kehulum bihier

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*