ስምንት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ሕዝብ በሞት አፋፍ ላይ ይገኛል::(ምንሊክ ሳልሳዊ)

Minilik Salsawi – በጥልቀት አትኩሮት እንዳይሰጠው እየተሸፋፈን እየተድበሰበሰ ያለው በሃገራችን ውስጥ የተከሰተው ድርቅ ስምንት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ሕዝብ በሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚወጡ ሪፖርቶች እየጠቆሙ ነው:: የወያኔው አገዛዝ በሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን የረሃብ አድጋ ተድበስብሶ ተደብቆ እንዲቀር እየቧጠጠ ያለው ነገር ሁሉ በከፊል ቢሳካለትም እንደ ተባበሩት መንግስታት ያሉ ትልቅ ድርጅቶች ግን ሊደብቁለት አልቻሉም::በመጪው አመት 2016 ከ15 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ በረሃብ አደጋ እንደሚጎዳ እንደሚፈናቀል የሚናገሩ ሪፖርቶች ከነሃሴ 2015 ጀምሮ ቢወጡም በኢትዮጵያውያን ዘንድ ግን ተሰሚነት እንዳያገኙ ወገን እንዲሞት ወያኔ እየሰራ እንደሚገኝ በገሃድ እያየን ነው::

የወያኔው አገዛዝ ለጋሽ አገሮችን እና የተለያዩ የእርዳታ ድርጅቶችን በድብቅ ቢጠይቅም ምንም ውጤት እንዳላገኘ ከዚህ ቀደም የሰማን ሲሆን የልማት በጀት አለኝ ለእርዳታ እውለዋለሁ የሚል ሃሰተኛ ማጭበርበሪያ ዲስኩር መጠቀሙ ይታወሳል::አሁን ግን ሕዝቡ ለከፍተኛ አድጋ ከመጋለጡም አልፎ የመጨረሻው እስትንፋሶች ከሕይወት እየተለዩ መሆኑ ታውቋል::በሕዝብ ላይ ቀልድ የያዘው አገዛዝ ለዜጎች ደንታ እንዳሌለው ከሚያጽድቃቸው ፖሊሲዎቹ ጀምሮ እስከሚተገብራቸው ሃሰተኛ ፕሮፓጋንዳዎች ድረስ አጋልጠውታል::

እስካሁን ድረስ ምላሽ ያላገኘው የእርዳታ ጥሪ እንዲሁም በዘረፋ የተራቆተው ባዶ የአገዛዙ ካዝና ወገንን ከሞት ለማዳን ባለመቻሉ ሃሰተኛው የአገዛዙ ፕሮፓጋንዳ አግጥጦ መውጣቱ እንዲሁም የሃገሪቱ ኢኮኖሚ ወደ ኋላ ማደጉ በተጨማሪም ሕዝብን ለማጭበርበር አገዛዙ የሚጠቀመው የቁጥር ቁልል ከፍተኛ አደጋ በሕዝብ ላይ እያደረሰ መሆኑ በተደጋጋሚ እየታይ ከመሆኑም በላይ ከ2.5 ሚሊዮን ውደ 8.2 ሚሊዮን ያደገው የረሃብተኛው ቁጥር እንዲሁም በተከታታይ እየሞቱ የሚገኙት እንሰሳት ቁጥር መጨመሩ ሕዝቡ ቀየውን እየለቀቅ ወደ ከተማ መጉረፉ አገዛዙ የሚከተለው ፖሊሲ ሕዝብን እየጎዳ መሆኑን ማረጋገጫ ነው::

Minilik Salsawi's photo.