ፍትሕን ማግኘት የምንችለው ስርዓቱን ታግለን ስናፈርስ ብቻ ነው።

ፍትሕን ማግኘት የምንችለው ስርዓቱን ታግለን ስናፈርስ ብቻ ነው።
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Justice‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎EthiopianOppositionparties‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በዛሬው እለት የወያኔው ፍርድ ቤት ቀርበው የነበሩት እነብርሃኑ ተክለያሬድን በተመለከተ ከዳኛው በኩል ከስርዓቱ ገዢዎች የወረደው ውሳኔ “መከላከያ ምስክር ማሰማት የለባችሁም ስለዚህ ለፍርድ ብይን ሃምሌ ፩፫፣ ፪፻፰ ቅረቡ”መባሉ በተደጋጋሚ የምናየውን የፍትሕን መቀበር እያሳየን ነው።ይህ ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ኣዲስ ባይሆንም የሕግ የበላይነት አለመከበሩን ካወቅን ስርዓቱ ፈርሶ የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ወገባችንን አጥብቀን እንታገል፥ ፍትህ ካለ ሰላም አለ::ፍትህ ካለ እድገት አለ:;ፍትህ ካለ እስር ቤቶች በንጹሃን አይሞሉም:: ፍትህ ካለ ነጻነት እና መብት አለ:; ፍትህ ካለ የሚሸማቀቅ አይኖርም::ፍትህ ከተረጋገጠ ሕጎች ሁሉ በበላይነት የሕዝብ ይሆናሉ::ይህ ሁሉ የሚረጋገጠው በኛ ለኛ ከኛ ነው::እኛ አዎ እኛ በአሁን ወቅት እና ጊዜ ላይ ቆም ብለን ካሰብን የሚያስፈልገን ነገር ቢኖር በራሳችን ትግል ነጻነታችንን እና መብቶቻችንን ታግለን ማረጋግጥ እንዲሁም አምባገነኖችን ላንዴና ላያዳግም መደምሰስ ነው::

በኢትዮጵያችን የሰብ አዊ መብት ጥሰት የመብቶችና የነጻነቶእ ገፈፋ የፍትህ ድንቁርና መንሰራፋቱን እናውቃለን ደጋግመን ብናወራው ለቀባሪው ጆሮ ፍሰት መፍጠር ካልሆነ በስተቀር ምንም አይፈይድም የሚፈይድልን ነገር ቢኖር እነዚህን እኩይ ተግባራት ታግለን በማስወገድ የሕግ የበላይነትን እና የራሳችንን ነጻነት እና መብት ማስከበር ነው:: አሁን ማወቅ ያለብን ይህንን ብቻ ነው::ፍትህ ፈላጊ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እስከፈለግን ድረስ ማንም ሰው ወይም አካል ከህግ በላይ ሊሆን አይችልም:: ህገ ወጥነትን መታገስም በራሱ ወንጀልን ማበረታታት ነው:: ስለዚህ የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ የማድረገ ትግላችን ተጠናክሮ መቀጠል አለበት:;ለሕግ የበላይነት የምናደርገው ትግል በተግባራዊ ስራዎች እና ግንዛቤን ከበፊቱ በበለጠ በመፍጠር ሕዝባዊ ሰቆቃዎችን ለማስቀረት ታላቁን ስኬት ከግብ ለማድረስ ከጀመርነው ጉዞ ማፈግፈግ አያስፈልግም ::ሕዝቡ በሃገሪቱ ላይ የሚካሄደውን እና እየተካሄደ ያለውን የወያኔዎች አምባገነን አገዛዝ የፈጠረውን ጸረ ፍትህ አካሄድ አብጠርጥሮ ያውቃል ::ይህ ማለት ደሞ የለውጥ ሃይሎች የሚጠበቅባቸውን የለውጥ ስራዎች በመስራት ትግሉን ከግብ ለማድረስ አስፈላጊዉን የትግል መንገዶችን በመጠቀም ሕዝብን ከጎን በማሰለፍ ድሉን ማረጋገጥ ይጠበቅብናል::

በሃገራችን የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የምእራባውያንን አሳሳቢ በሚል የታጀበ መግለጫ አሊያም ድጋፍ መጠበቅ ለኛ ምንም አይፈይድም::እና ጠንክረን ከታገልን በአምባገነኖች ጫና ስር የወደቀውን ሕዝባችንን ነጻ ለማውጣት በምንገፋው ትግል ላይ የምናሳየው የትግል ታማኝነት እና ስኬት ምእራባውያንን ራሳቸውን ልንማርክ እና ሳንጠይቃቸው እርዳታውንን ለብሄራዊ ጥቅማቸው ሲሉ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ሳይታለም የተፈታ ነው:: ስለዚህ እኛ ራሳችን በጋራ ሆነን ይህንን አምባገነን ስርአት ለመጣል ወደፊት መገስገስ ያለብን እኛው በኛ ሲሆን የሕግ የበላይነት አለመከበሩን ካወቅን የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ወገባችንን አጥብቀን እንታገል::ፍትሕን ማግኘት የምንችለው ስርዓቱን ታግለን ስናፈርስ ብቻ ነው። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.

5 Comments on “ፍትሕን ማግኘት የምንችለው ስርዓቱን ታግለን ስናፈርስ ብቻ ነው።”

  1. ስርዓቱን ታግለን ማፍረስ ብቻ ቢሆንማ ቀላል ነበር። ኢህአዴግ ደርግን አስወግዶ ካፈረሰው በኋላ፣ የተሻለች ኢትዮጵያን እናያለን የሚል ዕምነት ነበር። ሆኖም የሆነውን እያየነው ነው። ኢህአዴግን ካስወገድን በኋላስ? ሁሉም ሮጦ የስልጣን ኮርቻዋ ላይ ቁጢጥ ማለት እንጅ፣ አሁን ቃል የሚገባውን ሲፈጽም ባለማየታችን፣ እንደገና ሰዶ ማሳደድ እንዳይሆንብን፣ ወደፊት ለምንመሰርተው መንግስት ምን የማሰሪያ ልጓም አበጅተንለት ነው ልንቆጣጠረው የምንችለው? የዚህን መላ ሳንዘይድ እየሮጥን ብንውል፣ ትርፉ ድካምና ኪሳራ ብሎም የሞላጮችና ያጭበርባሪዎች ሰለባ ሆነን እንደገና ማዬት አልሻም። ሲሮጡ ከመዋል ዋና ዋና የመዉጫና መግቢያ በሮች (አንገቶች) መያዝ ይባል የለ!
    እስከዚያው ግን ትግላችንን ከማቀላጠፉ ጎን ለጎን፣ “ከማያውቁት መልዐክ የሚያውቁት ሰይጣን ይሻላል” እንደሚባለው፣ በያለንበት ሆነን የተሻለውን ለመሾም በማሰብ፣ ኢህአዴግ እስከነ ጉድፉ ይቆይ እላለሁ። ምናልባት መቆሸሹን ተገንዝቦ ጽዳት የጀመረ እንደሆነ።
    ቸር ይግጠመን

  2. Mr. ሰማኸኝ! አስተያየትህ ቅንነት የተሞላበት ሳይሆን ወያኔን በሥልጣን ላይ እንዲቆይ የሚያደርግ ማበረታቻ ነው፡፡ 25 ዓመት ሙሉ ምን ለውጥ መጣ? ንገረን! ወያኔ ወርዶ ሌሎች ይምሩ፡፡ ይሞክሩት፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ ያንተ አባባል ወያኔ እያለ ያለውን ነው የደገምክልን! ተግባባን!?

  3. እንግሊዝ ለኢትዮጵያ እስር ቤት መገንቢያ 27000000 (ሃያ ሰባት ሚሊዪን ፓውንድ) ለመስጠት ዝግጅት ላይ መሆኖ ቶኒቢሌር አዲስ አበባ የመጣው ለጉብኝት ወይም ኢትዮጵያ ናፍቃው አይደለም ለተንኮል መምጣቱን ማወቅ አለብን!
    እስር ቤቱ የሚገነባው በአማራ ክልል ሲሆን ጥናቶች ተጠናቀዋል፡
    ደጉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*