የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት መሥሪያ ቤት የቀድሞ የአገር ውስጥ ደኅንነት ኃላፊ የነበሩት አቶ ወልደ ሥላሴ ወልደ ሚካኤል፣ በአሥር ዓመት ጽኑ እስራትና 50 ሺሕ ብር እንዲቀጡ ተወሰነባቸው

በከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰው የነበሩት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት መሥሪያ ቤት የቀድሞ የአገር ውስጥ ደኅንነት ኃላፊ የነበሩት አቶ ወልደ ሥላሴ ወልደ ሚካኤል፣ በአሥር ዓመት ጽኑ እስራትና 50 ሺሕ ብር እንዲቀጡ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 15ኛ ወንጀል ችሎት ግንቦት 9 ቀን 2008 ዓ.ም. ውሳኔ ሰጠ፡፡

ከኃላፊው ጋር ተከሰው የነበሩት ወንድማቸው አቶ ዘርዓይ ወልደ ሚካኤል አራት ዓመት ጽኑ እስራትና 20 ሺሕ ብር እንዲቀጡ የተወሰነ ሲሆን፣ እህታቸው ወ/ሪት ትርሀስ ወልደ ሚካኤል ሦስት ዓመት ከሦስት ወራት ጽኑ እስራትና በ10 ሺሕ ብር እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ ያቀረበውን 11 ክሶች ሲመረምር የከረመው ፍርድ ቤቱ፣ ሚያዝያ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. በዋለው ችሎት አቶ ወልደ ሥላሴን በሰባት ክሶች፣ አቶ ዘርዓይን በሁለት ክሶችና ወ/ሪት ትርሀስን በአንድ ክስ ጥፋተኛ ማለቱ ይታወሳል፡፡

አቶ ወልደ ሥላሴ ጥፋተኛ የተባሉት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት መሥሪያ ቤት ዋና መምርያ የአገር ውስጥ ደኅንነት ኃላፊ ሆነው ሲሠሩ፣ ሥልጣናቸውን ያላግባብ በመጠቀም ‹‹Terrorism in Ethiopia and the Horn of Africa›› የሚል መጽሐፍ ማሳተማቸውን ፍርድ ቤቱ በቅጣቱ ላይ ጠቁሟል፡፡ በመሆኑም በመሥሪያ ቤታቸው ውስጥ ያላቸው ኃላፊነት ማማከር ሆኖ እያለ ከዚህ ውጪ የማማከር ኃላፊነታቸውን ያላግባብ በመገልገል፣ የመሥሪያ ቤቱን የሰው ኃይል ሠራተኛ መጽሐፋቸውን ለማሳተም የስፖንሰር ትብብር እንዲደረግላቸው የትብብር ደብዳቤ ማጻፋቸውን በቅጣት ውሳኔው ተገልጿል፡፡ በተጻፈው የትብብር ደብዳቤ አማካይነት በወቅቱ የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ዋና ሥራ አስኪያጅ ለነበሩት አቶ በየነ ገብረ መስቀል መጽሐፉ በግላቸው እንዲታተም መሥሪያ ቤታቸው መስማማቱን ገልጸውላቸው መጽሐፉ እንዲታተምላቸው በማድረግ፣ 600 ሺሕ ብር ሕገወጥ ገቢ በማግኘታቸው ጥፋተኛ መባላቸው ተገልጿል፡፡

አቶ ወልደ ሥላሴ ሌላው ጥፋተኛ የተባሉበት ወንጀል ወይዘሮ ግርማነሽ ይኩኖ አምላከ ወይም ሩት የተባሉ ግለሰብ፣ ለግል ጉዳያቸው ሲንቀሳቀሱ የመሥሪያ ቤቱን መኪና ነዳጅ እየሞሉና የመሥሪያ ቤቱን ሾፌር አገልግሎት እንዲሰጥ በማድረጋቸው ነው፡፡ ግለሰቧ በፍርድ ቤት የነበራቸውን ጉዳይ የመሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች እንዲያስፈጽሙ ማድረጋቸውንም ጠቁሟል፡፡ አቶ ወልደ ሥላሴ ለሚሠሩት ቤት የጣሊያን ሴራሚክ እንዲገዙላቸው ታዋቂውን ነጋዴ አቶ ሳቢር አርጋውን በማዘዝ፣ የ65 ሺሕ ብር ሴራሚክ አስገዝተዋል ተብለው ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡ አቶ ወልደ ሥላሴ ከ2001 ዓ.ም. እስከ 2005 ዓ.ም. ድረስ ያሳተሙትን መጽሐፍ የሸጡ ቢሆንም፣ ለግብር ሰብሳቢው መሥሪያ ቤት አሳውቀው መክፈል የነበረባቸውን 496,159 ብር የትርፍ ገቢ ግብር ባለመክፈላቸውም ጥፋተኛ መባላቸውን የቅጣት ውሳኔው በችሎት ሲነገር ተጠቅሷል፡፡ ከግንቦት ወር 2005 ዓ.ም. ጀምሮ ካገኙት የኪራይ ገቢ መክፈል የነበረባቸውን ተርን ኦቨር ታክስ ባለመክፈላቸውም ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡

አቶ ወልደ ሥላሴ ሦስት ክሶች ተጣምረው ጥፋተኛ ያሰኟቸው ሥልጣናቸውን ያላግባብ በመጠቀም መጽሐፍ በማሳተም ከሽያጩ 600 ሺሕ ብር በማግኘታቸው፣ የ65 ሺሕ ብር ሴራሚክ በማስገዛት የማይገባ ጥቅም በማግኘታቸው፣ 496,159 ብር ግብር ባለመክፈላቸው፣ ከኪራይ ገቢ ካገኙት ተርን ኦቨር ታክስ ባለመክፈላቸውና ከተጠቀሱት ወንጀሎች ያገኙትን ገንዘብ ከሕጋዊ ገንዘባቸው ጋር በመቀላቀል በባንክ የዝውውር ምኅዋር ውስጥ እንዲገባ በማድረግ ተጨማሪ ጥቅም ላይ በማዋላቸው መሆኑን፣ የቅጣት ውሳኔው በዝርዝር ያስረዳል፡፡

አቶ ዘርዓይ ጥፋተኛ የተባሉት በሁለት ክሶች ሲሆን፣ ከ2005 ዓ.ም. በኋላ ከቤት ኪራይ (የአቶ ወልደ ሥላሴን ቤት በማከራየት) ከተገኘ ገቢ ላይ ተርን ኦቨር ታክስ አሳውቀው ባለመክፈላቸውና ከአቶ ወልደ ሥላሴ ሙሉ ውክልና ከተቀበሉ በኋላ ከእሳቸው ሒሳብ ላይ 700 ሺሕ ብር ወደ ራሳቸው ሒሳብ እንዲተላለፍ በማድረግ፣ ገንዘቡ በተለያዩ ባንኮች እንዲንቀሳቀስ በማድረግ፣ ገንዘቡ የተገኘበትን ሕገወጥ ምንጭ ለመደበቅ ተሳትፈዋል በማለት መሆኑን ፍርድ ቤቱ ገልጿል፡፡

ወ/ሪት ትርሀስ ደግሞ ጥፋተኛ የተባሉት ከአቶ ወልደ ሥላሴ ጋር የብድር ውል በማዘጋጀት 350 ሺሕ ብር በማስተላለፍና ከሜጋ አሳታሚና ማከፋፈያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በሁለት ቼኮች ለአቶ ወልደ ሥላሴ የተጻፈን 399,920 ብር ለእሳቸው እንዲከፈል በማድረጋቸው ነው፡፡ አቶ ወልደ ሥላሴ በወንጀል ያገኙትን ገንዘብ ከራሳቸው ሕጋዊ ገንዘብ ጋር በመቀላቀል ለመርዳትና ገንዘቡ የተገኘበትን ሕገወጥ ምንጭ ለመደበቅ በመሳተፋቸው መሆኑ ፍርድ ቤቱ አብራርቷል፡፡

እንደ ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔ አገላለጽ፣ ሦስቱም ተከሳሾች የተጠቀሱባቸው የወንጀል ሕጐች በራሳቸው ከባድ በመሆናቸው፣ ዓቃቤ ሕግ ተፈጽሟል የተባለው የወንጀል ደረጃ ከፍተኛ እንዲሆን ያቀረበውን ጥያቄ አልተቀበለውም፡፡ የወንጀል ደረጃውንም ዝቅተኛ በማድረግ ተከሳሾቹ ያቀረቡትን ጥያቄ መቀበሉን ፍርድ ቤቱ አሳውቋል፡፡

የቅጣት ማቅለያን በሚመለከት አቶ ወልደ ሥላሴ ቀደም ባሉት ጊዜያት ምንም ዓይነት ወንጀል ስለመፈጸማቸው በዓቃቤ ሕግ በኩል የቀረበባቸው ማስረጃ ባለመቅረቡ የነበራቸው ባህሪ መልካም እንደሆነ ተደርጐ ስለሚታሰብ፣ እንደ አንድ የቅጣት ማቅለያ መያዙን ፍርድ ቤቱ ገልጿል፡፡ ከ1972 ዓ.ም. እስከ 1983 ዓ.ም. ሕወሓትን በመቀላቀል የደርግ ሥርዓትን ለመታገል በተደረገው ፍልሚያ ውስጥ በመሳተፍ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን፣ ከ1983 ዓ.ም. በኋላም በተለያዩ ኃላፊነቶች ለአገሪቱ ዕድገት አስተዋጽኦ ማድረጋቸውንና አራት መጻሕፍትን በማሳተም በተለይ የሽብርተኝነትን ጐጂነት ኅብረተሰቡ ማወቅ ስላለበት ነገር ከማሳወቃቸውም በላይ፣ በተለያዩ ጊዜያት ሥልጠና በመስጠት ከፍተኛ ተሳትፎ በማድረጋቸውም በሁለተኛ የቅጣት ማቅለያነት እንደተያዘላቸው ፍርድ ቤቱ ገልጿል፡፡

በሦስተኛ የቅጣት ማቅለያነት የተያዘላቸው የቤተሰብ አስተዳዳሪና ኃላፊ መሆናቸው በማስረጃ በማረጋገጣቸው መሆኑ ፍርድ ቤቱ ገልጿል፡፡ በመሆኑም አቶ ወልደ ሥላሴ ጥፋተኛ በተባሉባቸው ሰባት ክሶች የተጣለባቸው ቅጣት ሲደመር 31 ዓመት እስርና የገንዘብ መቀጮውም 79 ሺሕ ብር የነበረ ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ የእስራት ቅጣት ጣሪያ 25 ዓመት በመሆኑ፣ 31 ዓመታት የሆነው ቅጣት ወደ 25 ዓመት ዝቅ ተደርጐ በተያዘላቸው ሦስት የቅጣት ማቅለያ በእያንዳንዱ ሦስት እርከን፣ በድምሩ ዘጠኝ እርከን ተቀንሶላቸው አሥር ዓመት ጽኑ እስራት 50 ሺሕ ብር እንዲቀጡ በሙሉ ድምፅ መወሰኑን ፍርድ ቤቱ አስታውቋል፡፡

አቶ ዘርዓይ መልካም ባህሪ እንደነበራቸውና የቤተሰብ ኃላፊና አስተዳዳሪ መሆናቸው በመረጋገጡ፣ የሚጥል ሕመም እንዳለባቸው ማስረጃ በማቅረባቸውና ከ1976 ዓ.ም. ጀምሮ በሕወሓትና በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ በመሆን እስከ 1999 ዓ.ም. ድረስ ማገልገላቸው በማስረጃ በመረጋገጡ፣ አራት የቅጣት ማቅለያ ተይዞላቸውና እያንዳንዱ የቅጣት ማቅለያ ሦስት እርከን፣ በድምሩ 12 እርከን ተቀንሶላቸው፣ ለመነሻነት ከተያዘው 12 ዓመት እስርና 32 ሺሕ ብር የገንዘብ ቅጣት ተቀንሶላቸው፣ አራት ዓመት ጽኑ እስራትና 20,000 ብር እንዲቀጡ በሙሉ ድምፅ ውሳኔ መሰጠቱን ፍርድ ቤቱ ገልጿል፡፡

ወ/ሪት ትርሀስም ሁለት የቅጣት ማቅለያ ተይዞላቸው ለመነሻ ቅጣት ከተያዘው ዘጠኝ ዓመትና 30 ሺሕ ብር ቅጣት ተቀንሶላቸው፣ በሦስት ዓመት ከሦስት ወራት ጽኑ እስራትና 10 ሺሕ ብር እንዲቀጡ በሙሉ ድምፅ ውሳኔ መሰጠቱን ፍርድ ቤቱ በማስታወቅ መዝገቡን ዘግቷል፡፡ ከእነ አቶ ወልደ ሥላሴ ጋር ክስ ተመሥርቶባቸው እንዲከላከሉ ከተደረጉ በኋላ፣ በብቃት መከላከላቸው ተገልጾ በነፃ ስለተሰናበቱት የአቶ ወልደ ሥላሴ የቅርብ ጓደኛ መሆናቸው ስለሚነገረው አቶ ዶሪ ከበደ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

Reporter Amharic

4 Comments on “የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት መሥሪያ ቤት የቀድሞ የአገር ውስጥ ደኅንነት ኃላፊ የነበሩት አቶ ወልደ ሥላሴ ወልደ ሚካኤል፣ በአሥር ዓመት ጽኑ እስራትና 50 ሺሕ ብር እንዲቀጡ ተወሰነባቸው”

  1. can somebody tell me where they will keep this man …will it be with the usual prison population or does the weyane got a special prison for a its beloved cadres?

  2. Gedeffa Wako says:

    May 17, 2016 at 8:24 pm

    ንጉሡ ሞቱማ says:

    May 14, 2016 at 6:31 pm

    የዳግም አደዎ ዘመቻ
    ቁጥር 13 አሰቸኳይ መመሪያ
    +-+++++++++++++++
    ኢሐድግዬ(1000 ምርጥ ዘር አደዎዎች) ኢትዮጵያን ምን አይነት አገር እንደሆነች ሳያቋት፣ በአልበሽር ጠንቋዮች 17 አህያዎቹን ይዘው በጎርፍ ጋኔን ቤተ መንግስት ተሳካላቸው፣ ሕዝባችንንም በዘር ፓለቲካ እንደ አህያ እንዲያስብ አረጉት። ባንዲራችን ላይ በጋኔኑ አስገዳጅነት ለአለም የመጀመሪያው የጋኔን ምልክት ለውጥ በባንዲራ ላይ አርገው ሕዝባችንን የብሔር እኩልነት ብለው እንደ አህያ እንዶያስብ አረጉን። ኢትዮጵያ ከአለም በፊት 41 ጊዜ በላይ በመፃፍ ቅዲስ የከበረች እና ሂዱ እዛ ኑሩ የኣላ ሰላም አገር ብለው ነብዩ መሐመድ ያከበሯትን አላወቁ የሆን??? የአገራችን ህዝቦች አገራችን በየአቅጣጫው በረሀብ መከራ፣በስደት፣ተዋርደናል፣ታርደናል። ሰለዚህ እስከ መቼ ይህንን ሰቆቃ እየሰማን፣ እየደማን፣ እየተገደልን፣ እየተገለልን፣ ባህር እየወስደን፣ መሪር ሐዘን መቼ ነው በኦሮሚያ፣ በአማራ፣በትግራይ ፣ በሱማሌ፣በደቡብ፣ በጋምቤላ የሚቆመው ??? በመጀመሪያ ለሀያሉ አምላክ ሁሉም እንደእምነቱ ከልብ አምርረን ማልቀስ ያለንበት ወቅት ላይ ነን??? በችግር ለይ ችግር አሁን ብዙ ሺ ሕዝባችን በየቤቱ በጠኔ እያለቀብን ነው። ነገ ደግሞ በሚሊዮንዎች በረሐብ ሊያልቁብን ነው። ቀጥሎ በኃላፊነት ምን ለአገራቹ ስራቹ ተበሎ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የሚንጠየቅበት ደረጃ ላይ ደርሰናል። አዎ ከኢትዮጵያ አፈር ላይ መወለድ ፣ ኢሕአዴግ በዘር ከፋፍሎ የጨረሰን ለማከም በመተማመን ተራማጅ የአገር ውስጥ አሮሞ ኢትዮጵያዊያን የጋራ ጠላታችን ጋኔኗ ኢሕአዴግ ብቻ ነች ብለን ከሌሎች ወድ ኢትዮጵያዊያን ጋር የዱሮ ፈቅራችንን መልሰን በጋራ በማንዴላን ራዕይ የዘርን ፓለቲካ እጥፈተን እንድ ኢትዮጵያ ብለን ወደ ዋናው መንገድ ለመሰዋትነት ተዘጋጅተናል። አንዳንድ ሆዳም ኦሮሞዎች በተለያዩ ጊዜያት የራሳችንን ህዝብ አሰፈጅተዎል። በአንፃሩም እንዲሁም በአማራ፣ትግራይ ወዘተ አስፈጅተውናል። 1000 አደዎዎቹ አፉን አፍነው ሌላውን የትግራይ ህዝብ የከፋ የመረረ በደል አድርሰውበታል። አሁን ደግሞ ጥላሽት የተቀባውን የመጨረሻውን ግንቦት 20 ሊያከብሩት ነው። ጠ/ሚሩ ህዝቡ ነቅቷል በቃ ይህንን አንብበው እያላቹ ሳቅ እያፈነኝ ነው፣ አናንተ እየሰማችሁ “ስጥ” እንግዴ ትሉኛላቹ እናንተ ምን ቸገራችሁ ቆዳዬን ይጭነቀው እንጂ አሉ። በ25 አመት ውስጥ ከ10ኘ ክፍል ተስፋ ቢስ አርጎ ያባረራቸው ወጣቶች ፈክሻውን እየጠበቁ ነው።
    1ኛ፣ የኢሕአዴግ ስላዬቸ እና ጦሩን አብዛኛውን ሰለ ስራ አስመስለው ለወገኖቻችው እና ለአገራቸው ሲሉ እንዲስሩ ታዘዎል።
    2ኛ የኢህአዲግ አባላት ዝርዝር ፣ የኤፈርት በአለም ዙሪያ የለው ዝርዝር በእጃችን ገብቷል። በእስር ቤት ውስጥ ወገንን እያሰቃዬ ያሉት ስም ዝርዝር ደርሶናል። አፈቀላጤ ጌታቸው ረዳ መሽገህ ኢሳትን የምትሰማበት ቦታ ላይ ከጀርባህ ከች እንላለን።
    3ኛ ሕዝባችን ማንኛውም ንብረት ጊዜ ውል እንዳይገባ። ባንኮች ተገዳጁ የምታረጉትን መረጃ ያዙ ዘራፊዎችን ከገቡበት ገብተን ነገ ኢትዮጵያዊ ለፍርድ ያቀርባችኃል። የኢትዮጵያ እዳ በጤፍ ቁጥር ነው።
    4ኛ ኢትዮጵያ የምትፈልገው በእኩል የሚያስዳድር መሪ ብቻ ነው። ሕዝባችን ለሽግግር ለውጥ ተዘጋጁ ተራማጅ መረዎቻችን ደ/ር ብርሀኑ፣ ጄ/ር ከማል እንዲሁም አቶ ኦባንግ ለህዝባችን የቅድመ ሸግግር ሥርአት መረጃውን በኢሳት ላይ አገሪቷን ወዲያውኑ የሚረከበው ሃይል አስቸኳይ መረጃ ለህዝባችን ይተላለፈል።ጉዞ ወደ ፈት ከተረማጆች ኢትዮጵያዊያን ጋር።
    ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ከ እግዚአብሔር እርዳታ ጋር። ንጉሡ ሞቱማ ኦ.ማ.

    [Reply]

    Reply

    Geday Hagos says:

    May 14, 2016 at 6:34 pm

    We proud of u connected all Ethiopians together. We are united now more than anytime.
    Viva Negussu.
    All trash Adowas play game on
    Tigrians.

    [Reply]

    Reply

    Bertukan says:

    May 14, 2016 at 6:43 pm

    We need such progressive united view on 21st century.
    Thank you Negussu for you come in from Oromoia such great impressive connection under one Ethiopian. Great man and Great postive mind.

    [Reply]

    Reply

    Sammy P says:

    May 15, 2016 at 12:31 am

    Ethiopia is the “least” reported country in
    Africa compare to south Africa , Nigeria , Kenya ,
    Egypt , Angola , Zambia , Burkna Faso , Uganda and
    Ivory cost . Its not a bad record in respect .

    [Reply]

    Reply

    G,Michael H says:

    May 15, 2016 at 12:38 am

    My brother Sammy thank you for your comment
    you are absolutely right Ethiopia’s rank is
    much better than any country in the world .
    Ours is very insignificant .

    [Reply]

    Reply

    መርጋ ኃይሌ says:

    May 15, 2016 at 1:17 am

    ሆዳምቹ በግለሰብ ኪስ ሲምላ ዝም በሉ ኢትዮጵያ እየለማች አየአደገች ነው ይላሉ ግን በየአመቱ 3 ነጥብ 5 ቢሊየን በእርዳታ እና በብድር ወደ አገር ይገባል። የአንድ አመት ብቻ መንገድ ሰርቶ አባይን ገድቦ ይጨርሳል። የ24አመቱ ሆዳምቹ ኪስ ይገባል እንደተባለው ማስረጃው ተገኝቷል ሂሳቡ ይሰራል በነፃነት ቀን ላይ ሩቅ አይደለም።
    ያንን ሁሉ የቻይና እንደ ጤፍ ያለውን እዳ ማነው የሚከፈለው?????????

    [Reply]

    Reply

    siraj says:

    May 15, 2016 at 3:33 am

    @ngusu motuma you are not ngusu motuma you are the ortodox yetenkay zer.oromia is for oromo.yedebtera zer.viva oromia.

    [Reply]

    Reply

    Gedeffa Wako says:

    May 15, 2016 at 4:34 am

    Great Negussu bright mind works for all except 1000 Adowas.

    [Reply]

    Reply

    Tolla says:

    May 15, 2016 at 9:00 am

    oROMO BILO POLITICA AWRI .
    DENGAY IRASOCH . iNANTE INA
    WAHBBIST YEMETAWKUT SEAT MEBDAT
    BICH NEAW . AFER BILU

    [Reply]

    Reply

    Alo shokie says:

    May 15, 2016 at 9:27 am

    Siraj is tefa gmat gebreb ke eritrea
    yih luTi abatu gebreb orthodox new.
    Kdo woim selmo new orthodox misadeb.
    Lenegeru be qiTu sibeda hulemenaw zurobet new

    [Reply]

    Reply

    ገላን ወርዶፋ says:

    May 15, 2016 at 12:31 pm

    አሮሞ ማለት ምን አይነት ቀጥተኛ ትውልድ የሆነ ካመረረ የማይመለስ ፍቅርን ሰጥቶ መቀበል የሚችል ነው። ከላይ ቶላ እና ሲራጅ የሚባሉ የሚፅፍት ነገር ምን የህል ከገማ ጭንቅላት እና ሆዳምነት የወጣ ነው። ዳሩ ግን ሊታረድ መጨረሻ ሰአት ላይ የደረሰ
    ዶሮ ብዙ ይጮሃል ይባላል። ጉድ ነው ዘንደሮ የኦሮሞ ልጆች ከሌሎቹ ውድ ኢትዮጵያአዊ ጋር እትብታችን ይፈረደን። ከፈፈሎ በዘር መግዛት አበቃ። ሁላችንም ኢትዮጵያዊ ህብራችን ነው አስከ መጨረሻው ትውልድ ደረስ። ከእናንተ ጭንቅላት የላቀ ምላጭ የሆኑ በየአቅጣጫው በተጠንቀቅ በየከፍለሀገሩ ይገኛሉ። ጎበዝ ጀግና የአምቦ ውድ ኮራችን በኢትዮጵያውያን የሚኮራ አደረጃጀት ተከትሎ ነው። ወደ ኋላ መየት የለም በጅግኖቹ ወድ መሪዎቻችን ደ/ር ብርሀኑ፣ ጀኔራል ከማል፣ ወድ የትግራይ ነፃ አውጪ ታጋዬች አገር ውስጥ ካለው 30 ሚሊዮን ወጣት ኃይል ጋር ወደፈት ብለናል።
    ሞኛቹን ፈልጐ ከፋፍሎ በዘር መግዛት አበቃ፣ አሮም አንዱ ንፁህ ኢትዮጵያዊ ነው።

    [Reply]

    Reply

    አህመድ መኑር says:

    May 15, 2016 at 1:55 pm

    መልስ ለሲራጅ

    ኦሮቶዶክስ ሐይማኖት ከኢትዮጵያ ታረክ እና ፈደል ባለወረለታነች። ነብዪ መሐመድ እኮ አላ አስመልክቶአቸው እኮ በኦርቶዶክስ ደንብ በሚመሩት ንጉስ ነጋሢ ዘመን ነው። ሂዱ እዛ
    ኑሩ ብለው መልእክተኛ የላኩት ና መልክተኞቹም ነብዪ ያሉትን ቃል እውነት መሆኑን አረጋገጡ። ዛሬ ዛሬ ኦርቶዶክሱንም በተሐድሶ ስም እነ ታምራት ላይኔ አመሱት።
    ኦርቶዶክስ ሐይማኖት ለኢትዮጵያ እስለምና ተከታዮች ጌጣቸው ነች በሷ የመጣብንን አንምርም እኛም እነሱም በፍቅር አይነ አንድ ነን።

    [Reply]

    Reply

    ፈጤ ከድር says:

    May 15, 2016 at 3:24 pm

    እንወደሀለን አህመድ ሙስሊሙን ሕዝባችን ለ ኦርቶዶክሱ በመግለፀህ።

    [Reply]

    Reply

    ገብሩ ግርማይ says:

    May 15, 2016 at 4:22 pm

    ወንድም እና እህት ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ሁላቹንም በፍቅር እንወዳቹሀለን። በኢትዮጵያ ጥላ ስር ነው ያለነው በኢትዮጵያችን ቀልድ የለም። ጋኔኖቹንም እስከ መጨረሻው ጠራርገን እናጥባቸዋለን።

    [Reply]

    Reply

    Abay says:

    May 15, 2016 at 6:45 pm

    All of woyanes will be under arrest soon because They are thieves, killer and mafias. Do not expect good things from those canibalse.

    [Reply]

    Reply

    ሞላ አስግዶም says:

    May 15, 2016 at 8:49 pm

    ማፈሪያው ጌታቸው ረዳ ጦርነቱም እና ጎርፉ ከሻቦያ የተላከ ነው አልክ። ሌባ ነህ ሆሌ መሸገህ ኢሳትን የምታዳምጥበትን ሁሉ የነፀ አውጪዎች ጎርፍ ትንሽ ቀን እየጠበቀ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ጉዳን በቅርብ ቀን ይወራችኃል። የኢትዮጵያ ህዝብ አንጥሮ አውቋል የሻዕቢያ መንግስት ከወያኔ ይልቅ በተግባር እንደሚጨነቅ አሰወቋል። 90 ሚሊዬን ኢትዮጵያዊ 1000 አደዋ ሻርሙጦች 100% ይቻላል። ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!!!!!!!!!!!

    [Reply]

    Reply

    Eyasu says:

    May 15, 2016 at 11:09 pm

    Tilik sew!!Endihem aynet sew ale leka… yante aynet zega new tesfaChen yanureh.

    [Reply]

    Reply

    Eyasu says:

    May 15, 2016 at 11:16 pm

    Ahmed Menur,

    Tilik sew!!Endihem aynet sew ale leka… yante aynet zega new tesfaChen yanureh.

    [Reply]

    Reply

    ሳ.አ says:

    May 16, 2016 at 2:31 am

    ለምን መጡና ነው ዛሬ ታላቆን ኢትዮጵያ ሕልውና አደጋ ላይ ጥለው ገንዘብ፣ሃብት ባሃብት ሆነው ጉበቱ በእጃቸው የድንበር መሬት ለሱዳን ካሳ መስጠታቸው ጎንደርን መሬት የትግራይ ሕዝብ ነው አይደለምን!

    [Reply]

    [Reply]

    Reply

    Abay says:

    May 17, 2016 at 9:38 pm

    Don’t expect good things from devil. TPLF means simply a collection of mad , canibalse , killers and mafia groups. The only solution to avoid this cancer from our motherland Ethiopia , we have to stand together

    [Reply]

    Reply

    kiddi kuddi says:

    May 18, 2016 at 2:10 am

    zeraf……..zeraf

    [Reply]

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*