የኦሕዴድና የብአዴን አባላት ራሳቸውን ነጻ የሚያወጡበት ግዜ ላይ መሆናቸውን ሊገነዘቡ ይገባል:ነገን አትፍሩት!

የኦሕዴድና የብአዴን አባላት ራሳቸውን ነጻ የሚያወጡበት ግዜ ላይ መሆናቸውን ሊገነዘቡ ይገባል:ነገን አትፍሩት!
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎TPLF‬ ‪#‎ANDM‬ ‪#‎OPDO‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Freedom‬ ‪#‎Change‬

Minilik Salsawi – Ethiopian DJ – የኦሕዴድ ይሁን የብአዴን አባላት በባርነት ውስጥ መሆናቸው እሙን ነው:;ሃሳባቸውን በነጻነት መግለጽ አይችሉም ወክለነዋል ስለሚሉት ሕዝብም መናገር አይደለም መተንፈስ አይችሉም::ይልቅ በሙስና ውስጥ ተዘፍቀው ነገን እንዲፈሩ ሕወሓት ጢባጢቤ እየተጫወተባቸው ነው::አገሩ አየሩ አፈሩ መንደሩ ሕዝቡ ለውጥ ለውጥ እየሸተተ ያለበት ብሩህ ዘመን ላይ ደርሰናል ስለዚህ የብኣዴን እና የኦሕዴድ ካድሬዎች የሕዝቡን ንቃተ ሕሊና ሊጋሩ ይገባል:: እስከመቼ ድረስ የሕወሓት መጠቀሚያ ሆናቹ ከሕዝብ ተጣልታችሁ ትኖራላችሁ::መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሃገር ቤት ይሁን በውጪ ያለው በሕወሓት ላይ ከንፈሩን ነክሷል::ትግሉን አቀጣጥሏል::ራሳችሁን መርምሩ ሕዝብን አሊያም ውድቀትን መምረጥ የናንተ ድርሻ ነው::ሕዝብ ያነቃነቀውን ካልነቀለ ወደ ቤቱ አይገባም!!!

የቀድሞውን ወታደራዊ ስርኣት ለመጣል የአሁኑን የሽምቅ ሽብራዊ መንግስት ለማንገስ በበረሃ ትግል የተሳተፉት የኢሕኣዴግ ድርጅቶች በሃገሪቱ የትግል ታሪክ ውስጥ ጉልህ ድርሻ አላቸው::በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ስራትን ለማስፈን እጅ ለእጅ ተያይዘን በጋራ ታግለን ህዝባዊ ነጻነትን እናረጋግጣለን በማለት ጫካ የተደባለቁት ድርጅቶች የትግራይን ህዝብ ነጻ በማውጣት ታላቋን ትግራይን እፈጥራለሁ ያለውን ሕወሓት የትግሉ ስኬት ሲከሽፍበት ኢሕዴንን እና ኦሆዴድን በመንተራስ ተረማምዶ ለስልጣን ከበቃ 25 ድፍን አመታትን አስቆጠረ::

በ25 አመት የስልጣን ቆይታው የኢሕዴንን እና የኦሕዴድን የትግል አስታውጾ ላማኮላሸት እና ከታሪክ ሂደት መስመር ለማሳት የተጠቀመባቸው ዘዴዎች እና ወታደራዊውን እና የደህንነቱን ተቋም በአንድ ብሄር በማጠር አባል ድርጅቶቹ እና አባላቱ መላወሻ እንዲያጡ ሲሰራ በአደባባይ ታይቷል::ከአቶ ታምራት ላይኔ የፖለቲካ ጠለፋ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ቁጥራቸው ይህ ነው የማይባሉ የኢሕዴን ታጋዮች እና ካድሬዎች በተለያዩ የወንጀል ልጣፎች ከያሉበት ተጠልፈው ወደ ሞት እስር እና ስደት ተግዘዋል:: የኦህዼድ አባላትንም እንዲሁ በመጥለፍ በፖለቲካዊ የኦነግ ታርጋ በማሰር በመግደል እና በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች በማሸት አንደበታቸውን አሽጎታል:: ይህ የሕወሓት ስራ ማንም የሚያውቀው እና ጸሃይ የሞቀው ሃቅ ነው:: ቢተነተን የማያልቀው የሕወሓት የውስጥ እና የውጭ ሽብር የሚጋለጥበት ቀን መድረሱ የብኣዴን እና የኦህዴድ አባላት ተግተው በመስራት ላይ መሆናቸውን ሌሎችንም ካድሬዎች እንዲንቀሳቀሱ አድርጓል::

በገዛ ሃገራቸው በድርቅ እና በረሃብ እያለቁ እየተሰደዱ እየተገደሉ ጥያቄያቸው አልሰማ ያሉት የኦሮሞ እና የአማራ ህዝቦች ኦሕዴድ እና ብአዴንን የመሰለ አሳፋሪ ድርጅት በታሪካቸው ተጋርጠውባቸው አሊያም ባንዳ ሆነው አስፈጅተዋቸው አያውቁም። በጣሊያን ወረራ ጊዜ ለቅኝ ገዢዎች ያደሩ ባንዶች እንኳን ከዛሬዎቹ ኦሕዴዾችና ብአዴኖች የተሻለ ክብር ነበራቸው። ከዛሬዎቹም በተሻለ የድሮ ባንዶች በጌቶቻቸው ጣሊያኖች የሚሉት ይደመጥ ነበር። ኦሕዴድ እና ብአዴን ግን ራሳቸውን ከባንዳነትም አውርደው ባርነት ደረጃ ላይ የጣሉ ከመሆንም አልፎ ባሪያ ሆነው ተለጎመው በመነዳታቸው የሚደሰቱ ሆዳም ሰዎችን የሰበሰቡ ድርጅቶች ናቸው። ኦሕደዽ እና ብአዴን አለቃቸው ሕወሓት ያዘዘውን በመፈጸም የሚረኩ ጥርቅሞች ናቸው። አጉርሱኝ ሲላቸው ያጎርሳሉ፤ጉረሱ ሲላቸው በደስታና በችኮላ ተስገብግበው ይጎርሳሉ።

የብኣዴን እና የኦህዴድ አመራሮች እና ካድሬዎቻቸው ራሳቸውን ከሕወሓት የበላይነት የማላቀቅ ግዴታ አለባቸው::የሕወሓት የበላይነት ከምን የመጣ ነው? ትግል ከሆነ ሁሉን እኩል ድርሻ ያለውን ትግል በጋር ታግለው ነው ወታደራዊውን ስርኣት ያስወገዱት ለሕወሓት ብቻ ማን ይህን እድል ሰጠው? ሕወሓት ብቻውን አልታገለም ብኣዴንም የራሱ ድርሻ ኦሕዴድም የራሱ ድርሻ አለው:; የአማራውና የኦሮሞው ህዝብ ኢሕዴን/ብኣዴንን አይተው ኦሕዴድን አይተው እንጂ ለሕወሓት ሲሉ የእትዮጵያን መሬት በመምራት አልተባበሩም ስለዚህ የብኣዴን እና የኦሕዴድ አመራሮች እና ካድሬዎች ሊገነዘቡት የሚገባው ጉዳይ ትግሉ ሕወሓት ብቻ የመራው ያደራጀው ያሸነፈው አለመሆን እና የድርጅቶቹም ድርሻ እኩል መሆኑን ነው::

በመከላከያው እና በደህንነቱ ዘርፍ ከፍተኛውን ቦታ በመቆጣጠር ሌላውን የእንጀራ ልጅ ያደረጉት ሕወሓቶች የበረሃውን ዳገት እና ቁልቁለት እነሱ ብቻ የተወጡት አድርገው በማቅረብ የቀሪውን ታጋይ ደም እና ድካም ጥላሸት እየቀቡት ነው::የሕወሓት የበላይነት እንዲያበቃ በመከላከያው እና በደህንነት ተቋማት ውስጥ ያሉ የብኣዴን እና የኦሕዴድ ታጋዮች የራሳቸውን አስታውጾ ሊያበረክቱ ይገባል::የትግራይ ሕዝብንም እንደ አረና ካሉ ፓርቲዎች ጋር በመተባበር ከሕወሓት ጫና እና አፈና ልታላቅቁት ይገባል::የፖለቲካ ባርነት እንዲቆም ትግሉን የማቀጣጠል ሃላፊነት አለባቸው:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.

11 Comments on “የኦሕዴድና የብአዴን አባላት ራሳቸውን ነጻ የሚያወጡበት ግዜ ላይ መሆናቸውን ሊገነዘቡ ይገባል:ነገን አትፍሩት!”

  1. Ye etiopia wetader dergn godahu blo alwagam eyale letgrai woyanie ej seTe, beno qere, agerm tegoda.
    Esepa fezo denzzo zemenawi tTq taTqo woyanien medemses sichl zm blo ej seTe, tewardo qere.
    Ya ahun be badn ena be ohdd medegem yelebetm.
    Chgrachin tgrai woyanie new.
    Ye ager andnet eyenade, hzbn ers berasu eyablala new.
    Yhn makshef tchilalachuh. Mejemeriya tgrai woyanien bemedemsesu sra tesemaru, keziya ke teqawami ke melaw ethiopiawiyan gar hunachuh andit ye ekulnet demokratic etiopian le memesret tagelu.
    Selamuan meTebeq be enante lay wedqual.
    Haileslasie siwedq derg mehal gebto neber selamn yaregaga, selam yeTebeqe.
    Hzbu ers bersu alteblalam.
    Ahun yenante tera new.
    Tgrai woyanie ager eyaferares, hzbu ers bersu endiblala eyesera new.
    Bemehonum mejemeriya yechigru mnci woyanie slehone ydemses.

  2. ወያነ እኮ አገልጋይ ባሪያ ሲመርጥ ሕሊና የሌለውን መርጦ ነው የሚያቀምጠው።ኦህደድም ሆነ ባደን ሕሊና የሌለው የከብትና የሆዳም አሳማ ጥርቅም ነው።ጊዚያችሁን አታጥፉ።መጀምሪያ መደምሰስ ያለባችርው ሆዳሞቹ ናቸው።ኦህዲድ እንኳን ከባደን በብዙ ነገር ተሽሎ ተግርኝቷል።እስቲ ባደንን ተመልከቱይ በወልቃይት ጥያወ ላይ አቋም መውሰድ ፈርቶ በፍርሃት ቆፈን እየቀዘነ ነው።

  3. እውን ብአዴን ነጻ ድርጅት ነው፤
    ብአዴን ስሙን ከኢህዴንነት ማለት ሐገራዊ ድርጅትነት ወደ ጎጥ ድርጅትነት ከቀየሩበት ጊዜ አንስቶ ህልውና እንዳለው ድርጅት፣ በራሱ ሳምባ የሚተነፍስበት ማክተሙን ካሳወቀ ቆዬትየት አለ እኮ።
    በርከት ያሉ የኢህዴን ታጋዮች፣ ሕወሓት የሌለውን ጸባይ ትምህርት እያገኘ፤ ከህዝቡ ጋር እየተዋሃደ ሲሄድ ወደ ልቡ ይመለሳል ብለው በማሰብና እውነተኞቹን የሕወሓት ታጋዮችን የልብ ራስን አሳልፎ የመስጠት ሁኔታዎች በማዬት እንዲህ እንዳሁኑ በወረበሎቹ እጅ እንወድቃለን ብለው ሳያስቡ በሆደ ሰፊነትና በመቻቻል ብዙ በደሎችን ይቅር እያሉ እንደመጡ በውስጥም በውጭ ያለው ወገን አሳምሮ የሚያውቀው ነው።
    ታዲያ፣ ያ ሁሉ ተረስቶ እነርሱም ከጥቅሙ ተካፋይ በመሆናቸው፤ ቤተሰብ ተመስርቶ ካሁን በኋላ ሌላ ትግል ይቻላል ወይ በሚልና ወዘተ… ምክንያቶች ነገሩን ችላ ካሉት ቆይተዋል።
    ይሁን እንጂ ሐገር እንደዚህ እየሆነች ዝምታ፣ በኃላፊነት የሚያስጠይቃችሁ ብቻ ሳይሆን፣ ሃገራዊና ሞራላዊ ግዴታ እንዳለባችሁ መዘንጋት የለባችሁም።
    መንግስታት ያልፋሉ፣ አገርና ሕዝብ ግን ኗሪዎች ናቸው።
    ህወሓት፣ በእውነት በአሁኑ ሰዓት አይደለም ህዝብን የሚያታግል ድርጅት ለትግራይ ህዝብ የቆመ ሊሆን ይቅርና፣ ለሰብዓዊነት በጣም የራቀ ድርጅት በመሆኑ ራሳችሁን ከዚህ ቡድን ማራቅ ተገቢ መስሎ ይሰማኛል።
    ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ካስቀረበት ጊዜ አንስቶ ለኢትዮጵያ ጥቅሞች የማይቆም ድርጅት፣ እውን ይህ ኢትዮጵያዊ ፡ ትግራይ ስም መያዝ ይገባዋል?
    ዓላማው ኢትዮጵያን ለማጥፋት የተቀጠረ ጠላት መሆኑን ሁላችንም በመገንዘብ፣ የዘር መቋጠሩን ነገር እንተውና አገራችንን እናድን ወያኔን በማስወገድ።

  4. ተዎኝ ወንድሜ ኦሕዴድና ብአዴን የሚባል የለም አልነበረም የነበረውና ያለው ወያኔ፣ሻቢያ፣ሲ.አ.ኤ፣ሞሳድ ነው ያለው!
    ሰ.አ

  5. Atakileti Gebray says:

    March 11, 2016 at 7:07 am

    ንጉሡ ሞቱማ says: Wonderful Hero Negussu go a head we Tigray people behind you and proud to be fellow Ethiopian. they fullish us and making money. we know them…well. I am from Axum.

    March 11, 2016 at 6:09 am

    ዳግም አደዎ ዘመቻ አስቸኳይ ጥሪ!!!
    ነፃነት ወይም ባርነት!!!
    በቁመና መሞት ወይም በማእረግ ለኢትዮጵያ ብሩህ ቀን መሞት!!!
    ታህሣሥ 1 ቀን 2008 ዓ•ም•
    ••• መመረያ ቁጥር 4•••
    Are you ready for radical change for equal opportunity blessed land Ethiopia for all in the name of ” ADOWA victory again in coming soon!!!”
    ጥሪው ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው፣ሰሜን፣ደቡብ፣ምስራቅ አና ምዕራብ ፣ ኢትዮጵያዊ ማለት ማነው? ቅን ና እውነተኛ፣ሃይማኖተኛ/ፈረሃ እግዚአብሔር ያለው፣ጥበብን በልቡ ያሳደረ፣ ጠንካራ በአስተሳሰብ ጤነኛ ደፈር፣ ሃገር ወዳድ ጀግና አትንኩኝ ባይ፣ ሲጠቃ አሻፈረኝ ባይ ትውልድ አከባሪ ነው።
    1• ኢሕአዴግ ስልጣን የማስረከብ የተሰጠው ጊዜ ገደብ አበቃ። የተላኩት ጠ/ሚ ሀ/ማርያም እንደ እስስት ፓርላማቸው ላይ በጭንቀት ሌላ አሰመሰልው አጥፈተናል ብለው ተናዘዙ። የኢትዮጵያ ህዝብ ከአሁን በኋላ ሞኝ ነው። ወደኋላ የለም የሞቱ ት ሰዎች ቁንጫ አይደለሙ፣ በኦሮሚያ፣ በጉንደር፣በጋንቤላ፣በሱማሌ፣በአፈር፣ በትግራይ ክልል ከአደዎ ምርጥ 1000 ወርቃማ ባለስልጣቢች ቤተሰብ በስተቀር። በ25 አመት ውስጥ ሰንት መአት ሰው ጨርሳቸሃፀረ??? ከዚህ በኋላ በቃችሁ ሆዳም እሐዲግየ???
    2• ጥሪያችን ለሁሉም ኢሐዲግ ስራዊት እና ፓሊስ ውስጥ ገብቷል፣ ተደራጅተዋል ፣ በተጠንቀቅ ከአሁን በኋላ በሕዝባችን ላይ የሚተኩስ ከላ ቀድመው እንዲመቱ ታዛዙን ሁሉ በአብዛኛው መመሪያው ደርሷል። ሁሉም ቀን እና ዶሮ ሲጮህ እየጠበቀ ነው።
    3• ጦርነቱ ለይቶ በ1000 አደዎች ላይ ብቻ ነው፣ አንጂ ከጭቁኑ ወገናችን የትግራይ ህዝብ ጋር አይደለም። ከዚያ በኋላ ዶ/ር ብርሐኑ የሽግግር መንግስቱን እና ጄነራል ከማል ጦሩን ይመራሉ።
    4• ሕዝባችን በየአቅጣጫው ለለውጥ ስለተነሳ ጨዎነት በተምላበት ሁኔታ በለውጡ ማእበል ውስጥ እንዲሳተፍ እናሣስባለን።
    5• “ሮድ ማፕ” በሙሁራኖች አማካይነት በተከበሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ በኩል ለህዝባችን በቅርብ ቀን ይገለፃል።
    6• አገር ወዳድ በኢሐዲግ ውስጥ ያላችሁ ጦር ፣ ፓሊሶች የራሳችሁን ሂሊና ፍርድ ይዛቹ በለውጥ ውስጥ በሚስጣችሁ መመሪያ መሠረተ በኢትዮጵያ ውስጥ ማንኛውም ክፍተት ሳይፈጠር ከ ሽግግር መንግስቱ ጋር ተሠራላችሁ።
    7• የተደራጀ ሐይል በየአቅጣጫው ስላለ በጨዎነት እና በመረዳዳት ከእግዚአብሔር ጋር እንወጣዋለን። በፀሎት ወደ ፈጣሪ እንደ ሐይማኖታችሁ የምናለቅስበት ግዜ ነው። እነዚህን በ 17 አህያዎች ተቀምጠው ቤተመንግሥት በሱዳን አሰማት ስም የገቡትን ሴይጣኖችን በእግዚአብሔር ስም ይነቅላሉ። በኤፈርት በትግራይ ህዝብ ስም የዘረፈትን $50 ቢሎን ጋር ለፍርድ እናቀርባቨዎለን። ግን 50% ከ 1000 ውስጥ ተስፋ የቆረጡ የ ኤችአይቪ በሸተኞች ናቸው፣ ኢትዮጵያ የልጆቻቸው መኖሪያ እንኳን መሆኑን ረስተዎል???
    8• አቡነ መርቆሬዎስ አሁን ለሕዝባችን አንድነት መናገር የለቦት አጣብቅኘ ጊዜ ላይ ነን። አንድ ኢትዮጵያ ፣ አንድ ሲኖዶስ የኣባቶቻችን ሰርአትን ዶግማ እና ቆኖና ሳይቀየር ወደ አንድነት ማምጣት በእግዚአብሔር ስም ይጠበቅባቸዎል።

    ተራማጅ የኦሮሞ ታጋዬች ከ አምቦ ጫካ ጽሕፈት ቤት እና ይድረስ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ታጋዮች በየአሉበት፣ ለውድ መሪዎቻችን የሽግግሩ ዶ/ር ብርሐኑ ነጋ እና የጦሩ አሰረተባባረ ጀነራል ከማል ገልቹ።
    ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ከ እግዚአብሔር እርዳታ ጋር!!!
    ንጉሡ ሞቱማ አስተባባሪ ከአምቦ።

    [Reply]

  6. የወያኔ አቀንቃኝ ብአዲንና ኦህዲድ እንደለስዋእት በግ እስከምትታረድ ጠብቅ! የአዋሴ በጎች! ችግ!ነበሮች! ቻዉ!

  7. ወድም ንጉሡ i would like to connect with you.Howcould we do that ? ? I can give you a temporary email.would that work ? ? Stay cool Bro.We will write a new history that will be remembered for generations.Let me know how.

  8. To avoid woyane’s infilteration membership and joining must be in a stepwise process, that is to say a person who want to join must be screened by references (other persons) who have acquintances and they can give testimonials about the background of the applicant.

  9. I totally agree! ! ! woyanes have fulled us and have abused our kindness and trust for too long.

  10. ወዲ ዘለማኒት ቁምጥናም ቁስልም የአጋሜዎች በሽታ ነው።ቁስል is the first step to ቁምጥና። So its all yours አጋሚዶ man ! ! ! አንተ ገጣባ የልማኝ ልጅ ! ! ! ለእናንተ ችጋራምነት ማንም ተጠያቂ ሊሆን አይችልም።
    እስቲ ሱሪህን ከፍ አድርግና እግርህን አሳይ? One out of every three agame is infected with ቁስል። This also includes agame women. ዘሮችህ በንጹሃን ኢትዮጵያዊያን ላይ የፈጸሙትና እየፈጸሙት ያለው ወንጀል ውጤት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*