የሳምንቱ አጀንዳ — ገዱ አንዳርጋቸው ከአማራ ክልል – ብልጦች አይደለም ብልጣ ብልጦች ግን አይሸውዱንም::

የሳምንቱ አጀንዳ — ገዱ አንዳርጋቸው ከአማራ ክልል – ብልጦች አይደለም ብልጣ ብልጦች ግን አይሸውዱንም::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Amhara‬ ‪#‎Tigray‬ ‪#‎TPLF‬ ‪#‎ANDM‬ ‪#‎ገዱ_አንዳርጋቸው‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – አጣብቂኙ አላላውስ ሲለው ሕወሓት አጀንዳ ፈጠራ እና ማምታታቱን ማዘናጋቱን ተክኖበታል::ሕዝቡ ለእለት ኑሮው ስለሚጣደፍ የተባለውን ይሰማል ያፈሳል የምትለው ሕወሓት በአማራ ክልል ዙሪያ ለገባበት አጣብቂኝ እና መስራት ለሚፈልገው ስራ ገዱ አንዳርጋቸውን እንደ አጀንዳ ይዞ መጥቶ የማህበራዊ ድረገጽን እስት እያራገበበት ነው::

አያሌው ጎበዜ ሲወርድ ለሱዳን መሬት ቆርሼ አልሰጥም አልፈርምም ስላለ ነው ተባለ ተራገበ አያሌው ኢስታንቡል ላይ ተቀምጦ የተባለውን ተቃራኒ ተናግሮ አራጋቢዎቹን አሳፈረ ገዱ ወደ ስልጣን ሲመጣ የወያኔ አለቅላቂ ስለሆነ ተባለ ዛሬ ላይ ደሞ ለወያኔ የማዘናጊያ ስልት መጠቀሚያ ሲሆን አብረው የሚያጨበጭቡ ዝግምተኛ ዝንጉዎች ተፈጥረው የነበሩትም ሳይሻሻሉ ማየት እጅግ ይሳፍራል:;ገዱም ሲተካካ ተርቱለት…ካለፈው መማር የማንችል የራሳችን ጠላቶች ሆነን እስከመች???

ሀገሪቱ ለውጥ ለውጥ ትሸታለች ከትልቅ እስከ ትንሽ ለውጥ ይፈልጋል የወያኔ የፖለቲካ እና የኢኮኦሚ ዱላ አንገብግቦታል::ሁሉም ስርኣቱ እንዲለውጥ ይመክራል ይዘክራል ይጸልያል ይቃወማል አደባባይ ወጥቶ ደሙን እስከማፍሰስ እስከመሞት ደርሷል::ወያኔ እና ግብረአበሮቿ ክበፊቱ በበለጠ መልኩ ሊናበቡ አልቻሉም ፍትህ የለም ሰላም የለም ስራ የለም ኢኮኖሚው በአንድ ብሄር ስር ለማድረግ ሩጫው ተይዟል::የሃገር እና የውጪው የትምህርት እድል ለአንድ ብሄር ነው ስደት ተመራጭ ሆኗል ወዘተ ይህ ሁላ ባለበት አገር ላይ ሕዝቡ ለለውጥ እየታገለ አየሩም ለውጥ ለውጥ እየሸተተ ይገኛል::ይህ ደሞ ወያኔን አጣብቂኝ ውስጥ ስለከተታት ማዘናጊያ መደፍጠጫ ስልቶችን ሁሉ እየቧጠጠች ትገኛለች::የአማራው ሕዝብ ነጻ የሚወጣው አለቅላቂ እና አራጋቢ ባልሆኑ ሃቀኛ ልጆቹ ነው::

የሳምንቱ አጀንዳ ደጉ አንዳርጋቸው ከአማራ ክልል … ለሱዳን ተቆርሶ የተሰጠ መሬት የለም ሊኖርም አይችልም ፤ የልጆች ጨዋታ አይደለም መሬትን አንስቶና ቆርሶ መስጠት አይቻልም ፡፡ … የቅማንትን የማንነት ጥያቄ አስታከው አካባቢውን የትርምስ ቀጠና ለማድረግ የሚሯሯጡ ሃይሎች ከውስጥም ከውጭም አሉ ፤ እነርሱን በቃችሁ ልንላቸው ይገባል ፡፡ … የሚል በሳል ፣ ንቁ ፣ የሕዝብ ወገንተኝነት ያለው መሪ ማለት እርሱ ነው ፡፡ አሁንም በድጋሚ እጅ እንነሳለን የተከበሩ ….ዶሮን ሲያታልሏት …. ለማያቁሽ ሂጂና ታጠኝ አዳሜ .. ከጨዋታው በፊት በቂ መረጃ አለን አቦ ጭብርብር ካድሬዎች ተምታተው ሊያምታቱ ይፈልጋሉ::ብልጦች አይደለም ብልጣ ብልጦች ግን አይሸውዱንም::ማዘንጊያሽ … ሽሽሽሽሽሽሽሽ ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.

12 Comments on “የሳምንቱ አጀንዳ — ገዱ አንዳርጋቸው ከአማራ ክልል – ብልጦች አይደለም ብልጣ ብልጦች ግን አይሸውዱንም::”

  1. Ybelahal jbo, endaybelah jbo
    sewechn tgrie asefsfual zurihan kebo
    mreT guadochhn abro yemisera band lay tenabo.
    Ager ayqore engih endedabo.
    Yalaggal woyanie ende wushaw abdo.
    Ybelahal yeberhaw zendo.
    Belu tolo absru yewoyanie sreat tendo.
    kye woyanien motual tewardo.
    Wedaj desybelen, leTelatm merdo.

  2. Ybelahal jbo, endaybelah jbo
    sewechhn tgrie asefsfual zurihan kebo
    mreT guadochhn abro yemisera band lay tenabo.
    Ager ayqoresu endih endedabo.
    Yalaggal woyanie ende wushaw abdo.
    Ybelahal yebelahaw zendo.
    Belu tolo absru yewoyanie sreat mewdemun tendo.
    woyanien motual tewardo.
    Wedaj desybelen, leTelatm merdo.

  3. ይድረስ ለአማራ ክልል አስተዳዳሪ ለአቶ ገዱ አንዳርጋቸው መቼም ስው ሲኖር ለሃገሩና ለወገኑ እንጂ ለሆድ አይደለም እላለሁ ወንድሜ ሃገርን ያክል ነገር ከሕዝብ ጋር ተጣልታችሁ አጣልታችሁ አዋግታችሁ ወደም ዘላቂ ችግር አጋድማችሁ በወያኔ ልብ እየተነፈሳችሁ ነገ ከስልጣን መውረድ አይቀሬ ነው ልብልትሉት ይገባል የእናንተ ካድሬዎችና ነፍሰ በላይ ወታደራችሁ ይህ ሕዝብ እንዳላሳገደ፣እንዳላስተማረ እነሆ መሬቱን ለወያኔ ስትሰጡበት እንደ ዲር እንሰሳት ከክልሉ ከሃገሩ፣ከቤት፣ከሰፈሩ፣ከእምነቱ ስታፈናቅሉት እስከ ዛሬ ድረሰ ከሻቢያና ከወያኔ፣ከሱዳን ጋር በማበር የጎንደርን መሬት ይህ መሬት የኢትዮጵያዊያን መሆኑ ዘንግታችሁ.አለቆቻችሁ ቢያዞችሁም አይሆንም ማለት ስትችሉ ወልቃይቲ ጸገደይ ለትግራ እንስጥ ስትሉ ህሊናችሁ እንደት እንዳሰበ ለሕዝብ በይፋ ግልጽ ይሁን ያሉትን ሰዎች ስትገድሉ ነበር አሁንም እየገደላችሁ ነው!
    ጎርፍና መንግስት ያልፋል ግን ሕዝብ ይቀጥላል ነው ያሉት የላስታው አዛውንት! ገብቶሃል

  4. Smu A. t
    your message/melkt le ato gedu andargachew yalkew mnm glT aydelem.
    BeTam tnshyem bthon ye tgriewochn wede amara meriet mesfafat neqtobachewal.
    Yhn werera lemasqom yaseb ymeslal.
    Beziya boqbuaqa ayalew gobezie (dnqiem tgobz) gizie ye armacihon ena ye Telemtn meriet ke geberiew bemenTeq be meto shi hectar wede meriet bank asgeban, eyale le investors seTuh blo letgrie worari asrekbotal.
    Bahunu gizie yh neger qertual.

  5. Smu A. t
    your message/melkt le ato gedu andargachew yalkew mnm glT aydelem. Mnalbatm woyanie neh, behz lemasTelat yemtTr, dgaf lemasaTat eyemokerk new.
    Gn yemishalewn alTeqomkm.
    Le hzb kewegen gedun meriw argo amara merietun yTebqal.
    BeTam tnshyem bthon ye tgriewochn wede amara meriet mesfafat neqtobachewal.
    Yhn werera lemasqom yaseb ymeslal.
    Beziya boqbuaqa ayalew gobezie (dnqiem tgobz) gizie ye armacihon ena ye Telemtn meriet ke geberiew bemenTeq, yemengstn meriet be hge weT worewal asblo be meto shi hectar meriet wede meriet bank asgeban (adis quanqua feTrew) eyale le investors seTen blo letgrie worari asrekbotal. Ya shintam ayalew neber yhn yarege.
    Bahunu gizie yh neger qertual.

  6. እስከዛሬ ድረስ ግድም አልነበረኝ
    ከእንግዲህስ ወዲያ ከፋኝ ቆረቆረኝ።

    አሂሂሂሂ አሁንም ቁማሩ ቀጠለ
    ምናለበት ለእዉነት ብትኖሩ ከስልጣን መዉረድ እንደሆነ ብርቅ አይደል ትወርዷታላችሁ ግን ህሊናችሁ እረፍት የላትም። ለማንኛውም ትዝብት ነዉ ድሮውንም የአማራዉ ህዝብ ልጅ አልወጣለትም።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*