በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳደር አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ የቀረበው ሃሳብ በሕወሓት ውድቅ ተደረገ::

በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳደር አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ የቀረበው ሃሳብ በሕወሓት ውድቅ ተደረገ::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎OPDO‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎TPLF‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – የወያኔን ትንፋሽ በጣረ ሞት የሸበበው የኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ ቀጥሏል::በተለያዩ ወረዳዎች የቀጠለው ተቃውሞ ሕዝቡ በወያኔ አገዛዝ የሚደረግበትን የፖለቲካ ጫና የኢኮኖሚ በደል እና ወታደራዊ እርምጃዎች በመቃውም ተቃውሞውን ለማሰማት አደባባይ የወጣ ሲሆን በየአከባቢው መንገዶችን በመዝጋት ለለውጥ ያለው ቁርጠኝነት በትግሉ እያሳየ ይገኛል::በተለየ ሁኔታ በሃረርጌ ጉራዋ በዳዋ አከባቢ እንዲሁም በበደኖ ተቃውሞ የተደረገ ሲሆን በዳዋ ያሉ ነዋሪዎች የአግኣዚ ሰራዊት ወደ በደኖ ዘልቆ ለመግባት ሙከራ ሲያደርግ ድልድዩን በመዝጋት የመግባት አላማውን አጨናግፈውበታል::

በሻሸመኔ በአምቦ በወለጋ ቀለም ወረዳ በተከታታይ የሚደረጉት ተቃውሞዎች በዛሬው እለት ቀጥለው የዋሉ ሲሆን በጉጁ በተደረገው የቦኮ የአገር ሽማግሌዎች በየ8 አመቱ የሚፈጸመው የመሪዎች ሽግግር ክብር እንግዳው አሻንጉሊቱ ሙላቱ ተሾመ የተባለው የወያኔ ሹም ፕረዚዳንት ሲሆን በከፍተኛ የደህንነት እና ወታደራዊ ኮማንዶዎች አጀብ ተከቦ ውሏል::ርእሰ መስተዳደሩ ሙክታር ከድር ለሕክምና ባንኮክ ነው ይባል እንጂ ምናልባት በቁም እስር ላይ ሊሆን ይችላል የሚሉ የደህንነት ማስረጃዎች ቢገኝም በአይነቁራኛ ስር ሆኖ ከአስቴር ማሞ ጋር በበዓሉ እንዲታደም መደረጉ ተጠቁሟል::የአግኣዚ ወታደሮች አብዛናው የኦሮሚያ ክልል ከተሞችን ከበው እጥረት ለመፍጠር ቢሞክሩም ሕዝቡ ያለውን አቋም ዝንፍ ሳያደርግ በተቃውሞ ትግሉን ገፍቶበታል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳደር አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ የኦሕዴድ ከፍተኛ አመራር ሁለት አባላት በወይዘሮ አስቴር በኩል ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡት ሃሳብ አሻንጉሊዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ሳይደርስ በደህንነት ሹሙ በአላቃ ጸጋይ ውድቅ መደረጉን ምንጮች ጠቁመዋል::ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ኦሮሚያ የጦርነት ቀጠና ትሆናለች ያሉ አመራሮች ከሕወሓት የተሰጣቸው መልስ ግን ልክ እናስገባቹሃለን የሚል ነው::ከባለፈው ግምገማ በኋላ በሕወሓት እና በኦሕዴድ አመራሮች መካከል ከፍተኛ የከንፈር መነካከስ እንዳለ ሆኖ አለመተማመኑ እና በጥርጣሬ መተያየቱ ስብሰባዎችን እየወገኑ መጥራት እና የማይፈለጉ አባላትን ማግለል እና ማስደንገጥ በሕወሓት እየተፈጸመ መሆኑ ሲገለጽ ተቃውሞውም እየጋለ መምጣቱ ታውቋል::ሕወሓት በአሁን ወቅት ተቃውሞ በርዶ የክልሉን ባለስልጣናት በሰበብ በማሰር በማባረር እና በመበታተን በመፐወዝ ካድሬዎችን አዳዲስ ኦሮሚኛ በተማሩ የሕወሓት ሰዎች በመተካት አዲስ የጭቆና ስልት ለማስፈጸም ዝግጅት እያደረገ ይገኛል::ኦሮሚያ በከፍተኛ ደረጃ በተቃውሞ ባለችበት በዚህ ወቅት ላይ የአግኣዚ ጦር የዘር ማጥፋት ስራ ላይ ተሰማርቶ ባለበት በዚህ ቀውጢ ሰአት ላይ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አላውጅም ሲል ወያኔ ማገዱ ለሕዝብ ሕይወት ደንታ ቢስነቱን ከማሳየቱም በላይ ተቃውሞውን አቅልሎ ለማሳየት መሞከሩ የባሰ እያጋጋለው እንደመጣ ታውቋል::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.

14 Comments on “በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳደር አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ የቀረበው ሃሳብ በሕወሓት ውድቅ ተደረገ::”

  1. Woyane dergn awogeze
    yazachewna anazeze
    chefchafi alachew leismula
    yenore aTm awto betkus eyemola
    woyane neTanetn ayawq
    neTa awchu meslo sizebarq
    awjo kefelgachuh tegenTelu blo
    yerasn beras mewosen asmeslo
    oneg-n belaw amalo atalo
    ahunm bewelkayt alfo
    dersual ke konso
    maisaka tesfa bedem telewso

  2. Barentuma
    you are 100% right/correct
    go ahead, you are triuphant
    now time is with you, you are the valient oromtobiyan
    victory is in your hand.
    Yahulu yefesese dem kasaw neTanet new.
    let me remeber you artist tamay saying,
    “wegdu zor belu belachew
    dfretachew enj lensus manfeqedo lachew”

  3. Anonymous ትርጉሙ ትግሬዎችን ብዳቸው ማለት ነው !! ገባህ?? ካልገባህ የኮፈሌ ኦሮሞወች እየበዱ ያስተምሩሀል።

  4. there is only one choice for the woyane criminal gangs. Stop Killing Innocent People And Leave Without Further Bloodshed. Nothing Can Stop This Revolution Until The Oromo People Takes Its Freedom And Liberty Back From This Brutal And LOcal Colonizers. One Thing The Agazi Soldiers And Its Commanders Should Know Is That; You Might Kill Many Oromos And Commit Crime And At The Same Tme Consider That You Would Not Have Any Exit when The Real Self Defense Starts. I Would Rather Advise You To Supoort The Oromo freedom Movement.

  5. ለሆደ ስል ሰው እገድላለሁ!
    ለምን የወያኔን አላማ ግብ የሚመታው ጎሳዎችን እርስበርስ በማባላት በማናከስ እንቀጥላለን እንገድላለን ኦሮሞን ብቻ ሳይሆን በተለይ አማራን መሬቱን በመንጠቅ ከኢትዮጵያ ውጭ ማድረግ
    የአጋዚ ወታደር የተናገረው
    ሰ.አ

  6. የአማራው ግዛት ክልል እስከምን ድረስ ነበር?
    ከ80 አመት በፊት ሽሬ የቤጌምድር ጠቅላይ ግዛት ነበረች ዛሬ ግን ራስደጀንን፣አርማጭኆን፣ደባርቅን ፣ወሎን፣አፍርን፣ጠቅልለው ለወደፊቱ ከሱዳንና ከሻቢያ ጋር ለመዋሃድ የታቀደ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ
    ኢትዮጵያን ያልወጋ፣ያላደማ፣ያልነከሰ፣ያላፈረሰ ማን ነው?

  7. የዘረኝነት ክርፋታችሁን ይዛችሁ ድሮም ለማኝ ናችሁና ወደ ትግራይ አቅኑ ወልቃይትን ቅማንትን ጠገዴን ለሟን ምድር ትታችሁ የእርዳታ ሥንዴ ወዳለበት ሥፍራችሁ ተመለሱ የምትናፍቋት ኢትዬጵያን ሳይሆን ደም እየጠጣችሁ ጮማ እያራችሁ የዘረፋችሁት ሀብት ለትግራይ ነውና ግዜ አታጥፋ ኢትዬጵያን ትውልድ ከፍሎ የማይወጣውን ብድር እዳ ለ100 አመት ሸጣችሁናልና ይህ አገዛዝ ሊቀጥል አይችልም ሞት ለወያኔ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*