ማኅበረ ቅዱሳን የፓትርያርኩ ክሥ የእውነት ጠብታ የሌለበት እጅግ ከባድ አደጋ እንዳለው ገለጸ
የቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ኹኔታ ያሰጋው ማኅበረ ቅዱሳን የፓትርያርኩ የክሥ መመሪያ የእውነት ጠብታ የሌለበት እጅግ ከባድ አደጋ እንዳለው ገለጸ
– ቅዱስ ሲኖዶስ እርምትና አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥበት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ተማፅኗል
– ከኑፋቄ፣ ከአስተዳደር በደል እና ከዝርፊያ የተነሣ የቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ኹኔታ አስግቶታል
ቅዱስ ሲኖዶስ እርምትና አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥበት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ተማፅኗል ከኑፋቄ፣ ከአስተዳደር በደል እና ከዝርፊያ የተነሣ የቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ኹኔታ አስግቶታል በማኅበሩ መተዳደርያ ደንብ ማሻሻያ የፓትርያርኩ አካሔድ “እንግዳ እና አስገራሚ ነው” ብሏል በአካልና በግለሰቦች በኩል እንዲኹም በደብዳቤ 6 ጊዜ ለውይይት ቢጠየቁም ፈቃደኛ አልኾኑም በፓትርያርኩ ስም የሚጻፉ ደብዳቤዎች ክብርና ተኣማኒነትያላቸው ይኾኑ ዘንድ አመልክቷል አግባብነት ያለው ወቅታዊ እርምትና መተማመኛ ያለው አሠራር ተግባራዊ እንዲኾን ጠይቋል * * * (ሰንደቅ፤ ረቡዕ፤ ጥር ፳፭ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.) – የማኅበረ ቅዱሳን ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ፣ በመንፈሳዊ ኮሌጆች ውስጥ በስውር የሚካሔደውና ለቤተ ክርስቲያንን የህልውና ስጋት የኾነው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ አሳሳቢ ደረጃ ስለ መድረሱ በተከታታይ መዘገቡን ተከትሎ፣ ፓትርያርክ አባ ማትያስ፣ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የማያቋርጥ ትግል እንዲካሔድ ለኮሌጆቹ ያስተላለፉት የክሥና የቅስቀሳ መመሪያ፣ አንዳችም የእውነት ጠብታ በሌለው መረጃ ላይ የተመረኮዘና የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆቹን ክሥ የሚያስተጋባ እንደኾነ ማኅበሩ ገለጸ፡፡ ማኅበሩ፥ ትላንት ጥር 24 ቀን 2008 ዓ.ም.፣ በቁጥር ማቅሥአመ/239/02/ለ/08 ለፓትርያርኩ፣ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት እና ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በአድራሻ በጻፈውና ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱና ለተለያዩ መንግሥታዊ አካላት ደግሞ በግልባጭ ባሳወቀው ደብዳቤ፤ ለፓትርያርኩ የክሥና የቅስቀሳ መመሪያ በስፋት ምላሽ ሰጥቷል፡፡
ማኅበሩ በዚኹ ምላሹ፣ ፓትርያርኩ ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት 2007 ዓ.ም. ምልዓተ ጉባኤው ያሳለፈውን ውሳኔ መሠረት አድርገው፣ “መናፍቃንና የተሐድሶ አራማጆች በቤተ ክርስቲያናችን ኮሌጆች ተምረው ስውር ዓላማቸውን በማካሔድ ሕዝበ ክርስቲያኑን በመከፋፈል ላይ ስለሚገኙ ከኮሌጆቻችን ጀምሮ … በማስረጃ የተደገፈ ጥናት እንድታቀርቡ” በሚል አጽንዖት ችግሩን እንዲያጠና ለተቋቋመው ኮሚቴ ኅዳር 4 እና 11 ቀን 2007 ዓ.ም የጻፉትን ደብዳቤ ለትውስታ ጠቅሷል፡፡ የስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ መረጃም፣ የሊቃውንት መፍለቂያ በኾኑት ኮሌጆች ላይ ስለ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ እንቅስቃሴ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት ላይ የተመሠረተና ችግሩም በአጠቃላይ አሠራር ደረጃ እንዲፈታ የኹሉም የቤተ ክርስቲያን አካላት የነቃ ተሳትፎ እንዲያስፈልግ ለማስገንዘብ የተዘጋጀ እንጂ ከሣሾቹ እንደሚሉት፣ ኮሌጆቹን በጅምላ በሃይማኖት ሕጸጽ ለመወንጀል አልያም የግለሰቦችን ስም እየጠቀሱ ለማውጣት እንዳልቀረበ አስረድቷል፡፡
“እንደ እውነቱ ከኾነ፣ በጋዜጣው ላይ የወጣው አጠቃላይ የጽሑፉ ጭብጥ ሲታይ ቅዱስ ሲኖዶስ ከወሰነው ውሳኔ የተለየ ስምዐ ጽድቅ የጻፈችው ምን አለ?” ሲል የጠየቀው ማኅበሩ፣ በኮሌጆቹ አስተዳደር፣ ሠራተኞች፣ መምህራንና ደቀ መዛሙርት ስም የቀረበው አቤቱታ፣ ጋዜጣው በይፋ ያወጣው መረጃ፣ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ በእውነተኛ የቤተ ክርስቲያን አካላት ዘንድ ትኩረት በማግኘቱ የተደናገጡት የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆች የሰርጎ ገብ እንቅስቃሴያቸው እንዳይገታባቸው የፈጠሩት የማዘናጊያ ውንጀላ እንደኾነ አብራርቷል፡፡ “ከየኮሌጆቹ ከሚማሩ ደቀ መዛሙርት መካከል በውድም ኾነ በግድ እንዲፈርሙ ተደርገው ለቅዱስነትዎ የቀረበልዎት ጥያቄ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነው ውሳኔ መኾኑ ተዘንግቶና የማኅበረ ቅዱሳን አንድ ተወካይ እንኳ ተገኝቶ ማብራሪያ እንዲሰጥ ሳይደረግ እንዲኽ ዓይነት ብያኔ በርስዎ በቅዱስ አባታችን መሰጠቱ አሳዝኖናል፤” ሲል ቅሬታውን ገልጧል፡፡ አያይዞም፣“ጥቂት የተሐድሶ እምነት አራማጆችን በርቱ፣ ተቃውሟችሁንና ማደናገራችሁን ቀጥሉበት የሚል የሚመስል መልእክት የያዘ ሐሳብ በቅዱስነትዎ ፊት መሰጠቱም እጅግ አስደንቆናል፡፡ በጥሞና ከታየ የቀረበውን መረጃ ወስዶ በቅዱስ ሲኖዶስ እንደገና የተቋቋመው ኮሚቴ እንዲያጠናው ማድረግ የሚገባ እንጂ ሊያስከሥሥም ኾነ እንዲኽ ዓይነት ደብዳቤ ሊያስጽፍ የሚችል ነገር ለመኖሩ በፍጹም አልታየንም፤” ሲል የፓትርያርኩ አካሔድ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔና አሠራር የሚቃረን፣ ማኅበሩን የማይገልጽና ፍትሐዊነት የጎደለው እንደኾነ ተችቷል፡፡ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃን የእምነት መግለጫቸውን አሳትመው በይፋ በማሠራጨት የቤተ ክርስቲያናችንን ትምህርተ ሃይማኖትና ቀኖና በማንአለብኝነት በሚፃረሩበት፤ በአስተዳደራዊ መዋቅራችን ውስጥ ጥቅመኝነት ክብር ተሰጥቶት በግላጭ ዝርፊያ በሚፈጸምበትና አገልጋይ ካህናት በየቦታው በሚበደሉበት በአኹኑ ወቅት፤ በርእሰ መንበሩ ደረጃ ለቤተ ክርስቲያን የማይበጁ እንዲኽ ያሉ የሐሰት ክሥና የቅሰቀሳ መመሪያ ያዘሉ ደብዳቤዎች እየተፈረሙ ሲወጡ ማየት እጅግ ከባድ አደጋ እንዳለውም ማኅበረ ቅዱሳን በደብዳቤው አሳስቧል፡፡ ክሡን በግልባጭ እንኳ እንዲያውቀው አለመደረጉንና የደብዳቤው ዓላማና ተልእኮው ምን እንደኾነ ለመገመት መቸገሩን የገለጸው ማኅበሩ፤ ምንም እንኳ ማኅበሩን፣ አጥጋቢ ሥራ ሠርቷል ወይም አልሠራም፤ ስሕተቶችን ይፈጽማል አይፈጽምም ብሎ መከራከር፣ መውቀስና በሐሳቦቹም መወያየት፣ አስፈላጊም ሲኾንም መገሠጽ እየተቻለ ከአንድ ቅዱስ አባት ቀርቶ ከየትኛውም የተቋም ሓላፊ በማይጠበቁና የሰዎችን ስሜት በሚያስቆጡ ቃላት መሸንቆጥ በእጅጉ አሳዝኖኛል፤ ብሏል፤ በተለይም “የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና በመጣስ ታሪክ ይቅር የማይለው ጥፋት እየፈጸመ ይገኛል” የሚለው የፓትርያርኩ ጭፍን ብያኔ ለማኅበሩ አመራርና አባላት ቀርቶ ደብዳቤውን በየሚዲያዎቹ ያዩት ኹሉ፣ ትዕግሥትን የሚፈትን እንደኾነ እየገለጹለት እንደሚገኙም ጠቁሟል፡፡ አባታዊ መመሪያና ቡራኬ ለመቀበል፣ ለቤተ ክርስቲያን ቅን የማያስቡ አካላት በሚያነሡበትም ክፉ ጉዳዮች ለመወያየት÷ በአካል በመቅረብ፣ ለስድስት ጊዜያት ደብዳቤ በመጻፍ እንዲኹም ብፁዓን አባቶችን ጨምሮ በተለያዩ ግለሰቦችና አካላት በኩል ፓትርያርኩን ለማነጋገር በተደጋጋሚ ቢጠይቅም ጊዜ ሰጥተው ሊያወያዩት እንዳልቻሉ ማኅበሩ በጽሑፍ ምላሹ አውስቷል። በአንጻሩ ማኅበሩን በመክሠሥ ለሚቀርቡ የተለያዩ አካላት ፓትርያርኩ ጊዜ እየሰጡ እንደሚያነጋግሩ የጠቀሰው ደብዳቤው፣ “ለአንድም ቀን እንኳን በተከሠሥንበት ጉዳይ ቀርበን ቃላችንን እንድንሰጥ አለማድረግዎ አስደንቆናል፤” ብሏል። የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆች በሚያዘጋጇቸውና በሚመሯቸው ድረ ገጾችና ብሎጎች ማኅበሩን ለመክሠሥ የሚያወጧቸው ሐሳቦች በፓትርያርኩ መመሪያም ተጠቅሰው መታየታቸው እንዳሳዘነውና እንዳስገረመው ማኅበሩ ገልጾ፣ ከሣሾች ባቀረቡት ቃል ላይ ብቻ ተመሥርቶ ፍርድ መስጠት እውነተኛውን ሕግ በምትተረጉመው ቤተ ክርስቲያናችን ፍጹም እንግዳ ሥርዓት ነው፤ ሲል ተችቷል፡፡ እውነታውን ለማወቅና ለሚነሡ ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት የጉዳዩን ባለቤቶች ጠርቶ ፊት ለፊት በማነጋገርና በመመካከር መፍታት እንጂ አንድ ጩኸት በተሰማ ቁጥር ደብዳቤ መጻፉ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንደማይበጅም ማኅበሩ አስገንዝቧል። ላለፉት 23 ዓመታት፣ በብፁዓን አባቶች ቡራኬና መመሪያ ሰጪነት፣ በገዳማውያን ጸሎትና በምእመናን ከፍተኛ ድጋፍ ቤተ ክርስቲያንን በአገልግሎቱ ለማገዝ ላለፉት 23 ዓመታት የዐቅሙን ያህል ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን የጠቀሰው ማኅበሩ፣ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃንንና የአማሳኞችን ውንጀላ የሚያስተጋባው የፓትርያርኩ የክሥና የቅሰቀሳ መመሪያ በቅዱስ ሲኖዶስ በአንክሮ ውይይት ተካሒዶበት እርምት እንዲደረግበትና አስቸኳይ መፍትሔ መፍትሔም እንዲሰጠው ያደርጉ ዘንድ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ተማፅኗል፡፡ በፓትርያርኩ ስም የሚጻፉ ደብዳቤዎች፣ ቤተ ክርስቲያንን የሚወክሉና ክብርዋን የሚያስጠብቁ፣ በኹሉም አካላት ተኣማኒነት ኖሯቸው ትኩረት ሰጥተው የሚመለከቷቸው እንዲኾኑ ማኅበሩ አስተያየቱን አስፍሮ ለወደፊቱም፣ አግባብነት ያለው ወቅታዊ እርምትና መተማመኛ ያለው አሠራር ተግባራዊ እስካልኾነ ድረስ፣ “የሚከተለው አደጋ ትልቅነት ይታየናል፤” ሲል የፓትርያርኩ ወገንተኛና ያልተስተዋለ(እየገነገነ የቀጠለ ኢ-ፍትሐዊና ዓምባገነናዊ አካሔድ) የከፋ መዘዝ እንዳያስከትል በደብዳቤው አስጠንቅቋል፡፡
MK totaly outside the line command of the EOTC, trading in the name of the church all over the country, seeking power by appointing fake prists and brain washing the youg generation exaggerating and advertising himself as if like the only righteous assocation probably next to God is MK only.
I have been EOTC member all my life but i have never seen a sitting papa being looked down by MK like this. Now the question is who is in charge? I think i see fear in papasat and arrogance in MK. MK has no respect for them at all or may be MK has its own support group among papasat. It is really heart breaking to see the church fragmented like this even at home. Can they be just orthodox tewahdo why do they need to be MK first. May God save the church!!!
This Patriarch is politically appointed. The Girisa and wolfs have been shouting on MK for so long… MK remained firm…. unshaken… MK is the only hope of the church…. The wolfs are crying left and right. The Holy Synod is the highest organ of the church not the Patriarch. The Patriarch want to behave like the government system… like Melese did…above everything….above even the useless parliament…. We don’t give up our church to thieves like Begashaw….
For all real Orthodox Tewahedo Christians… the problem of this church is related with the problem of our political system…. we have to address the political system first to address the root causes of the church…
There are paid internet mouthpieces of the government who have been trying to spread rumors about MK (look the ones above)…. they can’t mentions a single fault of MK, they just want to cover their real face and pretend as if they are standing for the church. We know you and you want to take our church, it is over our grave… enatu begjib setebela komo yemiyay lej yelem…. don’t push us to the extreme…. the patriarch should respect the Synod (the highest body).
Our spiritual leaders are politicians and they are implementing their hidden agendas behind the Curtain at the expenses of Orthodox Christian followers.
when our fathers said No to devil MK they became politican when the they are yes for MK they are rightous. MK unlicensed trader in the name of EOTC.
Megbabiya:
he hu hi —- hie h ho
le lu li la lie l lo red color = qey qelem
goodness = chernet only = bcha
student = temari breast = Tut
monday = seño = seNo
one = and oozo = uzo
ethiopia = itiyopiya = etiopia
tortoise = ieli = eli
mother = enat = ènat
buyer =gex
brave = jegna start = mejemer
page = geT poet = gTm geTami
drink = meTeT study = Tnat
salt = Cew = chew
correct = right = tkkl
patience = tgst, but = gn
orange = brtukan
ethiopian bir = ye itiyopiya br
pen = b-er = eskrbito
picture = s-el duke = luul= lu-ul
your pencil = ersas-h, ersassh
your mattress = frashish, frashih
Megbabiya:
he hu hi —- hie h ho
le lu li la lie l lo
red color = qey qelem
goodness = chernet only = bcha
student = temari breast = Tut
monday = seño = seNo
one = and oozo = uzo
ethiopia = itiyopiya = etiopia
tortoise = ieli = eli
mother = enat = ènat
buyer =gex
brave = jegna start = mejemer
page = geT poet = gTm geTami
drink = meTeT study = Tnat
salt = Cew = chew
correct = right = tkkl
patience = tgst, but = gn
orange = brtukan
ethiopian bir = ye itiyopiya br
pen = b-er = eskrbito
picture = s-el duke = luul= lu-ul
your pencil = ersas-h, ersassh
your mattress = frashish, frashih
Mr Solomon
Please think twice before you write or return the name to whom it belongs, to the person with full of wisdom ever existed in this world. How can you say “MK is the only hope of the church…”. Hey brother it is 2008 now. The church has survived almost thousand years with out MK, but with the prayers of real K (kidusan) by their blood and their drops of tears. Mk was conceived 23 years ago by the student solders who went to fight the current regime. Their intention was not to save the church but the government (derg) that officially deny the existence of God. The place was not close to holly at all. I was there when we use marmalt and bread to remember kidusan and pray. It was baren desert that took many people life. As the cadet airborne solders told us there were at least 5ooo kids died there who were drafted from their farm and snatched at the cover of darkness. So you can imagine what kind of spirit it was there. MK is not the only hope of the church. Jesus Christ lord and savior is the only hope of the church. The church has survived all obstacles in the past and it will in the future WITH OUT MK. We worship a powerful living God and he sees and he acts accordingly and does not require our fleshy struggle or a sward of peter to protect the church. The church is his body and he feels her pain so do not declare MK the only hope of the church. In God eye MK may be the only problem of the church. Lib yistih
WOW thank you so much ! Speak for me! MK the group of blood sucker of EOTC in the name of super Christian !
ነዎይ ለአቡነ ማትያስ ፀልዩአላቸው ቀና ብለው ፈጠሩያቸውን እንድያዩ ምክንያቱም ቤተክህነት በሥውር አስመሳይ ተሀድሶዎች ተውጣለች። ሰለዚህ ጥሩ የሚሰሩት ጥላሸት
ከቤተ ክርስቲያናት እየረገፈ በተሀድሶዎች እየተተኩ
ነው። እንዳትረሱ ኢትዮጵያ ላይ ነው፣ ያላችሁት 365
ቀናት በእግዚአብሔር ፓውዛ የምትጠበቅ ነች እናንተ ግን
ነወአይ አሰከራቹ። የንፁሕ አባቶች እንባ ጠራሮጎ አችሁ ይሄዳል ቀኑ እየጨለመ ነው።
ማሕበረ ቅዱሳን የአቡነ ጎርጎሪዬስ ማህተም አለበት፣
በጥሩተግባር ነው የሚታወቀው። በርግጥ ነው ጥቂቶች አሉ ከእኔ በላይ ክርስቲያን የለም እያሉ ሌላውን ለማጥቀር ይቸኩላሉ፣ በመናገርም ሆነ በመፃፍ። በክርስትና እውነት
ወይም ወሸት ፈትለፈት ነው፣ የአባቶቻችን ያስቀመጡትን
ተከትለው ከሁሉም ጋር አብረው መስራት አለባቸው።
የዘመናችን የ666 ዘሮችን መናፍቅንናተሐድሶን መዋጋት
ትልቁ ዘመቻ ነው። እግዚአብሔር ይርዳን የመጣውን የአውሬ መንፈስ በፀሎት እያለቀስን አምላካችንን እያነባን
የምንጠይቅበት ጊዜ ነው።