የኦሮሞ ጀግኖች ተቃውሞ በየከተሞች እና በአዲስ አበባ ዙሪያ ቀጥሎ ሱሉልታ ላይ የባህርዳር መንገድ ተዘግቷል::
የኦሮሞ ጀግኖች ተቃውሞ በየከተሞች እና በአዲስ አበባ ዙሪያ ቀጥሎ ሱሉልታ ላይ መንገድ ተዘግቷል::
#Ethiopia #OromoProtests #AddisAbabaMasterPlan #MinilikSalsawi

Minilik Salsawi – የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ እና የሕዝብ ብሶት የወለዳቸው በራሱ በሕዝቡ መሪነት የሚካሄዱ ተቃውሞዎች ቀጥለዋል::በዛሬው እለት እየተደረገ ባለው ተቃውሞ የጎጃም በር በመዘጋቱ ወደ ባህርዳር የሚጓዙ የጭነት መኪኖች ይሁን የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች ከሱሉልታ ሲመለሱ ውለዋል::ሱሉልታ ላይ ሕዝቡ መንገዱን በመዝጋት ተቃውሞውን እያሰማ ይገኛል::
በሱልልታ ከተማ አየር ላይ ከደብረዘይት የተነሱ የታጠቁ ወታደሮችን የጫኑ ሂሊኮፕተሮች በማንዣበብ ላይ ይገኛሉ::በምእራብ ሸዋ ሜታ ሮቢ የፓርላማ ተወዳዳሪ የነበረው የኢላ አሙማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተማሪ ታደሰ ጸጋዬ ከሕወሓት ወታደሮች በተተኮሰ ጥይት መገደሉ ታውቋል::
በሱሉልታ ከተቃውሞው ጋር ግንኙነት ያሌላቸው 200 የወን ሰራተኞች በሕወሕት ወታደሮች ተይዘው ተውስደዋል::ሕዝቡ ተቃውሞውን እንደቀጠለ ነው::በአዲስ አበባ በዳግማዊ ምንሊክ ሆስፒታል በኦሮሚያ ክልል በሕወሓት የተገደሉትን ተማሪዎች ሃዘናቸውን ለመግለጸ የተሰበሰቡ የሆስፒታሉ ዶክተሮች እና ነርሶች በአገዛዙ ፖሊሶች ታፍሰው ተወስደዋል::የስዊዲን መንግስት በኢትዮጵያ የኦሮሚያ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጉዳይ ላይ የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን የጋራ አቋም እንዲይዝ ጥሪ አቀረበ። ዛሬ በአራዳ ካንጋሮ ፍርድ ቤት በርካታ እስረኞች ያመለጡ ሲሆን ከፍተኛ ቶክስ እንደነበር ተሰምቷል::

ተቃውሞው ቀጥሎ በወለጋ ኦብዲ በምእራብ ሸዋ ሜታ ሮቢ እጅግ ከፍተኛ ተቃውሞ በመሰማት ላይ ይግኛል::እንዲሁም በተለያዩ ዩንቨርስቲዎች ለሊቱን ወያኔ በተለያዩ ብሄሮች መካከል ሊያነሳ ያቀደውን ግጭት የከሸፈበት ሲሆን የኦሮሞን ሕዝብ የሚያንቋሽሹ ጽሁፎች በካምፓሶች ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ለጥፎ ያደረ ቢሆን የሚሰማው አጥቷል::ሕብረተሰቡ ይህ ሊወድቅ የተቃረበውን የበሰበሰ አገዛዝ የከፋፍለህ እና የአጋጭተግ ግዛ ዲስኩሩን እና ተንኮሉን ሳይሰማ ባለን አቅም ሁሉ በጋራ ቆመን በአንድነት ከስልጣን በማባረር ሕዝባዊ መንግስት በመመስረት ሕዝብን የስልጣን ባለቤት ማድረግ ይገባናል::



