ሰማያዊ ፓርቲ ለተገደሉት እና ጉዳት ለደረሰባቸው አጋርነቱን ገለፀ • ከመድረክ እና ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ለመስራት ወስኗል

ሰማያዊ ፓርቲ ለተገደሉት እና ጉዳት ለደረሰባቸው አጋርነቱን ገለፀ

• ከመድረክ እና ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ለመስራት ወስኗል

ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ ታህሳስ 3/2008 ዓ.ም በካሄደው የብሄራዊ ምክር ቤት ስብሰባ ከ‹‹ማስተር ፕላኑ›› ጋር በተያያዘ ለተገደሉትና ጉዳት ለደረሰባቸው የህሊና ፀሎት ያደረገ ሲሆን አጋርነቱን መግለፁንም የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ይድነቃቸው ከበደ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

የፓርቲው ብሄራዊ ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳዮች ውይይት ያደረገ ሲሆን የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በተቃወሙት ኢትዮጵያውያን ላይ መንግስት እየወሰደ ያለው ኢ-ሰብአዊ እርምጃ እና ለሱዳን በሚሰጠው መሬት ላይ ውይይት አድርጓል፡፡ ውይይቱ ከመጀመሩ በፊትም ማስተር ፕላኑን በመቃወማቸው በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ለገደሉትና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው የህሊና ፀሎት እንደተደረገ ሰብሳቢው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

ማስተር ፕላኑ አርሶ አደሮችን የሚያፈናቅል እና ለመሬት ቅርምት የሚዳርግ መሆኑን በመግለፅ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን በማሰማታቸው በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ለተገደሉትና ጉዳት ለደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን አጋርነት የገለፀው ሰማያዊ ፓርቲ በቀጣይነት በጉዳዩ ላይ ሰፋ ያለና የተደራጀ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግም ተገልጾአል፡፡ ፓርቲ ከመድረክ ጋር ለመስራት ውይይት መጀመሩን የገለፁት አቶ ይድነቃቸው ከበደ በቀጣይም ከመድረክና ከሌሎች በወቅታዊ ችግሮች ላይ ለመስራት ፈቃደኛ ከሆኑ ፓርቲዎች ጋር እንዲሰራ ብሄራዊ ምክር ቤቱ መወሰኑን ገልፀዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ኀዳር 27 ቀን 2008 ዓ.ም ‹‹በገዛ አፈ-ሙዙ መቃብሩን የሚቆፍር የሽንፈትን ጽዋ ይጎነጫል !›› በሚል ባወጣው መግለጫ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ ባሰሙት ኢትዮጵያውያን ላይ መንግስት የወሰደውን ኢ-ሰብአዊ እርምጃ ማውገዙ ይታወሳል፡፡

Negere Ethiopia's photo.
Negere Ethiopia's photo.

8 Comments on “ሰማያዊ ፓርቲ ለተገደሉት እና ጉዳት ለደረሰባቸው አጋርነቱን ገለፀ • ከመድረክ እና ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ለመስራት ወስኗል”

  1. awo ! ahunand kalhonahu meche lithono new

    MEAD ,, UDJ,, Medrek,, Semayawi,, ana llochim be and tela sir teseasebu !!!

    yehe yemot eshiret weqt ne

    Tenes !! Tenes ,Tenes ! ye Ethiopia Hizb !! le Oromo becha syhon ,, le Mlw Etiopia Hizb tenes

    And Ethiopia,, and Hiz ,, And Sendeq !!

    Mot le Tigray weyane !!!!!!!!!!!!!!!!

  2. melaw amaras? Min titebkaleh? Mot endehone lehulachinm new yete zegagelin tenesu tenesu Self yegegna dil yeegzabher new

  3. MEAD = Melw ye Ethiopia hizb,,!!!! dedeb neh

    Amara Hageru sitewerer,, Taliyanin Turkin,,, Derbushin,, yabarere Jegna new

    Oromo beca Nets yewta new yemitln ?? kkkk

    Log live Ethiopia !!!!

  4. If the “semayawi and madrek” parties come together that will be a vitory for the ethiopian people. VIVA semayawi party.encouraging news for our country.

    It is the wuyane who are on the loosing side. Amhara and Oromo unite !!!!!!!!!!!!!!!

  5. Woyane have been working hard to divide Christian and Muslim but failed, However woyane has been 100% succecessful dividing Amhara and Oromo. The minute these two tripes agree to work together, in order to bring democracy and freedom, Woyane is gone. IF these two tribes unite to work together most likely there won’t be a war. Woyane will ran away. Please we all have to remember that on this type of social media woyane qebero will try to sabotage by insulting either tribe pretending that the opposite tribe. Do not trust qebero. Our Tigrian brother and sister’s.. it is time to stand with ethiopian against woyane because every one will benefit from building democracy. WE are in 21st century so we have to think like 21st century.

  6. kszenamoch hulu inanten billo tagay
    yehie komata ke America yesebesebew
    dollar aleke meselgne .
    gimatam hullu . shintehen aydelem inde
    besurih yemetelekew .komata .

  7. ገና ነው፣

    ወያኔ እኛን እያፋጀ መቀጠሉ ጥርጥር የለውም ምክንያቱም ራሳችንን በዘረኝነቱ ልክፍት ውስጥ እያለን፣ መተማመንን ሳንገነባ፣ ኦሮሞ፤ አማራ፤ ወላይታ፤ ወዘተ እየተባባልን የኢትዮጵያን ስም እንኳን ለመጥራት ተጠይፈን እንዴት ተብሎ ነው በዚህ ሁኔታ ለውጥ ሊመጣ አይችልም።
    እያንዳንዱ ወደ ስልጣን ኮርቻ መቆናጠጫ ለማድረግ የጎጥ ካርድ እየመዘዘ ሰዉን ካስጨረሰና ካቆራቆሰ በኋላ፣ ቦታዋን ሲይዝ ያን ሁሉ ታጋይ ህዝብ ክዶ ለራሱ ጥቅም ሲሯሯጥ ነው የሚገኘው። ለዚህም ማስረጃ እንዲሆነን ሩቅ መሄድ አይኖርብንም፣ ወያኔ ራሱ አንድ ማስረጃ ነው። የትግራይን ህዝብ ነጻ አወጣሃለሁ፣ ወዘተ ብሎ ሲያበቃ አሁን ምን ደረጃ ላይ ጥሎት እንደሚገኝ ሁላችንም የምናውቀው ጉዳይ ነው በጭፍን ትግራይን የመጥላት አባዜ እስካልተጠናወተን ድረስ ማለት ነው።
    ስለዚህ፣ አሁንም ይህ የጎጥ ካርድ እየመዘዙ ከጎናችን ተሰለፍ ዓይነቱን የትግል ስልት ረጋ ብለን በመመርመር፣ ኢትዮጵያዊና ሃገራዊ ጥያቄን በማንገብ በአንድነት እስካልቆምን ድረስ፣ ችግራችን ይቀጥላል እንጂ ያሁኑ እንቅስቃሴ እንደ አለፉት ሌሎቹ ትግሎች እግብ ሳይደርስ ተደናቅፎ ሊቀር የማይችልበት ምንም ምክንያት የለም።
    መከራችንን ለማሳጠር፣ በአንድነት እንቁም። የጎጥ አጥር አይከልለን።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*