ጎጃም እና ጎንደር ክፍላተሃገራት የተቀናጀ ዘረፋ እና አፈሳ በወያኔ እየተካሄደ መሆኑ ተሰማ::
ጎጃም እና ጎንደር ክፍላተሃገራት የተቀናጀ ዘረፋ እና አፈሳ በወያኔ እየተካሄደ መሆኑ ተሰማ::
#Ethiopia #Gonder #Gojjam #EthiopianArmy #MiilikSalsawi
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – የመከላከያ ሰራዊቱ በሃገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ የማብራሪያ ጥያቄ በማንሳቱ ግምገማ እንዲገባ የተደረገ መሆኑ የተሰማ ሲሆን ከባድ ውጥረት ለረዥም ጊዜያት ያየለባቸው ጎንደር እና ጎጃም ክፍለሃገራት የኦሮሞ ተማሪዎችን እና ገበሬዎች የቀሰቀሱትን የመብት ጥያቄ ተከትሎ በአከባቢው ከፍተኛ ውጥረት ይነሳል በሚል ከፍተኛ ስጋት ያደረበት ወያኔ በጎንደር እና ጎጃም አፈሳ የጀመረ ሲሆን በድንበር ከተሞች በስራ ላይ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆችን ንብረት እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የአማራ ተወላጆችን ንብረት ባደራጀው የማፊያ ቡድኖች በማዘረፍ እና በማቃጠል ላይ መሆኑ ታውቋል::
ወትሮውም ከፍተኛ የተቃውሞ ድምጽ የሚሰማበት ጎንደር በከተማው እስር ቤቱን በአገዛዙ ሃይሎች መቃጠል ተከትሎ የወያኔ ካድሬዎች የቅማንትን ነዋሪዎች ከቀሪው የጎንደር ሕዝብ ለመለየት ያደረጉት ሙከራ አንስተኛ ግጭቶች ተነስተው የነበረ ቢሆንም ሕዝቡ ያለውን እውነት በመረዳቱ ፊቱን ወደ አምባገነኑ አገዛዝ መልሶ ከወያኔ ጭፍሮች ጋር ተፋጦ ይገኛል::አሁንም ወያኔ ለማጨፋጨፍ የሚጠቀምበት የቅማንት ሰዎችን ስለሆነ ይህንኑ አጀንዳ ይዞ ጎጃም አቸፈር በመሄድ አዲስ ግጭት ለመፍጠር እየሰራ መሆኑ ተደርሶበታል:: ይህንን ግጭት ለማሳካት ደፋ ቀና የሚለው ወያኔ በጎጃም ባህርዳርና ደብረማርቆስ የሚገኙ ወጣቶችን በማፈስ ላይ ሲሆን ለትምሕርት በክልሉ ዩንቨርስቲዎች የተመደቡ ተማሪዎችን አማሮች ሊያጠፏቹህ ስለሆነ ራሳችሁን አዘጋጁ በሚል አደገና የሃሰት ፕሮፓጋንዳ እየነዛ እንደሆነ ከባህርዳር የተገኙ መረጃዎች ጠቁመዋል::
Qmant bahunu adegeña weqt yewoyanie mesariya meTeqemiya athunu. Yeselasa amet yewoyanie bedel asmerron lewoyanie mareja yesalnewn slet ena zgjt aqTacha atastubn. Manñawm yebhier tnkosa yewoyanie siera bemehonu betgst enlefew, bedl kewetan behuala bemegeba fth yseTbetal..
ይህን የሚያደርግ ሰው ኢትዮጵያዊ አይድለም !! አቸፈሮች ወጣቶች በስሜት ተገፋፍታችሁ እጃችሁን እሳት ውስጥ እዳታስገቡ !!…..???
ወያኔ ጎጃምና ጎንደር ውስጥ የዘር መርዙ በፍጹም አይሰራለትም።በዚህ አጋጣሚ ለአስተዋዩና ለረጅም ጊዜ ባለታሪኩ የጎጃምና የጎንደር ሕዝብ የሚያልፍ ቀን የማያልፍ የታሪክ ቁስል በመካከልህ ትተህ እንዳታልፍ እኛ ወድሞችህና እህቶችህ አደራ እንልሃለን። እኛ ወንድምችህና እህቶችህ ከጎንህ ነን።አይዞህ ! ! ! ! በምንችለው ሁሉ ከጎንህ ነን።መኝታህን ለቀህ ለአንተ ይቅርብኝ ብለህ የእንግዳ እግር አጥበህ ስመህ የምትሸኝ ወርቅ ባህልህን ተጠቅሞ ዛሬ አንተኑ መቃብር ውስጥ ሊከትህ መርዙን እያዝረቨፈቨ ያለውን ወያኔ መጠቀሚያ እንዳትሆን።
it is harsh wayane.
My country’s people ! Please stand by unity for the downfall of the leading party !