ተዓምር እንሰራለን ያለው ዘራፊው የወያኔ አገዛዝ የሕዝብ ተቃውሞ አስደንግጦታል::ወያኔ አልተሳካለትም::

ተዓምር እንሰራለን ያለው ዘራፊው የወያኔ አገዛዝ የሕዝብ ተቃውሞ አስደንግጦታል::ወያኔ አልተሳካለትም::
ወደ ጅማ የሚወስደው መንገድ ተዘግቶ ትራንስፖርት ተሰተጓጉሏል::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ከተቃውሞ ጀርባ አሉ የሚባሉ ተጠርጣሪ የኦሕዴድ ባለስልጣናት ስልካቸው ተዘግቶ ከቤታቸው እንዳይወጡ እየተደረገ ነው::በቤተሰቦቻቸው ላይ ከባድ ክትትል ይደረጋል::ወያኔ ግራ ገብቶታል::ተቃውሞው እየበረታ መምጣቱን ተከትሎ ግራ የገባው ወያኔ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ያሉ የሌላ ብሄር ተወላጆች ላይ ለመዝመት ያደረገው ሙከራ ያልተሳካለት ሲሆን ይብሱኑ ሕዝቡ በአንድነት አደባባይ ወጥቶ አገዛዙን በመቃወም ድምጹን ማሰማቱን ለወያኔ የእግር እስት ሆኖቦታል::አዲስ አበባ በአስቸኳይ የሰበሰባቸው የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ባለስልጣናት ሌሎች ብሄሮች ከክልላችሁ አስወጡ የሚል መመሪያ ቢሰጣቸውም ሕዝቡ አይሰማንም ሌላ መፍትሄ ይፈለግ ሲሉ ለደህንነት ሹሞቹ ተናግረዋል::ከአዲስ አበባ ወደ ስሜን ኢትዮጵያ እንዲሆም ወደ ወለጋ የሚያስገቡ መንገዶች ወደ ጅማ የሚወስደው መንገድ ተዘግቶ ትራንስፖርት ተሰተጓጉሏል::

ከአገዛዙ ቁጥጥር ውጪ የሆነው ተቃውሞው በዚሁ ቀጥሎ መከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ ሳይዘልቅ ሩጫ ላይ የሆነው ወያኔ ከቤሻንጉል ጉምዝ እና ከጋምቤላ እንዲሁም ከደቡብ ክልል ተመልምለው የተመረቁ አዳዲስ የፌድራል ፖሊስ አባላት ለመመደብ የተዘጋጀው አገዛዙ ሰራዊቱ ውስጥ ያለው አለመተማመን ዝምታን አስመርጦታል::ወያኔ በየዩንቨርስቲው እና በየክልል ከተሞች የላካቸው የኦሕዴድ ባለስልጣት አልተሳካላቸውም:ወርቅነህ ገበየሁ የሚመራውን ስብሰባ የወዲወላቡ ተማሪዎች ረግጠው ባዶ አደራሽ አስታቅፈውት ወጥተዋል::በሌሎች ክልሎች ለውይይት ባለስልጣናት ይመጣሉ ቢባሉም ተማሪዎች ከውይይት ይልቅ ተቃውሞውን መርጠዋል ሲል የደህንነት ቢሮ ሪፖርት ያመለክታል::ተቃውሞውን በሃይል ለመምታት ቢሞክርም ያልተሳካለት አገዛዙ ሕዝቡ ባለው መንግስት ላይ ተስፋ መቁረጡን በገሃድ መስእዋት በመሆን አሳይቷል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

11 Comments on “ተዓምር እንሰራለን ያለው ዘራፊው የወያኔ አገዛዝ የሕዝብ ተቃውሞ አስደንግጦታል::ወያኔ አልተሳካለትም::”

  1. Tigray people’s solidarity to remove the mercenary Meles Zenawi’s rule.

    -Stop killing innocent people !
    -Stop land grabbing and fill up your pocket.
    -Let the people decide on their own land !
    -Confiscating land from poor and making Cadres millionaires is not a ‘Development’. A sustained and genuine development is transforming the poor and making the true owner of the land richer, not the regime’s Cadres to be millionaire.

    STOP the illegal and secretive demarcation with Sudan IMMEDIATELY and UNCONDITIONALLY !!

    Freedom and democracy to Ethiopia !

  2. የኦህዴድ ወታደሮች አፈ ሙዙን ወደ ባንዳው ወያኔ ላይ ማዞር ግድ ይላቸዋል 90% በላይ የሚሆነው በሀገራችን የኦሮሞ ብሄር መሆናቸው ይታወቃል ታድያ ይህን ንቅናቄ የማደራጀት ሥርአቱን የምንጥልበትን መላ ማበጀት ግድ ይላል።

  3. ሰሞኑን በአገራችን እየተካሄደ ያለው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በገሃድ እየተመለከትን ነው፡፡ በተለይ ከሁለት ቀናት በፊት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተወሰደው አቋም እጅግ የሚያስደንቅና የሁላችንንም ዕይታ የሳበ ነው፡፡ ተማሪዎቹ እንደተለመደው ወደ መመገቢያ ቦታቸው ሲደርሱ ምግባቸውን ወስደው በሥፍራቸው ተቀመጡ፡፡ ወደ ፈጣሪያቸው እየሞቱ፣ እየተሰቃዩና እየተራቡ ለሚገኙት ወገኖቻቸው ጸሎት አደረሱ፡፡

    ከምግቡ አንዲት ቁራሽ ሳይቀምሱ ከተቀመጡበት በመነሳት ምግቡ ጠረጴዛው ላይ በመተው የመመገቢያ አዳራሹን ለቅቀው ወጡ፡፡ 15 ሚሊዮን ወገናቸው እየተራበ፣ ሌላው ደግሞ እየተፈናቀለ፣ እየተገደለ፣ የመኖር ኅልውናውን እያጣ በሰላም እየበሉ ለመኖር እንደማይፈቅዱ ሰላማዊ በሆነ መንገድ አሳዩ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*