መንግስት የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ለህዝብ ይፋ የሚደርግበትን ፕሮግራም ሰረዘ፤

ሰሞኑን በኦሮሚያና ሌሎች ክልሎች ባሉ ዪኒቨርስትዎችና ት/ቤቶች የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተግባራዊነት ጋር ተያይዞ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ መንግስት በተማሪዎች ላይ አሰቃቂ እርምጃ እየወሰደ ተቃውሞውን ለማፈን የሚቻለውን ሁሉ እያደረገ ቢሆንም ከዚህ በፊት ‹‹ማንም የማስተር ፕላኑን ተግባራዊነት አያስቀረውም›› ካለው አቋም እንዲያፈገፍግ የተገደደበት ሁኔታ መኖሩን የከተማ ልማትና ቤት ሚ/ር ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ለዚህም ባለፈው ሳምንት የከተማ ልማትና ቤት ሚ/ር ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጽ/ቤት ጋር በመሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት በአፍሪካ ኅብረት የስብሰባ አዳራሽ ለሚከናወነው ፕላኑን ለማስተዋወቅ የተዘጋጀው ፕሮግራም ለባለድርሻ አካላት ጥሪ ከተላለፈ፣ የአዳራሽና መስተንግዶ ቅድመ ክፍያ ከተከፈለና አስፈላጊው ዝግጅት ከተጠናቀቀ በኋላ ፕሮግራሙ እንዲሰረዝ መደረጉን በማስረጃነት አቅርበዋል፡፡

ምንጮቹ ህወኃት መራሹ መንግስት ይህንኑ የአዲስ አበባ ማስፋፊያ ማስተር ፕላን የሚያስፈጽም ጽ/ቤት አደራጅቶ ለሁለት ዓመታት ዝግጅት ሲያደርግና ተፈጻሚነቱ በምንም መንገድ አይደናቀፍም ሲል ከርሞ አሁን የተነሳውን ህዝባዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ በአደባባይ በተደጋጋሚ የገለጸውን ይህን ሃሳብ ቀይሮ ቀድሞውኑ ፕሮግራሙ የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ልማት ማስተር ፕላን እንጂ የአዲስ አበባ ማስፋፊያ ማስተር ፕላን አልነበረም ለማለት መገደዱን በተጨማሪ ማስረጃነት ያቀርባሉ፡፡

እነዚሁ ምንጮች – ይህንኑ እንዲያስፈጽም የተቋቋመው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ማቴዎስ በአሁኑ ጊዜ ውጪ አገር እንደሚገኙና ከሄዱበት መመለሰ/አለመመለሳቸው እንዳልታወቀ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ ምንጮቹ ህዝባዊ እንቅስቃሴው ይህ የማስተዋወቂያ ፕሮግራም (ለጊዜውም ቢሆን?) እንዲሰረዝ ማድረግ ቢችልም ይህ በአገራችን ካለው የህወኃት ፍጹም የበላይነት አምባገነናዊ የጠቅላይነት አገዛዝ አንጻር ዘላቂ ውጤት ያለመሆኑንና እነዚህ የፊንፊኔ ልዩ ዞን ከተሞች ቀርተው ታላላቅ የኦሮሚያ ከተሞች( አዳማ፣ ጂማ፣ ሻሸመኔ፣ጭሮ፣ ነቀምት፣…) እና ኦሮሚያ ክልል በአጠቃላይ በህወኃት ቁጥጥር ሥር መሆናቸውን አስታውሰው ይህ አጠቃላይ የስርዓት ለውጥ ጥያቄውንና የአንድነትና የዲሞክራሲ ግንባታ ትግሉን እንዳያዘናጋ ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡
ምንጮቹ በቀጣይ ከዚህ ሂደት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን እየተከታተሉ ለህዝብ እንደሚያደርሱ ቃል ገብተዋል፡፡

8 Comments on “መንግስት የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ለህዝብ ይፋ የሚደርግበትን ፕሮግራም ሰረዘ፤”

  1. ትግሉ ተቀናጅቶ ወደ ፊት መቀጠል አለበት ሌሎችም አንድ ላይ በመሆን የመንግስት ለውጥ መቀጠል አለበት

  2. It so sad, our fathers and people have been suffering from consecutive slaughtering, subjugations and exploitations by the inhuman greediest rulers since long while. የሚያሳዝነው… ይህንን መከራ አሁንም ድረስ መግታት ያለመቻላችን ነው፡፡ …. አሁን ግን መቆም አለበት… በነኚህ አናሳ የዘራፊዎች ቡድን ከመጨቆንና መበዝበዝ በላይ … በቁም ሞት የትም የለም! Weyanie will never defeat the people of Oromo… we’ll never quit struggling and submit to the domination of this disgraceful criminal minorities…..why not It’ll get armed with nuclear bomb, leave alone the light machine guns it is producing in Bishoftu and around now.

  3. It so sad, our fathers and people have been suffering from consecutive slaughtering, subjugations and exploitations by the inhuman greediest rulers since long while. የሚያሳዝነው… ይህንን መከራ አሁንም ድረስ መግታት ያለመቻላችን ነው፡፡ …. አሁን ግን መቆም አለበት… በነኚህ አናሳ የዘራፊዎች ቡድን ከመጨቆንና መበዝበዝ በላይ … በቁም ሞት የትም የለም! Weyanie will never defeat the people of Oromo… we’ll never quit struggling and submit to the domination of this disgraceful criminal minorities…..why not They’ll get armed with nuclear bomb, leave alone the light machine guns and Tanks they are producing in Bishoftu and around now.

  4. We never ever trust Woyane. Whenever they open their filthy mouth, only lie comes out. Woyane is cancer to Ethiopia.

  5. In the first place, Weyane is responsible for partitioning the country along ethnic lines in a manner that the ethnic groups remain hostile to one another. Now, Weyane’s evil intention has come back to hunt them.

  6. weyanina +yeoromo hzb tagayoch liba siserk ysmamana sikafel ytalal yetebalew lenate new sijemer yezer federalizm weym yezer kll be ethiopiya mdr lemn asfelege manew ager sechina ager neshi yaderegachu 25 amet weyanin tekamchu lemetekem yaderegachut propa ganda ye ethiopiyan hzb beamharawoch kN gzat endeteyazuna ethiopiyawi lemehonachew amhara teteyaki bemadreg yeamharan sm bemagelebabet silachu yeasiwochu sreat eske mengstu yalew sreat amharawoch bezer tederajtew endatefachu sebekachu gobez wshet le ljochachu eyesebekachu yachnu ethiopiyan lemekefafel bemecheresha fukcha getemachu ayders meslat bekat arach endetebalew amharawn baed new weron new bemalet beamhara yetejemerew yezer masdat begabila ,besumali, beafar eyale zer bematfat zer bemasdat ager mekemat mewrer tekahide zari yh hidet adis aydelem 25 amet honotal slezih behaset propaganda lezerochachn ager kll enfelgalen malet ttachu ageru yegara endehonena kezer gara mnm aynet gnNunet endelilew amnachu be ethiopiya wst yeyandandu bhir kanka ena bahl yemidabrew bezer sletekolefe sayhon hulm mahbereseb Nesanet sinorew new sle oromo yemiyasb ethiopiyan ayweklm sle tgrim yemiyasb ethiopiyan ayweklm yanew ende ager zigoch be ethiopya mdr megbabat yemaychlubet endit seferu lila tyakinew betarikachn oromo sisefr amhara alseferem weym lilaw mahbereseb alneberem yemil yelem ethiopiya ende ager stkom manm kll alneberewm slezih ke 3000shi amet jemro ethiopiya wst yalu hzboch kandu tarik wedandu bemeshgager lezari mannetachew meseret honachewal yann masdat aychlm

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*