ብሪታንያ በኢትዮጵያ ልዩ ኃይል በመባል ለሚታወቀው የፈጥኞ ደራሽ ፖሊስ ኃይል ወደ ሀያ አራት ሚልዮን ዶላር የርዳታ ገንዘብ ትሰጣለች ተባለ።

ባጭር ቃል-ፈረንዮች ሶማሊያ ላይ ተሸነፉ።ከዓለም አቀፉ አሸባሪ ድርጅት ከአል-ቃኢዳ ጋር ያበረዉ፥ በአፍሪቃዉያን ጦር ዉጊያ የተዳከመዉ አሸባብ ባንፃሩ ታ

ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ የሚካሄደው 29ኛው የአፍሪቃ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር በፊታችን ቅዳሜ ይጀመራል። በጆሃንስበርጉ የዓለም ዋንጫ ስታዲዮም ጨዋታውን የሚከ

በምርጫ አስፈፃሚው፣ ከምርጫ አስተዳደርና በምርጫው ሂደት ላይ የሚታዩ መሠረታዊ ችግሮችን በማንሣት ችግሮቹ ስለሚፈቱበት መንገድ የውይይት /ምክክር/ መድረክ እንዲመቻች ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድና ለመንግሥት አካላት ጥያቄአችንን ማቅረባችን ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የማያሣምኑ ምክንያቶች በመስጠት ጥያቄዎቻችንን ሙሉ በሙሉ ውድቅ ማድረጉን በቃል የገለፀልን ሲሆን ለመንግሥት ላቀረብነው ጥያቄ ምላሹን እየተጠባበቅን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የተጣለበትን […]

“በአለም ማየት የምትፈልገውን ለውጥ ሆነህ ተገኝ።” ማህተማ ጋንዲ ኢሳት ጃንዋሪ 8፡2013 ላይ እንዲህ የሚል አጭር የቪዲዮ ሰበር ዜና ለጥፎ ነበር፡ “የ FBI መርማሪዎች አበበ ገላውን ለመግደል የታቀደ ሴራ አከሸፉ(።) በሴራው የተሳተፉ የህወሃት ሰላዮች ምርመራ እየተደረገባቸው ነው።” ‘ሴረኛ’ ከተባሉት ሰዎች አንዱ አቶ ጉዑሽ አበራ ነው። ትናንት አርብ ምሽት አቶ ጉዑሽ አበራ ነው የተባለ ሰው በፓልቷክ የሲቪሊቲ […]

CNN HEROES, በ2007 እ ኤ አ ጀምሮ በአለማችን ለሰውልጆች መልካም አሳቢና አድራጊ ናቸው የሚባሉ ግለሰቦችን በመፈለግ ለመልካም ተግባራቸው አለማቀፍ እውቅና እንዲያገኙና ለመልካም ተግባራቸው ምስጋና ይሆን ዘንድ በአንደርሰን ኩፐር በአመት አንድ ጊዜ የሚዘጋጅ የምርጫ ቀን ነው። መልካም ስራ ያከናወኑ በዚህ ቀን የሰሩት ተግባራት ለአለም በCNN ኔትወርክ ቀርቦ ከመሃላቸው በላጭ ተግባር ላደረገ ተገቢ ሽልማት ይሰጠዋል። ጀግናን ማወደስ […]

ቻይና እአአ በ 2012 ዓም የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ በአፍሪቃ ያፈሰሰችው ግንዘብ 45 ቢልዮን ዶላር ነበር። ይህም የቻይና እና የአፍሪቃ የንግድ ግንኙነ…

በመስከረም አበራዐፄው ስለትምህርትበሀገራችን ዘመናዊ ትምርት የተጀመረው በዐፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት ቢሆንም ከመስፋፋቱ ጋር ስማቸው በታሪክ መዛግብ

አስራደው ከፈረንሳይ
ተጣፈ ተኔ « ወተህ ወርደህ የላብህን ወዝ ትበላለህ » ብለህ ወደ መሬት ከላከው የአዳም የልጅ፤ ልጅ፤ ልጅ፤ ልጅ፤ ልጅ፤……………………

የማሊ ጦር በፈረንሣይ አየር ሃይል በመረዳት ኮና የተሰኘችውን ሰሜናዊት ከተማ የአል-ቃኢዳ አበር ከሆነው እስላሚስት ቡድን ማስለቀቁን አስታወቀ። በዘመቻው…

(መልዕክተ ተዋሕዶ -ዘ ሮኪ፤ በተለይ ደጀ ሰላም እንደጻፉት/ PDF)፦ በዚህ በውጭው ዓለም ለምንገኘው ለብዙዎቻችን፣ በተለይ ባለፉት 7 እና 8 ዓመታት ላቋቋምናቸው…

ከገና ዋዜማ ምሽት እንግዳችን የሙዚቃ አቀናባሪና ፒያኖ ተጫዋቹ አረአያ ወልደሚካል ጋር በምናደርገው ቆይታ ገና ከማለዳ ዕድሜው የጀመረውን የሙዚቃ ህይወት…

የአቶ መለስ ዜናዊ ዜና እረፍት በተሰማ ማግስት አንድ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵአዊ ከአውሮፓ ለአበበ ገላው ስልክ ይደውልለታል። ግለሰቡ ደጋግሞ ሲደውል የአበበ የእጅ ስልክ ጠፍቶ ስለነበር ሶስት ተከታታይ የድምጽ መልእክቶችን ትቶ ነበር። “አበበ እባክህን ባስቸኳይ መልሰህ ደውልልኝ። አንተን በተመለከት ከአገርቤት የመጣ መረጃ አለ።እባክህን መልሰህ በዚህ ቁጥር አስቸኳይ ደውልልኝ።” ይላል መልእክቱ። ደዋዩ ከልብ እንደተጨነቀ ከድምጹ መረዳት ይቻላል። አበበም […]

ጉዳዩን ያጠኑ ድርጅቶችና ባለሙያዎች እንደሚሉት ግን ኢትዮጵያ ባጭር ጊዜ ዉስጥ ሙስና በተለይ የባለሥልጣናት ሙስና አለቅጥ ከተንሰራፋባቸዉ ሐገራት አንዷ …

–>ዋኤል ጎኔም የግብጽ ደኅንነት ሰዎች ደብድበው የገደሉትን ካሊድ ሰኢድ ለማሰብ ‹‹እኔም ካሌድ ሰኢድ ነኝ›› የተሰኘ የፌስቡክ ገጽ ከፍቶ ለግብጽ አብዮት ያበቃ ሰው ነው፡፡ የመጀመሪያውን የአደባባይ እንውጣ ጥሪ ያቀረበው ይኸው የፌስቡክ ገጽ ነው፡፡ ዋኤል አደባባይ የወጡበትን የመጀመሪያ ቀን (ጃንዋሪ 25) አንድ ዓመት ለማክበር (Revolution 2.0 የተባለ) መጽሐፍ አሳትሟል፡፡ የመጽሐፉ ገቢ በሙሉ በአብዮቱ ለተጎዱ ሰዎች መደጎሚያ እንደሚውልም ተነግሯል፡፡ አሁን እዚህ ልጽፍላችሁ ያሰብኩት ግን ዋኤል ገጹን እና የግል ማንነቱን አስመልክቶ ለሚቀርብለት ጥያቄ ይሰጥ የነበረውን መልስ ነው (መጽሐፉ ላይ እንዳሰፈረው)፤ ዋኤል ኢትዮጵያዊ ቢሆንና የከፈተው ገጽም ኢትዮጵያዊ ቢሆን ኖሮ… በሚል ምናባዊ ምሳሌ፡፡ ስለዚህ ጽሑፉ በዋኤል የተጻፈው በኢትዮጵያኛ ተተርጉሞ ነው ልትሉት ትችላላችሁ፡፡

ስምህ ማነው?
[1]ስሜ ሽብሬ ደሳለኝ ነው፤
[2]ስሜ ዩሱፍ አብደላ ነው፤
[3]ስሜ እስክንድር ነጋ ነው፤
[4]ስሜ ርዕዮት አለሙ ነው፤
[5]ስሜ አሕመዲን ጀበል ነው፤
[6]ስሜ አንዱአለም አራጌ ነው፤
[7]ስሜ በቀለ ገርባ ነው፤
[8]ስሜ ኦልባና ሌሊሳ ነው፤
[9]ስሜ መስፍን ነጋሽ ነው፤
[10]ስሜ አርጋው አሽኔ ነው፤
ስሜ…. ብዙ ነው፡፡
እኔ በጎዳና ላይ የተገደልኩ፣ ያለወንጀሌ የታሰርኩ፣ ያለሀጢያቴ የተገረፍኩ፣ መብቴን በፍርሐት የተነጠቅኩ፣ ከገዛ አገሬ የተሰደድኩ ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡
ዕድሜህ ስንት ነው?
ዕድሜዬ ይህን ያህል ነው አልልም፤ ነገር ግን ከተወለድኩ ጀምሮ ያለው ያው አምባገነን መሪ ነው፤… ሙስናውም ያው ነው፤…. ጭቆናው ያው ነው፤… እናም በአገሬ የገነነው የፖለቲካ ፓርቲ ‹‹ተስፋ የለም›› ይባላል፡፡
ከጠቀስካቸው ሰዎች ጋር ዝምድና አለህ?
እነዚህ ሰዎች የተኛውን ውስጤን ቀስቅሰውታል… ዕድሜ ለነርሱ አሁን ለውጥ ማምጣት እንደምችል ይሰማኛል፤… ታዲያ በራዕይ አልተዛመድንም ማለት ይቻላል?… አንድም ቀን አግኝቻቸው የማላውቃቸው እነዚህ ሰዎች ወንድሞቼ/እህቶቼ ናቸው፡፡
ይህንን የምታደርገው ለምንድን ነው?
ወገኖቼ ላይ የሚደርሰውን በደል ተመልክቼ ወደጥናት ክፍሌ ስገባ እምባዬን መግታት አልችልም፤… ፍርሐት የተጫናቸው ኢትዮጵያውያን ምን ያህል ውርደትን እንደሚታገሱ አየሁ… ከራሴ በመጀመር በፍርሐት የምሠራውን ስህተት ሁሉ ማረም ጀመርኩ፤ እናም ለዛ ነው ይህንን ገጽ የፈጠርኩት፡፡ ለተበደሉ ወገኖቼ ያለቀስኩት ለሞቱ ዘመዶቼ ካለቀስኩት በላይ ነው… በየዕለቱ ፎቷቸውን ስመለከት ድብታ ውስጥ እገባለሁ፤ ኢ-ፍትሐዊነትን እስከመጨረሻው ለመዋጋትም ለራሴ ቃል እገባለሁ፡፡
ማነው በገንዘብ የሚረዳህ?
ፈጣሪ ይመስገን፣ የገንዘብ ምንጮቼ ብዙ ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ንቃተ ሕሊናዬ ነው… ይህ ምንጬ በቀን አራት ሰዓተ ብቻ እንድተኛ እና ጠዋትም ፊቴን ከመታጠቤ በፊት የፌስቡክ ገጼን እንድከፍት ያስገድደኛል፡፡

ሁለተኛው ምንጬ መማሬ ነው፡፡ በመማሬ ደስተኛ ነኝ፤ ዕውቀቴን አገሬን ለማገልገል አውለዋለሁ፡፡
ሦስተኛው ምንጬ የልጆች አባት መሆኔ ነው፡፡ ሁሌም የሚጨንቀኝ ልጆቼ አንድ ቀን ‹‹አባዬ፤ ዜጎች ሲጨቆኑ እያየህ አቅምህ የሚፈቅደውን ለምን አላደረግክም?›› ብለው ይጠይቁኛል ብዬ ነው፡፡
የመጨረሻው ምንጬ የሕዝብ ፍቅር ነው፡፡ አይቶኝ የማያውቅ፤ አይቼው የማላውቀው እና በስም የማንተዋወቀው ሕዝብ ፍቅር… በየዕለቱ የአመሰግናለሁ ማስታወሻ ይደርሰኛል…. የተለያዩ ዲዛይኖች፣ ሎጎዎች፣ ቪዲዮዎች ይልኩልኛል… ገጹ ብዙ ሰዎች ጋር እንዲደርስ ያስተዋውቁልኛል፡፡
ስለዚህ ምንድን ነው የምትፈልገው?
ይህንን ገጽ የፈጠርኩት ራሴን ከአደጋ ለመጠበቅ ብቻ አይደለም.. ነገር ግን አገራችን መልሳ የኛው የሕዝቦቿ እንድትሆን ከመፈለግ በላይ ሌላ ዓላማ የለኝም… አንድ ቀን እንዲህ ይሆናል ብዬ አልማለሁ፡- እርስ በእርስ ዳግም እንዋደዳለን፤ ሁላችንም ኢ-ፍትሐዊነትን እንቃወማለን፤ ከመሐከላችን ማንኛውም ሰው ክፉ ነገር ቢያይ ራሱ ይፈታዋል… እናም የመንግሥት ቅጥረኛ አንድን ዜጋ በጥፊ ከመምታቱ በፊት አንድ ሺሕ ጊዜ ያስብበታል፡፡
አትፈራም?
በጣም እፈራለሁ እንጂ፤… ፍርሐት እኮ የሰው ልጅ ተፈጥሮ ነው… ለተጨቆኑ ዜጎች የሚቆረቆር እንደእኔ እና እናንተ ያለ ሰው ግን ካለ ፍርሐቴ ይከስማል… ዕጣፈንታችንንም የምንወስነው እኛው ራሳችን እንሆናለን… እንዲህ እያልን፡- ‹‹ማንም ያለዕድሜው አይሞትም፣ ማንም ያለወንጀሉ አይታሰርም፣ ማንም አገሩን ለቅቆ አይሰደድም…›› አንድ ዘመዴ በ25 ዓመቱ ሞተ… ቁም ነገር ካልሠራሁበት የኔ ዕድሜ መርዘሙስ ምን ዋጋ አለው?
ብዙ ሰዎች ይህንን ለማመን ይቸገራሉ፤ እውነቱን ለመናገር ቃሉ የወጣው ከልቤ ነው… አገሬን ከልቤ እወዳታለሁ እናም በተሻለ ሁኔታ የምንኖርባት አገር እንድትሆን እፈልጋለሁ፡፡ መፈንቅለ መንግሥት ወይም አብዮት የማቀጣጠል ዓላማ የለኝም… እራሴን እንደፖለቲካዊ መሪም አልቆጥርም… ዋሊያዎችን እና ሉሲዎችን የሚደግፍ፣ ካፌ ደጃፍ ላይ ቁጭ ብሎ ተቆራጭ እየበላ፣ ማኪያቶ እየጠጣ ጋዜጣ የሚያነብ ተራ ዜጋ ነኝ፡፡… የሚከፋኝ ብሔራዊ ቡድናችን በሰው አገር ሲሸነፍ ነው፡፡ … ቁምነገሩ በኢትዮጵያዊነቴ መኩራት እፈልጋለሁ፡፡… ማንም ሰው የዜግነት ክብሩን ተገፍፎ እንዲጨቆን አልፈልግም፡፡ ይኸው ነው ምኞቴ፡፡
—-
[1] – ሽብሬ ደሳለኝ፤ ምርጫ 97ን ተከትሎ በተነሳው ብጥብጥ የመንግሥት ጥይት ሰለባ የሆነች ወጣት ተማሪ፤ [1] – ዩሱፍ አብደላ፤ በተመሳሳይ ወቅት የተገደለ የኮተቤ መምህራን ኮሌጅ ተማሪ፤
[3] – እስክንድር ነጋ፤ በሽብርተኝነት ተከሶ የተፈረደበት ጋዜጠኛ፤
[4] – ርዕዮ ዓለሙ፤ መረጃ ለሽብርተኞች አቀብለሻል በሚል የተፈረደባት ጋዜጠኛ፤
[5] – አሕመዲን ጀበል፤ በሙስሊሞች የመጅሊስ ይቀየር ጉዳይ የታሰረ፣ ጋዜጠኛ እና ደራሲ፤
[6] – አንዱአለም አራጌ፤ ሽብር አሲረሃል በሚል የተፈረደበት የአንድነት ፓርቲ አባል፤
[7] – በቀለ ገርባ፤ ከኦነግ ጋር ግንኙነት አለህ በሚል የተፈረደበት የኦፌዴን ም/ሊቀመንበር፤
[8] – ኦልባና ሌሊሳ፤ ከኦነግ ጋር ግንኙነት አለህ በሚል 8 ዓመት የተፈረደበት የኦብኮ አባል፤
[9] – መስፍን ነጋሽ፤ በሽብርተኝነት አዋጅ/ክስ ምክንያት ከተሰደዱ የቀድሞዋ አዲስ ነገር ጋዜጠኞች አንዱ፤
[10] – አርጋው አሽኔ፤ የመረጃ ምንጩን እንዲሰጥ በመንግሥት ኃይሎች በግዴታ በመጠየቁ የተሰደደ ጋዜጠኛ፤

click here for pdfከጥቂት ቀናት በፊት ታዋቂው ምሁር ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ‹መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ› በሚል ርእስ አንድ አነጋጋሪ፣ አከራካሪና …

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለዉ “ከሁሉም ግን ፍቅር
ይበልጣል።”

(READ THIS ARTICLE IN PDF)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በውስጧ ብቻ ሳይሆን ከ

ርዕዮት ዓለሙ ከዚሕ ቀደም የበታች ፍርድ ቤት አስራ-አራት ዓመት እስራትና የገንዘብ መቀጮ በይኖባት ነበር።ይግማኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ግን ቅጣቱን ወደ አምስት-ዓመታት እስራት ዝቅ አድርጎታል።ርዕዮት ዓለሙ ለሰበር ሰሚዉ ችሎት አቤት ያለችዉ የአምስት ዓመቱ እስራትም የሕግ አተረጓገም ክፍተት አለበት በሚል ነበር የጋዜጣ …

የርዕዮት ዓለሙ ክስና የጠበቃዋ ተቃዉሞ Read more »

እንዲህ ያለ ዘመን ፣ዘመነ ጋንድያ፤ ሰው እንዴት ይሆናል፣ ከርሞ እንዳ ጥጃ፤ በሃገራችን ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ተማሪዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ ይገለፃል። ይህንንም ለማስቆም በትምህርቱ ዓመት መጀመሪያ ላይ የተመዘገቡትን ተማሪዎች ቁጥር መምህራን ተረክበው በዓመቱ መጨረሻ ማስረከብ እንዳለባቸው ለመፍትሔነት ቀርቧል። መምህራንም የደረጃ እድገት፣ የደመወዝ ጭማሪ ለማግኘት የተረከቧቸውን ተማሪዎች ቁጥር ሳይቀነሱ ማስረከብ እንደሆነ ተገልጿል። ይህን ዓይነት ቁጥጥር በሰሜን ኮሪያ ‘labor […]

click here for pdf ይህንን ደብዳቤ ላንቺ የምጽፈው የገናን በዓል ከልቤ የምወደው በዓል ስለሆነ ነው፡፡ የምወደው ደግሞ የገና ዛፍ ተተክሎ፣ በጥጥ ተውጦ፣ በከ…

በጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ላይ የበታች ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ማፅናቱ ያሣዘናቸው መሆኑን ዓለምአቀፉ የሴቶ

በኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስለተመሰረቱት ሶስት የስራ ዘርፎች እንዲያራሩልን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፓብሊሲቲ ጉዳዮች ሚኒስትር ዲኤታ…

የሰው ልጅ ላይ ሊፍጸም የማይገባው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት የመን ውስጥ ባሉ የተደራጁ አፋኞች ዜጎቻችን ላይ እየተፈጸመ ነው፡፡ ሰኞ ታህሳስ 29 ቀን በዓልን በገመድ ታንቀው ሲደበደቡ ከነበሩ እና ከሞት ተርፈው ሰነዓ ከገቡ ልጆች ጋር አሳለፍኩ፡፡ ሰውነታቸው ላይ በድብደባ ያረፈውን ቁስል እያየን አንገታቸው ላይ ገመዱ የከረከራቸው ምልክት ሰቅጥጦን ከሞት እንዴት እንደተረፉ እያወጉን በእንባ ታጅበን አሳለፍን፡፡ በዓልን ለማክበር ሁሌም […]

የሰው ልጅ ላይ ሊፍጸም የማይገባው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት የመን ውስጥ ባሉ የተደራጁ አፋኞች ዜጎቻችን ላይ እየተፈጸመ ነው፡፡ ሰኞ ታህሳስ 29 ቀን በዓልን በገመድ ታንቀው ሲደበደቡ ከነበሩ እና ከሞት ተርፈው ሰነዓ ከገቡ ልጆች ጋር አሳለፍኩ፡፡ ሰውነታቸው ላይ በድብደባ ያረፈውን ቁስል እያየን አንገታቸው ላይ ገመዱ የከረከራቸው ምልክት ሰቅጥጦን ከሞት እንዴት እንደተረፉ እያወጉን በእንባ ታጅበን አሳለፍን፡፡ በዓልን ለማክበር ሁሌም […]

ከጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ህልፈተ ህይወት በኋላ ባለፈዉ መስከረም ወር አጋማሽ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የጠቅላይ ሚንስትርነቱን ስልጣን ሲይዙ ፤ የ