የደኅንነትና ፀጥታ መጠበቅ ለአንዲት ሀገር ያለው ፋይዳ መኖርንና አለመኖርን በሚወስን መልኩ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ ለዚህም ሲባል ሁሉም የዓለም ሀገሮች ከውስጥም ሆነ ከውጭ ሊሠነዘሩ የሚችሉ የደኅንነትና የፀጥታ ሥጋቶችን ከወዲሁ ለመከላከልና የመከላከል ደረጃንም አልፈው በእውን ቢከሠቱ ትልቅ ጉዳት ሳያስከትሉ ለማምከን ብዙ ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ለዚህ ተግባር ስኬት ሲባልም የደኅንነት(ኢንተሊጀንስ)፣ የፀረ-ደኀንነት(ካውንተር ኢንተሊጀንስ)፣ የምጣኔ ሀብታዊ ደኅንነት (ኢኮኖሚክ ኢንተሊጀንስ) የመከላከያ፣ የፖሊስና […]

ቃላት እየከዱኝ እንዴት እንደምጅምር ተቸገርኩ፡፡ አንዳንዴ ደስታ ያደርጉትን ያሳጣል፡፡ በተለይማ ደስታና ተስፋ በጠፉበት የጨለማ ዘመን ውስጥ አልፎ አልፎ እንደብርቅ የሚታዩ የሃሤት ምንጮች ሲገኙ በደስታ ብዛት ጮቤ ያስረግጣሉ፡፡ ቴዲ አፍሮ ያደረገውን ስሰማ ጆሮየን ማመን አቃተኝ፡፡ በዚህ ዘመን እንዲህ ዓይነት ፍቅር – (Agape, Platonic love,) ሊኖር ስለመቻሉ ጥርጣሬ ስለነበረኝ የአለማመን ስሜቴ አየለብኝ፡፡ ነገር ግን ልጁ – ይህ […]

አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን/ዳላስ ቴክሳስ በዚህ በያዝነው ሰሞን ከአገርቤት የሚሰማው ሁሉ መልካም ነገር አይደለምና ብዙ ሰው ዳግም ሀዘን ውስጥ ገብቷል። የዚህ ትውልድ ብርቅ ልጆች በመታሰር ላይ ናቸው። አቶ አንዷለም አራጌና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከሌሎች ጋዜጠኞች ጋር ሆነው ወደ እስር ዳግም ተወርውረዋል። እነዚህ ለዚህች አገር መልካም አሳቢ፣ ተቆርቋሪ ወጣቶች ይህ የመጀመሪያ ጊዜአቸው አይደለም። ምርጫ 1997 አስታኮ ሕወሐት/ኢሕአዴግ […]

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሰንበቻውን የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ ያወጣው አዋጅ በኅብረተሰቡ ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

“በሽብር” ተግባር ተጠርጥረው ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ከሚገኙት እስረኞች መካከል የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ /ኢብአፓ/ ፕሬዝደንት አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር፣ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፣ጋዜጠኛ ርዕዮትዓለሙና ወ/ሮ ሂሩት ክፍሌ በትላንትናው ዕለት ፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል፡፡ መዝገቡ ተቀጥሮ የነበረው በክስ አቀራረቡ ላይ የተከሳሽ ጠበቆች ባቀረቡት ተቃውሞ ክሱ እንዲሻሻል ፍ/ቤቱ ብይን በመስጠቱ ነው፡፡ ተሻሽሎ በቀረበውም ክስ በተመሳሳይ ሁኔታ ጠበቆች […]

ሊቢያን ለአርባ ሁለት ዓመታት ቀጥቅጠው የገዙት ኮሎኔል ጋዳፊ በትውልድ መንደራቸው ስርት ውስጥ እጎርፍ ማስወገጃ ቱቦ ውስጥ ተገኙ። እንደተባለው ከሆነ ከወርቅ የተሠራ ሽጉጣቸውን የመጠጣት እድል እንኳን ሳያገኙ በአልባሌ ጥይት ቆሰሉ። “አይጦች፣ በረሮዎች፣ ሃሽሻሞች፣ ዱርየዎች” እያሉ በሰደቧቸው እና የመድፍ ናዳ ሲያወርዱባቸው በነበሩ ወጣት አብዮተኞች ጫማ ተረገጡ፣ ተጎሸሙ። በጥፊ ተመቱ፤ ተዋረዱ። በመኪናም ታስረው ተጎተቱ:: እየጮሁ በአሳዛኝና በአዋራጅ ሁኔታ […]

ከሰሞኑ የመለስ ካድሬዎች አንድ ሙግት ይዘዋል። እንደ መለስ ያለ ብሄራዊ ስሜት ያለው መሪ በኢትዮጵያ አልተነሳም የሚል። መለስ ለአሜሪካና ለአውሮፓ መንግስታት ከሚያጎበድዱ ሞታቸውን ይመርጣሉ ብለውም ያሞካሿቸዋል። ይሄንንም እውነት ነው ብለን እንድንቀበለው ይገፋፉናል። መለስ ዜናዊ ያን አሳፋሪ ተክለ ሰውነቱን እንዲገነቡለት አይጋ ፎረም የተባለውን ድህረ ገጽ አቋቁሞና ነውረኛ ግለሰቦችን ቀጥሮ ነጋሪት እያስጎሰመ ነው።የአይጋ ፎረምና የእድምተኞቹ ከንቱ ጩኽት የአገሪቷን […]

በአውሮፓ ከሚገኙ 11 አገሮች የተወጣጡ የግንቦት 7 የአህጉርና የአገራት ተወካዩች ባለፈው ቅዳሜና እሁድ እንደፈረንጆች አቆጣጠር ኦክቶበር 22 እና 23 ከአውሮጳ ዋና ከተማ ከብራስልስ 30 ኪሜትር ርቄት ላይ በሚትገኘው የሉቨን ከተማ ተሰባስበው ንቅናቄያቸው ስለሚያካሄደው ሁለገብ ትግል በሰፊው እንደተወያዩና የአቋም መግለጫም እንዳወጡ የንቅናቄው የህዝብ ግንኙነት ክፍል አስታወቀ። ከስዊድን፤ ከኖርዌዬ፤ ከዴንማርክ፤ ከፊንላንድ፤ ከሲውዘርላንድ፤ ከኢስፔን፤ ከፈረንሳይ፤ ከጀርመን ከእንግሊዝ፤ ከኒዘርላንድስና […]

ተቃዋሚዎቻቸውን አንዴ ሽብርተኞች ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ በሃሺሺ የደነዘዙ አይጦች በማለት ሲያጣጥሉ የነበሩትን የሙአመር ጋዳፊ የውርደት አሟሟት የተመለከቱ በርካታ ኢዮጵያዊያን የመለስ ዜናዊ የመጨረሻ እጣ ፋንታ ተመሳሳይ ሊሆን እንደሚችል በስፋት እየተነበዩ መሆኑን በአዲስ አበባና አጎራባች ከተሞች የሚኖሩትን የህዝብ አስተያየት ያሰባሰቡ የግንቦት 7 ዘጋቢዎች ለዝግጅት ክፍላችን በላኩት ዜና ገለጹ። ሙአመር ጋዳፊ በዙሪያቸው ያደራጁትን የመከላኪያ ሠራዊት ብዛትና ጥንካሬ […]

ሰሞኑን አምባገነኑ መለስ ለአሻንጉሊቱ የኢትዮጵያ ፓርላማ ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ ፤ ከወትሮው በተለየ መልኩ በዘረኛው መለስ አስተያዬት ዙሪያ ሀሳባቸውን ለመስጠት እንዳልተፈቀደላቸው መጥቀሳቸውን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት ዘገበ። “ይህ ነገር መታረም ካልቻለ  ምናልባትም ለምክር ቤቱ ጥያቄዎቻችንን አስገብተን መለስ መልስ እንዲሰጥና እኛም ሂደቱን በቴሌቪዥን ብንከታተል የሚሻል ይመስለኛል” ያሉት አቶ ግርማ፤ “የምክር […]

ኢትዮጵያን በዘርና አሃይማኖት ከፋፍሉ የመግዛት አባዜ የተጠናወተው የወያኔ አገዛዝ የከፋፋይነት መርዙን በሃገሪቱ ከረጨ ወዲህ በበርካታ የኢትዮጵያ ክልሎች ግጭቶች እየተከሰቱ ሲሆን ላለፉት 13 ዓመታት “እኛ ሃላባዎች እንጂ ሃድያዎች አይደለንም፤” በሚል የማንነት ጥያቄ ሲያነሱ የቆዩ ናቸው የተባሉ በሃዲያ ዞን ውስጥ የሚገኙ ሦስት ወረዳዎች፣ ጥያቄያቸው ምላሽ በማጣቱ ወደ ግጭት በማምራት ላይ መሆናቸው ታወቀ። ቁጥራቸው አሥር የሚደርሱ በሃዲያ ዞን […]

ኢትዮጵያዊያንን በጠመንጃ ሃይል ረግጦና በስልጣን ወምበር ላይ ተፈናጥጦ ለዘመናት መቆየት የሚፈልገው ዘረኛ የወያኔ አገዛዝ እድሜየን ያሳጥራሉ ብሎ የፈራቸውን የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራር አካላት፣ አባላት፣ አክቲቪስቶችና ጋዜጠኞች  ሽብርተኞች ናችሁ የሚል ታፔላ እየለጠፈ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት በግፍ ሲያጉር እንደቆየ የሚታወቅ ሲሆን ይህኑ ተግባሩን በማስፋፋት፣  በመድረክ አባላት ላይ የሚያደርገውን ማሳደድ አጠናክሮ መቀጠሉ ተዘገበ። የኢትትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት […]

በብሪታኒያ ጥልቅ የፖለቲካ የምክክር መድረክ የሆነዉ ቻታም ሃዉስ የአፍሪቃ ፕሮግራም አማካሪና ተመራማሪ ሮጀር ሚድልተን ኢትዮጵያ ሶማሊያን በመዉረር አልሼባብን አጠናክራለች ሲሉ  ገለጹ።  ተመራማሪው ይህንን የገለፁት ባለፉት አምስት ቀናት ዉስጥ የኬንያ ወታደሮች በሶማሊያ ዉስጥ ጣልቃ መግባታቸዉን በማስመልከት በሰነዘሩት አስተያየት  ነዉ። ሮጀር ሚድልተን ይህን መሰል ያልታሰበበትና አሉታዊ የሆነ ጣልቃ ገብነት የሚያስከትለዉን ዉጤት ካለፈዉ የኢትዮጵያ ወረራ ያለመማር ስህተት እንደሆን […]

የእኛኑ ገሀነብ ማን እንዲያፈርስልን? እፉኝ ነኝ እንዴ ወፍ ዘራሽ መደዴ በንፋስ አቅጣጫ  ሚወሰን መንገዴ። ብናኝ አቧራ ነኝ? ከጠጠር የከሳ እፍ ባሉት ቁጥር በኖ የሚነሳ ። ቆሻሻ ነኝ እንዴ? የምድር ላይ ጥራጊ ከግም ከብስብሱ አንድ ላይ ታሻጊ። አረም ነኝ ወይ እንዴ? ተመዝዤ እምጣል የማበብ መብት ያጣሁ ከፍጥረታት መሃከል። እንዴት ልገልጸው ነው ሰውነት የኔን የክብር አቅል አጥቶ  […]

ከሎሬት ጸጋዬ ገብረመድን በጦቢያ  መጽሄት  ቅጽ 12 ቁጥር 10 ግንቦት ወር 1997 ወጥቶ ከነበረ የተወሰደ ይድርስ ግንቦት ሰባት ይድረስ እናት ዓለም ግንቦት ሰባት፣ ተራሮችሽ ተሰለፋ! ግንቦት ሃያን አሳፈሩ! በድል ድባብ ተንሳፈፉ የጥላቻን ዓይን ጥላ፣ በአንድነታቸው ገፈፉ ትውልድሽ እምቦቀቅላሽ፣ በአገር ፍቅር ተቃቀፉ የኢትዮጵያዊነትን ማተብ፣ በቁርጥ ቃል አበሰሩ የምስራች ተቀዳጁ! የምስራች ተባበሩ። እናት ዓለም ግንቦት ሰባት፣ ትውልድሽ […]