ሐምሌ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአረና የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ወይዘሪት ተክለ ደስታ የኣብራሃ ደስታ እህት በመሆንዋ ብቻ ከስራዋ ታግዳለች ። ወይዘሪት ተክለ ደስታ የጤና ባለሙያ ስትሆን የህወሓት ኣባልና የራያ ዓዘቦ ወረዳ የጤና ፅህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ ሁና ታገለግል ነበር። የወረዳው ባለስልጣናት “አንቺ እንደ ወንድምሽ ዓረናነሽ ፣ ላንቺ የሚሆን የህወሓት ሃላፊነትም ይሁን የሞያ ስራ …

ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-”ለከፈልነው መስዋትነት አቻ ውጤት እናመጣለን” በሚል መፈክር የተካሄደው ተቃውሞ ወደ ደም አፋሳሽ ግጭት አምርቷል። የፌደራል ፖሊሶች ሆን ብለው ባስነሱት ግጭት ቁጥሩ በውል ያልታወቀ ሙስሊሞች ቆስለዋል። በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ እየታፈሱ ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። ኢሳት እስካሁን ከገለልተኛ ወገን ለማረጋገጥ ባይችልም አንዳንድ ሙስሊሞች  ስልክ በመደወል  የተገደሉ ሙስሊሞች መኖራቸውን ተናግረዋል። …

ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያኑ በእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት በመገኘት ፣ የኢህአዴግ መንግስት በግንቦት7 ዋና ጸሃፊ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ በወሰደው ህገወጥ እርምጃ የእንግሊዝ መንግስት ጠንካራ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል። በስፍራው የነበረውን ዘጋቢያችን ወንድማገኝ ጋሹን አነጋግረነዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ፎሬን ፖሊሲ መጽሄት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በተመለከተ ሰፊ ዘገባ አቅርቧል። በምስራቅ …

ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትግራይ ክልል ባለስልጣናት በጸገዴ ወረዳ አካባቢ የሚገኙ በአማራው ክልል ስር ተካለው የሚገኙ በርካታ ቀበሌዎችን መውሰዳቸውን ተከትሎ ፣ የአማራ ክልል ታጣቂዎች ድርጊቱን በመቃወም ከትግራይ ክልል ታጣቂዎች ጋር ተፋጠው እንደሚገኙና በማንኛውም ሰአት ግጭት ይፈጠራል ተብሎ እንደሚፈራ የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ወደ 400 የሚጠጉ የአማራ ክልል ታጣቂዎች ወደ ድንበሩ የተጠጉ ሲሆን፣ …

ሐምሌ ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለሰአታት በቁም እስር ላይ የነበሩት የታዋቂው ፖለቲከኛና የሰብአዊ መብት ታጋይ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ታላቅ እህት ወ/ሮ ብዙአየሁ ጽጌ የወንድማቸውን ጉዳይ ለመከታተል በሚል ከ10 ቀናት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ቢያመሩም፣ ከትናንት በስቲያ ደህንነት ጽ/ቤት  ከተጠሩ በሁዋላ አገሪቱን በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ ተነግሯቸዋል። በታዘዙበት ሰአት ለመመለስ እንደሚቸገሩ የተናገሩት ወ/ሮ ብዙአየሁ፣ የ 24 ሰአት …

ሐምሌ ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የመከላከያ ምንጮች እንደገለጹት ባለፉት 20 ቀናት ብቻ ከባድሜ ግንባር ከ 107 ያላነሱ ሰዎች ከድተው ወደ ኤርትራ እና ወደ መሃል አገር አቅንተዋል። ከ15 ቀናት በፊት በባድሜ አካባቢ ሲያጎ በተባለው ቦታ ላይ የሰፈሩ 60 የ 33ኛ ክፍለጦር አባላት በአንድ ሌሊት ሰራዊቱን ጥለው የጠፉ ሲሆን፣ ኤርትራ መድረስና አለመድረሳቸውን ለማወቅ የተደረገው ጥረት …

ሐምሌ ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወራት በፊት በየረር ባሪ ጎሳዎች የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ከታሰሩት 19 አገር ሽማግሌዎች መካከል 2ቱ በእስር ቤት ውስጥ ማረፋቸው ታውቋል። የማረሚያ ቤቱ ሃላፊዎች አስከሬን ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው ሟቾቹን በራሳቸው ጊዜ በመቅበራቸው የብሄረሰቡ ተወላጆች ተቃውሞ አስነስተዋል። ተቃውሞውን በሃይል ለመጨፍለቅ የክልሉ ፕሬዚዳንት ልዩሚሊሺያዎችን ወደ አካባቢው በመላክ ላይ እያሉ ፣ ከአዲስ አበባ …

ሐምሌ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በርካታ ቁጥር ያላቸው በደቡብ አፍሪካ የተለያዩ ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከጆሃንስበርግ ተነስተው የእንግሊዝ ቆንስላ ወደሚገኝበት ፕሪቶሪያ በማምራት በግንቦት7 ዋና ጸሃፊ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የተወሰደውን ህገወጥ እርምጃ ከማውገዝ በተጨማሪ ከእነሱ የሚጠበቀውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። በተቃውሞ ሰልፉ ላይ የተገኘችው ዝናሽ ሃብታሙ  ኢትዮጵያውያኑ አንዳርጋቸውን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን ነጻ እናወጣለን ማለታቸውን ገልጻለች …

ሐምሌ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲዎቹ ለኢሳት በላኩት መግለጫ   የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የቅድመ ውህደት ስምምነት ፊርማ ካኖሩ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት ውህደቱን ምሉዕ ለማድረግ የጋራ ኮሚቴ በማቋቋም እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ አስታውሰው፣ ለውህደቱ መሳካት የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን ሰፊ በመሆኑ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ደጋፊዎቻችን የአቅማቸውን ድጋፍ ለማድረግ በስምምነት …

ሐምሌ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተለያዩ ሰበቦች እየቀረቡበት የሚራዘመው የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የፍርድ ሂደት ዛሬም በችሎት አዳራሽ ለውጥ ምክንያት እንዲራዘም ተደርጓል። በአቶ አቡበክር ምዝገብ የተከሰሱት ኮሚቴዎች፣ የመከላከያ ምስክር ለፍርድ ቤቱ ማስደመጥ እንደጀመሩ ነበር የችሎት ሂደቱ በሰባሰብ እንዲራዘም የተደረገው። ዳኞችና አቃቢ ህጎች በቃሊቲ የሚገኘው የችሎት አዳራሽ ለትራንስፖርት የማያመች በመሆኑ እንዲቀየርላቸው ባመለከተቱት መሰረት አዲሱ …

ሐምሌ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤድስ ኤጀንሲ እንደገለጸው ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ በብዙ አገሮች የኤደስ ወረርሽኝ ስርጭት እየቀነ ሲሆን ፣ ስርጭቱንም ከ14 አመታት በሁዋላ  ማቆም እንደሚቻል ገልጿል። አሁንም በርካታ ዜጎች መድሃኒት አጥተው በመሰቃየት ላይ መሆናቸውን ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ገልጿል። በዚህ አመት በአለም ደረጃ 2 ሚሊዮን 300 ሺ ሰዎች ብቻ በኤች …

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ለእንግሊዝ የአፍሪካ ክፍል ሃላፊ በጻፈው ደብዳቤ፣ አቶ አንዳርጋቸው የህግና የማማከር አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ ” የሚመለከታቸው አካላት” መፍቀድ አለባቸው ብሎአል። የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ” የሚመለከታቸው አካላት” ያላቸውን አካላት በስም ከመጥቀስ ተቆጥቧል። ይሁን እንጅ የመረጃው ምንጮች እንደሚሉት ” የሚመለከታቸው አካላት” የተባሉት የደህንነት ሰዎች ናቸው። የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ይህን መልስ የጻፈው፣ …

ሐምሌ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረታቦር ከተማ የከተማው እና የዞኑ አመራር ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ኗሪዎች በመሰረተ ልማት ፤ በመልካም አሰተዳደር ችግር እየተሰቃዩ መሆናቸውን ገልጸዋል። ይህ አለም ደጉ የተባሉ የደብረ ታቦር ኗሪ ” የጋማ ከብት እና ሰዎች በአንድ ላይ እየጠጡ መሆናቸውንና ይህም ሁኔታ ለውሃ ወለድ በሺታ እንደዳረጋቸው ተናግረዋል፡፡ አቶ ፍስሃ ይ …

ሐምሌ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮ ቴሌኮም በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ፈሶበት  በሥራ ላይ የነበረውን የኖኪያ ኔትወርክ ነቅሎ በመጣል በቀላሉ ለስለላሥራ በሚመች መልኩ በአዲስ መልክ ለመትከል በቻይናው ሁዋዌ ኩባንያ እየተከናወነ ያለው የአዲስ አበባ የቴሌኮም ማስፋፊያ ሥራ በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ማሳካት አለመቻሉን  ምንጮቻችንገልጸዋል፡፡ ሁዋዌ በ800 ሚሊየን ዶላር በያዝነው ዓመት ህዳር ወር 2006 የማስፋፊያ ስራውን በአዲስ …

ሐምሌ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃማስና በእስራኤል መካከል የተጀመረው ጦርነት ፣ በግብጽ አደራዳሪነት ለሰአታት ጋብ ብሎ የቆየ ቢሆንም፣ እስራኤል ድብደባውን እንደገና መጀመሯን ቢቢሲ ዘግቧል። በግብጽ የቀረበውን የሰላም ስምምነት እስራኤል ብትቀበለውም፣ ሃማስ ግን ስምምነቱ ሽንፈትን እንደመቀበል ይቆጠራል በሚል ሳይቀበለው ቀርቷል። ይህን ተከትሎም እስራኤል የአየር ድብደባውን እንደገና ጀምራለች። እስካሁን በደረሰው ጥቃት ከ192 በላይ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል፤ በብዙ …

ሐምሌ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያኑ ዛሬ በኖርዌይ የእንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ የአቶ አንዳርጋቸውን ተላልፎ መሰጠት በእጅጉ አውግዘዋል። ከፍተኛ ቁጣ ባስተናገደው ተቃውሞ እንግሊዝ እየወሰደችው ያለው እርምጃ እንዲብራራላቸው ጠይቀዋል። በኖርዌይ  የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት  ፊት ለፊት ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ ደግሞ በቅርቡ ከደቡብ ሱዳን ተይዘው ለኢህአዴግ የደህንነት አባላት ተላልፈው የተሰጡትን የአቶ ኦኬሎ አኳይን …

ሐምሌ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቅዳሜ እና እሁድ በጠቅላይ ሚኒስትር አዳራሽ  የጸረ ሽብር ግብረሃይሉና የኢህአዴግ ባለስልጣናት በጋራ የመከሩ ሲሆን፣ስኬታማ ስራዎችን ለመስራት  3 ሚልየን 400 ሺ ዶላር ወጭ ማድረጉን ገልጿል፡፡ “ኢሳያስ ቢያስፈልገን  እርሱን የመያዝ አቅም ላይነን” በማለትራሱን ያሞካሸውግብረሃይሉ ፣ “ኢህአዴግንግስት ንቧን በመያዙየቀጣዩምርጫድልበርላይይገኛል” ሲልበሪፖርቱ አትቷል። ከሁሉምክልሎችየደህንነትሃይሎችአመራሮችበተካፈሉበትውይይትበቀጣይከግንቦትሰባትሊፈፀምይችላልየተባሉ ስጋቶችም ተነስተዋል።  የመከላከያሃይሉልዩትዕዛዝተሰጥቶትየተዘናጋበትንክልልእንዲሸፍንናከፍተኛጥንቃቄእንዲወስድመመሪያእንዲሰጠው ተወስናል፡፡ “ግንቦትሰባትእስከጎንደርያለምንምእንከንቀድሞመግባትይችላል”የሚለው ሪፖርቱ፤የመከላከያሃይሉእናየደህንነትስራውየላላበመሆኑመጠናከርአለበትብሎአል። ይህንን ተከትሎም በተሰብሳቢዎች መካከል …

ሐምሌ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአስተዳደር ፀጥታ እና የፖሊስ ኮሚሺን በጋራ የ2006 ዓ.ምየ11 ወራት አፃፀም በገመገሙበት ውይይት የጎጃም ፤የጎንደር ፤የሺዋ እና የኦሮሞ አርሶ አደሮች  ዛሬምበድብቅመሳሪያዎችንበነፍስወከፍበየቤቱይዘው እንደሚገኙያወሱሲሆን፣ አርሶ አደሩ የጦር መሳሪያውን እንዲመልስጥረትቢደረግምአልተሳካምብለዋል፡፡ አዲስህግእንዲወጣየጠየቁትየፀጥታሃይሎች  በአርሶአደሩበህገወጥእጅየተሰገሰገውከ 4 ሚሊዩንበላይየሚገመትየተለያየየጦርመሳሪያ በአገሪቱ ለሚፈጸም ግድያ ዋና መንስኤ መሆኑን   አመልክተዋል፡፡ በዘመቻየጦርመሳሪያማስፈታትእናየቅጣትወሰንመመሪያእንደሃገርአለመኖርችግር  መሆኑንበማንሳትየፊደራል መንግስት የህገወጥመሳሪያቁጥጥርአዋጅእንዲያወጣበሪፖርታቸውጠይቀዋል፡፡ የፌድራልፖሊስ መረጃ እንደሚያመለክተው ከአማራ ክልል በመቀጠል አፋር እና …

ሐምሌ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርላማ : ባህል ፣ ቱሪዝምና መገናኛ ብዙሃን ቋሚ ኮምቴ ስብሳቢ 73ኛ የምስረታ ዓመቱን በቅርቡ ያከበረውን የኢትዮጽያ ፕሬስ ድርጅት በቁሙ እየሞተ መሆኑን በመጠቆም በራሱ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይትችትአቀረቡ፡፡ የቋሚ ኮምቴው ስብሳቢ ወ/ሮ ፈቲያ ዩሱፍ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ዓርብ እና ቅዳሜ እለት በታተመ ቃለ ምልልሳቸው እንደተናገሩት የአዲስ ዘመን ፣ ኢትዮጵያ …

ሐምሌ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የየመን መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ህገወጥ በሆነ መልኩ አሳልፈው ከሰጡዋቸው በሁዋላ ኢትዮጵያውያን አሁንም ቁጣቸውን እየገለጹ ሲሆን፣ አንዳንድ ወገኖች ” የአቶ አንዳርጋቸው መታሰር ልብን የሚሰብር ቢሆንም፣ ወሳኙ ነገር ማዘን ሳይሆን ለለውጥ ቆርጦ በመነሳት መታገል ነው” ብለዋል። በሌላ በኩል ደግሞ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የየመን መንግስት የወሰደውን እርምጃ እንዲሁም …

ሐምሌ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በረመዳን ጾም ተጠናክሮ የቀጠለው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ፣ ዛሬም በበኒ መስጂድ እጅግ ከፍተኛ ህዝብ በተገኘበት ተካሂዷል። ኢትዮጵያውያኑ ሙስሊሞች ” የእምነት ነጻነታችን ይከበር፣ ለከፈልነው መስዋትነት ተመጣጣኝ ውጤት እናመጣለን” የሚሉ መፈክሮችን ጽፈው አሳይተዋል። ከሁለት አመት በላይ የዘለቀው የሙስሊሙ ተቃውሞ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መሪዎቹ እየገለጹ ነው።

ሐምሌ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ተጠናክሮ የቀጠለው እስር በአገሪቱ ውስጥ ምንም አይነት ተቃውሞ እንዳይኖር ያደረገ ነው ብሎአል። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ያሉበት ሁኔታ አለመታወቁንና ለከፍተኛ ስቃይ ሊዳረጉ እንደሚችሉ መግለጹንና አለማቀፉ ማህበረሰብ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ ማሳሰቡን ያስታወሰው አምነስቲ፣ ከዚሁ ጋር በተያያዘ አቶ ደንኤል ሽበሺ፣ አብርሃ ደስታ፣ የሽዋስ አሰፋና ሀብታሙ …

ሐምሌ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ሰሞኑን ከአገር ቤት በሚደወሉ ስለኮች የተጨናነቀ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ደዋዮች የኢህአዴግን ስርአት በሃይል ለመፋለም መቁረጣቸውን የሚገልጹ ናቸው። እንደሰሞኑ ሁሉ ” መንገዱን አሳዩን እና አቶ አንዳርጋቸው ይዘውት የተነሱትን ራእይ እውን እናድርገው ” የሚሉ ወጣቶች እየተበራከቱ ሲሆን፣ አንዳንዶች ደግሞ ህዝቡ ራሱን እያደራጀ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባው እያሳሰቡ ነው። አንድ አስተያየት ሰጪ መንግስት …

ሐምሌ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በፌደራል ፖሊሶች እየተደበደበ ወደ አልታወቀ ስፍራ ተወስዶ የነበረው ታዋቂው ፖለቲከኛና ጸሃፊ አብርሃ ደስታ ማእከላዊ እስር ቤት መታሰሩ ታውቋል። የአብረሃ መኖረያ ቤት በፖሊሶች እንደተፈተሸም ለማወቅ ተችሎአል። የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወጣት ሃብታሙ አያሌው፣ የፓርቲው ምክትል የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ዳንኤል ሽበሺ እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ የሽዋስ …

ሐምሌ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህወሃት አባል የሆነውና በሶማሊ ክልል የደህንነት ሃለፊ በመሆን ሲሰራ የነበረው መቶ አለቃ አወጣሃኝ በክልሉ ፕሬዚዳንት ትእዛዝ እንዲታሰር ተደርጓል። ግለሰቡ በምን ምክንያት እንደታሰረ ለማወቅ ባይቻልም፣ በክልሉ ፕሬዚዳንት እና በህወሃት የጸጥታ ሰራተኞች መካከል እየተካረረ የመጣው አለመግባባት ማሳያ መሆኑን ከስፍራው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።

ሐምሌ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአገር ውስጥ እና በውጭ ከፍተኛ ጫና የተፈጠረበት የኢህአዴግ መንግስት የአቶ አንዳርጋቸውን ምስል በቴሌቪዥን ካቀረበ በሁዋላ የተለያዩ አስተያየቶች በማህበራዊ የመገናኛ መንገዶችና በስልክ እየተሰጡ ነው።አብዛኛው አስተያየት ሰጪ በቴሌቪዥን የቀረበው ምስልና ድምጽ መቆራረጡን ፣ ኢቲቪን የሚያክል ድርጅት ጥራት ያለው  ቀረጻ ለማካሄድ አለመቻሉ ገዢው ፓርቲ ለፕሮፓጋንዳ የሚሆን ነገር ለማግኘት አለመቻሉን ገልጸዋል። ሚኒሊክ ሳልሳዊ  …

ሐምሌ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ከአገር ቤት በተከታታይ የሚደወሉ ስልኮችን ለማስተናገድ ከአቅሙ በላይ እንደሆነበት እየገለጸ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ደዋዮች አቶ ለአቶ አንዳርጋቸው ያላቸውን ከበሬታ የሚገልጹና ኢህአዴግን በሃይል ለማንበርከክ የሚታገሉትን ቡድኖች ለመቀላቀል እንዴት እንደሚቻል የሚጠይቁ ናቸው። በሌላ ዜና ደግሞ የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የተፈጸመውን የአፈና ተግባር አውግዟል። ትህዴን ” የወያኔ አምባገነን …

ሐምሌ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢህአዴግ  የጸጥታ  ሃይሎች  የአንድነት ፓርቲን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ  የሆነውን ወጣት ሃብታሙ  አያሌውን ፣  የፓርቲውን  የድርጅት ጉዳይ  ምክትል  ሃላፊ  አቶ  ዳንኤል ሽበሺ፣ የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነውን የሽዋስ አሰፋን እንዲሁም በማህበራዊ የመገናኛ ብዙሃን ከመቀሌ በመጻፍ የሚታወቀውና አረና ፓርቲ አባል የሆነው  መምህር አአብራሃ ደስታን ይዞ አስሯል። እሰረኞቸ ማእከላዊ በሚባለው …

ሰኔ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የየመን የጸጥታ ሃይሎች የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አሳልፈው በሰብአዊ መብት ጥሰትና ህዝብን በማሰቃየት በአለም የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ዘወትር ለሚወገዘው ለኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች አሳልፈው መስጠታቸው ያበሳጫቸው በአገር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የነጻነት ትግሉን የምንቀላቀልበትን” መንገዱን ምሩን” በማለት ጥያቄ ሲያቀርቡ፣ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ደግሞ የተቃውሞ ሰልፎችን እያዘጋጁ ነው። ለኢሳት …

ሰኔ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ታዋቂው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሂውማን ራይትስ ወች ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ፣ አቶ አንዳርጋቸው ከማንም ጋር እንዳይገናኙ ተደርጎ ለኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች ተላልፎ መሰጠቱን ከታማኝ ምንጭ ማግኘቱን ገልጿል። የየመን ባለስልጣናት ሰነዓ ከሚገኘው ኤል ራህባ አየር ማረፍያ ላይ እኤአ ጁን 23 ወይም 24 ከእንግሊዝ ኢምባሲ ጋር እንዳይገናኝ አድርገው አቶ አንዳርጋቸውን ወዲያውኑ ወደ ኢትዮጵያ …

ሰኔ ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጅቱ ፣ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓም ባወጣው መግለጫ ፣ “የየመን መንግሥት በህገወጥ መንገድ ያገተብንን የንቅናቀዓችንን አመራር በአስቸኳይ እንዲፈታ በተለያዩ መንገዶች ላለፈው አንድ ሣምንት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም ” ብሎአል። “የአገሩን የረዥም ጊዜ ጥቅም ማየት የተሳነው የየመን መንግሥት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ይልቅ አምባገኑን ወያኔ መርጦ መሪያችንን ለእርድ አሳልፎ ሰጥቶብናል ፣በዚህም …

ሰኔ ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንዲት እናት ” እኔ ሁለት ልጆች አሉኝ፣  ልጆቼን ዛሬ ብሰጥ ደስ ይለኛል” ሲሉ በአቶ አንዳርጋቸው መያዝ የተሰማቸውን ስሜት በለቅሶ ገልጸዋል። አንድ ወጣት ደግሞ እርሱና ጓደኞቹ በአቶ አንዳርጋቸው መያዝ ወደ ትግል ፈጥነው እንዲገቡ እንደሚያደርጋቸው ገልጸዋል። “ቀድሞ ዘርዘሩን ዘርቷል” በሚል ቅኔ የተቀኙት አንድ ኢትዮጵያ ደግሞ በአንዳርጋቸው መስዋትነት፣ ነጻነታችንን እውን እናደርጋለን …

ሰኔ ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአንዋር መስጊድ እጅግ በርካታ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በተካሄደው ተቃውሞ ፣ መንግስት “መጅሊሱን ለህዘበ ሙስሊሙ እንዲያስረክብ እንዲሁም የታሰሩትን መሪዎች እንዲፈታ” ጠይቀዋል። “ትግሉ የጽኑዎች ነው፣ ፍትህ ይስፈን፣ የእምነት ቤቶቻችን ይከበሩ፣ የታሰሩት ይፈቱ፣ የትግላችንን መነሻ እናሳካው የማነፍርበት የትግል መዳረሻችን ነው፣ አፈና ግፍና ማስገደድ ይቁም” የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል። ሙስሊሙ ኢትዮጵያውያን በረመዳን ጾም …

ሰኔ ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በርካታ የሌሎች አካባቢ ሰዎች ተፈናቅለው፣ በቴፒ ከተማ ኤግዢቢሽን አዳራሽ ሰፍረዋል። ሰፋሪዎች በምግብ እና በውሃ ችግር ለአደጋ መጋለጣቸው ታውቋል። እስካሁን ከ700 ያላነሱ ሰዎች ተፈናቅለዋል። ግጭቱ ካለፉት 3 ቀናት ጀምሮ ከቁጥጥር ውጭ መውጣቱ ተነግሯል። ልዩ ፖሊስና የወረዳው ፖሊስ፣ ዘመናዊ መሳሪያ ከታጠቁት የሸኮና መዠንገር ተዋጊዎች ጋር እየተዋጋ መሆኑ ታውቋል። ሸኮና መዠንገር …

ሰኔ ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል ” አንዳርጋቸው የማይጨበጥ ጽኑ መንፈስ እንጂ አንድ ግለሰብ አይደለም” በሚል ርእስ ባወጣው ጠንካራ መግለጫ ” የየመን መንግሥት የፈጸመው ድርጊት እጅግ  ስህተት  መሆኑን  ዘግይቶም ቢሆን  ተረድቶ የነፃነት ታጋዩን እንዲለቅ” አስጠንቅቋል።  ይህ ባይሆን ግን ይላል የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል ” አንዳርጋቸው ወያኔ እጅ ውስጥ ከገባ  የትውልዱ  የበቀል ሰይፍ …

ሰኔ ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመላ አገሪቱ የስልክ መልእክቶችን በመደወል ለአቶ አንዳርጋቸው ጀግንነት ድጋፋቸውን የሚገልጹ፣ በእርሱ መታሰር የኢትዮጵያ ህዝብ የተሰማውን ስሜት የሚገልጹና ስለቀጣዩ ህዝባዊ እርምጃ አስተያየቶችን የሚሰጡ በርካታ የስልክ መልእክቶች ለኢሳት እየደረሱ ነው። “እድሜየ 50ዎቹ አጋማሽ ነው፣ ከስራ ውየ ስገባ የሰማሁት ዜና አስደንግጦኛል፣ ስሜቴን መቆጣጠርም አልቻልኩም፣ ቤተሰቤን ልጆቼን ትቼ ትግሉን ለመቀላቀል ወስኛለሁ” በማለት …

ሰኔ ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአፓ የየመን የጸጥታ ሃይሎች በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የወሰዱትን እርምጃ በጽኑ አውግዞ፣ የአገሪቱ መንግስት በአስቸኳይ እንዲለቀው ጠይቋል። አንዳርጋቸው በአምባገነኖች ፍርድ ቤት በሽብር ወንጀል ተከሶ ሞት የተፈረደበት በመሆኑ፣ ተላልፎ ቢሰጥ ለከፋ ስቃይና ሞት ሊዳረግ እንደሚችል አስጠንቅቋል። የአቶ አንዳርጋቸው መታሰር አደገኛ የሆነ አሰራር የሚፈጥር በመሆኑ ድርጊቱ በጽኑ ሊኮነን ይገባዋል ሲል ኢህአፓ …

ሰኔ ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአሜሪካ መንግስት ባወጣው መግለጫ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያላቸው የሽብር ድርጅቶች ጥቃት ለመፈጸም በመዘጋጀት ላይ ለመሆናቸው አስተማማኝ መረጃ እንደደረሰው አመልክቷል። ይህን ተከትሎም በእንግሊዝ፣ በአሜሪካ እና በሌሎችም አገራት አየር መንገዶች ላይ የሚታየው ጥበቃ ተጠናክሯል”” ኡጋንዳም በአየር መንገዷ ላይ ሽብር ሊፈጸም ይችላል በሚል ከፍተኛ ጥበቃ እያደረገች ነው።

ሰኔ ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የየመን መንግስት የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን  ማገቱን ተከትሎ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚኖሩ ዜጎች ቁጣቸውን እየገለጹ ነው። አላማጣ አካባቢ የሚኖሩ አንድ አስተያየት ሰጪ  ” የየመን መንግስት ያገተው አንዳርጋቸውን ብቻ ሳይሆን መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ነው። በዚህ የቁርጥ ቀን ልጅ ላይ አንድ ነገር ቢደረግ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆ ብሎ …

ሰኔ ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድ ታፍኖ የተወሰደ የፍልስጤም  ወጣት መገደሉን ተከትሎ ፍልስጤማውያን ቁጣቸውን እየገለጹ ነው። የ17 አመቱ ወጣት ሙሃመድ አቡ ካድር በመኪና ታፍኖ ሲወሰድ የአይን ምስክሮች ማየታቸውን ተናግረዋል።  ፍልስጤማውያን ከእስራኤል ፖሊሶች ጋር መጋጨታቸውን ተከትሎ የእስራኤሉ መሪ ቤንጃሚን ናታንያሁ  ግድያውን አውግዘው፣ የእየሩሳሌም ከንቲባ የህዝቡን ቁጣ እንዲያበርዱ አሳስበዋል። የፍልስጤም መሪዎች በበኩላቸው እስራኤል 3 ወጣቶች …

ሰኔ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የንቅናቄው የስራ አስፈጻሚ አባልና የህዝባዊ እምቢተኝነት ዘርፍ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አበበ ቦጋለ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፣ የየመን የጸጥታ ሃይሎች አቶ አንዳርጋቸውን በአስቸኳይ ይለቁት ዘንድ ለአገሪቱ ፕሬዚዳንት ደብዳቤ ከመጻፍ ጀምሮ በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፎችን እና ሌሎች እንቅስቃሴዎችን የሚያደርጉበትን መንገድ እያመቻቹ ነው። ግንቦት7 ለየመን ፕሬዚዳንት ፊልድ ማርሻል አብዱ …

ሰኔ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የየመን የጸጥታ ሃይሎች የግንቦት7 ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸውን ማፈናቸውን ተከትሎ በፌስቡክ፣ በቲውቲርና በድረገጾች ላይ የተለያዩ አስተያየቶች ተሰጥተዋል። አክቲቪስት አበበ ገላው በበኩሉ የመንአቶአንዳርጋቸውጽጌንማገቷሌላአደገኛናበጣምአሳሳቢክስተትነው።የአንባገነኑየህወሃትስርወመንግስትተቃዋሚዎችንማንምአገርበምንምአይነትሁኔታማፈን፣ማሰርናማንገገላታትአለምአቀፍህግንየሚጥስህገወጥድርጊትነው።የመንአቶአንዳርጋቸውንለወያኔአሳልፋእንዳትሰጥናያለምንምቅድመሁኔታእንድትለቅሁሉምነጻነትናፋቂኢትዮጵያዊሁሉበጋራጥረትሊያደርግይገባል።የየመንኤምባሲዎችንበያሉበትበተቃውሞማጨናነቅናእንቅልፍመንሳትእንዲሁምአለምአቀፍጫናማድረግያስፈልጋል።ግዜሳይረፍድይህንንየቁርጥቀንኢትዮጵያዊለመታደግበያለንበትበጋራእንረባረብ።” ሲል ጥሪ አቅርቧል። ፕራይድ ዲ ባሰፈረው ጽሁፍ ደግሞ ” እውነተኛ ታጋይ ሊታሰር ሊሞት ይችላል፣ የተጀመረውን ትግል ግን ሊያስሩትም ሆነ ሊገሉት ከቶ አይቻላቸውም። ኢትዮጵያም አንድ …

ሰኔ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሶስት የእስራኤል ወጣቶች ታፍነው ከተወሰዱ በሁዋላ መገደላቸው እንደታወቀ የእስራኤል መንግስት ድርጊቱን በፈጸመው በሃማስ ላይ እርምጃ እንደምትወስድ ማስታወቁዋን ተከትሎ በአካባቢው ያለው ውጥረት አይሏል። የአገሪቱ መሪ ጠ/ሚ ናትኒያሁ ” ወጣቶቹ በሰው እንስሶች ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ” ተገድለዋል ያሉ ሲሆን፣ በሃማስ ላይ አስፈላጊው እርምጃ ይወሰዳል ሲሉ ዝተዋል። ይህን ተከትሎም ማምሻውን እስራኤል በሃማስ …

ብአዴን ለመጪው ምርጫ ዝግጅት በሚል በተለያዩ የአማራ ክልሎች እያካሄደ ባለው ውይይት የአዊ ዞን ነጋዴዎችና ነዋሪዎች መንግስት በየጊዜው በሚያወጣው መመሪያ መሰላቸታቸውንና ቤት አፍርሱ በመባላቸው ለችግር መደረጋቸውን ገልጸዋል። በውጭአገራት ለረጅም አመታት ኖራ፣ በአነገሯ ኢንቨስት እንድታደርግ ተጠይቃ ወደ አገሯ የገባች ነዋሪ ፣ ወደ አገሯ ከመግባቱዋ በፊት ሲነገራት የነበረው ማግባቢያና ወደ አገሯ ከተመለሰች በሁዋላ በአካል ያየችው ነገር እንደተለያየባት ገልጻለች። …

በማህበራዊ ድረገጾች በመጻፍ የሚታወቁት የዞን ዘጠኝ አባላት እሁድ እለት ችሎት ቀርበው የነበረ ቢሆንም፣ አሁንም ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል። ፖሊስ ምርመራየን አልጨረስኩም፣ ግብረአበሮቻቸውም አልተያዙም በሚል ሰበብ የ28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ የ15 ቀናት ጊዜ ተፈቅዶለታል። አቤል ዋበላ፣ በፈቃዱ ሃይሉና ማህሌት ፋንታሁን የተባሉ ወጣት ጸሃፊዎች ለሀምሌ 7 ቀን 2006 ዓም ተቀጥረዋል። ችሎቱን ለመከታተል የሄደው ህዝብ ወደ ችሎት …

አፍሪካን ፕሬስ ኤጀንሲ እንደዘገበው 10 የሱዳን ወታደሮች በኢትዮ -ሱዳን ድንበር አካባቢ ከተገደሉ በሁዋላ በድንበር አካባቢ ውጥረት ሰፍሯል። እሁድ እለት ደግሞ ተጨማሪ 13 የሱዳን ወታደሮች መቁሰላቸው የተዘገበ ሲሆን፣ ጥቃቱም በኢትዮጵያ ሚሊሺያዎች ሳይፈጸም እንዳልቀረ ተዘግቧል። የሱዳን ኮማንዶ ጦር ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ሃይሉን እያሰባሰበ መሆኑን የገለጸው ዘገባው፣ በአንድ ወር ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ መካሄዱን ጠቅሷል። ሱዳንና ኢትዮጵያ የድንበር ከተሞቻቸውን …

መንግስት በሙስና ወንጀል የከሰሳቸው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ የቀድሞዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ እና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ገብረ ዋህድ ወልደጊዮርጊስ የእምነት ክህደት ቃላቸውንለፌዴራልከፍተኛፍርድቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት የሰጡ ሲሆን፣ አቶ ገብረውሃድ “በኢትዮጵያቴሌቪዥን 16 ቤትአለውተብሎበካሜራተቀርፆመነገሩየሚያሳዝንመሆኑን ፣ እርሳቸውበአዲስአበባውስጥአንዲትጐጆእንደሌላቸውና ቢኖራቸው ኖሮ ልጆቻቸው መጠለያ እንደማያጡ ተናግረዋል። ‹‹እንደከሳሾቼ 100,000 የማከራየውቤትየለኝም፤›› በማለት ንጽህናቸውን ለማስረዳት የሞከሩት አቶ አቶ ገብረውሃድ፣ …

ሰኔ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የሰላማዊ ተቃውሞ ታሪክ ውስጥ ረጅም ጊዜ በማስቆጠር ክብረወሰን የሰበረው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ፣  በረመዳን ጾም መግቢያም ” በአንድነታችን እንጸናለን” በሚል መፈክር ተካሂዷል። እንደወትሮው ሁሉ እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በአንዋር መስጊድ በተካሄደው  የጸሎት ስነስርአት፣ ሙስሊሙ “በአንድነታችን እንጸናለን” የሚሉ በወረቀት ላይ የተጻፉ መፈክሮችን ከፍ አድርጎ በማሳየትና እጅ ለእጅ በመያያዝ መልእከቱን አስተላልፏል። …