መኢአድና አንድነት በጋራ የጠሩት የባህርዳር የተቃውሞ ሰልፍ ቅስቀሳ በተሳካ ሁኔታ እየተካሄ ነው ሲሉ አስተባባሪዎች ገለጹ
የካቲት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሰልፉ አስተባባሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት የመኢአድ ሰሜን ቀጠና አደራጅና የተቃውሞ ሰልፉ ግብረሃይል ለኢሳት እንደገለጹት የተቃውሞ ሰልፉን ለመከልከል መንግስት የተለያዩ መንገዶችን ቢጠቀምም፣ አስፈላጊውን መስዋትነት በመክፍል ቅስቀሳቸውን እያደረጉ ነው። የክልሉ መስተዳደር ዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ፈቃድ መስጠቱንም አቶ ሽፈራው ተናግረዋል። የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አለምነው መኮንን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው …