ታኀሳስ ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ሙክታር ከድር ሰሞኑን ለክልሉ 5ሺ473 ፖሊሶች የሰጡት የማዕረግ ዕድገት መጪውን ምርጫን በመንግስት መዋቅር፣ በጀትና ጊዜ ተጠቅሞ ለማሸነፍ ኢህአዴግ የዘረጋው ስትራቴጂ አካል እንደሆነ ታዛቢዎች ተናገሩ፡፡ መጪው ምርጫ ሊካሄድ አምስት ወራት ብቻ በቀሩት በዚህ ጊዜ የማእረግ እድገት በብዛት መስጠት ለምርጫ ከሚሰጥ የጉቦ ቀብድ ተለይቶ አይታይም ያሉት …

ታኀሳስ ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ነዋሪዎች እንደገለጹት በሰሜንና በደቡብ የአገሪቱ ክፍሎች የነዳጅ እጥረቱ ተባብሶ ቀጥሎአል፡ በአዋሳ ነዳጅ ለመቅዳት መኪኖችና ሞተረኞች ተሰልፈው ሲጠባባቁ ታይቷል። የነዳጅ  ዋጋ በመላው አለም በከፍተኛ ደረጃ  ቢቀንስም በኢትዮጵያ መጥፋቱ ጉዳዩን አነጋጋሪ አድርጎታል።

ታኀሳስ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የውሃ፣ የመስኖና የኢነርጂ ሚኒስትር አለማየሁ ተገኑ ህዳር 26 ቀን 2007፣ በቁጥር ውመአሚ 1/01/67 በጻፉት ደብዳቤ ” በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች በከፍተኛ ወጪ ተገንብተው ለበርካታ ኢንተርፕራይዞች የመስሪያና መሸጫ አገልግሎት የሚውሉ ህንጻዎችና ሼዶች በኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ችግር ምክንያት ለታለመላቸው አላማ ለማዋል ” አልተቻለም ብለዋል። “በእነዚህ ማእከላት ውስጥም በከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ የገቡና …

ታኀሳስ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው  የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን ጨምሮ 10ሩም ተከሳሾች የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ 19ኛው ወንጀል ምድብ ችሎት  ቤት ቢቀርቡም ሌላ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች የሆኑት አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና አቶ …

ታኀሳስ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባንኩ እንደሚለው በርካታ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩባቸው አገሮች ቅርንጫፎችን በመክፈት በአመት እስከ 2 ቢሊዮን ዶላር የሚሆነውን፣ ከባንክ ውጭ የሚደረገውን ገንዘብ የማስተላለፍ ዘዴ ለመቆጣጠር አስቧል። አሜሪካ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስና ሳውድ አረቢያ በመጀመሪያው ዙር የንግድ ባንኮች ቅርንጫፎች ከሚከፈትባቸው አገራት ተርታ ተመድበዋል። ባንኮቹ መከፈታቸው ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው የሚልኩትን ገንዘብ ለመጨመር እንደሚረዳም …

ታኀሳስ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከፍተኛ ዝግጅት ይከበራል የተባለው የህወሃት 40ኛ አመት በአል ወጪ የሚሸፈነው ከመንግስት ካዝና መሆኑ በአባል ድርጅቶች መካከል መነጋገሪያ አጀንዳ እየሆነ መምጣቱን የሚናገሩት የኢህአዴግ ምንጮች፣ ከመንግስት ካዝና ለሚወጣው ገንዘብ የተሰጠው ሰበብ  ገጽታ ግንባታ የሚል መሆኑን ገልጸዋል። ህወሃት በአሉን ከድርጅቱ ካዝና በተለይም የአገሪቱን ሲሶ ሃብት ከተቆጣጠረው ኢፈርት ካዝና መጠቀም እየቻለ፣ ወጪውን …

ታኀሳስ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክልሉ መንግስት የሃማኖት፣ የእድር፣ የአፎቻ መሪዎችን፣ የአገር ሽማግሌዎችንና ታዋቂ ግለሰቦችን በራስ መኮንን የህዝብ አዳራሽ ታህሳስ 5 ቀን 2007 ዓም ሰብስቦ ባወያየበት ወቅት ፣ ከ1990-2004 ዓም ባለው ጊዜ ውስጥ የተሰሩ ቤቶች በሰነድ አልባ ቤትነት የተመዘገቡ እና ከከተማው ማስተር ፕላን ጋር የማይጋጩ ከሆነ ህጋዊ ይደረጋሉ፣ ከ2004 ዓም እስካሁን ካርታና ፕላን …

ታኀሳስ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን እንደ ሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች በነዳጅ አቅርቦት ሲቸገሩ የቆዩት የባህርዳር የታክሲና ባጃጅ አሽከርካሪዎች ዛሬም ድረስ ችግሩ ተባብሶ መቀጠሉን ለዘጋቢያችን ተናግረዋል። በትናንትናውና በዛሬው እለት በከተማዋ ካሉት ከአስር በላይ ማደያዎች በአንዱ ብቻ ነዳጅ የሚገኝ መሆኑን የተናገሩት አሽከርካሪዎች ፣ በዚህ ነዳጅ ማደያ ለመቅዳት እስከ ሁለት መቶ ሜትር ተሰልፈው ለሰዕታት እንደሚቆዩ ተናግረዋል፡፡ …

ታኀሳስ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለአንድ አመት ያክል ተቋርጦ የነበረው የደቡብ ሱዳንን የሰላም ስምምነት እንደገና ለማስጀመር እንቅስቃሴ መጀመሩን የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስዩም መስፍን አስታውቀዋል። ድርድሩ የተጀመረው በአዲስ አበባ ነው። ሁለቱ ተፋላሚ ሃይሎች በተለያዩ ጊዜያት ለድርድር ቢቀመጡም እስካሁን ይህ ነው የሚባል መፍትሄ ሊያመጡ አልቻሉም። የኢሳት የዲፕሎማቲክ ምንጮች እንደሚሉት በደቡብ ሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል ያለው …

ታኀሳስ ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ የፌደራልና የክልል የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊዎች በባህርዳር በተሰባሰቡበት ወቅት የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም ፣ ይህን የተናገሩት የሃይማኖት ተቋም የፖለቲካ ፍላጎት ማራመጃ መሆኑን ለማስረዳት ነው። ዶ/ር ሽፈራው ከአፋር የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ ” መንግስት ለምን በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ይገባል? ለምንስ በአገራችን የሌለ ችግር ያመጣብናል?” በሚል ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። …

ታኀሳስ ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ሰዎች እንደገለጹት በአፋርና በኢሳ መካካል ያለውን የቆየ የድንበር ውዝግብ ተከትሎ መንግስት የተወሰኑ ቦታዎች ወደ አፋር ክልል እንዲካተቱ መወሰኑን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ 7 ሰዎች በጸጥታ ሃይሎች ሲገደሉ ከ30 በላይ የሚሆኑ ደግሞ ቆስለዋል። በርካታ ሰዎችም ተይዘው ወደ አልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል። አሁንም በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት የሰፈነ ሲሆን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች መንግስትን …

ታኀሳስ ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ንግድ ሚኒስቴር የዋጋ ቅናሹን ካደረገ በሃላ ማደያዎች አዲሱ ታሪፍ አያወዋጣንም በሚል መናገራቸውን ተከትሎ የአቅርቦት እጥረት የተፈጠረ ሲሆን ሚኒስቴሩ የተወሰኑ ማደያዎችን በማሸግና በማስፈራራት ነገሩን ለማርገብ ቢሞክርም ችግሩ ሳይቀረፍ  8ኛ ቀኑን ይዞአል፡፡ በቦሌ፣ በካዛንቺስ፣ በንፋስስልክ በሌሎችም የከተማዋ አካባቢዎች በየማደያው ረጃጅም ሰልፎች የሚታዩ ሲሆን የችግሩ ትክክለኛ መንስኤ ምን እንደሆነ እንዳላወቁያ ያነጋገርናቸው …

ታኀሳስ ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ ባለስልጣናትን ጠቅሶ እንደሰገበው በታሊባን የተፈጸመ ነው በተባለው በሲህ ጥቃት ከሞቱት መካከል በርካታዎቹ ህጻናት ናቸው። ወታደራዊ ዩኒፎርም የለበሱ አምስት ወይም ስድስት የሚሆኑ ታጣቂዎች ወደ ትምህርት ቤቱ መግባታቸውን የትናገሩት ባለስልጣናቱ፤ ወዲያውኑ አካባቢው በደህንነቶች እንዲከበብ መደረጉን ተከትሎ የተኩስና የፍንዳታ ድምጽ መሰማቱን ተናግረዋል። ወደ 500 ከሚጠጉ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች በርካቶቹ ማምለጣቸውን …

ታኀሳስ ፮(ስድት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመድረክ የህዝብ ግንኙነት ሃለፊ አቶ ጥላሁን እንዳሻው የገዢው ፓርቲ የጸጥታ ሃይሎች ሲያደርሱት ከነበረው ጫና አንጻር ሲታይ የተሳካ የሚባል ሰላማዊ ሰልፍ መደረጉን ገልጸዋል። መጪው ምርጫ ነጻና ፍትሃዊ እንዲሆን፣ የሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እረገጣ እንዲቆም፣ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች፣ ጋዜጠኞች፣ የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ በመፈክሮች መጠየቃቸውን ገልጸዋል። በሰልፉ ላይ …

ታኀሳስ ፮(ስድት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአየር መንገድ ውስጥ ሱፐርቫይዘር አፒራንስ በሚል የሃላፊነት ቦታ ላይ ሲሰሩ የነበሩት አቶ ወረታው ዋሴ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም በሚል በፈረንጆች አቆጣጠር ከዲሰምበር 8፣ 2014 ጀምሮ ከስራቸው እንደተባረሩ የሚገልጽ ደብዳቤ ደርሶአቸዋል። አቶ ወረታው በበኩላቸው ውዝግቡ የቆየ መሆኑን በማንሳት ፣ አየር መንገዱ የወሰደው እርምጃ ከፖለቲካ አቋማቸው ጋር የተያያዘ መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ …

ታኀሳስ ፮(ስድት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ሽመልስ ከማል ከ ሚኒስትሩ ሬድዋን ሁሴን ጋር መግባባት ባለመቻላቸው አኩርፈው ቤት በመቀመጥ መደበኛ ሥራቸውን እያከናወኑ አለመሆኑን  ምንጮች ገልጸዋል። አቶ ሽመልስ ከደባል ሱስ  ጋር በተያያዘ በመደበኛ የስራ ሰዓታቸው ሊገኙ ባለመቻላቸው ሚኒስትሩ ይህን ባህሪያቸውን እንዲያስተካክሉ ቢነግሩዋቸውም ሊያስተካክሉ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የተፈጠረ መሆኑን ምንጮች ይገልጻሉ። …

ታኀሳስ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድ ከፍተኛ አቃቢ ህግ ለስዊድን ሬዲዮ እንደገለጹት ምርጫ 97ትን ተከትሎ በህወሃት/ኢህአዴግ መራሹ ጦር ለተገደሉ ንጹህ ዜጎች ተጠያቂዎች ናቸው የተባሉ 12 ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና አንድ ስዊድን አገር በሚገኝ ሌላ ወታደራዊ አዛዥ ላይ ምርመራ  እየተካሄደ ነው። ማስረጃዎች ተሰባስበው እንዳለቁ ክስ ሊመሰረት እንደሚችል የገለጹት አቃቢ ህጓ ፣ባለስልጣናቱ በየትኛውም አገራት ቢዘዋወሩ ተይዘው …

ታኀሳስ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ውስጥ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ለማድረግ የሚያስችሉ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ ለመጠየቅ መድረክ የፊታችን እሁድ የጠራው ሰልፍ እንዲደናቀፍ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ተጽእኖ ቢያሳርፉም፣ ተጽኖውን ሁሉ ተቋቁሞ የሰፈር ለሰፈር ቅስቀሳውን እያካሄደ መሆኑን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው አቶ ጥላሁን እንዳሻው ተናግረዋል። አዲስ አበባ መስተዳድር ሰላማዊ ሰልፉ እንዲካሄድ እውቅና ቢሰጥም፣ ቅስቀሳ ለማድረግ ሌላ እውቅና …

ታኀሳስ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእስር ላይ የሚገኙ የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን እንዲሁም የህሊና እሰረኞችን ጉዳይ የሚከታተሉት ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ከዚህ በፊት ለሎሚ መጽሄት በሰጡት አስተያየት ነው። ሰማያዊ ፓርቲ የሽብረተኞች መጠቀሚያ ሆኗል በሚል በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የቀረበውን ዘገባ በመተቸታቸው እንዲሁም በኢትዮጵያ የጸረ ሽብር ህግ ላይ አስተያየት በመስጠታቸው የዲሲፕሊን ክስ ቀርቦባቸዋል። አቶ ተማም የኢትዮጵያ …

ታኀሳስ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፊደራል ፍ/ቤት ከወንጀል ነፃ ናቸው በሚል ያሰናበታቸወን ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ  የክልሉ አስተዳደር እና ፀጥታ ነፃ አይደሉም በሚል ባቀረበው አቤቱታ ጉዳያቸው በክልሉ ካቢኔ መታየት ጀምሯል፡፡ የክልሉ ካቢኔ ባደረገው ውይይት ለሁለት የተከፈለ ሲሆን አንደኛው ወገን እንፍታቸው ሲል ሌላው ወገን ደግሞ በምርጫው  ላይ አሉታዊ ተጽኖ ስለሚያሳርፉ መፈታት የለባቸውም በሚል ሲከራከሩ ከቆዩ …

ታኀሳስ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በትውልድ ኢትዮጵያዊ እና በዜግነት ፊላንዳዊ የሆኑት ከፍተኛ የእርሻ ሳይንቲስት  ዶ/ር የሺጥላ ደገፉ የክብር ሜዳልያውን የተሸለሙት ባለፈው ቅዳሜ ፣ ፊንላንድ 97ኛ አመት የነጻነት በአሉዋን ባከበረችበት ወቅት ነው። ዶ/ር የሺጥላ  ዕጽዋት ከየትና እንዴት በሽታ እንደሚይዛቸው፤ እንዴትስ በውስጣቸው እንደሚተላለፍና በራሳቸውም እንዴት እንደሚከላከሉ ከ23 ዓመታት ምርምር በሁዋላ  ሂደቱን ለመጀመሪያ ጊዜ በማግኝታችው ነው። …

ታኀሳስ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ህዳር 27 በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ሲዘጋጁ በፖሊስና በደህንነቶች ቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት የ9 ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት ከእስር የተለቀቁ ሲሆን፣ ብዙዎቹ በእለቱ በደረሰባቸው ድብደባ ከመጎዳታቸውም በተጨማሪ በእስር ቤት ውስጥ የነበራቸው አያያዝ አስከፊ እንደነበር ታውቋል። የሰማያዊ ፓርቲ የአመራር አባል የሆነው ይድነቃቸው ከበደ  ደህንነቶች ወደ እስር ቤት በተደጋጋሚ …

ታኀሳስ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከህዝብ የተሰባሰበው መረጃ እንደሚያመለክተው ህዝቡ በሙስና በመማረሩ ስራ መስራት በማይቻልበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ሙስና የሚጠይቁ ሰዎችን ማጋለጥ ህይወትን እስከ ማስከፈል እንደሚደርስም የተሰባሰበው መረጃ ያመለክታል። አንድ አስተያየት ሰጪ እንደተናገሩት ሙስናን ለማጋለጥ ቢፈለግም ፣ ለሚያጋልጡ ሰዎች በቂ የሆነ የህግ ከለላ አያገኙም ሙስናን ለማጋለጥ ስንሄድ  “ጀርባቸው ይጠና ተብለን እንደገና ጉዳቱ ሙስናን …

ታኀሳስ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የምስራቅ አፍሪካ የሰብአዊ መብት ሊግ የተባለው ተቋም ለኢሳት በላከው መግለጫ በምእራብ ወለጋ በጊምቢ እስር ቤት በተከሰተው ምንነቱ ያልታወቀ በሽታ አቶ ያቆም ኒጋሩ የተባሉ የፖለቲካ እስረኛ አርፈዋል። ሌሎች በበሽታው የተያዙት 60 ዎቹ እስረኞችም ተመሳሳይ እጣ ሊገጥማቸው እንደሚችል ስጋቱን ገልጿል። ሟቹ አቶ ያእቆብ ባለፈው ሚያዚያና ግንቦት ወር በኦሮምያ ተከስቶ ከነበረው …

ታኀሳስ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው በቅርቡ በየመን የባህር ዳርቻ ያለቁትን ከ70 በላይ ኢትዮጵያውያንን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ  አደጋው ዜጎች በሀገራቸው ሰርተው መኖር አለመቻላቸውንና ሰርክ የሚለፈፈው የ11 በመቶ እድገት ዜጎችን ከስደትና ከመከራ ሊታደጋቸው እንዳልቻለ የሚያሳይ ነው ብሎአል። አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በዜጎች ሞት የተሰማውን ሀዘን ገልጾ፣   ስደትና እልቂት ከዚህ የከፋ ጉዳት ከማድረሱ በፊት ህዝቡ …

ታኀሳስ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምክር ቤቱ ህዳር 30/ 2007 ዓም ባወጣው መግለጫ “በሀገራችን ህዝባዊ ሥርዓት ለማምጣትና በህግ የበላይነት የሚያምን መንግስት ለመመስረት በምናደርገው ትግል ሁሉ የሚጠበቅብንን መስዋእትነት ለመክፈልና ሀገራዊ ግዴታችንን ለመወጣት ዝግጁ” ነን ብሎአል። “ሰማያዊ ፓርቲን ጨምሮ ዘጠኝ ትብብር የፈጠሩ ፓርቲዎች በህዳር ወር ያወጡት መርሐ ግብር አንድ አካል የሆነውን የ24 ሰዓት የተቃውሞ የአደባባይ …

ታኀሳስ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንዳንድ ተጓዞች ለኢሳት እንደገለጹት ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚታየው ፍተሻ ጨምሯል። ከዲላ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ ተሳፋሪ ለኢሳት እንደገለጸው ፖሊሶቹ ተሳፋሪውን ወዴት ነው የምትሄዱት? ለምንድነው የምትሄዱት በማለት ከመጠየቅ ጀምሮ የሰዎች ኪሶች በመግባት ፍተሻ ያደርጋሉ። በሽተኞችንና ህጻናትን የታቀፉ እናቶች ሳይቀሩ ፍተሻ በሚል ፖሊስ ጣቢያ ታጉረው መዋላቸውን …

ታኀሳስ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን ወደ የመን ሲጓዝ የነበረ ጀልባ ሰጥሞ ከ79 ያላነሱ ኢትዮጵያዊያን ያለቁ ሲሆን እስካሁን ከ14 ያልበለጡ ሰዎች ብቻ አስከሬን መገኘቱን ጋዜጠኛ ግሩም ተክለሃይማኖት ገልጿል። የሟቾች ቁጥር አስቀድሞ በመገናኛ ብዙሃን እንደተገለጸው ሳይሆን 79 መሆኑን ግሩም አክሎ ተናግሯል። በሌላ በኩል ደግሞ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሕጋዊ ጉዞን ከአንድ ዓመት በላይ አግዶ …

ታኀሳስ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት  አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት በካውች ማሞና ኦብዱል ኦቻር የሚባሉትን ባለስልጣኖች አውርዷቸዋል። ግለሰቦቹ ያለመከሰስ መብታችን የተነሳው በህገወጥ መንገድ ነው በማለት ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትን ለማግኘት ሙከራ ቢያደርጉም፣ ደህንነቶች ይዘው አስረዋቸዋል። ባለስልጣኖቹ ከውጭ ሃይሎች ጋር ትገናኛላችሁ በሚል መከሰሳቸውን የአኝዋ ሰርቫይቫል ዋና ሃላፊ አቶ ኒካው …

ታኀሳስ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘጋቢያችን በአራት ኪሎ፣ በቦሌ፣ በካዛንቺስ፣ በልደታ አካባቢዎች የሚገኙ ነዳጅ ማደያዎችን ተዘዋውሮ እንደተመለከተው በብዙዎቹ ማደያዎች በዛሬው እለት ነዳጅ ቢኖርም ነዳጅ ለመቅዳት የተሰለፉ ተሸከርካሪዎች በመብዛታቸው ረጃጅም ሰልፎች መታጣቸውንና የትራፊክ መጨናነቅ መከሰቱን መታዘብ ችሎአል፡፡ በዓለም ገበያ ላይ የነዳጅ ዋጋ መቀነስን ተከትሎ ከትላንትና ህዳር 30 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ ንግድ ሚኒስቴር መጠነኛ …

የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ስብስብ የሆነው መድረክ የኢህአዴግ አገዛዝ በህዝባችን ህገመንግስታዊ ነጻ የመምረጥ መብት ላይ የሚፈጽማቸውን የመብት ረገጣዎች እንዲያቆም፣ በሃገራችን ነፃ ፣ ፍትሃዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ተአማኒነት ያለው ምርጫ እውን እንዲሆና የምርጫ ሜዳውም ለሁሉም እኩል የተመቻቸ እንዲሆን ለመጠየቅ ለታህሳስ 5 ቀን 2007 ዓም የተቃውሞ ሰልፍ በአዲስ አበባ መጥራቱን አስታውቋል። መድረክ ለኢህአዴግ አገዛዝ የውይይትና የድርድር ጥያቄዎችን በተደጋጋሚ ቢያቀርብም፣ አገዛዙ …

ኀዳር ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ የሽግግር ካውንስል ለኢሳት በላከው መግለጫ የአፓርታይድ ስርአትን እአካሄደ ያለው የወያኔ አገዛዝ በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ የወሰደው ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ ሊወገዝ ይገባዋል ብሎአል። የኢኮኖሚ እድገት አምጥቻለሁ እያለ ፕሮፓጋንዳ የሚነዛ መንግስት ፣ በስልጣን ላይ ለመቆየት ብቸኛ መተማመኛው ሃይል መሆኑን አሳይቷል ያለው የሽግግር ካውንስል፣ ሁሉም የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎችና የአለማቀፉ ማህበረሰብ ድርጊቱን እንዲያወግዙ …

ኀዳር ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክልሉ የጸጥታ ሃላፊ እንደገለጹት በደቡብ እና በቤንሻንጉል ክልሎች አጎራባች ወረዳዎች አሉ ችግሮችን ለመፍታት አንዳንድ ሙከራዎች ቢደረጉም፣ ከሶማሊ ክልል ጋር ያለውን ችግር ለመፍታት አለመቻሉን ገልጸዋል። በደቡብ ክልል በአንዳንድ ወረዳዎች የድንበር ችግር መኖሩን የገለጹት ሃላፊው፣ ችግሩን ለመፍታት እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጸዋል። ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ጋር ያለውን የድንበር ውዝግብ ለመፍታት ተደጋጋሚ ሙከራ መደረጉን …

ኀዳር ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዳ ጉንዶመስቀል ከተማ ላይ አንድ ከተማ ውበቱ የተባለ ሰው ሃብታሙ ሺበሺ የተባለን ሰው መግደሉን ተከትሎ፣ ገዳይን ለመያዝ በተደረገ ጥረት ሰኞ ህዳር 29፣ 2007 ዓም በአካባቢው ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ተካሂዷል። ከተማ ውበቱ የተባለው ሰው በ1999 ዓም የሰዎች ለሰዎች የተባለውን ድርጅት ገንዘብ ከዘረፈ በሁዋላ …

ኀዳር ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ስደትን የህይወታቸው የመጨረሻ አማራጭ በማድረግ በጅቡቲ በኩል አድርገው ወደ የመን ለመግባት የሞከሩ 70 ኢትዮጵያውያን ቀይ ባህር ላይ ሰጥመው መሞታቸውን የየመን ባለስልጣናት ገልጸዋል። ታይዝ በምትባለዋ ግዛት የሚገኙ ባለስልጣናት ለአሶሴትድ ፕሬስ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያውያኑን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረችው ጀልባ ባጋጠማት ከባድ አውሎ ንፋስና ማእበል አል ማክታ እየተባለ ከሚጠራው ወደብ ራቅ ብሎ …

ኀዳር ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የምርጫ ስርዓት ለውጥ እንዲደረግ ለመጠየቅ ህዳር 27 ቀን የአዳር ተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ወደ አደባባይ በወጡት 9 የተቃዋሚ ድርጅት አመራሮች ላይ የፌደራል ፖሊስ አባላት ድብደባ በመፈጸም ወደ እስር ቤት ቢወስዱዋቸውም፣ የትብብሩ አመራሮች ግን ትግሉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ኢትዮጵያውያን ለትግሉ የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል። ሶስተኛ እየተባለ በሚጠራው እስር ቤት …

ኀዳር ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከዚህ ቀደም ሶማሊያ ውስጥ ዘምተው የነበሩና መከላከያን የአገልግሎት ዘመናቸውን በመጨረስ ወይም በጉዳት የለቀቁ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ መከላከያ ተመልሰው እንዲዘምቱ በደብዳቤ ጥሪ ቀርቦላቸዋል። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ጥሪው የደረሳቸው ወታደሮች ጥሪውን ለመቀበል ፈቃደኞች አልሆኑም። ጥሪ የተደረገላቸው የሰራዊት አባላት “የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለሰላም አስከባሪ ሃይል በሚል ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ …

ኀዳር ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤትን ከበው ካደሩ በሁዋላ የተወሰኑ ወጣቶችን እየለቀሙ በማሰር የተቃውሞ ሰልፉን ለማደናቀፍ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው። የነገረ ኢትዮጵያ ምክትል ዋና አዘጋጅ በላይ ማናየ፣ የሰማያዊ ፓርቲ የወጣቶች ጉዳይ ምክትል ሃላፊ እና የብሄራዊ ምክር ቤት ጸሃፊ ወጣት ሳሙኤል አበበ፣ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አባል …

ኀዳር ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ያቀረቡ የከንባታ ጠንባሮ ነዋሪዎች ህዳር 26/2007 ዓም በዱራሜ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። የከምባታ ህዝብ ኮንግረንስ ሊቀመንበር አቶ ኤርጨፎ ኤርዴሎ እንደተናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች ለኮሌጅ መስሪያ ተብሎ የተፈቀደውን ቦታ የመንግስት ሹማማምንት  ለዘመዶቻቸው አከፋፍለው በመገኘታቸው እንዲሁም ከሾኔ እስከ ዳውሮ ያለውን አስፋልት ለማድረግ ታቅዶ በለመሳካቱ ህዝቡ ተቃውሞውን …

ኀዳር ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለስልጣኑ አሳታሚዎች ዓመታዊ የንግድ ፈቃዳቸውን ለማሳደስ ወደንግድ ሚኒስቴር ሲሄዱ በየዓመቱ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ እንዲያቀርቡ የሚገደዱ ሲሆን የሙያ ብቃቱን ለማግኘት ባለፉት ወራት ወደብሮድካስት ባለሰልጣን የሄዱ አሳታሚዎች ያልጠበቁትን ግዴታ እነዲገቡ የሚቃወሙ ከሆነ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሠርተፊኬት እንደማይሰጣቸው በተነገራቸው መሠረት አብዛኛዎቹ ተገደው ፈርመዋል፡፡ በንግድ ምዝገባ ፈቃድ መስጫ መደብ ቁጥር 89 …

ኀዳር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ባዘጋጀው የ2006 የጸጥታ የደህንነት ግምገማ ላይ የተገኙ የተለያዩ ክልሎች የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊዎች ባቀረቡት ሪፖርት በአዲስ አበባ የሃይማኖት አባቶች የተሰጣቸውን የደህንነት ተልእኮ በፈቃደኝነት አምነው ሲፈጽሙ በትግራይና ፣ በአማራ ክልሎች ግን የሃይማኖት አባቶች ተልእኮዋቸውን በአግባቡ ሳይወጡ ቀርተዋል። የትግራይ ጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ እንደተናገሩት በክልሉ አብዛኛው ህዝብ የኦሮቶዶክስ …

ኀዳር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲዎቹ ጥሪውን ያስተላለፉት ህዳር 27 እና 28 የሚካሄደውን የ24 ሰአት የተቃውሞ ሰልፍ በማስመልከት ባወጡት መግለጫ ነው ገዥው ፓርቲ ወደ ስልጣን ከመጣ ጊዜ ጀምሮ በህገ መንግስቱ ካስቀመጠውና በየ መድረኩ ከሚናገረው በተቃራኒ የእምነት ተቋም መሪዎችን ካድሬዎቹ በማድረግ ህዝብን ለመያዝ እየጣረ እንደሚገኝ የሚያትተው መረጃው፣   የገዥውን ፓርቲ አካሄድ የተቃወሙ ምዕመናን በአሸባሪነት፣ …

ኀዳር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየአመቱ ህዳር 29 የሚከበረው የብሄር ብሄረሰቦች በአል አምና በጅጅጋ ሲከበር ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ሲያስወጣ ዘንድሮ ደግሞ በአሶሳ በሚከበረው እስከ 300 ሚሊዮን ብር ያስወጣል። ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች እንደሚሉት የብሄር ብሄረሰቦችንም ሆኑ  የባንዲራ፣ የመከላከያና ሌሎች አገር አቀፍ በአላትን በብቸኝነት ለማዘጋጀት የተፈቀደለት ወዛም ኮሚኒኬሽን የተባለው ድርጅት ለህወሃት ባለስልጣናት …

ኀዳር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ዞን በምስራቅ በለሳ ወረዳ የጸጥታ አስተዳደር ሰራተኞች እርስ በርስ ሲገማገሙ ከቆዩ በሁዋላ ፖሊሶቹ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊውንና አቶ ባዩ ማሩንና ሌላ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊውን በጥይት ደብድበው ገለዋል። አቶ አባይ ማሩ በጃናሞራ ወረዳ መካነ ብርሃን ከተማ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ህዳር 3 ቀን ተቀብረዋል። በተራ ፖሊስ አባላት የተወሰደው …

ኀዳር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ  ህዳር 25/2007 ዓም የመከላከያ ምስክርነቱን የሰጠ ሲሆን  ጥር 11/2004 በታላቁ አወሊያ መስጂድ ቅጥር ጊቢ ተገኝቶ  የሙስሊም መሪዎች በነጻ ምርጫ መመረጣቸውን ተናግሯል። ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሃምሌ 9/2004 የህግ አዋቂውን ኡስታዝ ካሚል ሸምሱን፣ ኡስታዝ አቡበክር አህመድን፣ ኡስታዝ አህመድ ሙስጠፋን፣  ኡስታዝ አህመዲን ጀበልን ማናገሩን ገልጿል።  የመንግስት ባለስልጣን …

ኀዳር ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፋይናንሻል ታይምስ የተባለው አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ከአለማቀፍ የግል ባንኮች ለመበደር የወሰነው የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ለግል አበዳሪ ተቋማት ባላሃብቶች የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች አስተያየቶችን እየሰጡ ነው። ፋይናንሻል ታይምስ 1 ቢሊዮን ዶላር ለመበደር ጫፍ ላይ የደረሰው መንግስት ለውጭ ባለሀብቶች የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ያልተለመደ ወይም እስከዛሬ ያልታየ ነው ብሎታል። …

ኀዳር ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ትብበሩ የንግዱ ማህበረሰብ ህዳር 27/28 2007 ዓ.ም በሚደረገው የአዳር ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ከመሳተፍ ጀምሮ በገንዘብና በሌሎችም መንገዶች ድጋፉን እንዲገልጽ ጠይቋል። ኢህአዴግ ወደ ስልጣን በመጣበት ጊዜ ጀምሮ ነጻ ገበያን እንደሚከተል በመግለጹ የንግዱ ማህበረሰብ በነጻ ገበያ መርህ ተወዳድሮ ራሱንም አገሩንም ይጠቅማል የሚል ተስፋ የነበረ ቢሆንም ይህ ተስፋ እውን ሳይሆን …

ኀዳር ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-9ነኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል የሚያስተናግደው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል  ዝግጅት ማጠናቀቁን ቢገልጽም፣ በአካባቢው መንግስትን  የሚቃወሙ ኃይሎች በተለያየ ጊዜያት በደፈጣ ውጊያ ጥቃት  ማድረሳቸው ያሰጋው መንግስት በአካባቢው ከፍተና ወታደራዊ ሃይል አሰማርቷል። ህዳር 29 ከሚካሄደውን በዓል ጋር ተያይዞ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል ብዙዎች የሚሰጉ ሲሆን፣  ጥቂት የማይባሉ አመራሮች፣ ባለሃብቶችና ታዋቂ ሰዎች …

ኀዳር ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ጀርመንን ለመጎብኘት መገኘታቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያውያኑ መንግስትን የሚያወግዝ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። ጠ/ሚንስተሩ ከጀርመን መሪ አንግላ መርከል ጋር ተገናኝተዋል። ታዋቂው የጀርመን ባንክ ለኢትዮጵያ መንግስት በድር ለመስጠት ከተዘጋጁት ባንኮች መካከል ቀዳሚው ነው። ጉብኝቱም ከዚሁ ጋር የተያያዘ መሆኑን መዘገባችን ይታወቃል።  

ኀዳር ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል መንግስቱ የ2006 የጸጥታ አጠባበቅ ግምገማ በሚያደርግበት ስብሰባ ላይ እንደተገለጸው በአዲስ አበባ 7ቱም የሃይማኖት ተቋማት ከመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ጋር በጋራ በመቀናጀት የደህንነት ስራ እየሰሩ ነው። አጠቃላይ ውይይቱን በተመለከተ ለኢሳት የደረሰው ሚስጥራዊ የድምጽ መረጃ እንደሚያስረዳው በአዲስ አበባ በተቋቋመው መዋቅር ውስጥ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች የሚገኙበት ሲሆን፣ መንግስት መኪና፣ ኮምፒዩተር፣ …