ኀዳር ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ትብብሩ ህዳር 27 እና 28 በመስቀል አደባባይ ለሚደረገው የአንድ ቀንና ሌሊት የተቃውሞ ሰልፍ ህዝቡ የተጀመረውን የሰው በሰው ቅስቀሳ እንዲደግፍ፣ የገንዘብ የሞራልና ቁሳቁስ ድጋፎችን እንዲያደርግ እንዲሁም ለትግሉ ይጠቅማል ያሉትን ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቋል። ህዝቡ በዝግጅቱ ከሚያደርገው ድጋፍ ባሻገር በመስቀል አደባባይ በሚኖረው ቆይታ የሚያስልጉት ቁሳቁሶች በተለይም ደረቅ ምግብና ውሃ …

ኀዳር ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ2003 ዓ.ም ወዲህ በተከሰተ አደጋ በክልሉ 18ሺ 994 የመኪና አደጋዎች ተከሰተዋል፡፡ በትራፊክ ሳምንት ውይይት ላይ እንደተገለፀው በአጠቃላይ በአምስት አመታት በተከሰተው አደጋ 6ሺ 668 ሰዎች ህይዋታቸውን አጠዋል፡፡ 6ሺህ 581 ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት ፤ 11 ሺ 781 ሰዎች ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ሲደርስባቸው  994 ሚልዮን 626 ሺህ 866 …

ኀዳር ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትሩ አገሪቱ ከግል የገንዘብ ተቋማት ለመበደር መወሰኑዋን ተከትሎ የኢትዮጵያን ብድር በበላይነት በሚያስተባብረው በጀርመን ትልቁ ባንክ አማካኝነት በተዘጋጀ ዝግጅት ላይ ይገኛሉ ተብሎአል። ኢትዮጵያ ከአለማቀፍ ገንዘብ ተቋማት ለመበደር መወሰኑዋ ብዙ ኢኮኖሚስቶችን እያነጋገረ ነው። ጠ/ሚኒስትሩ ከጀርመን ቻንስለር አንግላ መርክል ጋር እንደሚነጋገሩም ታውቋል። አቶ መለስ ዜናዊ ከዚህ ቀደም ለኢትዮጵያ ማዳበሪያ ከሚያቀርብ …

ኀዳር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃገሪቱ ህገ መንግስት አንቀጽ 31 መሰረት በህጋዊ መልኩ ተመዝግበው ሰላማዊ የፖለቲካ እንቃስቃሴ የሚያደርጉ ተቀናቃኝ ፓርቲዎችን በሽብርተኝነት እና ጽንፈኝነት በመፈረጅ የጥቃት ኢላማ ለማድረግ መታሰቡን ኢሳት የፌደራል መንግስት የጸጥታ ጉዳዮች ሰሞኑን ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር  ካካሄደው ውይይት ለመረዳት ተችሎአል፡፡ የትግራይ፣ቤንሻንጉል ጉሙዝና አማራ ክልል ሃላፊዎች ሰማያዊ ፣አንድነትና መኢአድ ፓርቲዎች ጽንፈኞች በመሆናቸው …

ኀዳር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሺን፣ ፓርቲዎቹ ይህን አስታወቁት ባወጡት መግለጫ ነው። ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው ደብዳቤ ለመቀበል አሻፈረን ሲል የነበረው መስተዳድሩ በፖስታ የተላከለትን ደብዳቤ ከተቀበለ በሁዋላ ከህገመንግስቱና ከአዋጁ ቁጥር 3/1983 ተቃራኒ የሆኑ ምክንያቶችን በመደርደር ለሠላማዊ ሠልፉ ዕውቅና አልሰጠሁም ሲል ህዳር 22 ቀን  ድብዳቤ መጻፉን አስታውቀዋል፡፡ “በመሠረቱ መስተዳድሩ ጊዜና ቦታ እንዲቀየር አስተያየት …

ኀዳር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወራት በፊት 111 በመቶ የደሞዝ ጭማሪ ያደረገው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሺን፣ በአማራ እና በኦሮምያ ክልል በተከታታይ ተገቢ የሆነ የደሞዝ ማስተካካያ አላደረገም በሚል ጥያቄ ሲቀርብብት ቆይቷል። ሰሞኑን የካቢኔ አባላት ተሰብስበው   የአማራ ክልል ጋዜጠኞች ከግንቦት ሰባት እና አርበኞች ግንባር እንዲሁም  የኦሮምያ ክልል ጋዜጠኞች ከኦነግ ጋር የሚሰሩትና ለኢሳት መረጃ በማቅረብ በክልሎች …

ኀዳር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወኪላችን እንዳለው በዋና ከተማዋ ጁባ አንድ ወንድና አንድ ሴት ሲገደሉ ሁለት ሴቶች ግን በጠና ቆስለው ወደ ኢትዮጵያ ተወስደዋል። የሁለቱም ሟቾች አስከሬንም በኢትዮጵያውያን እርዳታ ወደ ኢትዮጵያ መሄዱ ታውቆል:: ሰዎቹ በምን ሁኔታ እንደተገደሉና እንደቆሰሉ እንዲሁም ጥቃቱን ያደረሱትን ወገኖች ዝርዝር ለማወቅ አልተቻለም። በደቡብ ሱዳን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በኢትዮጵያውያን የሚደረገውን ግፍና …

ኀዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም ከፌደራልና ከክልሎች ለተውጣጡ የጸጥታና ደህንነት ሃላፊዎች እንደተናገሩት መንግስት አራት የጸጥታ ችግሮች አጋጥመውታል፡፡ የመጀመሪያው የሽምቅ ውጊያ የሚያደርጉ ሃይሎች የፈጠሩት ስጋት ነው ያሉት ዶ/ር ሽፈራው እነዚህን ሃይሎች እና ሽብርተኞችን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ፈተና መሆኑን ሲገልጹ፣ ከሃይማኖት ጋር ተያይዞ የሚፈጠረውን የአክራሪነት አደጋ ሙሉ …

ኀዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቀድሞው የመከላከያ ኢታማጆር ሹም ሌተናንት ጄኔራል ጻድቃን ገብረትንሳይ የቦርድ ሰብሳቢነት የሚመራው ራያ ቢራ በቀድሞ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትና ህወሃትን ተጠግተው በሚነግዱ ነጋዴዎች ከፍተኛ አክስዮን የተመሰረተ መሆኑን ምንጮች ይገልጻሉ። ማይጨው ከተማ ላይ የተገነበው ፋብሪካው 600 ሚሊየን ብር የተከፈለ ካፒታል አለው። ከራያ ቢራ አክስዮን ባለድርሻዎች መካከል   ሌተናንት ጄኔራል ጻድቃንን …

ኀዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያውያኑ ኦስሎ በሚገኘው የእንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት ገዢው ሃይል የወሰደውን እርምጃ ከማውገዝ በተጨማሪ የኢንግሊዝ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ስላሉበት ሁኔታ ወቅታዊ መረጃ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ ባዘጋጀው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ አቶ አንዳርጋቸው የፍትህ ተምሳሌት፣ የነጻነት በር ከፋች ነው የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል። ኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን …

ኀዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወኪላችን እንደገለጸው የመንግስት ታጣቂዎች ወደ ሰማያዊ ብርሃን ቤተክርስቲያን በመሄድ ማፍረሳቸውን ለማወቅ የተቻለ ሲሆን አንድ ፓስተር እስከባለቤታቸውና ሌላ አገልጋይ ታስረዋል። የሃረር አብያተ ቤተከርስቲያናት ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ዮሴፍ አምደማርያም ታስረው ሲፈቱ ሌላው የቤተክርስቲያኑዋ ፓስተር አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ። ቤተክርስቲያኗ በአገር አቀፍ ደረጃ ተመዝግባ የምትንቀሳቀስ መሆኗ ታውቋል። የክልሉ አፍራሽ …

ኀዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የገዢው መንግስት በምርጫ 2007 ያለውን ተቀባይነት ለማጠናከር በማሰብ የተለያዩ የህብረተሰቡን ክፍሎች በየክፍለ ከተማው በማሰባሰብ የተሰሩ ስራዎችን በማቅረብ ለመመስገን ሙከራ ቢያደርግም፤ተሰብሳቢዎች ግን ምንም እንዳልተሰራና ተሰራ የተባለውም ችግር ያለበት እንደሆነ  ተናግረዋል፡፡ የመንገዶች መበላሸት ያሳሰባቸው ነዋሪዎች በአካባቢው ላሉ አመራሮች የስራውን የጥራት ጉድለት ቢያሳውቁም የተስተካከለ ነገር እንደሌለ ገልጸዋል፡፡  “በ2006 የተሰራው …

ኀዳር ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ትብብሩ ህዳር 18 ለመስተዳድሩ ባስገባው የእውቅና ጥያቄ ፣ የተቃውሞ ሰልፉን በመስቀል አደባባይ ከህዳር 27 እስከ ህዳር 28፣ 2007 ዓም ለማካሄድ ማቀዱን ገልጿል። የእውቅና ደብዳቤውን ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲና የትብብሩ ሊቀመንበር፣ የከንባታ ህዝቦች ሊቀመንበርና የትብብብሩ ም/ሊቀመንበር አቶ ኤርጫፎ ኤርጌሎ፣ አቶ ግርማ በቀለ ከኦሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅትና …

ኀዳር ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አርበኛ ጋሻው ሽባባው በሰሜን ጎንደር ዞን አዳርቃይ ወረዳ ከመንግስት ታጣቂ ሃይሎች ጋር ለ4 ወራት ሲፋለም በቁጥጥር ስር መዋሉን ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት የገለጸ ሲሆን፣ በዚህም ድርጊቱ የ4 አመት ከ8 ወር እስራት እንደፈረደበት ገልጿል። አርበኞች ግንባር በወቅቱ ባደረገው ተደጋጋሚ ጥቃት ከ60 ያላነሱ የመንግስት ወታደሮችን መግደሉን …

ኀዳር ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የብአዴን አመራሮች ሰሞኑን በዞኑ ባካሄዱት የወጣቶችና ሴቶች ጉባኤ ላይ ፣ የአካባቢው ወጣቶች የጸረ ሰላም ሃይሎች መሳሪያ ከመሆን እን  ዲቆጠቡ ጠይቀዋል። ወጣቶቹ በግፍ የታሰሩ የአካባቢው የአንድነት ፓርቲ አመራሮች የሆኑት አንጋው ተገኝ፣ አባይ ዘውዱና ሌሎችም አባላት ታፍነው መወሰዳቸውን ተቃውመዋል። በተለይ የጋብላ እና የዘመነ መሬቅ ወጣቶች እውን ዲሞክራሲ የሚባለው …

ኀዳር ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ትብብሩ ባወጣው መግለጫ ህዳር 21 ለሚደረገው ስብሰባ ለመስተዳድሩ የሰለማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ደብዳቤ ቢላክለትም ለመቀበል ፈቃደኛ ካለመሆኑም በተጨማሪ፣ ስብሰባውን የሚያስተባብሩት የመኢዴፓ ሊቀመንበርና የትብብሩ ገንዘብ ያዥ የሆኑት አቶ ኑሪ ሙደሲር ላይ የድብደባ ወንጀል እንደተፈጸመባቸው ገልጿል።‹‹ነጻነታችን በእጃችን›› ነው የሚለው ትብብሩ፣  በኢህገመንግሥታዊና ኢዲሞክራሲያዊ እርምጃዎች ወደኋላ እቅዱን በህጋዊ መንገድ …

ኀዳር ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት የጀመራቸውን የሃይል፣ የመንገድ፣ የባቡርና የስኳር ፋብሪካዎችን ለመጨረስ የሚያስችለውን ገንዘብ ከአለማቀፍ አበዳሪ ድርጅቶች ለመበደር የሚያስችለውን ድርድር ከሁለት የአውሮፓ እና ከአንድ የአሜሪካ ባንክ ጋር ጀምሯል። መንግስት ገንዘቡን ለመበደር የሚያስችለውን ቦንድ ለገበያ የሚያቀርብ ሲሆን፣ አለማቀፍ አበዳሪ ተቋማትም የመንግስትን የመክፈል አቅም በማየት ብድሩን ይፈቅዳሉ። መንግስት ከአለማቀፍ የግል አበዳሪ ድርጅቶች …

ኀዳር ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ለከተማ አስተዳደሩ ከላከው ቅጽ ለመረዳት እንደሚቻለው ፓርቲው በአዲስ አበባና ኦሮምያ የተቀናጀ የከተማ እቅድ ዙሪያ በመንግስት ሰራተኛው ውስጥ ያለውን የአመለካከት ክፍተት ለመሙላት ስልጠና ይዘጋጃል። ፓርቲው የተለያዩ ቅጾችን ለሰራተኛው በመበተን ሰራተኛው እስካሁን ስለነበሩት ክንውኖችና ድክመቶች አስተያየቱን እንዲጽፍ ተጠይቋል። እጅግ አወዛጋቢ ሆኖ ተቃውሞ ያስነሳውንና በርካታ …

ኀዳር ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስአበባ ከተማ የተጋነነ የትምህርት ቤት ክፍያ ዋጋ በመጨመር ህብረተሰቡን ለአላስፈላጊ ወጪ ዳርገዋል በተባሉ 130 የግል ትምህርት ቤቶች ላይ ክስ መመስረቱን የአዲስአበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን እና የግል ትምህርት ቤቶች ማህበር በጋራ ያጠኑትና በሐምሌ ወር 2006 ዓ.ም ይፋ የተደረገ አንድ ጥናት እንደሚያሳየው በአዲስአበባ …

ኀዳር ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ካቢኔ የከተማዋ ነዋሪዎች ጭማሪው እንዲከፍሉ የወሰነው ለከተማው ውሃ ለመዘርጋት ከፍተኛ ገንዘብ ማውጣቱን በመግለጽ ነው። የክልሉ የውሃ ሀብት ም/ል ሃላፊ ለክልሉ ካቢኔ እንደገለጹት ለከተማዋ የውሃ መስመር ዝርግታ 6 ሚሊዮን 300 መቶ ሺ ብር ለማስፋፊያ ስራ ደግሞ 60 ሚሊዮን ብር በመውጣቱ፣ አጠቃላይ ወጪውን ለማስመለስ ተጠቃሚው ህብረተሰብና የንግድ …

ኀዳር ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዊ ዞን አንከሻ ወረዳ ውስጥ የሚማሩ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች የኢህአዴግን የአባልነት መሙያ ፎርም ወስደው እንዲመዘገቡ በርእሰ መምህራቸው አማካኝነት ቢጠየቁም፣ ከ700 ያላነሱ ተማሪዎች ድርጊቱን ተቃውመዋል። ተማሪዎቹ የአባልነት ቅጹን በሁለት ቀናት ውስጥ የማይሞሉ ከሆነ ከትምህርት ቤት እንደሚባረሩና ለፈተናም እንደማይቀርቡ ተነግሯቸዋል። “ከእንግዲህ ኢህአዴግ የሚባል ነገር ማየት አንፈልግም” ያሉት ተማሪዎች …

ኀዳር ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል የደቡብ ወሎና የሰሜን ሸዋ ዞን ወረዳዎችና አብያተክርስቲያናት ተገቢ ጥበቃ ባለማግኘታቸው የተለያዩ ቅርሶች የተዘረፉና የጠፉ መሆኑን የዞኑ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ በአመት አንድ ጊዜ በሚዘጋጀው የቅርስ ጉባኤ ላይ ገለጸ፡፡ በሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ በተለያዩ ወረዳዎች 37 ቅርሶች መሰረቃቸውን ይፋ ያደረጉት የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ አቶ አለበል …

ኀዳር ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእየአመቱ ህዳር 29 ቀን የሚከበረው የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን ለማክበር መንግስት እስከ 300 ሚሊዮን ብር እንደሚያወጣ መረጃዎች አመለከቱ። ለኢሳት የደረሱ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ዝግጅቱን ከማቀድ ጀምሮ የተለያዩ ስራዎችን የሚፈጽሙት ከህወሃት ባለስልጣናት ጋር ግንኙነት ያላቸው ድርጅቶች ናቸው። በኢትዮጵያ የሚከበሩ በአላትን እነዚህ ተቋማት ያለተቀናቃኝ በመውሰድ እየበለጸጉበት መሆኑን ምንጮች ይናገራሉ። ኢህአዴግ ካወጣው …

ኀዳር ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው አርብህዳር 12፣ 2007 ዓም የሃረሪ ክልል ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ሙራድ አብዱላሂ በሀረሪ ሊግ ዋና ጸሃፊና በንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃለፊ አቶ ነቢል መሃዲ ጽ/ቤታቸው ውስጥ እንዳሉ ተደብድበዋል። የክልሉ ባለስልጣናት ለሁለት መከፈላቸው የጸጥታ ስጋት መደቀኑንም ምንጮች ተናግረዋል። በክልሉ ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን የነበራቸው አቶ ነቢል መሃዲ ከወራት በፊት …

ኀዳር ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢህአዴግ መንግስት ከማሃል አገር ሰፍረው የቆዩትን የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ሁመራና ሌሎች የድንበር አካባቢዎች በስፋት እየሰማራ መሆኑን ወታደራዊ ምንጮች ገለጹ። ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ከኤርትራ ጋር በሚያዋስነው ድንበር ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እየታየ መሆኑን የገለጹት ምንጮች፣ ምክንያቱ ደግሞ ኢህአዴግን በሃይል አስገድደው ለማውረድ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ጥቃት ሊሰነዝሩ ይችላሉ የሚለው ስጋት …

ኀዳር ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በበጎፈቃደኝነት ወደምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ሄደው ለመስራት ካመለከቱ ባለሙያዎች መካከል የተመረጡ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል።  ሌሎች ምንጮች ደግሞ አብዛኛዎቹ ባለሙያዎች በመከላከያ የጦር ክፍሎች ውስጥ በሕክምና ሙያ እያገለገሉ የሚገኙ ዶክተሮች ፣ ነርሶችና የጤና መኮንኖች ናቸው ይላሉ። ወዶ ዘማች ናቸው የተባሉትና 210 የሚደርሱት እነዚሁን ባለሙያዎች የፊታችን ሰኞ ህዳር 22 ቀን 2007 …

ኀዳር ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሱዳን የሰሜን ግዛት በምትገኘዋ ኤል ዳባ የሚኖሩ ከ2 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ተጠርንፈው ወደ ካርቱም የተላኩ ሲሆን፣ የከተማዋ ባላስልጣናት ኢትዮጵያውያኑ ሄፒታይተስ ሲ የተባለው የጉበት በሽታና የኤድስ ቫይረስ ስላለባቸው መላካቸውን ገልጸዋል። የኤል ዳባ ፖሊስ ኮሚሽነር  ኢስላም አብደል ራህማን ለሱዳን ትሪቢዩን እንደተናገሩት የግዛቱ ባለስልጣናት በውጭ አገር ዜጎች  ላይ በድንገት ባደረጉት …

ኀዳር ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድነት ለዴሞክራሲያዊና ለፍትሕ ፓርቲ በመጪው 5ኛ ሀገራዊ ምርጫ እንደሚሳተፍ አስታውቋል፡፡ ፓርቲው በኢትዮጵያ ውስጥ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ለማድረግ ሁኔታዎች ምቹ አለመሆናቸውን ቢጠቅስም “ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሆኖ ህዝቡ እንዲሳተፍ በመቀስቀስና በማበረታታት የተዘጋውን የዴሞክራሲ በር በምርጫ ካርዱ ሊያስከፍት እንደሚችል ከፍተኛ እምነት” እንዳለው አስታውቋል። መንግስት  የመድበለ ፓርቲን ስርዓት ለማጎልበት ምንም ዓይነት …

ኀዳር ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቀድሞ የአርቲስቲክ ማተሚያ ቤት ስራ አስኪያጅ በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተው ከሰራተኛው ጋር በተፈጠረ ውዝግብ ስማቸው በተደጋጋሚ ሲነሳ የነበሩት የኢህአዴግ አባሉ አቶ አባዲ ተካ ከተሾሙ ካለፈው አመት ጀምሮ ብርሃንና ሰላም መረጋጋት ተስኖት ከቆየ በሁዋላ በቅርቡ ደግሞ ድርጅቱ በኪሳራ ምክንያት ይሸጣል መባሉ ሰራተኛውን አስደንግጧል። በተለያዩ የሙስና ወንጀሎች የሚከሰሱት አቶ ተካ …

ኀዳር ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአንድ ዓመት ላላነሰ ጊዜ በአሜሪካን ሀገር በቺካጎ ከተማ በሚገኝ አንድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሲያስተምሩ ቆይተው በቅርቡ ወደሀገር ቤት መመለሳቸውን የተናገሩት  የወቅቱ የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ዲያስፖራውን ወቅሰዋል። ፕሮፌሰሩ በዛሬው ዕለት ለንባብ ከበቃው መንግስታዊው ዘመን መጽሄት የጥቅምት 2007 ዕትም ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ «ዲያስፖራው ተስፋ የቆረጠና የተናደደ ነው፡፡ ተስፋ …

ኀዳር ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ወሎ ዞን በኮምቦልቻ ወረዳ ቀበሌ 11 በተለምዶ ጋሪሳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ይኖሩ የነበሩ 470 ሰዎች ቦታው ለኢንቨስትመንት ይፈለጋል ተብሎ ሰብአዊ መብታቸው ተጥሶ እንዲፈናቀሉ ከተደረገ በሁዋላ፣ በካሬ ሜትር 1 ብር ከ46 ሳንቲም መሬታቸው እንዲጨጥ ተደርጓል። ጉዳዩ የህዝብ መነጋገሪያ ሆኖ ከቆየ በሁዋላ ሰሞኑን ከህዝቡ እየጨመረ የመጣውን ግፊት ተከትሎ …

ኀዳር ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአንድነት ፓርቲዎቹ ሃብታሙ አያሌውና ዳንኤል ሽበሺ፣ የሰማያዊ ፓርቲው የሽዋስ አሰፋ፣ የአረና ፓርቲው መምህር አብረሃ ደስታ እና ሌሎች 6 የመብት ተሟጋቾች ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ በፍርድ ቤት ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። በአቶ ዘላለም ወርቃገኘሁ መዝገብ የተከሰሱት አስሩ ፖለቲከኞችና የመብት ተሟጋቾች፣ ህገመንግስቱን ጠቅሰው የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ቢጠይቁም ፍርድ ቤቱ አልተቀበለውም። ሁሉም …

ኀዳር ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በላይኛው አዋሽ ተፋሰስ ከመስከረም 28 ቀን 2007 ጀምሮ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት የተፈናቀሉ በሺ የሚቆጠሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ከእለት ዕርዳታ ባለፈ ድጋፍ እየተደረገላቸው አለመሆኑን ገለጸዋል፡፡ የአካባቢው ተወካይ እንደገለጹት መንግስት በአካባቢው የገነባው የዝናብ መከላከያ ደረጃውን የጠበቀ ባለመሆኑ ምክንያት በጎርፍ በቀላሉ መሰበሩን ጠቅሰው በዚህ ምክንያት ማሳ ላይ የነበረ ምርታቸውን ጨምሮ …

ኀዳር ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽንን ጠቅሶ እንደዘገበው ባለፉት 37 ቀናት ከ6 ሺ ያላነሱ ኤርትራውያን ብሄራዊ ውትድርናን በመሸሽ ተሰደዋል። ኮሚሽኑ እንደሚለው የስደተኞች ቁጥር ካለፈው ወር ጋር ሲነጸጻር በእጥፍ ጨምሯል። የኤርትራ መንግስት በበኩሉ ብሄራዊ ወትድርና ዘመቻ ያስፈለገው በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ድንበር አካባቢ ያለው ውጥረት እየጨመረ በመምጣቱ  እንደሆነ ገልጿል። …

ኀዳር ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፕሬዚዳንት ሙሃመድ ሙርሲ መንግስት ከተገለበጠ በሁዋላ በሱዳንና በግብጽ መንግስታት መካከል ያለው ልዩነት ሰፍቶ እርስ በርስ እስከመነቃቀፍ ደርሰው የነበረ ቢሆንም፣ ሱዳን የሙርሲ ፓርቲ የሆነውን ሙስሊም ወንድማማጮች የተባለው ፓርቲ እንደምታግድ በማስታወቁዋ ሁለቱ አገራት ወደ አዲስ የዲፕሎማሲ ግንኙነት እያመሩ መሆኑን የሱዳን መንግስት ቃል አቀባይ ገልጸዋል።ሁለቱ ሃገራት በውሃ አጠቃቀም ዙሪያ ተፈጥሮ …

ኀዳር ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሮምያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙክታር ከድር፣ የገንዝብ ሚኒስትሩ ሶፍያን አህመድና የኦሮምያ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊው ከጅማ ዞን የተውጣጡ የተለያዩ ድርጅት ተወካዮችን በጊዜ አዳራሽ ሰብስበው ባነጋገሩበት ወቅት፣ ህዝቡ በአስተዳደሩ ተስፋ መቁረጡንና ለውጥ የሚፈልግ መሆኑን ተናግሯል። የምርጫ ቅስቀሳ በሚመስለው መድረክ ፣ አቶ ሙክታር ተሰብሳቢው የሚሰማውን እንዲናገር ፈቅደዋል። ነዋሪዎቹ በዞኑ ልማት የሚባል …

ኀዳር ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ማክሰኞ ከቀኑ 9 ሰአት ላይ ኮቸሬ ከሚባል አካባቢ የመጡ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ 4 ሰዎች ዲላ ሪፈራል ሆስፒታል መግባታቸውን ተከትሎ፣ በሆስፒታሉ ውስጥ ከፍተኛ ድንጋጤ ተፈጥሮ እንደነበር ምንጮች ገልጸዋል። ድንጋጤው የተፈጠረው ሰዎቹ በኢቦላ በሽታ ተይዘዋል በሚል እምነት ነው።  ዛሬ ረቡዕ ደግሞ 4ቱም ሰዎች መሞታቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የመንግስት ባለስልጣናት …

ኀዳር ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ2006 ዓም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ረብሻ አስነስታችሁዋላ በሚል ከታሰሩት መካከል 4 ተማሪዎች በ2 አመት ከ3 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላልፏል። ሁለቱ የ4ኛ 5ኛ አመት የህክምና ተማሪዎች ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ ድገሞ የ3ኛ አመት የነርሲንግ ተማሪዎች ናቸው። በሌላ በኩል ደግሞ መንግስት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሚከተሉትን የአለባባስና የምግብ ስነስርአት መመሪያን …

ኀዳር ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፕሬዚዳንት ብሌስ ካምፓወሬን መንግስት በመገልበጥ ጊዜያዊ መሪ መሆናቸውን ካስታወቁ በሁዋላ ስልጣናቸውን ለሲቪል አስተዳደር ያስረከቡት ሌ/ኮሎኔል አይዛክ ሲዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። ጊዜያዊው ፕሬዚዳንት ሚኬል ካፋንዶ ኮሌኔሉን ጠ/ሚኒስትር አድርገው የሾሙት በስልጣን ጉዳይ ሲደረግ የነበረውን ድርድር ተከትሎ ነው። ሁለቱም መሪዎች አገሪቱን ለአንድ አመት ያክል ካስተዳደሩ በሁዋላ ምርጫ ይካሄዳል። …

ኀዳር ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ የሚታሰሩ ዜጎች ቁጥር መበራከት የአለምን የመገናኛ ብዙሃን ሰፊ ሽፋን ባገኘ ማግስት፣ አሁንም ዜጎችን በሰበብ አስባቡ እያሰሩ ለፍርድ አቅርቦ ማስፈረድ ቀጥሎአል። አፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብት ሊግ ያወጠው ሪፖርት እንደሚያሳየው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በአምቦ ከተማ እና በሚዳ ቀኒ ወረዳ ከ20 ያላነሱ ተማሪዎች፣ መምህራንና አርሶ አደሮች ታስረዋል። እስራቱ የተፈጸመው መንግስት …

ኀዳር ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የማጅራት ገትር ወረርሺኝ ጋር ተያይዞ ከሳምንት በፊት ለ10 ተከታታይ ቀናት ዕድሜያቸው ከ1 እስከ 29 ኣመት ክልል ላሉ ዜጎች ክትባት የመስጠት ሒደት የተከናወነ ቢሆንም አፈጻጸሙ ከተጠበቀው ውጪ ሆኖአል፡፡ በተለይ ዕድሜያቸው ከ29 ዓመት በላይ መከተብ አያስፈልጋቸውም፣ ከተከተቡ የጎንዮሽ ችግር ያመጣባቸዋል መባሉ ግማሽ ያህል የህብረተሰብ ክፍል ቢሞትም ግድ የለንም እንደማለት ተደርጎ …

ኀዳር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪነት 9 የፖለቲካ ድርጅቶች በጋራ የጠሩት የአደባባይ ስብሰባ በገዢው ፓርቲ የጸጥታ ሃይሎች እንዲበተን ከተደረገ በሁዋላ ድርጅቶቹ ባወጡት መግለጫ ” መንግሥት ከገባበት ከፍተኛ የፍርኃት ስሜት ለመውጣት ያስቀመጠው የሴራ መፍትሄ  መስዋዕትነቱን ይጨምር እንደሆን እንጂ፣ ትግሉን አያቆመውም” ብለዋል። ፓርቲዎቹ ለአንድ ወር ባወጡት የስራ መርሃ ግብር መሰረት ከአራት ኪሎ እና …

ኀዳር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ፣ በደቡብ እና  በአማራ ክልሎች በተካሄደ የመረጃ አመራር ስልጠና ላይ አሰተያየት የሰጡ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ጋዜጠኞች ‹‹ቡጨ›› በማለት የሚጠሩት  ቡጨቃ ፤ቆረጣ ወይም ሃብትን መካፈል የሚባለው አሰራር  እንዳማረራቸው ገልጸዋል። ባለስልጣኖቹ “መንግስት ከከፈላቸው አበል ውጭ በድጋሜ አበል ካልተከፈላቸው ፕሮግራሞቻችን በደንብ አይሸፈኑም፤ ምንም አይነት ሂሳብ ካላገኙ ወይም የምግብ ፤ የነዳጅ እና …

ኀዳር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብሌስ ካምፓወሬ መንግስት በ2 ቀናት አመጽ ከተገለበጠ በሁዋላ ስልጣን ለሳምንታት ተረክቦ የነበረው የመከላከያ ሰራዊት ስልጣኑን ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ ለተመረጡት ለቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚኬል ካፋንዶ እንደሚያስረክብ ታውቋል፤፡ሌ/ኮ አይሳክ ዚዳ ስልጣናቸውን በፍጥነት እንደሚያስረክቡ ቃል ገብተዋል። የ72 አመቱ ካፋንዶ ከሃይማኖት፣ ከጦር ሰራዊት፣ ከፖለቲካ፣ ከሲቪክ ማህበረሰቡና ከባህላዊ መሪዎች ተውጣጦ በተመሰረተው ጉባኤ …

ኀዳር ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘንድሮ የሚጠናቀቀው የኢህአዴግ የአምስት ዓመት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን የተለጠጠ ዕቅድ በግብርና ዘርፍ መዳከም ምክንያት ሳይሳካ መቅረቱን ኢህአዴግ ለመጀመሪያ ጊዜ  በይፋ አመነ፡፡ ኢህአዴግ «አዲስ ራዕይ» በተሰኘው በርዕዮተ ዓለም ልሳኑ የመስከረም- ጥቅምት 2007 ዓ.ም ዕትም ላይ የአምስት ዓመት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የአራት ዓመታት አፈጻጸም አስመልክቶ ባሰፈረው ሐተታ እንደጠቆመው ለጥጦ የያዘውን ዕቅድ …

ኀዳር ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጋምቤላና በደቡብ ክልል አዋሳኝ በሆነው   በጉራ ፈርዳ ወረዳ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ከፍተኛ የሰው ህይወትና ንብረት ከወደመ በሁዋላ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣኖች ባለፉት ሁለት ቀናት የአካባቢውን አመራሮች በመሻርና በመሾም መረጋጋት እንደተፈጠረ በመግለጽ ተፈናቃይ አርሶደሮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ለማግባባት ቢሞክሩም፣ አብዛኞቹ አርሶአደሮች ግን ለህይወታችን ዋስትና የሚሰጠን ስለማይኖር ወደ አካባቢው ለመመለስ ፈቃደኞች …

ኀዳር ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ተሰድቤአለሁ በሚል ምክንያት አንድ አዛውንትን እስከ ልጃቸው በሌሊት የገደለው ወታደር ግድያውን ከፈጸመ በሁዋላ ወደ መካለከያ ካምፕ ቢያመራም ህግ ፊት ይቀርብ አይቀርብ የታወቀ ነገር የለም። ወጣት ዮናስ በ16 ጥይቶች ተባስስቶ መገደሉን  ከቅርብ ሰዎች የተገኘው መረጃ የሚያመልክት ሲሆን ወ/ሮ መንበረም ከ10 ያላነሰ ቦታ ላይ ተደብድበው ተገድለዋል። የከተማው ህዝብ ወደ አደባባይ …

ኀዳር ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ በአካባቢው የሰፈሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት በህዝቡ ላይ የሚወስዱት እርምጃ እየተባባሰ መጥቶ ረቡዕ ሌሊት ለሃሙስ አጥቢያ ፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የፌደራል ፖሊሶች ወደ አንድ ወጣት መኖሪያ ቤት ሰብረው በመግባት እርሱንና እናቱን በአምስት አምስት ጥይኦች በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለው ወደ ካምፓቸው አምርተዋል። የከተማው ህዝብ ተቃውሞውን ለማሰማት …

ኀዳር ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቦሌ ለሚ በሚባለው አካባቢ የማሪያም ቤተክርስቲያን እንዲፈርስ መደረጉን የተቃወሙ ነዋሪዎች ከፖሊሶች በደረሰባቸው ጥቃት በርካታ ሰዎች የተጎዱ ቢሆንም፣ ፖሊስ ሃይሉን አሰባስቦ በመምጣት በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን ይዞ አስሯል። አብዛኞቹ ወጣቶች በኮብል ስቶን ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን፣ ፖሊስ ወደ ድርጅቶቹ በመሄድ ወጣቶችን በጅምላ ማሰሩን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ወንድሞቹ …

ኀዳር ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብቶች የተባለው ድርጅት ለኢሳት በላከው መግለጫ የቶም ላንሶቶስ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ዙሪያ ታዋቂ ሰዎች ሃሳባቸውን እንዲያካፍሉ ጋብዟል። ተናጋሪዎቹ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብት አያያዝ በመገምገም የአሜሪካ መንግስት የዲፕሎማቲክና የገንዘብ ድጋፉን ተጠቅሞ በኢትዮጵያ የሚታየው የተበላሸ የሰብአዊ መብት አያያዝ እንዲሻሻል ግፊት ያደርጋል ተብሎ …