ጎጃምን ከጎንደር የሚያገናኘው የአባይ ድልድይ ትክ የሚሰራበት የቆይታ ጊዜ በመርዘሙ አደጋ ያደርሳል በሚል ስጋት ላይ መሆናቸውን የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
ጥር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በባህርዳር ከ1949 ዓ.ም ጀምሮ ነዋሪ የሆኑት አስተያየት ሰጪ ሲናገሩ ድልድዩ ሲሰራ አለሁ የመሰረት ዲንጋዩ ሲቀመጥ ነበርኩ ካሉ በኋላ ከ25 እስከ 30 ዓመት እንደሚያገለግል በይፋ ተነግሮ እንደተሰራ ከዚህ ዓመት በላይ ከቆየ አደጋ ለያደርስ እንደሚችል በወቅቱ በነበሩ የግንባታ ባለሙያዎች እንደተነገረ በማስታወስ ገልጸው ምንም አይነት የተሰራ አዲስ ነገር ሳይኖር ከ50 …