የጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ ህይወት አደጋ ላይ መሆኑ ተገለፀ፤ እንዲሁም በሰማያዊ ፓርቲ አባል አቃቤ ህግ ምስክር አሰማ
ታኀሳስ ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶበት የሶስት ዓመት እስር የተበየነበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ደህንነቱ አደጋ ላይ መውደቁን ቤተሰቦቹ ገለፁ፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን፣ በዝዋይ ወህኒ ቤት፤ ኮማንደር ቢኒያም ተብሎ በሚጠራው የወህኒ ቤቱ አስተዳዳሪ ጠዋትና ማታ ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰበት ከመሆኑም በላይ በቀን ለአምስት ጊዜ ያህል ሌሊትን ጨምሮ በሰበብ አስባቡ ከክፍሉ እየተጠራ …