ጋዜጠኛ ርዕዮት ዐለሙ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የሻካሮቭ ሽልማት የ2013 ዕጩ ሆነው ተመረጡ።
መስከረም ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጋዜጠኛ ርዕዮት ዐለሙን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን እና አሜሪካዊው ኤድዋርድ ስኖውደንን ጨምሮ ሰባት ሰዎች የአውሮፓ ህብረት ለነፃነት ታጋዮች በየአመቱ ለሚያዘጋጀው የ “ሻካሮቭ ሽልማት” የ2013 ዕጩ ሆነው ተመረጡ። የአውሮፓህብረት የሻካሮቭ ሽልማት ኮሜቴ-ከህብረቱ የውጪ ጉዳይና ልማት ኮሚቴ እና ከሰብዓዊ መብት ንዑስ ኮሚቴ ጋር በመሆን ትናንት ሰኞ ይፋ እንዳደረጉት ማላላ ዩሳፍዛይ ከፓኪስታን፣ ኤድዋርድ ስኖውደን …