ለኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና ጋዜጠኞች በድጋሜ ታላቅ ግብዣ ተዘጋጀ
ነሃሴ ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአራት ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የወጣበትና በኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነት የኪነጥበባት ባለሙያዎች፣ ምሁራንና የሚዲያ ባለሙያዎች ቡድን የተሳተፉበት የጉብኝት ፕሮግራም ከግንቦት 24 እስከ ሰኔ 4/2005 ዓ/ም በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን ይህንን መነቃቃትና የገጽታ ግንባታ አጠናክሮ ለመቀጠል ያስችላል የተባለ ታላቅ ድግስ ጳጉሜ 3 ቀን 2005 በሸራተን …