የስዊድን የጦር ኮሚሽን በኦጋዴን ስለተፈጸመው ወንጀል አፋጣኝ መልስ እንደሚሰጥ አስታወቀ
ጥቅምት ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦጋዴን የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰትና የጦር ወንጀል የሚያሳየው ዘጋቢ ፊልም በቅርቡ በስዊድን ቴሌቪዥን መለቀቁን ተከትሎ ዛሬ አርብ፣ የስዊድን የጦር ኮሚሽን ማስረጃዎችን ተረክቧል። ማስረጃዎችን ለኮሚሽኑ ያስረከቡት ሂደቱ ዋና ተወናይ የሆነው ወጣት አብዱላሂ የሱፍና የአለማቀፍ የህግ ባለሙያዎች ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ስቴላ ጋርደ ናቸው። የጦር ኮሚሽኑ የቀረበለትን ማስረጃ በማየት አፋጣኝ ውሳኔ እንደሚሰጥ …