ታህሳስ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር እና በቀድሞው ምክትላቸው ሪክ ማቻር መካከል የተነሳው ውዝግብ የዲንቃና የኑዌር ጎሳዎችን እርስ በርስ እንዲዋጉ እያደረጋቸው መምጣቱን ዘገባዎች ያመለክታሉ። የሪክ ማቻር ደጋፊዎች ጆንግሌ አካባቢ የሚገኙ የተለያዩ ቦታዎችን መቆጣጠራቸው ተሰምቷል። ምንም እንኳ የአገሪቱ መሪ መፈንቅለ መንግስቱን ማክሸፋቸውን ቢናገሩም፣ በሌሎች አገሪቱ ክፍሎች አሁንም ውጊያዎች እየተካሄዱ ነው። ከስልጣን የተባረሩት ሪካ …

ታህሳስ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ዋና አቃቢ ህጓ ምርመራውን ለማቋረጥ የተገደዱት ሁለቱ ዋና ምስክሮችን ለማግኘት ባለመቻላቸው ነው። ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከ6 አመት በፊት በተነሳውና ከ1 ሺ 200 በላይ ሰዎች የተገደሉበትን የምርጫ ማግስት ረብሻ አነሳስተዋል በሚል ነው። በምክትላቸው ዊሊያም ሩቶ ላይ የተጀመረው ክስ ይቀጠል አይቀጥል የታወቀ ነገር የለም። የአፍሪካ መሪዎች ክሱ እንዲቋረጥ ሲወተውቱ ቆይተዋል። ፕሬዚዳንቱ …

ታህሳስ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በጌዲዮ ዞን በሚገኙ 9 ወረዳዎች ውስጥ በዚህ ወር ውስጥ ባልተለመደ ሁኔታ ከፍተኛ ረሀብ በመከሰቱ የዞኑ የአገር ሽማግሌዎች ህዝቡ ያለበትን አሳሳቢ ሁኔታ በመግለጽ የተፈራረሙበትን ደብዳቤ ዛሬ ለዞኑ መስተዳድር አስገብተዋል። በከፍተኛ ደረጃ ተደናገጡት የዞኑ ባለስልጣናት መረጃው ይፋ እንዳይወጣ ለማድረግ ዛሬ ቀኑን ሙሉ በስብሰባ ተወጥረው መዋላቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። የአገር ሽማግሌዎቹ  የገጠሩ …

ታህሳስ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ህዝባዊ ሀይሉ የተመሰረተበትን አንደኛ አመት በማስመልከት ባወጣው መግለጫ ” ያለፈው አንድ አመት የመሰባሰብ ድርጅት መሰረታዊ የሆኑ የፖለቲካና የወታደራዊ ስልጠና የተሰጠበት፣ የድርጅት ማጠናከሪያና የማጥራት ሂደት የተካሄደበት ” ነበር ብሎአል። መጪውን አመት የተለየ የሚያደርገው ህዝባዊ ሀይሉ በህዝብ ላይ በሚደርሰው ግፍና ውርደት ከሚሰማው ከፍተኛ ብስጭትና ቁጭት አልፎ ባለፈው አመት ሊደርስላቸው ያልቻለውን የአገራችንን …

ታህሳስ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በአሁኑ ወቅት በሃገራችን ያሉት የቆዳ ፋብሪካዎች የግብዓት ፍላጎታቸው በዓመት ከ40 ሚሊዮን በላይ የበግና ፍየል ሌጦና ከ2 ሚሊየን በላይ የበሬ ቆዳ ሲሆን፥ እየቀረበላቸው ያለው የቆዳ መጠን  ከ16 እስክ 17 ሚሊየን ሌጦ እና በቆዳ ደግሞ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በታች ነው። ከዚህ በመነሳት ሃገሪቱ ከዘርፉ የምትጠብቀውን ገቢ ማሳካት አስቸጋሪ እንደሆነ ነው …

ታህሳስ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ሪክ ማቻር ከተደበቁበት ቦታ ሆነው ለአለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን እንደገለጹት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ተቃዋሚዎቻቸውን ለመምታት የተጠቀሙበት ዘዴ ነው ብለዋል። የፕሬዚዳንቱ ጠባቂዎች እርስበርሳቸው መጋጨታቸውን የገለጹት የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ማቻር፣ ይሁን እንጅ የሳልቫኪር መንግስት አጋጣሚውን ተጠቅሞ ተቀናቃኞችን እያሰረ ነው ሲል አክለዋል። በአገሪቱ ውስጥ የሚታየው ውጥረት በማየሉ አዲሲቷ አፍሪካዊት አገር በእርስበርስ የጎሳ ጦርነት ትታመሳለች …

ታህሳስ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዳያስፖራ ተሳትፎ ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ጀኔራል የተገኘ መረጃ  በግምት ከ2-3 ሚሊዮን የሚደርሱ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ የአለም ከፍሎች ቢኖሩም ለአገራቸው ያላቸው አስተዋጽኦ ግን አነስተኛ ነው ብሎአል። አውሮፖና አሜሪካ የኢትዮጵያውያኑ ዳያስፖራዎች ዋነኛ መዳረሻዎች ሲሆኑ በርካታ የዳያስፖራው አባላትም በእነዚሁ አህጉራት ይገኛሉ ይላል። እውቅና ያገኙ ተመራማሪዎች ፤ የጤና ባለሙያዎች ፤የዩንቨርስቲ …

ታህሳስ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-የመንግስት ሰራተኛው በከፍተኛ የኑሮ ውድነት እየተሰቃዩ መሆኑን እንደሚያዉቁ የተናገሩት ሁለት የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣኖች፣ ይሁን እንጅ በሚቀጥሉት ሶስትና አራት አመታት በጉልህ የሚታይ ደሞዝ ጭማሪ እንደማይኖር ገልጸዋል። በየአምስት አመቱ የቤተሰብ ፍጆታቸው በተመረጡ ናሙናዎች ተወስዶ በሚለካው የግሽበት አሃዝ ስሌት መንግስት የኑሮ ውድነቱ በአንድ አሃዝ መውረዱን ቢገልጽም፣ የኑሮ ውድነት ግን አለመርገቡን ነዋሪዎች ይናገራሉ። …

ታህሳስ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በተለይ ከመሬት ይዞታ ጋር በተያያዘ ውሳኔ የሚያስፈልጋቸውና በታችኛው አመራር ጭምር ሊፈቱ የሚገቡ ጉዳዮች ተጠያቂነትን ከመፍራት አኳያ ወደ መካከለኛና ከፍተኛ አመራሩ የመግፋት ጉዳይ በተደጋጋሚ መከሰቱ አሳሳቢ መሆኑ ሰሞኑን በተደረገው ግምገማ ላይ ቀርቧል፡፡ አስተዳደሩ የ2006 የመጀመሪው ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም  በገመገመበት መድረክ ላይ ተጠያቂነትን ለመሸሽ ሲባል ስራዎችን ወደላኛው አካል የመግፋት ጉዳይ …

ታህሳስ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ተሞክሮ የነበረው መፈንቅለ መንግስት መክሸፉን በተናገሩ ማግስት ግጭት መነሳቱን ረዩተርስ ዘግቧል። አልፎ አልፎ ይሰማ የነበረው ተኩስ በተከታታይ መሰማቱን የገለጸው ረዩተርስ፣ የአሜሪካ ልዩ ልኡክ የሆኑት ዶናልድ ቡዝ ሁኔታው ውጥረት የበዛበትና ያልተረጋጋ መሆኑን ገልጸዋል። እስካሁን ባለው መረጃ 26 ሰዎች እንደተገደሉ ቢታወቅም አንዳንድ የመገናኛ ብዙሀን ከ60 በላይ ወታደሮች እንደተገደሉ እየዘቡ …

ታህሳስ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በመንግስት የሀላፊነት ቦታ ላይ የሚገኙ አንድ ስማቸው እንዳይገለጸት የፈለጉ ሰው ለኢሳት እንደተናገሩት በክልሉ በቆዩባቸው ቀናት የታዘቡት ነገር ቢኖር በክልሉ የሰላም እጦት ዋናው ችግር መሆኑን ነው። ምንም እንኳ መንግስት ያለምንም ችግር በአሉ መጠናቀቁን ቢገልጽም እውነታው ግን ከዚህ የተለየ እንደነበር ሃላፊው ይናገራሉ። በከተማዋ ዳርቻዎች ታንኮች፣ ከባድ መሳሪያ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ፣ ልዩ …

ታህሳስ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-የወደፊቱ ጠ/ሚንስትር ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ የሚነገርላቸው ዶ/ር ቴዎድሮስ ግሳጼው የቀረበባቸው ” በሳውድ አረቢያ ላይ ተመጣጣኝ የአጸፋ እርምጃ እንወስዳለን” ብለው መናገራቸውን ተከትሎ ነው። ኢህአዴግ በጉዳዩ ላይ ለመነጋገር አስቸኳይ ስብሰባ የጠራ ሲሆን ዶ/ር ቴዎድሮስም ” ያለግንባሩ ውሳኔ እንዲህ አይነት ጠንካራ አስተያየት ለምን እንደሰጡ እንዲያብራሩ ተጠይቀዋል። “ዶ/ር ቴዎድሮስ በቂ ማብራሪያ ለመስጠት ባለመቻላቸው …

ታህሳስ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በሲዳማ ዞን በአለታ ጩኮ ወረዳ የግብርና ፅ/ቤ ባለሙያ የሆነው  ወጣት ነጋልኝ ፀጋዬ በሙያው ለአመታት ህብረተሰቡን ሲያገለግል ቢቆይም የመንግስትን አሰራር በተደጋጋሚ በመተቸቱ፣ ከመስርያ ቤቱ ኃላፊዎች ጋር በተለያዩ ግዜያት ግጭት ውስጥ ከመግባቱም በላይ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ሳይቀር ደርሶት ነበር። ወጣት ነጋልኝ ፀጋዬ መንግስትን በግልፅ በመቃወም፤ መስተካከል ያለበትን ጉዳይ በግልፅ መናገር ልዩ ባህሪው …

ታህሳስ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-የአዲሲቷ አገር መሪ የሆኑት ሳልቫኪር  የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር ታማኝ ወታደሮች መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ሌሊቱን ተኩስ መጀመራቸውን ተናግረዋል። ችግሩ በቁጥጥር ስር መዋሉን የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ እንዲህ አይነቱን ድርጊት እንደማይታገሱትና ሙከራውን ባደረጉት ላይ ሁሉ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስዱ ተናግረዋል። የአገሪቱ ቴሌቪዥን ከጠፋ ከሰአታት በሁዋላ እንደገና ስራ ጀምሯል። እስካሁን ድረስ ምን ያክል …

ታህሳስ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በቀረረበባቸው የፕሬስ ክስ ወደ አዋሳ በተጉዋዙበት ወቅት በድንገት በተከሰተ የተሸከርካሪ አደጋ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበትን የኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ  አዘጋጅ ለሆነው ለወጣት ኤፍሬም በየነ የሕክምና ወጪ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ምሽት ሰኞና ማክሰኞ በአዲስአበባ እንደሚካሄድ ከዕርዳታ አስተባባሪዎች መካከል አንዱ ለሪፖርተራችን ገልጿል፡፡ በዚህ የእራት ምሽት ላይ 500 ብር ዋጋ ያላቸው ትኬቶች ተዘጋጅተው …

ታህሳስ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አልፎ አልፎ አንዳንድ አመራሮች በአመለካከትም ሆነ በተግባር በሙስና ተዘፍቀው ተገኝተዋል ያለው የአስተዳደሩ ሰነድ፣ በከተማው ውስጥ ሕገወጥ የመሬት ወረራ፣ ሕገወጥ ግንባታና ሕገወጥ ንግድ አሁንም አሳሳቢ ችግሮች ሆነው መቀጠላቸውን አትቷል፡፡ በትላንትናው እለት የአዲስ አበባ ከተማ አመራሮችን ጠርቶ የመከረው ቢሮው ችግሮች በስፋት የመልካም አሰተዳደር እጦት መገለጫ እየሆኑ መምጣታቸውን …

ታህሳስ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ትእዛዙን የሰጠው የቦሌ ክፍለከተማ ሲሆን፣ ነዋሪዎቹ እስከ ማክሰኞ ቤታቸውን ለቀው ካልወጡ ፣ አፍራሽ ግብረሀይል በጉልበት እንደሚያፈርስባቸው አስታውቋል። “በሶስት ቀናት ውስጥ የት እንሄዳለን?’ ሲሉ የሚጠይቁት ነዋሪዎች ፣በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ የሚታየው የቤት ኪራይ መጨመር አስግቶናል ብለዋል። ሜዳ ላይ እንዃ እንዳንወድቅ ሜዳውም እየታረሰ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ምሬታቸውን ገልጸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በኦሮሚያ …

ታህሳስ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- በኢትዩጵያ  62 በመቶ የሚሆኑት ከ 20- 49 እድሜ ክልል የሆናቸው ሴቶች ጋብቻ የመሰረቱት እድሚያቸው ከ 18 ዓመት በታች በነበሩበት ወቅት ነው፡፡ አቶ ተስፋየ ተካ የህዝብ ጤና ባለሙያ ባደረጉት ጥናት በላፈው ዓመት ልዩነቶችን ለማወቅ በተካሄደ ጥናት  በአማራ ክልል ያለ እድሜ ጋብቻ  ከፍተኛውን መጠን እንደያዘ ይኸው ጥናት ይጠቁማል፡፡48 በመቶ በገጠር …

ታህሳስ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- በሽብር ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት የድምጻችን ይሰማ መሪዎች ተከላከሉ መባላቸውን ጠበቃ  ተማም አባ ቡልጉ ተናግረዋል። 12 ሰዎች በነጻ የተለቀቁ ሲሆን፣ እነ አቶ አቡበከር አህመድና ሌሎች ደግሞ በተከሰሱበት ሽብር የማድረግ ወንጀል ሳይሆን ሽብር በማነሳሳት ጉዳይ ላይ እንዲካለከሉ ተበይኖአል። ሙራድ ሹኩር ጀማል፣  ኑሩ ቱርኪ  ኑሩ፣ ሼህ ባህሩ ኡመር ሸኩር …

ታህሳስ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መድረክ  ዓርብ ታህሳስ 4 ቀን 2006 ዓ.ም በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጥ ሲሆን፣  ዶ/ር መረራ ጉዲና ለኢሳት እንደገለጹት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው አፈና እየተባባሰ መሄዱ መግለጫውን ለመስጠት አስገድዷቸዋል። የሳውድ አረቢያ መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደውን እርምጃ ለመቃወም መድረክ ቢጠይቅም በገዢው ፓርቲ መከልከሉን ዶ/ር መረራ አውስተዋል …

ታህሳስ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- የቀድሞ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ ክሳቸው በየትኛው ፍርድ ቤት ይታይ በሚለው ጉዳይ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የመጨረሻ ውሳኔውን እንዲያሳውቅ ሲል የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ትእዛዝ በመስጠት ለታህሳስ 22 ቀን 2006 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ። ፍ/ቤቱ ቀደም ሲል በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ጉዳዩን …

ታህሳስ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- ማክሰኞ በደቡብ አፍሪካ ስዌቶ በተደረገው የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት የኔልሰን ማንዴላ መታሰቢያ  ከመድረክ ይተላለፍ የነበረውን ዝግጅት በምልክት ቋንቋ መስማት ለተሳናቸው ዜጎች እንዲያስተላልፍ  ተመድቦ የነበረው  ሰው፤ ያሳይ የነበረው አካላዊ እንቅስቃሴና ምልክት የውሸት እንደነበር መጋለጡን ዓለማቀፍ ብዙሀን መገናኛ እየዘገቡ ነው። ድርጊቱ የደቡብ አፍሪካን መንግስትና በ ዓለማቀፍ ደረጃም መስማት የተሳናቸውን የህብረተሰብ …

ታህሳስ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- መንግስት በውጭ አገር ለሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ሀቅሙ ላላቸው ዜጎች የ40 በ60 እንዲሁም በአዲስ አበባ በአነስተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ዜጎች ደግሞ የ10 በዘጠና እና የ20 በ80 የቤት ልማት እዶችን ዘርግቷል። በ10/90 850 ሺ በ 20/80 ደግሞ 350 ሺ የአዲስ አበባ ነዋሪ ተመዝግቦ እድሉን በመጠባበቅ ላይ ሲሆን ከ12 ሺ በላይ በውጭ አገር …

ታህሳስ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች እና በሰሜን የአገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ከተሞች መብራት በተደጋጋሚ እየተቋረጠ ሲሆን፣ መብራት ሀይል የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተናበው ለመስራት አልቻሉም በሚል ወቀሳ አሰምቷል።  በጉዳዩ ዙሪያ ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው የኢትዩጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ     40 በመቶ የሚሆነው ኤሌክትሪክ ሃይል መቆራረጥ የሚፈጠረው በሰው ሰራሺ አደጋ ነው ያሉ …

ታህሳስ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- መምህራኑ ለኢሳት እንደተናገሩት ያለፍላጎታቸው ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል ከደሞዛቸው ላይ ገንዘብ መቆረጡን በመቃወም የተቆረጠው ገንዘብ ተመልሶ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ሙሉ ደሞዛችን እስካልተሰጠን ድረስ ምንም አይነት ክፍያ አንቀበለም ያሉት መምህራኑ፣ እስከ ፊታችን አርብ ሙሉ ደሞዛችን የማይሰጠን ከሆነ የስራ ማቆም አድማ እንዳርጋለን ሲሉ አስጠንቅቀዋል። በደቡብ ክልል መንግስት ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል …

ታህሳስ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተለያዩ ዞንና ወረዳዎች አማራ ናችሁ ተብለው በተባረሩ በሺዎች በሚቆጠሩ ዜጎች  ላይ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና አካላዊ ጉዳት እንደተፈፀመ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ባካሄደው ጥናት አረጋግጧል ፡፡ በክልል በተለያዩ ዞንና ወረዳዎች ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ቁጥራቸው ከ10 ሺህ  በላይ የሚገመቱ ዜጐች ለረዥም አመታት ይኖሩበት ከነበረው አካባቢያቸው የዚህ ክልል “ተወላጆች አይደላችሁም” …

ታህሳስ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ብሉምበርግ እንደዘገበው  ከአራቱም አገራት የተውጣጣ ኮሚቴ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከተቋቋመ በሁዋላ፣ በግድቡ ላይ ጥናት የሚካሂዱ ምሁራንንና ይመርጣል። ይህ ቡድን ጥናቱን ሲያጠቃልል ለሶስቱም መንግስታት የጥናት ውጤቱን ያቀርባል። ከዚህ ቀደም የተቋቋመው አንድ አለማቀፍ ቡድን በግድቡ ፕሮጀክት ላይ ተጨማሪ ጥናት እንዲካሄድ ጠይቆ ነበር። ባለፈው ወር በሚቋቋመው ኮሚቴ ላይ አለማቀፍ ተወካዮች እንዲገኙ …

ታህሳስ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የፕሬስ ታሪክ ውስጥ ለ18 ኣመታት በሕትመት ላይ የቆየው የሪፖርተር አማርኛ እና እንግሊዝኛ ጋዜጦች አሳታሚ የሆነው ሚዲያ ኤንድ ኮምኒኬሽን ሴንተር ባለቤትና የቀድሞው የህወሃት ታጋይ አቶ አማረ አረጋዊ በጠና ታመው በአዲስ አበባ በኮሪያ ሆስፒታል ሕክምናቸውን እየተከታተሉ መሆኑን የቅርብ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ አቶ አማረ ባደረባቸው ድንገተኛ ሕመም በኮሪያ ሆስፒታል ሲረዱ 10 ቀናት …

ታህሳስ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያኑ ለኢሳት በላኩት መረጃ ሰኞ እለት ፕራግ በሚገኘው የሳውዲ ኢምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት በጩኸትና የተለያዩ መፈክሮችን በመጠቀም አውግዘዋል። ያዘጋጁትን የተቃውሞ ደብዳቤ ለኢምባሲው ተወካይ ማስረከባቸውንም አክለው ገልጸዋል።

ታህሳስ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-የአለማችን ታላላቅ መሪዎች፣ እና ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት በዚህ ዝግጅት የማንዴላ የትግል ጉዜ ተዘክሯል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ይህን ታላቅ የታሪክ ሰው ለመግለጽ አስቸጋሪ ነው ብለዋል፡፤ እስረኞችን ብቻ ሳይሆን አሳሪዎችንም ነጻ ያወጣ፣ሀሳብን ወደ ተግባር የለወጠ  ሲሉ ማንዴላን ገልጸዋቸዋል። ከእንግዲህ እንደማንዴላ አይነት ሰው አናገኝም ያሉት ኦባማ፣ከማንዴላ ባንስም ማንዴላ ግን የተሻልኩ ሰው …

ህዳር ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በጅጅጋ ከፍተኛ መስሪያ ቤቶች ውስጥ የሚሰሩ የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የህወሀት  ከፍተኛ የመከላከያ አዛዦች ወደ ሶማሊ ክልል ሲመዱ  ከክልሉ መንግስት ጋር በመተባበር ከፍተኛ ሀብት አጋብሰው እንደሚመለሱ ተናግረዋል። በአሁኑ ጊዜ ተቀማጭነታቸው ጅጅጋ የሆኑት እና በክልሉ ቁጥር አንድ ሀብታም የሚባሉት /ወ/ት ሀዋ የሌተናንት ጄኔራል ዮሀንስ ገ/መስቀል ሁለተኛ ሚስትና የልጅ እናት ሲሆኑ፣ ግለሰቧ …

ህዳር ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በከፍተኛው ፍርድ ቤት ታስረው ከተለቀቁ በሁዋላ ተመልሰው እንዲታሰሩ የተደረጉት የቁጫ ወረዳ የአገር ሽማግሌዎች፣ የዋስትና መብታቸው ተነስቶ ተመልሰው በአርባምንጭ እስር ቤት እንዲታሰሩ መደረጉን ከሽማግሌዎች አንዱ ገልጸዋል። ችግሩን ለፌደራል መንግስት አቤት ለማለት እስከዛሬ ሲመላለሱ የቆዩት የአገር ሽማግሌዎች አንድም ባለስልጣን ሳያገኙ በመቅረት ነገ ወደ አካባቢያቸው ተመልሰው ፍርድ ቤት እንደሚቆሙና እንደ ጓደኞቻቸው የዋስትና …

ህዳር ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል ያለፈቃዳቸው የአንድ ወር ደሞዛቸው የተቆረጠባቸው የቦንጋ መምህራን፣ የስራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ ካስታወቁ በሁዋላ፣ ዋና አስተዳዳሪው ማከስኞ ከመምህራን ጋር ለመነጋገር ቀጠሮ መያዛቸው ታውቛል። ከመምህራን ተወካዮች ጋር የተነጋገሩት ባለስልጣኑ፣ ስምምነት ለመድረስ ባለመቻላቸው ከመላው መምህራን ጋር ለመነጋገር ወስነዋል። መምህራን የተቆረጠባቸው ደሞዝ መልሶ የማይሰጣቸው ከሆነ በአድማው ለመቀጠል እየተናገሩ ነው።

ህዳር ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ደቡብ አፍሪካውያን ለነፃነት አባታቸውና ለቀድሞ መሪያቸው ለኔልሰን ማንዴላ ሀዘናቸውን ለመግለጽ ወደ ጁሀንስበርግበና ሶዌቶ እየተሰበሰቡ ሲሆን፤ ታላላቅ የዓለማችን መሪዎችና ታዋቂ ሰዎችም በማንዴላ ሞት ሀዘናቸውን እየገለፁ ነው። በርካታ ደቡብ አፍሪካውያን በስዌቶ በሚገኘው በቀድሞው የኔልሰን ማንዴላ መኖሪያ ቤት በመሰባሰብ በባህላዊ ስርአታቸው መሰረት በልዩ ልዩ የብሔረሰቦች የሀዘን ጭፈራ  ለመሪያቸው ያላቸውን አክብሮች እየገለፁ …