የቁጫ ነዋሪዎች መኖር አልቻልንም ሲሉ ምሬታቸውን ገለጹ
ህዳር ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጋሞጎፋ ዞን በቁጫ ወረዳ ከማንነት ጋር በተያያዘ የተነሳው ተቃውሞ መፍቴ አጥቶ እንደቀጠለ ባለበት ወቅት በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እየታሰሩ መሆኑን የአነጋግረናቸው የአገር ሽማግሌዎች ገልጸዋል። በዛሬው እለት በርካታ የአገር ሽማግሌዎች የጸጥታ ሀይሎች እያደረሱባቸውን ያለውን ስቃይ ለማስታወቅ በጠቅላይ ሚኒሰትሩ ጽህፈት ቤትና በፌዴሬሽን ምክር ቤት ቢገኙም የሚያነጋግራቸው አጥተው ተመልሰዋል። አገር ሽማግሌዎቹ …