በደቡብ ሱዳን ግጭቱ እንደቀጠለ ነው
ታህሳስ ፳፫( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲሲቷ አፍሪካዊት አገር የተጀመረው የእርስ በርስ ጦርነት በሺ የሚቆጠሩ የአገሪቱ ዜጎች ህይወት ከቀጠፈ በሁዋላ የሁለቱም ተፋላሚ ሀይሎች ተደራዳሪዎች በአዲስ አበባ ቢገኙም አሁንም ጦርነቱ ቀጥሎአል። በአዲስ አበባ ይጀመራል ተብሎ የሚጠበቀው የሰላም ድርድር የተኩስ አቋም ስምምነት እንዲፈረም ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። የተቃዋሚው መሪ ሪክ ማቻር በበኩላቸው የተኩስ ማቆም ስምምነት …