የአሜሪካ ኮንግረስ ለኢትዮጵያ የሚሰጠው እርዳታ ህዝብ የማያፈናቅልና የሰብአዊ መብት ጥሰት የማያባብስ መሆኑ እንዲረጋገጥ የሚያደርግ ውሳኔ አሳለፈ።
ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኦክላንድ የምርምር ተቋም ውሳኔውን ታሪካዊ ብሎታል። በኮንግረሱ የጸደቀው ኦምኒበስ አፕሮፕሬየሽንስ ቢል እየተባለ የሚጠራው ህግ (Omnibus Appropriations Bill) አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው እርዳታ ዜጎችን ለማፈናቀል እንደማይውል፣ ይህንንም ተከትሎ ሰብአዊ መብቶች እንዳይጣሱ ያረጋግጣል። በኦሞ ሸለቆና በጋምቤላ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ነዋሪዎችን በማፈናቀል በሚደረገው ልማት ላይ የአሜሪካ እርዳታ ጥቅም ላይ …