የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር -አንድነት አባላት ላይ የተወሰደውን የጭካኔ እርምጃ በጥብቅ አወገዘ።
ጥር ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ትብብሩ ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ ፤ገዥው ፓርቲ በአንድነት የውስጥ ጉዳይ ገብቶ የሚፈፅመውን ደባ ለመቃወም ሰልፍ በወጡ የአንድነት አመራሮች፣ አባላት፣ ደጋፊዎችና በፓርቲው ጽህፈትቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ቤተ ክርስትያን አካባቢ በነበሩ አዛውንቶቸ ላይ ሳይቀር ድብደባ በመፈጸም ፤ጭካኔውን ዳግመኛ አሳይቶናል ብሏል። ትብብሩ ጠርቶት በነበረው የአዳር ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተወሰደውን ዘግናኝ እርምጃ …