ታኀሳስ ፳፱(ሃያ ዘጠኖ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ራዲዮው  ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ የውሎ ሰፈር የውስጥ መንገዶች ግድግዳ ላይ የተጻፉት መፈክሮች-ህዝበ-ሙስሊሙ መብቱን ለማስከበር ያነሳቸውን ያቄዎች የሚያሰተጋቡና  መብታቸውን በመጠየቃቸው የታሰሩት የሙስሊም  መሪዎች እንዲፈቱ የሚጠይቁ ናቸው። ከተለጠፉት መፈክሮች መካከል፦”አዐባሪዎች አይደለንም፣ የታሰሩት ሙስሊሞች ይፈቱ!ኮሚቴው ይፈታ!የሂጃብ ገፈፋው ይቁም! ትግሉ ይቀጥላል! እና ፍትህ ናፈቀን!”የሚሉት ይገኙበታል። በግድግዳ ላይ ከተጻፉትና ከተለጠፉት ባሻገር ሙስሊሞች …

ታኀሳስ ፳፱(ሃያ ዘጠኖ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳትና የኢትዮጵያ ጳጳሳት ጉባዔ ፕሬዚዳንት ብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስ ሱራፌል የካርዲናልነት ማዕረግ አገኙ፡፡ ብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስን ጨምሮ ለ15 ሊቃነ ጳጳሳት የካርዲናልነት ማዕረግና ለአምስት ሊቀ ጳጳሳትና ጳጳሳት ደግሞ ድምፅ አልባ  የካርዲናልነት ሹመት ባለፈው እሑድ ረፋድ ላይ በቫቲካን በመስጠት ይፋ ያደረጉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ …

ታኀሳስ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድነት፤ ከምርጫው ከታገድኩ  ውሳኔው ፖለቲካዊ ነው የሚሆነው አለ። አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት)እና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)  የውስጥ ችግሮቻቸውን ካለፈቱ የምርጫውን ሂደት ላይሳተፉ ይችላሉ ሲል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስጠነቀቀ። የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ  ዶክተር አዲሱ ገብረ እግዚአብሄር ፦ሁለቱ ፓርቲዎች በውስጥ  ህገ ደንባቸው ሊሄዱ እንዳልቻሉ በመጥቀስ፤ ይህንንም …

ታኀሳስ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ሊግ፤ ከአማራ ክልል ኦሮሚያ ዞን ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ  ታስረው ከስምንት ወራት በላይ ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ታሳሪዎችን ስም ዝርዝር ይፋ አደረገ። ሊጉ  የ 26  እስረኞችን ስም ዝርዝር በማያያዝ ባወጣው መግለጫ፤ ከወራት በፊት የአዲስ አበባን አዲስ ማስተር ፕላን በመቃወም ተነስቶ ከነበረው ሰላማዊ ተቃውሞ …

ታኀሳስ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምርጫ 97 ወቅት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን የሸለመው “ያራ” የተሰኘ የኖርዌይ ድርጅት  በሙስና ተከሰሰ ፤ ኢትዮጰያውያንም ተጨማሪ ክስ ያቀርባሉ። በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1997 ዓመተ ምህረት ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ 200 000 ዶላር የሸለመውና- ሽልማቱን ተከትሎ  በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የኢትዮጵያ ብቸኛ የማዳበሪያ አቅራቢ የሆነው የ”ያራ ኩባንያ”ዳይሬክተር ቶርሊፍ ኢንገር፤ …

ታኀሳስ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እንደ ጋዜጣው ዘገባ የአክሊል ክሬቲቭ ኤጄንሲ ባለቤት የሆነው ተከስተ ስብሀት  ነጋ፤ በአካባቢው ያለን 4000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር መሬትን ለተለያዩ መዝናኛዎች፣እንዲሁም  43 ትልልቅ ጎተራዎችን ለማስታወቂያ ስራ  ነው በ600 ሺህ ብር ለአምስት ዓመት ኮንትራት የወሰደው። ለጥቂት ቀናት የሚለጠፍ አንድ ማስታወቂያ ብቻ ብዙ ሺህ ብር  በሚያስከፍልበት በአሁኑ ወቅት፤ ትልቅ አደባባይ …

ታኀሳስ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በጣና ሐይቅና በዙሪባ በሚገኙ የእርሻ መሬቶች ላይ የተከሰተውን አደገኛ አረም ለማየት የተንቀሳቀሰው ቡድን ሃምሳ ሽህ ሄክታር የሚሸፍን የጣና ሐይቅ እና ዙሪያው በእምቦጭ አረም መወረሩን ለመገናኛ ብዙሃን ገልጿል ፡፡ ይህም ለሐይቁ ህልውና አስጊ መሆኑን፤ የተለያዩ ከፍተኛ የገዢው መንግስት አካላትና በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ምሁራን ተናግረዋል፡፡ አርሶ አደሮች በበኩላቸው፦” የምናርሰው …

ታኀሳስ ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ረቡዕ ታህሳስ 15፣ 2007 ዓም ኢሳት 4 የአየር ሃይል አብራሪዎች ወደ ኬንያ ማምራታቸውን በሰበር ዜና ካቀረበ በሁዋላ፣ አንድ ተጨማሪ የአየር ሃይል ባልደረባ ጠፍቶ ተቃዋሚዎችን መቀላለቀሉ ተሰምቷል። ባለፈው ሮብ የጠፉት የሚግ 23 አብራሪ ሻምበል ገዛሃኝ ደረሰ፣ የኤም አይ 35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር አብራሪ ሻምበል ዳንኤል ግርማ፣  የኤም አይ …

ታኀሳስ ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመጪው ግንቦት በሚካሄደው ምርጫ ሂደት ላይ ቅሬታዎች አሉኝ ያለው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ፤    ከገዥው ፓርቲ ጋር በአስቸኳይ መወያየት እንደሚፈልግ አስታውቋል፡፡ መድረክ በትናንትናው እለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በምርጫ ታዛቢዎችና አስፈፃሚዎች አመራረጥና በምርጫው ለሚሳተፉ ፓርቲዎች ከመንግስት በሚሰጠው የድጐማ ገንዘብ ክፍፍል ላይ ቅሬታ እንዳለው ተናግሯል። መድረክ አያይዞም፦”ምርጫውን ለማስፈፀምና ለመታዘብ …

ታኀሳስ ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት፤ ታህሳስ 26- 2007  ዓመተ ምህረት  ጧት እና ምሽት ላይ  በርካታ ታንኮችን እና ከባድ  ብረት ለበስ የጦር ተሽከርካሪዎችን ወደ ሰሜን ኢትዮጰያ አጓጉዟል። ከየት ቦታ እንደተነሱ ያልታወቁትና ወደ ሰሜን አቅጣጫ ያመሩት ታንኮች፤ ምሽት ላይ ወልዲያ ከተማ ማረፋቸውን  ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። መንግስት ከሰሜን አካባቢ ጥቃት ሊሰነዘርብኝ ይችላል የሚል ግምገማ ማካሄዱን …

ታኀሳስ ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብአዴን ዋና ጸሃፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን ይህን የተናገሩት መጪውን ምርጫ አስመልክቶ ለተመረጡ የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባላትና ለባለድርሻ አካላት ባደረጉት ገለጻ ነው። አቶ አለምነው ነጻ ሚዲያ በሌለበት አገር ኢሳትና ቪኦኤን የመሳሰሉ ነጻ ሚዲያዎችን ማፈን ተገቢ ነወይ የሚል የጽሁፍ ጥያቄ የቀረበላቸው ሲሆን፣ ቪኦኤ በአሜሪካ መንግስት ሳንባ የሚተነፍስ ነው …

ታኀሳስ ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አራት ከፍተኛ ማእረግ ያላቸው የአየር ሃይል አብራሪዎች መጥፋታቸውን ተከትሎ በድሬዳዋ የአየር ሃይል ምድብ ሲካሄድ የነበረው የ3 ቀናት ግምገማ ሃሙስ እለት ተጠናቋል። በግምገማው ላይ አብራሪዎች፣ አሰልጣኞች፣ ቴክኒሻኖችና ሰራተኞች የተገኙ ሲሆን፣ ሰራተኞቹ ስለጠፉት አብሪዎች የተሰማቸውን ስሜት እንዲናገሩ፣ የሚያውቁትን ሚስጢር እንዲያወጡ ሲገደዱ ሰንብተዋል። ብዙዎች ” ስለጠፉት አብራሪዎች ምን ትላላለችሁ?’ እየተባሉ …

ታኀሳስ ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው ችግር እየከፋ መሄዱ ለህዝባዊ አመጽ በር ሊከፍት ይችላል የሚል ስጋት ያደረባቸው ምእራባዊያን በአሜሪካ ፊት አውራሪነት በአገር ውስጥና በውጭ ያሉትን ተቃዋሚዎች ከኢህአዴግ ጋር ለማቀራረብ እየተሯሯጡ መሆኑን የዲፕሎማቲክ ምንጮች ገለጹ። እንደምንጮች ገለጻ በአገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ከሚታገሉት ድርጅቶች ውስጥ አንዳንዶችን በማካተት፣ በውጭ ከሚገኙ ገዢውን መንግስት በሃይል …

ታኀሳስ ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰንደቅ ጋዜጣ እንደዘገበው፣የቀድሞው የህወሀት ሊቀመንበር አቶ ስብሀት ነጋ ይህን ያሉት የህወሀትን 40ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ሰሞኑን ወደ ትግራይ ለተንቀሳቅቀሱት  ጎብኝዎች የደርግ 604ኛ ኮር የተደመሰሰበትን ወታደራዊ ሳይንስ አስመልክቶ  በሽሬ ከተማ በተሰናዳ መድረክ ላይ ባደረጉት ገለጻ ነው። “የቀዝቃዘውን ጦርነት ማክተም ተክትሎ ታላቋ ሶቪየት ህብረት መፈራረስ ጀመረች ያሉት አቶ ስብሀት፤ክስተቱን …

ታኀሳስ ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የተከሰሱት 6 የተቃዋሚ ድርጅቶች አመራሮችና ሌሎች ዜጎች በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ 19ኛው ወንጀል ምድብ ችሎት ሁለት ተለዋጭ ቀጠሮ እንደሰጠባቸው ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች የሆኑት አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና አቶ …

ታኀሳስ ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት በጋምቤላ ክልል በጎደሬ ወረዳ ከመጋቢት እስከ ጳጉሜ በነበሩት ግጭቶች የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ12 አይበልጥም በማለት በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቢቆይም፣ አቃቢ ህግ የክልሉን ባለስልጣናት ለመክሰስ ባቀረበው የክስ ቻርጅ ላይ 79 ሰዎች መገደላቸውን ፣ 273 ቤቶች መቃጠላቸውን ከ13 ሺ በላይ ዜጎች እንዲፈናቀሉ ማድረጋቸውን ገልጿል። አንዳንድ ወገኖች የተገደሉት ሰዎች …

ታኀሳስ ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ጎንደር እስቴ ወረዳ የሚገኙ  መምህራን ለ3 ቀናት የሚቆይ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ስብሰባ እንዲካፈሉ ቢጠሩም፣ መምህራኑ በስብሰባው ላይ ከተገኙ በሁዋላ፣ በአንድ ድምጽ ስብሰባ ኣንሳተፍም በማለት ጥለው ወጥተዋል። መምህራኑ መንገድ የመሳሰሉ የመሰረተ-ልማቶች አልተሟሉም፣ ለመምህራን በቂ የሆነ ክፍያ አይሰጥም በማለት ተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያቀርቡ ቆይተዋል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ የተጠራው ስብሰባ …

ታኀሳስ ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የየመን አገር ውስጥ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ኢትዮጵያውያኑ  ሞቻ በሚባለው የወደብ ከተማ አቅራቢያ  ሲደርሱ የተሳፈሩበት ጀልባ በመስጠሙ 24ቱም አትዮጵያውያን አልቀዋል። የሁሉም አስከሬን መገኙቱን ባለስልጣኑ ሲናገሩ፣ የተረፉ ካሉም በማፈላለግ ላይ መሆኑን አስታውቋል። ባለፈው ወር ከ79 ያላነሱ ኢትዮጵያውያን ባህር ላይ ማለቃቸው ሲታወስ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ባህር ላይ የሞቱ ኢትዮጵያውያንን ቁጥር …

ታኀሳስ ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ተማሪዎች ኢህአዴግን እንዲመርጡ በሚል በግዳጅ በተዘጋጀው የፖለቲካ ስልጠና ላይ ተማሪዎች ፈታኝ የሆኑ ጥያቄዎችን አስተያየቶችን ሰጥተዋል ። ኢህአዴግ እነ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋን የመሰሉ ሰዎችን አሸባሪዎች ማለቱ ትክክል አለመሆኑን የሚገልጹት ተማሪዎች፣ ኢህአዴግን የሚበልጡት በመሉ  አሸባሪ እያለ እንደሚፈርጃቸው ተናግረዋል ፕ/ት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የሚኖርበት ቤት 400 ሺ ብር እንደሚከፈልበት የተናገሩት ተማሪዎች፣ …

ታኀሳስ ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ ከመላው አገሪቱ ለተውጣጡ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች መጪውን ምርጫ በተመለከተ ስልጠና እየሰጠ ሲሆን፣ ከስልጠናው በፊት ማንኛውም ባለስልጣን ስልክ ይዞ መግባት እንደማይችል ጥብቅ የሆነ መልእክት በመተላለፉ፣ ሁሉም ባለስልጣናት ስልካቸውን መኪናቸው ውስጥ እየተዉ ወይም ለሹፌሮቻቸው እየሰጡ መግባታቸው ታውቋል። ወደ ስብሰባው የሚገባ ሰው ማንኛውንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን መያዙንና አለመያዙን ለማረጋገጥ  …

ታኀሳስ ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ጥቅምት ወር በጎንደር፣ በትግራይና በጎጃም አካባቢዎች የተያዙ የተቃዋሚ ድርጅት አመራሮች ፍድር ቤት ቀርበው የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል። ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው የሰማያዊ፣ የአንድነትና የመኢአድ ፓርቲዎች የዞን አመራሮች  ታህሳስ 21 ቀን 2007 ዓ.ም አራዳ ፍርድ ቤት ቀርበው ፣ አመራሮቹ ለ3ኛ ጊዜ የ28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል፡፡ “ፖሊስ ምርመራየን አልጨረስኩም፣ …

ታኀሳስ ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል  በተለይም በአምቦ፣ በአለማያና በሌሎችም ዩኒቨርስቲዎች ለተፈጸሙ ግድያዎችና  በሌሎች  አካባቢዎች ለደረሱ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተጠያቂ የሆኑት ኮማንደር ፣ ታህሳስ 17 ቀን 2007 ዓም ሲያሽከረክሩት የነበረው መኪና ተገልብጦ ከ3 ጠባቂዎቻቸው ጋር በሂርናና አሰበ ተፈሪ መካከል በሚገኝ አንድ ገደላማ ቦታ ላይ ገብተው ህይወታቸው ወዲያውኑ አልፎአል። ኮማንደሩ የተሳፈሩበት …

ታኀሳስ ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው እሮብ ጀምሮ ለ3 ቀናት በተካሄደው የመሰናዶና የመምህራን የፖለቲካ ስልጠና ላይ የገዚውን ፓርቲ ካድሬዎች በጥያቄ ከማፋጠጥ ጀምሮ በአገሪቱ ውስጥ በሚታየው ዘረኝነት፣ የፍትህ እጦትና ሙስና ላይ አስተያየቶችን የሰጡ ተማሪዎች ከስብሰባው መጠናቀቅ በሁዋላ ተማሪውንና ህዝቡን ለአመጽ ለማነሳሳት አስባችሁዋል በሚል ማስጠንቀቂያና ባስፈራሪያ እንደደረሳቸው ዘጋቢያችን ገልጻለች። ለተማሪዎች በሚሊኒየም ትምህርት ቤት በፕላዝማ የተደገፈ …

ታኀሳስ ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአሜሪካ የስቴት ዲፓርትመንት ባወጣው የ2014 ሪፖርት ኢትዮጵያ ለግዳጅ ሥራ፣  ለወሲብ ንግድና  ለሕገወጥ የሰዎች ዝውውር የተዳረጉ ወንዶች፣ ሴቶች እና ሕፃናት መነሻ፤ በተወሰነ ደረጃም መዳረሻ አገር ናት ብሎአል። አዲስ አበባ የሚገኘው ዋና የገበያ ማዕከል ከአፍሪካ ቀዳሚው የወሲብ ንግድ ቤቶች መገኛ ነው የሚለው ሪፖርቱ፣  ዕድሜያቸው እስከ 8 ዓመት የሚሆኑ ልጃገረዶች በነዚህ …

ታኀሳስ ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሥራ ላይ ያለውን የብሮድካስት አዋጅ የሚሽርና ለመጀመሪያ ጊዜ በኢንተርኔት ድረገጾች እንዲሁም ተንቀሳቃሽ ስልክንበመጠቀም የሚቀርብ የብሮድካስት አገልግሎቶችን  ላይ ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግ የሚዲያ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል፡፡ የኢትዮጵያ የብሮድካስት ባለስልጣን ያዘጋጀውና በዚህ ዓመት ለፓርላማው ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቀው ይህው የሚዲያ ረቂቅ አዋጅ አሌክትሮኒክስ መገናኛ ብዙሃን ማለትም ራዲዮ፣ቴሌቪዥን፣ የኢንተርኔት ድረገጾች እንዲሁም የሕትመት …

ታኀሳስ ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ታህሳስ 16 ቀን 2007 ዓም በሶረቃ ከተማ ከ70 ያላነሱ ከትግራይ ክልል የመጡ ታጣቂዎች፣ ከምስላል ወደ  ስላንዴ በረሃ የሚሰራውን መንገድ ለማስቆም ተኩስ በመክፈታቸው 2 አርሶ አደሮች ሲቆስሉ፣ በአብራጅራ ወረዳ የሚገኙ  ጸረ ሽምቅ እየተባሉ የሚጠሩ ሃይሎች ከህዝቡ ጋር በመሆን   የአጸፋ ተኩስ በመክፈታቸው ታጣቂዎች ከአካባቢው ተሰውረዋል። ፌደራል …

ታኀሳስ ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአየር ሃይል ባልደረባ የሆኑት ሻምበል ሳሙኤል ግደይ፣ መቶ አለቃ ቢልልኝ ደሳለኝ ከበረራ ቴክኒሻኑ ጸጋ ብርሃን ግደይ ጋር በጋራ በመሆን የሚያበሩትን ሄሊኮፕተር ይዘው ከጠፉ በሁዋላ በአሁኑ ጊዜ በምልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ የኢሳት ምንጮች ግልጸዋል። ምንጮቹ አብራሪዎቹ ያሉበትን ቦታ ለመግለጽ ፈቃደኛ ባይሆኑም፣ በአሁኑ ጊዜ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙና አስፈላጊው …

ታኀሳስ ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል ያወጣውን ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብሩን ታህሳስ 17 ቀን 2007 ዓ.ም ይፋ ሲያደርግ፣ ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብሩም ለ2 ወራት የሚቆይ እንደሚሆን አስታውቋል። የትብብሩ አመራሮች በሰማያዊ ጽ/ቤት የሰጡትን  መግለጫ ተንተርሶ ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው በሁለተኛ ዙር የትብብሩ መርሃ ግብር መሰረት የካቲት 15 …

ታኀሳስ ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ   ከቀናት በፊት በባህርዳር የተካሄደውንና  ምእመናን የተገደሉበትን የተቃውሞ ሰልፍ – የሚቃወም  ሌላ የግዳጅ ሰልፍ  ሊጠራ መሆኑን የከተማው ነዋሪዎች  ገለጹ። እንደ ምንጮች ገለጻ በግዳጁ ሰልፍ የማይገኝ የባህርዳር ነዋሪ ቅጣት ይጣልበታል ተብሏል። ገዥው ፓርቲ በአማራ ክልል አስተዳደር ባህር ዳር ከተማ የቤተ ክርስቲያን ንብረት የሆነውን የታቦት ማደሪያ ለመንገድና ለጥቃቅንና አነስተኛ …

ታኀሳስ ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ህዳር 11 ቀን 2007 ዓም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በደቡብ ሱዳን በአቤይ ግዛት ተሰማርቶ የነበረው የሰላም አስካባሪ ቡድን አዛዥ ሌ/ጄኔራል ዮሃንስ ገብረመስቀል ተስፋማርያም በእኤአ ጁን 19፣ 2014 ተልእኮዋቸውን ጨርሰው በሜ/ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ገላልቻ መተካታቸውን ቢገልጽም፣ ኢሳት በዜና እወጃው አዛዡ ጊዜያቸውን ሳይጨርሱ መሰናበታቸውን ጠቅሶ ዘግቧል። የዲፕሎማቲክ ምንጮች እንደገለጹት ሌ/ጄኔራል …

ታኀሳስ ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቦርዱ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በየምርጫ ክልሉ ጽሕፈት ቤቶች ከታህሳስ 16 እስከ ጥር 27 ቀን 2007 ዓ.ም ምዝገባ እንደሚካሄድ የሚታወቅ ቢሆንም አንድነትና መኢአድ ፓርቲዎች ከምርጫ ቦርድ ጋር ከገቡት አሰጥ አገባ ጋር ተያዞ በምርጫው የመቀጠላቸው ነገር አጠራጣሪ መሆኑ ታውቆአል፡፡ አንድነት እና መኢአድ በመጪው ምርጫ ለመወዳደር ወስነው የምርጫ ምልክት …

ታኀሳስ ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከፌደራል ፕራይቬታይዜሽንና የመንግስት የልማት ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ተረክቦ ቦታውን ለልማት ለማዋል ዝግጅት የጀመረው የክልሉ የኮንስትራክሺንና ቤቶች ልማት ኤጀንሲ ሆቴሉን ነጻ ለማድረግ ከህዳር 15 ቀን ጀምሮ አገልግሎቱን እንዲያቋርጥ እና በውስጡ ያሉትን የግለሰብ ንብረቶች  ለማስወጣት ያደረገው እንቅስቃሴ ለአንድ ወር ያህል አለመሳካቱን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ኤጀንሲው በቁጥር ኮቤልኤ-ዋሥ/32/1108 በቀን 16/ 03/07ዓ.ም በተጻፈ …

ታኀሳስ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የአየር ሃይል ደህንነቶች ወደ ጠፉት አብራሪዎች ቤት በድንገት በመሄድ ፍተሻዎችን ያካሄዱ ሲሆን፣ በቤቶች ውስጥ የተገኙ ሰነዶችን፣ የበረራ ማኑዋሎችን፣ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን፣ ትጥቆችንና ሌሎችም ቁሳቁሶች ወስደዋል። ከደህንነቶች ጋር ምንም አይነት ፖሊስ ያልነበረ ሲሆን፣ ደህንነቶች ፍተሻውን ለማካሄድም የፍርድ ቤት ማዘዣ አላሳዩም። የመከላከያ ሰራዊት ባወጣው መግለጫ ሁለቱ …

ታኀሳስ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የክልሉ ወኪላችን እንደገለጸችው ማንነቱ በውል ያልታወቀው እንግሊዛዊ ጧት ላይ ባዶ እጁን ወደ ጊዮርጊስ አካባቢ ሲንቀሳቀስ በአንድ የሚሊሺያ አባል ተገድሏል። ገዳዩ መሳሪያ በመያዝ ድብ አንበሳ እየተባለ በሚጠራው ሆቴል አካባቢ ሟቹን ሲጠባበቀው እንደነበር ዘጋቢያችን ያነጋገረቻቸው ሰዎች ገልጸዋል። በሆቴሉ አካባቢ ጫማ በመጥረግ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች  ገዳዩ መሳሪያውን ይዞ ከእነሱ ጋር …

ታኀሳስ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ በሽብርተኝነት ወንጀል የተከሰሱት የሰማያዊ፣ የአንድነትና አረና አመራሮች ከሌሎች 6 ተከሳሽ ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ልደታ በሚገኘው 19ኛው ወንጀል ችሎት ቀርበው በእስር ቤት ውስጥ ስለሚደርስባቸው እንግልትና የደህንነት ስጋት ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አሰምተዋል። የተከሳሾች ቤተሰቦች እስረኞችን ለመጠየቅ በሚሄዱበት ጊዜ በተለየ መዝገብ መመዝገባቸውን በመቃወም ለፍርድ ቤት ባሰሙት …

ታኀሳስ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የደቡብ አፍሪካው መሪ ጃኮብ ዙማ ደቡብ ሱዳናዊያን ለ2 ሚሊዮን ህዝብ መፈናቀል ምክንያት የሆነውን ጦርነት በድርድር እንዲፈቱ ጠይቀዋል። በአዲስ አበባ የሚካሄደው የሰላም ድርድር ውጤት ለማምጣት በተሳነው  በዚህ ወቅት፣ ደቡብ አፍሪካ ተጨማሪ ግፊት እያደረገች ነው። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሁለቱ ተፋላሚ ሃይሎች ችግሮቻቸውን የማይፈቱ ከሆነ ማእቀብ ይጣልባቸዋል ሲሉ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።

ታኀሳስ ፲፬(አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአየር ሃይል ባልደረባ የሆኑት ሻምበል ሳሙኤል ግደይ፣ መቶ አለቃ ቢልልኝ ደሳለኝ ከበረራ ቴክኒሻኑ ጸጋ ብርሃን ግደይ ጋር በጋራ በመሆን የሚያበሩትን ሄሊኮፕተር ይዘው ከጠፉ በሁዋላ የአየር ሃይል አዛዦች አስቸኳይ ግምገማ ከተጠሩ በሁዋላ እርስ በርስ እየተገማገሙና ከእነዚህ ሰዎች ጋር ግንኙነት አላቸው ብለው የሚያስቡትን የአየር ሃይል አባላት ለማሰር እንቅስቃሴ መጀመራቸውን …

ታኀሳስ ፲፬(አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መድረክ ባወጣው መግለጫ  በሀገራችን የምርጫ ሂደት የነበሩ ጉድለቶችንና በተለይም በ2002 የሀገራችን የምርጫ ሂደት የወረደበትን አዘቅት በሚገባ በጥልቀት ገምግሞ እነዚህን ቀደም ባሉት ምርጫዎች የነበሩ ጉድለቶችን ማረምና ማሰተካከል ለ2007 ምርጫ ነፃ፣ ፍትሓዊና ዴሞክራሲያዊ መሆን የምኖረውን ወሳኝ ሚና በግልጽ ቢያስቀምጥም፣ ይህንን እውነታ በአግባቡ መገንዘብ ያልቻሉና ከ1997 እና ከ2002 ምርጫዎች ደካማ …

ታኀሳስ ፲፬(አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ታህሳስ 10 /2007 ዓ.ም ለአምስት ሰዎች ሞትና ለበርካቶች አካል መጉደል ምክንያት በሆነው የተቃውሞ ሰልፍ ዙሪያ የገዢው መንግስት አስቸኳይ  መግለጫ እንዲሰጡ ያስገደዳቸው የኃይማኖት አባቶች በመስቀል አደባባይ ዙሪያ ላይ የቀረበውን ጥያቄ በደስታ እንደተቀበሉት በመግለጫቸው መስጠታቸው እና ምዕመኑን እንደ ጥፋተኛ በመቁጠር ማግለላችው እንዳበሳጫቸው በትላንትናው ዕለት በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ግቢ …

ታኀሳስ ፲፫(አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የአየር ሃይል ምንጮች እንደገለጹት ሰሞኑን ኤም አይ 35 የተባለ የውጊያ ሄሊኮፕተር ይዘው በመጥፋት ወደ አልታወቀ ስፍራ የተጓዙት ሁለቱን አብራሪዎችና አንድ ቴክኒሻንን ለመፈለግ አየር ሃይል በተለያዩ አካበባዎች  አሰሳ ሲያደርግ ቢቆይም በመጨረሻ ፍለጋው እንዲቋረጥ ተደርጓል። ፍለጋው እንዲቋረጥ የተደረገበት ዋና ምክንያት አብራሪዎቹ ሆን ብለው መጥፋታቸውና ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስባቸው …

ታኀሳስ ፲፫(አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘጠኝ የፖለቲካ ድርጅቶችን ያቀፈው ትብብር ባወጣው መግለጫ የባህርዳር ከተማዋ ነዋሪዎች ባዶ እጃቸውን ሆነው በሰላማዊ መንገድ ባሰሙት የተቃውሞ ድምጽ መንግስት የህዝቡን ጥያቄ ለማፈን በወሰደው ዘግናኝና አሰቃቂ በጥይት የታገዘ የኃይል እርምጃ እስካሁን የአምስት ንፁኃን ዜጎች ህይወት መቅጠፉን አስታወሶ፣  ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑ አዛውንት እማሆይንና አካል ጉዳተኛ ጨምሮ በርካቶችን በማቁሰል የአካል …

ታኀሳስ ፲፫(አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ፓርላማ አሸባሪ ብሎ ከፈረጃቸው ድርጅቶች ጋር በቀጥታ እየተገናኙ የሀገራችንን ጥቅምና ሰላም ለማወክ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች አሉ ሲሉ ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ዛሬ በጽ/ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የፓለቲካ ፓርቲ አባላት እየታሰሩ መሆናቸውን አስመልክቶ በቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ አሸባሪ ከሚባሉ ቡድኖች በቀጥታ እየተገናኙና እያቀዱ ሀገር …

ታኀሳስ ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በትላንትናው እለት በባህርዳር ከተማ በተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ የገዢው መንግስት ወታደሮች በህዝቡ ላይ እያደረሱ ያለውን ተመጣጣኝ ያልሆነ  እርምጃ የባህርዳር ከተማ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች በአስቸኳይ እንዲያቆም በሰጡት መግለጫ ጠይቀዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ የሃይማኖት አባቶችን ከሁለት ቀን በፊት በመሰብሰብ በመስቀል አደባባይ ላይ ሊሰሩት ያሰቡትን ጉዳይ እንዳወያዩዋቸው የገለጹት የሃይማኖት አባቶች …

ታኀሳስ ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለምዶ የመስቀል አደባባይ ተብሎ የሚጠራውን የታቦት መውረጃ ቦታ ለግል ባለሃብቶች ለመሸጥ  ታስቧል በሚል ሰሞኑን እንቅስቃሴ በጀመረው የባህርዳር ከተማ አስተዳደር የከተማ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ድርጊት የተቆጡት የከተማዋ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች እና በፖሊስ መካከል በተነሳው ግጭት ከ 3-5 የሚደርሱ ሰዎች መገደላቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያስረዳል፡፡ 27 ሰዎች ታስረው እየተደበደቡ …

ታኀሳስ ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድንገተኛ ተቃውሞው የተካሄደው በመላ አገሪቱ ያለውን የሙስሊም ኢትዮጵያውያን የመብት ጥያቄን በሃይል መቆጣጠራቸውን የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያምንና አዲስ አበባ መስተዳድር የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ ባስታወቁ ሁለት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነው። ዶ/ር ሽፈራው ሙስሊሙ በአደባባይ የሚያደርገውን ተቃውሞ ማቆሙንና ሌላ ስልት መጠቀም መጀመሩን ተናግረው ነበር። ይሁን እንጅ ሙስሊሙ ከዚህ …

ታኀሳስ ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በጅማ ዞን ኤዳ ደሌ ቀበሌ ታዋቂ ቡና ነጋዴ የሆኑት አቶ ነፍሶ ላቫዥ ለዝርፊያ በሄዱ በአራት የፖሊስ አመራሮች ተገድለዋል። አቶ ነፍሶ ጅማ ውስጥ ቡና ነግደው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ መንገድ ላይ አድብተው ይጠብቁዋቸው የነበሩት ፖሊሶች የያዙትን ገንዘብ እንዲሰጧቸው ሲጠይቋቸው ነጋዴው ፈቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረቸው ፣ ሊያጋልጡን ይችላሉ በሚል ተኩሰው …

ታኀሳስ ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ሙክታር ከድር ሰሞኑን ለክልሉ 5ሺ473 ፖሊሶች የሰጡት የማዕረግ ዕድገት መጪውን ምርጫን በመንግስት መዋቅር፣ በጀትና ጊዜ ተጠቅሞ ለማሸነፍ ኢህአዴግ የዘረጋው ስትራቴጂ አካል እንደሆነ ታዛቢዎች ተናገሩ፡፡ መጪው ምርጫ ሊካሄድ አምስት ወራት ብቻ በቀሩት በዚህ ጊዜ የማእረግ እድገት በብዛት መስጠት ለምርጫ ከሚሰጥ የጉቦ ቀብድ ተለይቶ አይታይም ያሉት …

ታኀሳስ ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ነዋሪዎች እንደገለጹት በሰሜንና በደቡብ የአገሪቱ ክፍሎች የነዳጅ እጥረቱ ተባብሶ ቀጥሎአል፡ በአዋሳ ነዳጅ ለመቅዳት መኪኖችና ሞተረኞች ተሰልፈው ሲጠባባቁ ታይቷል። የነዳጅ  ዋጋ በመላው አለም በከፍተኛ ደረጃ  ቢቀንስም በኢትዮጵያ መጥፋቱ ጉዳዩን አነጋጋሪ አድርጎታል።

ታኀሳስ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የውሃ፣ የመስኖና የኢነርጂ ሚኒስትር አለማየሁ ተገኑ ህዳር 26 ቀን 2007፣ በቁጥር ውመአሚ 1/01/67 በጻፉት ደብዳቤ ” በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች በከፍተኛ ወጪ ተገንብተው ለበርካታ ኢንተርፕራይዞች የመስሪያና መሸጫ አገልግሎት የሚውሉ ህንጻዎችና ሼዶች በኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ችግር ምክንያት ለታለመላቸው አላማ ለማዋል ” አልተቻለም ብለዋል። “በእነዚህ ማእከላት ውስጥም በከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ የገቡና …

ታኀሳስ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው  የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን ጨምሮ 10ሩም ተከሳሾች የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ 19ኛው ወንጀል ምድብ ችሎት  ቤት ቢቀርቡም ሌላ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች የሆኑት አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና አቶ …