ዓለም በኤቦላ ስጋት መታመስ ሲጀምር በቀድሞዋ ዛየር በዛሬዋ ዴሞክራቲክ ሬፐብሊክ ኮንጎ ተኅዋሲውን ያገኙት የቤልጅየም ተወላጁ ፕሮፌሰር ፒተር ፒዮ መታወስ ጀመሩ።ፕሮፌሰሩ በአሁኑ ወቅት የለንደን የግል ንጽህናና የምድር ወገብ አካባቢ በሽታዎች ትምህርት ቤትን በሃላፊነት ይመራሉ።

ዋይ ! ዋይ ! (በሙሾ ዜማ ይውጡት) ንዋይ ዋይ! ዋይ! ንዋይ ንዋይ ሞተ አሉ በቁሙ ንዋይ ሞተ አሉ በቁሙ ጨለመችበት ዓለሙ (2) ንዋይ በንቁላል ተመታ ንዋይ በንቁላል ተመታ ሊዘፍን መጥቶ በማታ (2፟) ዋይ! ዋይ! ንዋይ ዋይ! ዋይ! ንዋይ ምን ይላት ይሆን ለሚስቱ ምን ይላት ይሆን ለሚስቱ በንቁላል ገምቶ ደረቱ (2) ጀግናው ፈረሰ ለሆዱ ጀግናው ፈረሰ […]

በቅድሚያ መጽሓፉን ጊዜ ሰጥተህ በማንበብ አስደማሚ ምልከታ በመስጠትህ ከልብ አመሰግናለሁ ። የተጻፈበትም አንዱ አላማ ይህ ስለሆነ። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በእይታህ ላይ እነዚህ ጉድለት ይታይባቸዋል ብለህ ያነሳኸው እና የወደፊት ግምቶችህ ላይ የተወሰነ አስተያየት ለመስጠት የሚጋብዙ ስለሆነ ትንሽ ማለት ፈለኩ። በዚህ አጋጣሚ ሌሎች በመጵሀፉ ይዘት ላይ ዝርዝር ግምገማ ላደረጉ ሰዎች ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። ለእያንዳንዱ አስተያየት መስጠት ከጊዜ አኳያ በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ የማልዘልቅበትን መንገድ ልጀምረው አልፈለኩም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተመስገን ደሳለኝ

በዚህ ተጠየቅ ጨርፈን የምንመለከተው በኮሙኑዮኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ የነበረውና ዛሬ በስደት የሚገኘው የአቶ ኤርሚያስ ለገሰን “የመለስ ትሩፋቶች፣ ባለቤት አልባ ከተማ” የተሰኘው መጽሐፍን ነው፡፡ የመድብሉ ጻሐፊ ኤርሚያስን በግል አላውቀውም፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በአካል ያየሁት አቶ በረከት ስምዖን እርሱን እና ሽመልስ ከማልን ምክትሎቹ አድርጐ በሚኒስቴር ዲኤታ ማዕረግ መሾሙን በግዮን ሆቴል ለጋዜጠኞች ይፋ ባደረገበት ዝግጅት ላይ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

“ዩናይትድ ስቴትስ የራሷን ጥቅሞች ለማስጠበቅ ወደ ኋላ እንደማትል ሁሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተመሰረተበትና ያለበትን ዓላማም ከማክበርም አታፈገፍግም፤” የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ።

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

መስከረም ፲፬(አሥራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን የአብዮታዊ ዲሞክራሲ የትምህርት መመሪያን ለማጥመቅ ያወጣውን መመሪያ ተከትሎ በአገሪቱ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ስልጠናውን በግዳጅ እንዲወስዱ እየተደረጉ ነው። በአንዳንድ አካባቢዎች ተማሪዎቹ የፖለቲካ ስልጠና እንዳለ አስቀድመው በመስማታቸው ፣ ከስልጠናውን የቀሩ ሲሆን፣ የገዢው ፓርቲ የወረዳ ሹሞች መምህራን ተማሪዎችን እንዲያመጡ የተለያዩ ዘዴዎችን እንዲጠቀሙ እያግባቡ ነው። አንድ …

መስከረም ፲፬(አሥራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብአዴን ንብረት በሆነው ጥረት ኮርፖሬት ውስጥ የሚገኙት ጣና ሞባይል ና ዘለቀ እርሻ ልማት ድርጅቶች በያዝነው አመት ከ225 ሚልዩን ብር በላይ ኪሳራ እንዳጋጠማቸው በ2007 ዓም መግቢያ ላይ በተደረገው የድርጅቱ ግምገማ ላይ ተገልጧል። አቶ አለምነው መኮንን የአማራውን ህዝብ መሳደባቸውን ተከትሎ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ አመራሮችን ለማሳመን የተደረጉ ስብሰባዎች ና የተሃድሶ …

መስከረም ፲፬(አሥራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመላ አገሪቱ ከ40 ሚሊዮን በላይ መጻፍና ማንበብ የማይችሉ ወጣት እና ጎልማሶች አሉ ያሉት አቶ ሺፈራው ፤  ይህንን የትምህርት እድል ያለገኙ ወጣቶች እና ጎልማሶች አማራጭ ትምህርት እንዲያገኙ የተደረገው ሙከራ አፈፃጸሙ ከዜሮ በታች ነው ብለዋል። በኢህአዴግ የእቅድ ትውውቅ መድረክ ላይ እንደቀረበው በጎልማሶች የትምህርት አቀራረብ  አማራ 0.9፣ ኦሮምያ ፣ 0.71 …

መስከረም ፲፬(አሥራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዋጋ ንረትን ያረጋጋሉ ተብሎ በመንግሥት ልዩ ድጋፍ በተለይ በአዲስአበባ ከተማ የተቋቋሙት የሸማቾች የህብረት ሥራ ማህበራት በሙስናና ብልሹ አሠራር ውስጥ በመዘፈቅ አንዳንዶቹ በተቃራኒው የዋጋ ንረትን የሚያባብሱ ሥራዎች ውስጥ መሰማራታቸው መረጋገጡን ከአስተዳደሩ የተገኘ ሰነድ ጠቆመ፡፡ 250ሺ ያህል አባላት ያሉዋቸው 153 መሰረታዊ ማህበራትና 10 ዩኒየኖች እንዲሁም 1 ሺ 815 አዲስ …

ዓለም በኤቦላ ስጋት መታመስ ሲጀምር በቀድሞዋ ዛየር በዛሬዋ ዴሞክራቲክ ሬፐብሊክ ኮንጎ ተኅዋሲውን ያገኙት የቤልጅየም ተወላጁ ፕሮፌሰር ፒተር ፒዮ መታወስ ጀመሩ።ፕሮፌሰሩ በአሁኑ ወቅት የለንደን የግል ንጽህናና የምድር ወገብ አካባቢ በሽታዎች ትምህርት ቤትን በሃላፊነት ይመራሉ።

Jennifer Hudson ሶስትኛዋ የሆንውን የእስቱዲዮ አልበሟን በገበያ ላይ አወላለቸ ፡፡ የአልበሙ መጠሪያ JHUD የተባለ ሲሆን በወስጡ 10 ዜማዎችን አካቷል በዛሬው የሙዚቃ ቃና ፕሮግራም ከዚሁ አዲስ አልበም የተመረጡ ዜማዎችን እና ሰለሞን ክፍሌ ስለ Frank Sinatra ያዘጋጀው ፕሮግራም ትካቷል፡፡

የስዊድን የሕግ ባለሞያዎች በስብዕና ላይ ወንጀል ፈፅመዋል ባሉዋቸው ከፍተኛ የኤርትራ ባለሥልጣናት ላይ ክስ እንዲመሠረት ያቀረቡበትን ጥያቄ የስዊድን ዓቃቤ ሕግ ውድቅ ካደረገባቸው በኋላ ይግባኝ ማመልከቻ አስገብተው መልሳቸውን በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።

በሶርያ እና በኢራቅ የሚንቀሳቀሱትን የ«አይ ኤስ» ተዋጊዎች የሚቀላቀሉት አውሮጳውያን ቁጥር ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ በአንድ ሶስተኛ መጨመሩን የአውሮጳ ኅብረት የፀረ ሽብርተኝነት ክፍል አስታወቀ።

በተወለዱ 28 ቀናት ጨቅላዎች ለሞት የሚዳረጉበት ምክንያት ከነፍሰጡር እናት ጤንነትና አመጋገብ ጋር በቀጥታ የተገናኘ ነው። የእርግዝና ክትትልና በወሊድ ወቅትና ከወሊድ በኋላ እንክብካቤ በማድረግ በተወለዱ እስከ 28 ቀናት ውስጥ የሚሞቱ ህጻናትን ቁጥር መቀነስ ይቻላል።

መስከረም ፲፫(አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጄኔቫ ሲካሄድ በሰነበተው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ግምገማ ላይ አቋሙን ያስታወቀው አለማቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ኢትዮጵያ የሰአብአዊ መብት ድንጋጌዎችን እንደምታከብር ቃል መግባት ብቻ ሳይሆን፣ በተጨባጭ ገለልተኛ ወገኖች እስር ቤቶችን እንዲገበኙ፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት የሚካሄዱባቸውን ቦታዎች እንዲጎበኙና በደል የደረሰባቸውን ወገኖች ለማነጋገር እንዲፈቀድላቸው ጠይቋል። የሰብአዊ …

መስከረም ፲፫(አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው በተመራው ስብሰባ ላይ ዳኞች የስርአቲ ደጋፊ እንዲሆኑ እየተገደዱ ባለበት ሁኔታ እንዴት ነጻ ዳኝነት ሊሰጥ ይችላል በማለት ጠይቀዋል። የድርጅት አባላት ያልሆኑ ዳኞችም ስራቸውን ለመስራት እየተቸገሩ መምጣታቸውን መናገራቸውን ጋዜጣው ዘግቧል። ይሄው በመላው አገሪቱ በሚደረገው የፖለቲካ ስልጠና የገዢው ፓርቲ ደጋፊ አባላት ሳይቀሩ በስርአቱ ላይ …

መስከረም ፲፫(አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ስራ በሚገኘው ደጀና አቬሺን ውስጥ የሚሰራ ስሙ በውል ያልታወቀ አንድ ወታደር በግቢው ውስጥ ለሚሰሩ  ሰራተኞች  በተከፈተው ሻሂ ቤት ውስጥ በአስተናጋጅነት የምትሰራዋን በደብረዘይት ነዋሪ የሆነች ወጣት በስድስት ጥይቶች ተኩሶ መግደሉን የአይን እማኞች ገለጹ። ትናንት 11 ሰአት ላይ ሰራተኞች ሰርቪስ አውቶቡስ ለመያዝ በተሰለፉበት ወቅት፣ ወታደሩ በአስራዎች …

መስከረም ፲፫(አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከደቡብ ሱዳን ታፍነው የተወሰዱት የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ በእስር ቤት ውስጥ ከሌላ እስረኛ ጋር ተጋጭተዋል በሚል ሰበብ ከፍተኛ ድብደባ ከደረሰባቸው በሁዋላ ጸሃይ ላይ ለረጅም ሰአት እንዲቀመጡ ተደርገዋል። አቶ ኦኬሎ ድብደባው የተፈጸመባቸው ቂልንጦ እየተባለ በሚጠራው  እስር ቤት ውስጥ ሲሆን፣ በእስር ቤት ሃላፊዎች መረጃ እንዲያቀርብ ተብሎ …

መስከረም ፲፫(አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መግለጫ 130 የሚሆኑ የቻይና ኩባንያዎች ለአፍሪካ መሪዎች በእስር ቤት ጥቅም ላይ የሚሆኑ የማሰቃያ መሳሪያዎችን ይሸጣሉ። የኤልክትሪክ ንዝረት ያላቸው   ከብረት የተሰሩ ሹል ዱላዎችና ሌሎችም  የማሰቃያ መሳሪያዎች ለአፍሪካ እና ለእስያ አገራት መሸጣቸው በአህጉራቱ ውስጥ የሚታየውን ሰብአዊ መብት እረገጣ አባብሶታል። በአለም ላይ ስለት ያላቸውን የንዝረት ብረቶችን የምታመርተው …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

በተወለዱ 28 ቀናት ጨቅላዎች ለሞት የሚዳረጉበት ምክንያት ከነፍሰጡር እናት ጤንነትና አመጋገብ ጋር በቀጥታ የተገናኘ ነው። የእርግዝና ክትትልና በወሊድ ወቅትና ከወሊድ በኋላ እንክብካቤ በማድረግ በተወለዱ እስከ 28 ቀናት ውስጥ የሚሞቱ ህጻናትን ቁጥር መቀነስ ይቻላል።

ሐይማኖት አለሙ በተዋኝነት፤በአዘጋጅነትና በፀፌ ተዉኔትነት በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ዉጪ በተለይ ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ በበርካታ ድራማዎች ተሳትፏል። ሐይማኖት በተለያዩ ቲያትሮች በሥራ-አስኪያጅነትና በአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲም በመምሕርነት ያገለገለ የጥበበብ ሰዉ ነበር። 68 ዓመቱ ነበር።

የጀርመን መከላከያ ሚኒስትር ኦዙላ ፎንዴር ላይን፤ የኤቦላ ተዋኅሲ ስርጭትን ለመግታት በሚደረገዉ ጥረት ለመካፈል በፈቃደኝነት ወደ ምዕራብ አፍሪቃ ለሚሄዱ ወታደሮችን እና ሲቪል ሰራተኞች ትናንት ጥሪ አደረጉ።

ከፊል ሰነዓን ባመሰቃቀለዉ ዉጊያ 350 ሐምሳ ያክል ሰዎች ተገድለዋል።በሺሕ የሚቆጠሩትን ከቤት ንብረታቸዉ አፈነቃሏል።ሁለቱ አማፂያንና የሐገሪቱ መንግሥት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሸምጋይነት ተኩስ ለማቆም ከተስማሙ ካለፈዉ ዕሁድ ወዲሕ ግን ከተማይቱ ተረጋግታለች።

ትክክለኛ የቋሚና አላቂ ንብረት ምዝገባና አስተዳደር፣ ተቀባይነት ያለውና እምነት የሚጣልበት የገንዘብ ገቢና ወጪ እንቅስቃሴ፣ ግልጽና ወጥነት ያለው የግዥ አፈጻጸም፣ ብቁ የቁጥጥር ሥርዐት ባለመዘርጋቱ የቤተ ክርስቲያናችን ጥቅል ሀብት አይታወቅም፡፡ በማንኛውም ሕጋዊና ዘመናዊ የሒሳብ ምርመራ አሠራር እጅግ ኋላ ቀር በኾነው በነጠላ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ እና በሞዴላሞዴሎች አሠራር የቤተ ክርስቲያንን ገንዘብ እና ንብረት ከብኩንነት፣ ከመዘረፍ እና ከመጭበርበር ለማዳን …

መስከረም ፲፪(አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምዕራብ አርማጮሆ ወረዳ የአብርሃጅራ ነዋሪዎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በተደረገው ህዝባዊ ስብሰባ በመሬት ስሪት ፣በልማት ና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ ቅሬታወች ቀርበዋል፡፡በውይይቱ ላይ በመገኘት ቅሬታቸውን ያቀረቡት ነዋሪዎቹ “የወረዳው አመራሮች እርስ በርስ በመሻኮት ስልጣን ለመያዝ ሰዎችን ያስገድላሉ የበላይ አመራሮችን የኑሮ ሁኔታ በማጥናት ቤት ሰርተዋል፣ሃብት አከማችተዋል በማለት እነርሱም የበላይ አለቆቻቸውን …

መስከረም ፲፪(አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ባወጣው መግለጫ ፍትህ ሚኒስቴር ሃምሌ 28፣ ቀን 2006 ዓም በፋክት፣ ሎሚ፣ ጃኖ፣ አዲስ ጉዳይ፣ እንቁ መጽሄቶችና አፍሮ ታይምስ ጋዜጣ ላይ ያቀረበው ክስ በህገመንግስቱ የሰፈረውን ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት ፣  ኢትዮጵያ በፈረመቻቸው የሰብአዊ መብቶች አለማቀፍ መግለጫ አንቀጽ 19 ፣ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች አለማቀፍ ቃልኪዳን አንቀጽ 19 …

መስከረም ፲፪(አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ገዢው ፓርቲ ለመጪው ምርጫ በሚያደርገው ዝግጀቱ የመንግስት ሰራተኞችን፣ መመህራንና ተማሪዎችን በማስገደድ የሚሰጠው የፖለቲካ ስልጠና እንደቀጠለ ሲሆን፣ ባሳለፍነው ሳምንትም በርካታ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጥያቄዎች ተነስተዋል። በአዲስ አበባ በኢትዮ-ቻይና ቲቪቲ በነበረው ስልጠና ላይ ” ከ23 አመታት በሁዋላ አሁንም እራሳችሁን ከደርግ ጋር እያነጻጸራችሁ ነው? ደርግ ከሻእቢያ፣ ከእናንተ ጋርና ከሶማሊያ ጋር ጦርነት …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የ85 ሰዎች ገቢ ከግማሽ ከሚበልጠዉ የዓለም ሕዝብ ይበልጣል።—የዓመዓቱ ግብ ያልተሳካዉ በፖለቲካዊ ዳተኝነት፤ በዕዉቀት እጦት ብቻ አይደለም።በጥቅም ሽኩቻ እና ዕቅዱ የሐብት ክፍፍል የሚያነሳ በመሆኑም ጭምር እንጂ

የአፍጋኒስታኑ የቀድሞ የገንዘብ ሚኒስትር አሽራፍ ጋኒና የቀድሞዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዱላህ አብዱላህ ምንም እንኳን ሁለቱ ተፎካካሪዎች ስለምርጫዉ ዉጤትና ስለወደፊት የስልጣን ክፍፍል ሲወዛገቡ ቢቆዩም በመጨረሻ የብሔራዊ አንድነት መንግሥት ለመመስረት ተስማምተዋል። ይህ ለአፍጋኒስታን የስልጣን ፉክክር መጨረሻ ይሆን ይሆን?

ከአምስት ወራት ገደማ በፊት የተመረቀው የአዳማ አዲስ አበባ የፍጥነት መንገድ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ አንድ ሳምንት ሆነው። አዲሱ መንገድ የባለአሽከርካሪዎችን ጊዜ መቆጠብ ማስቻሉንተገልጋዮች በደስታ ገልጸዋል።

ደራሲ – እንዳለ ጌታ ከበደ

ዋጋ – 49 ብር

አታሚ – ኤች ዋይ ማተሚያ ቤት

እንዳለ ጌታ የጻፈውን እምቢታ መጽሐፍ ከአዲስ አበባ ወደ አውስትራልያ እየተጓዝኩ አውሮፕላን ውስጥ ነው ያነበብኩት፡፡ መጽሐፉ ለገበያ ሲቀርብ እንደማልኖር ስላወቀ ቀድሜ እንዳገኘው በማድረጉ አመሰግነዋለሁ፡፡ ይኼ በታሪክና በሥነ ቃል(ፎክሎር) ላይ የተመሠረተ ልቦለድ በአንዲት ብዙዎቻችን በማናውቃት ከዘመን የቀደመች ሴት ጀግና ላይ የሚያጠነጥን ነው፡፡

ቃቄ ወርድወት ትባላለች፡፡ በነገራችን ላይ ቃቄ የአባቷ ስም ነው፡፡ የእርሷ ስም ወርድወት ነው፡፡ በጉራጌ ባሕል የአባትን ስም ከልጅ የሚያስቀድም ጥንታዊ ሥርዓት ነበረ ማለት ነው፡፡ ምናልባትም በዕውቀቱ ስዩም ‹በኢትዮጵያ ከልጅ ስም በፊት የአባት እንደሚቀድም ማስረጃ አለኝ› ያለው አንዱ ይኼንን ሳይሆን አይቀርም ብዬ ገምቻለሁ፡፡ የመጽሐፉን ረቂቅ መመልከቱን መግቢያው ላይ ያሳያልና፡፡

ቃቄ ወርድወት በ1840ዎቹ አካባቢ ከጉራጌ ማኅበረሰብ የፈነጠቀች ኢትዮጵያዊት ኮከብ ነበረች፡፡ በሴቶች ላይ የነበረውን አድሏዊ ልማዳዊ ሥርዓት ለመታገል፣ በጋብቻ ሥርዓት ወንዶቹ ከሴቶቹ ይልቅ ሥልጣን ለማደላደል፤ ሴቶች ከለፉበት ትዳራቸው ያለ አንዳች ንብረት በፍቺ መባረራቸውን ለማስቀረት የታገለች ጀግና፡፡ ዛሬ እንኳን ለብዙ ኢትዮጵያውያን ሴቶች አስቸጋሪ የሆነውን ‹ሴት ልጅ ተመርጣ ብቻ ሳይሆን መርጣም ማግባት አለባት› የሚለውን ሐሳብ ይዛ የታገለች፤ ታግላም በራሷ ላይ የፈጸመች ጀግና ሴት ናት፡፡

በዚያ የሴቶች መብት፣ የጾታ እኩልነት የሚሉ ዘመናዊ ሐሳቦች ባልዳበሩበት፤ ለሴቶች መብት ቆመናል የሚሉ ተቋማት ባልነበሩበት ዘመን ከዘመኗ ቀድማ ችግሩን የተረዳች፤ የሴቶችን ችግር ለመቅረፍና እናቶቻችን ፍትሕ እንዲያገኙ ለማድረግ በጉራጌ ማኅበረሰብ ባሕል ከፍተኛው ሸንጎ እስከሆነው ኧጆካ አደባባይ ድረስ የተሟገተች ጀግና ናት፡፡

እንዳለ ጌታ የዚህችን የማናውቃትን ጀግናችንን የተጋድሎ ታሪክ ከልዩ ልዩ ምንጮች ሰብስቦ፣ ሥነ ቃሉን አስማምቶ፣ ከሀገራችን ታሪካዊ መዛግብት ጋር አዋሕዶ በልቦለድ መልክ አቅርቦልናል፡፡ ወጥ ልቦለዶች እያነሡ፣ የትርጉም ሥራዎች ቦታችንን እየወሰዱ ባሉበት ዘመን የራሳችንን ታሪክ መልሰን እንድናይ የሚያደርግ እንዲህ ያለውን ሥራ ማግኘት ለሥነ ጽሑፋችን አንድ እመርታ ነው፡፡

ሰው የሚያውቀውን ሲያቀርብ፣ የሚያቀርበውንም ሲያውቅ ደስ ይላል፡፡ የኖረበትን፣ የተሠራበትንና የተዋሐደውን ነገር ሲተርክ ከውስጡ ስለሚመነጭ ከዛፍ ሥር የሚመነጭን ውኃ እንደመጠጣት ይቆጠራል፡፡ አንድን ማኅበረሰብ በዕንግዳ ዓይን ማየት ተለምዶ የሚመስሉትን ነገሮች በሚገባ ለማንጠር ይረዳል፡፡ የውስጡ ሰው ለምዶት የሚያልፈውን ዕንግዳ ሰው ትኩረት ይሰጠዋል፡፡ አንድን ማኅበረሰብ በውስጥ ሰው ማየት ደግሞ የሚያውቁትን፣ የኖሩበትንና ትርጉሙንም በሚገባ የሚያውቁትን ነገር እንደ ልብ ምት አዳምጦ ለማቅረብ ይረዳል፡፡ የቃቄ ወርድወት ታሪክ እንዲህ ሆኖ ነው የቀረበው፡፡ ማኅበረሰቡ የተሰፋበትን እያንዳንዷን ሰበዝ ታዩበታላችሁ፡፤ ያውም ሳይታወቃችሁ፡፡

የእንዳለ ጌታ መጽሐፍም የኖረበትንና ያጠናውን ማኅበረሰብ ያቀረበበት ስለሆነ ሁለት መቶ ዓመታትን ተሻግራችሁ ትነጉዱና ከቃቄ ወርድወት ጋር ለመብት ትታገላላችሁ፣ ጉራጌ ገብታችሁ ደመራ ታበራላችሁ፣ መስቀል ታከብራላችሁ፣ ክትፎ ትበላላችሁ፣ ከነገሥታቱና መኳንንቱ ጋር ትዋጋላችሁ፡፡ ኧጆካ ትወጣላችሁ፣ ጀፎረ ላይ ትቀመጣላችሁ፡፡

በጉራጌ ማኅበረሰብና በማዕከላዊው መንግሥት መካከል፣ በጉራጌ ማኅበረሰብና በሌሎች የአካባቢው ማኅበረሰቦች መካከል ፍቅርም፣ ጠብም፣ ጦርነትም፣ ዕርቅም ነበረ፡፡ እነዚህ ግንኙነቶች በማኅበረሰብ ውስጥ የሚፈጥሩትን አሉታዊና አዎንታዊ ነገሮች በእንዳለ ጌታ ዓይን ስናያቸው አንድን ታላቅ ማኅበረሰብ በመፍጠር ሂደት ውስጥ የተከናወኑ የሂደቱ መገለጫዎች እንጂ የቂም መቋጠሪያዎች ሆነው አናገኛቸውም፡፡ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ በሚገኙ ልጆች መካከል የሚኖር መጣላትና መዋደድ የልጆቹ የዕድገታቸው ሂደት አካል እንደሚሆነው ማለት ነው፡፡

በየአካባቢው የሚገኘውና የማናውቀው ታሪካችንና ባሕላችን እንዲህ ለነገዋ ሀገራችን መቀመሚያ በሚሆን፣ ያለፈውንም ለማወቂያና ለማረሚያ በሚያገለግል፣ በሌላ በኩል ደግሞ አቃፊ እንጂ አግላይ ባልሆነ መንገድ ቢቀርብልን የአንዱ አካባቢ ታሪክ የሁላችንም እየሆነ ‹የኢትዮጵያ› ስንል የሚጎድለን አይኖርም ነበር፡፡ አሁን አሁን ግን ‹የኢትዮጵያ› ስንል የሚጎድሉን ነገሮች አሉ፡፡ አንድም አንዳንዶች ‹የኼማ የራሳችን ብቻ ነው› ብለው ቆርጠው በማስቀረታቸው፣ አንድም ደግሞ ‹የኢትዮጵያ› የተባለው ነገር አንዳንዶችን አግልሎ በማስቀረቱ፡፡ ሁለቱም ግን እኩል ነው የሚጎዱት፡፡ የጉራጌ ክትፎ የሁላችንም እንደሆነው ሁሉ የየአካባቢው ሥነ ቃል፣ ታሪክ፣ ባሕልና ቅርስ እየወጣ የሁላችንም እየሆነ መሄድና ወደ ዋናው አካል እየተቀለቀለ፣ ለዋናው አካል ግንባታም አስተዋጽዖ እያደረገ መሄድ አለበት፡፡ ማግለልም መገለልም አንድ ናቸው፡፡

የአካባቢውን ሥነ ቃል፣ ታሪክና ባሕል ከምናገኝባቸውና የራሳችን ከምናደርግባቸው መንገዶች አንዱ ኪነ ጥበባዊ በሆነ መንገድ ማግኘታችን ነው፡፡ ‹የእገሌ ብሔረሰብ ታሪክና ባሕል› እየተባሉ ብቻ የሚወጡ፣ ሲጀምሩ ሌላውን አውግዘው፣ ኮንነውና ጠልተው የሚነሡ ‹መጻሕፍት› አጥሩን በአደገኛ አጥር ከማጠናከር ያለፈ ፋይዳ አይኖራቸውም፡፡ ቁስሉን ማሳየት እንጂ ማሻርም አይፈልጉም፡፡ ምናልባትም የጉዳዩ ባለቤት ነኝ ብሎ ከሚያስበው አካል በቀር የሌላውን ልብ ለመማረክም አይችሉም፡፡ ጎጣዊ ጀግና ከመፍጠር ባለፈ ሀገራዊ ጀግና አያስገኙም፡፡ በላይ ዘለቀን የጎጃም፣ ዐፄ ዮሐንስን የትግሬ፣ ቃቄ ወርድወትን የጉራጌ ብቻ አድርገው ለማስቀረት የሚያልሙ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያዊ ጀግና፣ ሀገራዊ ታሪክ፣ ሀገራዊም ማንነት ሊፈጠር የሚችለው እንዲህ የአንዱ አካባቢ ታሪክ የሌላው እንዲሆን አድርጎ በማቅረብና ለታሪኩና ሥነ ቃሉ ብቻ ሳይሆን ለአቀራረቡም ጭምር በመጨነቅ ነው፡፡ ‹ሲያዩት ያላመረ ሲበሉት ያቅራል› ይባል የለ፡፡ የእንዳለ ጌታን መጽሐፍ አንብቡት የምላችሁም ለዚህ ነው፡፡ በሞቴ አንብቡት፡፡  

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

መግቢያ

ለአዘማሪ ሙያ ተስማሚ የግብር መግለጫ መሆን ያለበት የቱ ነው? አዘማሪ ወይስ አርቲስት? በሚል በአቶ ዓለም ነጻነት ሬድዮ የቀረበው ውይይት ለዚህች ጦማር መነሻ ሆኖኛል። ከቀደሙ አባቶች እንደሰማሁት አዘማሪ ብቻውን የቆመ አይደለም። ከብዙ ነገሮች ጋራ ከቅኔያችን፣ ከዜማችንና ከስሜታችን ጋራ የተያያዘ ነው። አዘማሪ የሚለውን ቃል ከነዚህ ነጥሎ ለማቅረብ መሞከር ያዘማሪን ክብርና ቦታ ዝቅ ያደርገዋል የሚል ስጋት አለኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ …