ቫቲካን እና የአዛውንቱ ኢትዮጵያዊ አርበኛ ጥያቄ
ሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተጀመረበት 75 ኛ ዓመት ከጥቂት ጊዚያት በፊት መታሰቡ የሚታወስ ነው። ይሁንና፣ ኢትዮጵያውያን የታሪክ ምሁራን ፣ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተጀመረው ፋሺስት ኢጣልያ የዓለም መንግሥታት
ሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተጀመረበት 75 ኛ ዓመት ከጥቂት ጊዚያት በፊት መታሰቡ የሚታወስ ነው። ይሁንና፣ ኢትዮጵያውያን የታሪክ ምሁራን ፣ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተጀመረው ፋሺስት ኢጣልያ የዓለም መንግሥታት
መስከረም ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ አብዲ ሙሃመድ 7 የስራ አስፈጻሚ የኮሚቴ አባላትን ማበረራቸውን ተከትሎ ወደ አዲስ አበባ በአስቸኳይ እንዲመጡ ቢታዘዙም፣ የቀረበላቸውን ጥሪ ባለመቀበል ጅጅጋ ውስጥ እንደሚገኙ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ምንጮች ተናግረዋል። ለአቶ አብዲ ቅርበት ያላቸው የመከላከያ ባለስልጣኖች በተደጋጋሚ ስልኮችን በመደወል አቶ አብዲን ለማግባባት እየሞከሩ ሲሆን አቶ አብዲ በበኩላቸው ” ኢትዮጵያ ውስጥ 30 …
መስከረም ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ለሁለተኛ ዙር እየተካሄደ ያለው የኢህአዴግ ስልጠና በአንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች በአለመግባባት ሲቀጥል፣ በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ ተማሪዎች በመሰላቸት ውይይቶችን እንደማይከታተሉ ከተሳታፊዎች የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። የተለያዩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ውይይቱ አሰልቺ በመሆኑ አብዛኛው ተማሪ የግሉን ስራ እንደሚሰራና ውይይቱን እንደማይከታተል ገልጸዋል። ለመምህራን በሚሰጠው ስልጠና ደግሞ በአንዳንድ የማሰልጠኛ ቦታዎች መምህራን ሃሳብ …
መስከረም ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በማዕከላዊ ምርመራ ታስሮ የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ የሽዋስ አሰፋ የአራት ቀን የርሃብ አድማ ማድረጉን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። አቶ የሸዋስ ከጳጉሜ 4 ጀምሮ አዲሱን አመት በርሃብ አድማ ያሳለፈ ሲሆን ቅዳሜ መስከረም 3/2007 ዓ.ም ምግብ እንደቀመሰ ባለቤቱ ወይዘሮ ሙሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጻለች፡፡ አቶ የሽዋስ የርሃብ አድማ …
መስከረም ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሶስት ሳምንት በፊት ለአጭር ቀን ስልጠና ወደ አሜሪካ ለመብረር ዝግጅታቸውን ጨርሰው ቦሌ አየር ማረፊያ የተገኙት ምክትል ከንቲባው፣ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ በሚል ከአገር እንዳይወጡ ተደርጓል። ዋናው ከንቲባና አንድ ባለሙያ ስልጠናውን ተካፍለው መመለሳቸው ታውቋል። ምክትል ከንቲባው የእስልምና እምነት ተከታይ እና በኦነግ አባልነት እንደሚጠረጠሩ ምንጮች ገልጸዋል። በከንቲባውና በምክትሉ መካከል የተፈጠረው ልዩነት …
መስከረም ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሁለት አመት በኦሮምያና በሶማሊ ክልሎች የድንበር ከተሞች የተነሳውን ግጭት መርተዋል የተባሉና ቁጥራቸው በውል ላልታወቀ ዜጎች ሞትና ለንብረት መውደም ምክንያት ሆነዋል የተባሉ የሞያሌ ወረዳ አስተዳዳሪን ጨምሮ ሌሎች 29 ሰዎች እስከ 19 አመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል። 21 ተከሳሾች በሌሉበት ሲወሰንባቸው የሞያሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጉዩ ዋርየን በ14 …
የአንድነት ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው፣ በአንድነት ራዲዮ ቀርበው፣ በሚሰጡት አመራር ዙሪያ እየተነሱ ያሉ በርካታ ቅሬታዎችን በተመለከተ፣ ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል። ኢንጂነሩ የሚሊዮኖች ንቅናቄ ለጊዜው የተቋረጠው፣ ከመኢአድ ጋር የዉህደት እንቅስቃሴ ስለነበረና ክረምት በመሆኑ እንደሆነ ጠቅሰው፣ የተቋረጠው እንቅስቃሴ እንደሚቀጥል አሳስበዋል። ለሚሊዮኖች ንቅናቄ የመሬት ባለቤትነት ዘመቻ የተሰበሰበው ገንዘብም ለተሰበሰበበት አላማ እንደሚዉል፣ ሰላማዊ ሰልፎች ባልተደረጉ ቦታዎች እንደሚደረጉም አረጋግጠዋል። ከሰባት […]
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
በእስር ላይ የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የሽዋስ አሰፋ የርሃብ አድማ አደረገ ።
የሽዋስ አሰፋ በርሃብ አድማው ምክንያት ሰውነቱ እንደተዳከመ ባለቤቱ ገልጻለች፡፡
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
በማዕከላዊ ምርመራ ታስሮ የሚገኘውና የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነው አቶ የሽዋስ አሰፋ የአራት ቀን የርሃብ አድማ አደረገ፡፡ የሸዋስ ማክሰኞ ጱግሜ 4 ጀምሮ አዲሱን አመት በርሃብ አድማ ያሳለፈ ሲሆን ቅዳሜ መስከረም 3/2007 ዓ.ም ምግብ እንደቀመሰ ባለቤቱ ወይዘሮ ሙሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጻለች፡፡ አቶ የሽዋስ የርሃብ አድማ ያደረገው ከታሰረበት ሐምሌ 1/2006 ዓ.ም ጀምሮ ከጠበቃው ጋር ከአንድ ጊዜ በላይ መገናኘት ባለመቻሉና ዘመድ አዝናድ እንዲሁም የኃይማኖት አባት እንዳይጎበኘው በመከልከሉ ነው፡፡ የሽዋስ አሰፋ በባለቤቱ ብቻ ከሳምንት አንድ ቀን እንዲጎበኝ የተፈቀደለት ሲሆን የርሃብ አድማ ባደረገባቸው ቀናት ባለቤቱ ምግብ ስታስገባ ለየሸዋስ ምግቡ እንደደረሰው ተደርጎ ባዶ ሳህን ሲደርሳት ቆይቷል፡፡
ባለቤቱ የበዓል ቀን ልትጎበኘው በሄደችበት ወቅት ‹‹ወጥቷል›› ተብላ የተመለሰች ሲሆን በማግስቱ ልጆቹን ይዛ ልትጠይቅ ስትሄድም ‹‹ስብሰባ ላይ ናቸው!›› በሚል እንዳታገኘው በመደረጓ ለ15 ቀናት ሳትጠይቀው ቆይታለች፡፡ አቶ የሽዋስ ‹‹የርሃብ አድማውን ያደረኩት ቤተሰብና ጠበቃዬ እንዳይጠይቁኝ በመከልከላቸው ነው፡፡ ለምን እንዲጠይቁኝ አይደረግም? ብዬ ጥያቄ ሳቀርብ ማንም አልመጣም፡፡ ቢመጣ እንድትጠየቅ እናደርግ ነበር፡፡›› የሚል መልስ እንደሚሰጡት ገልጾአል፡፡
በሌላ በኩል ጠበቃው ተማም አባ ቡልጉ የሽዋስን ለማግኘት በተደጋጋሚ ወደ ማዕከላዊ አቅንቶ የተለያየ ምክንያትና መሰናክል እየፈጠሩ ሳያገናኙት እንደቀሩ ገልጾአል፡፡ ጠበቃ ተማም ‹‹ለበርካታ ቀናት አመላልሰውኛል፡፡ ለምሳሌ አንድ ቀን ረቡዕ ጠዋት ሄድኩኝ፡፡ መብትን መለመን ጥሩ ባይሆንም እንዲያገናኙኝ ብለምናቸውም ሊያገናኙኝ አልቻሉም፡፡ ከሰዓት እንድመለስ ነግረውኝ ከሰዓት ብሄድም አሁንም ሊያገናኙኝ አልቻሉም፡፡ ለቀጣይ ረቡዕ ቀጠሩኝ፡፡ አሁንም ረቡዕ ስሄድ የተለያየ ምክንያት እየፈጠሩ ሊያገናኙኝ አልቻሉም፡፡ እንዲያውም ‹‹ምን ታመጣለህ አናገናኝህም!›› አሉኝ፡፡ ብዙ ጥረት ባደርግም ሊያገናኙን አልቻሉም፡፡ የሚገርመው የዳንኤልና የሃብታሙ ጠበቃ የሆኑ ሌሎች ጓደኞች አሉኝ፡፡ አንድ ሰው ከአንድ ጠበቃ በላይ ሊኖረው እንደሚችል እየታወቀና እኔም ደንበኞቼን ማግኘት እንዳልችል ከልክለውኝ እነሱን ግን ‹‹እኛ የምናውቀው ተማምን ነው›› ይሏቸዋል፡፡ እኔ ስሄድ ደግሞ ደንበኞቼን እንዳላገኝ እደረጋለሁ፡፡›› ሲሉ ሁኔታውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
የሽዋስ ምግብ ሲገባለት ምግቡን የሚያደርሱለት አካላት መልሰው ለሚስቱ እንዲሰጧት ይነግራቸው እንደነበር የተናገረ ሲሆን የርሃብ አድማ ላይ እንደሆነ እንዳይታወቅ ምግቡን የበላ አስመስለው እቃውን ባዶ አድርገው መመለሳቸው አሳፋሪና ቅጥ ያጣ አፋኝነት መሆኑን መግለጹ ታውቋል፡፡ የሽዋስ አሰፋ በርሃብ አድማው ምክንያት ሰውነቱ እንደተዳከመ ባለቤቱ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጻለች፡፡
ቴዲ አፍሮ በሆላንድ ባቀረበው ኮንሰርት ላይ በመድረክ ያቀነቀነው አዲስ ዘፈን
ቀስተ ደመናው ላይ አንበሳው ከሌለ
የኢትዮጵያ ባንዲራ ትርጉሙ የታለ፥
ምድሪቱ አረንጋዴ ‘ላዩ ሰማያዊ
ተባብሮ ከሰራ ያድጋል ኢትዮጵያዊ፥
ሣባና ሰሎሞን እናትና አባቴ
አትማልዷትም ወይ ለኢትዮጵያ እናቴ፥
ምን ይላል ምኒሊክ ካሳ ቴዎድሮስ
የአንድነቱ ጎጆ በዘር ሲታመስ፥
ምን ይላል ምኒሊክ ካሳ ቴዎድሮስ
ምን ይላል ዮሐንስ ተፈሪ ቴዎድሮስ
የተዋለደ ሰው በዘር ሲታመስ ::
– የዩንቨርስቲው ስልጠና በግሩፕ እንዲደረግ ቢሞከርም ከፍተኛ አለመግባባት በመፈጠሩ ተበትኗል።
– ሽመልስ ከማል ከለገሃር ሙልሙል ጫት ቤት ተጠርቶ አለቃ ጸጋይ ፊት በመቅረብ ማስጠንቀቂያ ተሰቶታል።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
ለአንድ ሳምንት ያህል ሊሰጥ የታሰበው እና ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች መምህራን የተጀመረው የወያኔ የልማታዊ ዲሞክራሲ ስልጠና ገን ክጅምሩ ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠመው ከተለያዩ መምህራን የተሰበሰቡ መረጃዎች ጠቁመዋል። ገና ስልጠናው ከመጀመሩ መምህራኑ መንግስት ያለብንን ችግር እና የሃገሪቱም ሁኔታ ማገናዘብ እና መፍታት ካልቻለ የስራ ማቆም አድማ እናደርጋለን ሲሉ በጭብጫባ የታጀበ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። ይህ የግዳጅ ስልጠና በተለያዩ አደራሾች የተጀመረ ሲሆን መምህራኑ እንዳሉት የውይይቱ የመግቢያ ሰነድ ተረስቶ በሃገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ እና በመምህራን ሕይወት ዙሪያ ከባድ የሆነ ንትርክ ተገጥሞ ለወያኔ አሰልጣኞች ከባድ ጋሬጣ ሆነው እንደነበር መምህራኑ ክላኩት መልእክት ለማወቅ ተችሏል። የመምህራኑ ስልጠና በነገው እለትም የሚቀጥል ሲሆን ለወያኔ የእግር እሳት እንደሚሆኑ ይጠበቃል።ምንሊክ ሳልሳዊ
በዛሬው እለት ጠዋት በሽመልስ ከማል ሲመራ የነበረው እና የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የኢንዱስትሪ ካምፓስ ተማሪዎች የግዳጅ ስልጠና በጩኸት ቢበተንም ሽመልስ ከማል ደንግጦ ከስብሰባ አደራሹ በመውጣት ተደብቆ የጠፋ እና ወደ ተለመደው የጫት ሱስ ተግባሩ የሄደ መሆኑን ሁኒታውን ሲከታተሉ የነበሩ እና አብረውት በአስተባባሪነት እና በተባባሪ አሰልጣኝነት የተመደቡ ካድሬዎች ጠቁመዋል። ለአለቆቹ ሪፖርት ሳያደርግ ወደ ጫት ቤት ያቀናው ሽመልስ ከማል በአስቸኳይ የስልክ ጥሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ካለው የአለቃ ጸጋይ ቢሮ ተጠርቶ በመሄድ ከስልጠናው ጋር በተያያዝ ከፍተኛ የሆነ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ሲሆን ከቢሮው ሲወጣ ፊቱ ተለዋውጦ እና ደንግጦ እንደነበር አስተባባሪዎቹ እና ተባባሪ አሰልጣኞቹ ከሰጡኝ መረጃ ለማወቅ ችያለው።
የስልጠናው አስተባባሪዎች ስልጠናውን ለመቀጠል አቶ ሽመልስ ከማልን ትተውት ወደ አ አ ዩ ኢንዱስትሪ ካምፓስ ቢደርሱም ተማሪው ከተባለበት ሰአት ሁለት ሰአታት ያህል በመዘግየት ከቀኑ 9 ሰአት ላይ በየግሩፑ ቢመጣም የግሩፕ ስልጠና አስተባባሪ እና አሰልጣኝ ካድሬዎች ተማሪውን በፍጹም ሊያሳምኑት ያልቻሉ ሲሆን ተማሬው አቴንዳስ ሲደረግ የታደለውን ኖትቡክ እና ቢክ እስክርቢቶ እንዳልተጠቀመበት ታውቛል።ብዚህ ስልጠና ላይ ተዋት ተማሪው በጩኸት እና በፉጨት ስለረበሸ የውሃ እና የሻይ አቅርቦት ተከልክሏል።ምንሊክ ሳልሳዊ
የከሰአት በኋላ ስልጠና በግሩፕ የተከፋፈለ ሲሆን ይህንን ያደረጉት ተማሪው በጋራ ሆኖ ተቃውሞ እንዳያሰማ እና በግሩፑ ተቃውሞ ቢኖር እንኳን በቀላሉ መቆጣጠር እንዲቻል ተማሪው ጎን ለጎን እንዳያወራ አራርቆ በማስቀመጥ
ተማሪው እርስ በ እርስ እንዳይደጋገፍ ለማድረግ ነው። አሰልጣኞቹ ካድሬዎች ስልጠናውን በተማሪው መሰላቸት በመደናበራቸው 9 ሰአት ስልጠናውን ጀምረው ወዲያው ተማሪው ጥያቄ ካለው ብለው ጥያቄ እንዲጠይቅ ሲያደርጉ ከተጠየቁ ጥያቄዎች መካከል ስልጠናው ጥቅም የለውም?፣ አላማው ምንድነው?፣የቀድሞ ስራቶችን ክፋት ብቻ ለምን ታወራላችሁ ?፣ ራሳችሁን በ21ኛው ክፍለዘመን ለምን ከኋላቀር የቀድሞ ንጉሳውያን አስተዳደር ጋር ትመዝናላችሁ፡? ከናንተ በፊት መንግስታት እንጂ የሚበድሉት በህዝብ መካከል ፍቅር እና የሃይማኖት መቻቻል ነበር ይህን አምናቹሃል አሁን የት ገባ?፤ ወደ ኋላ እየተመለስን ከምናላዝን ለምን አሁን ባሉት እና ወደፊት በሚኖሩት አስቸጋሪ ፈተናዎች እና ጉዳዮች ላይ አናተኩርም ? ወዘተ የሚሉ ጥያቂዎች ቢነሱም ምላሾቻቸው የማያረኩ የተድብሰበሱ እና የሚያደናግሩ ነበሩ ። እንዲሁም በነገው እለት በነጻ ፕሬስ በጋዜጠኞች እና በመንግስት መካከል ስላለው ሁኔታ ለመወያየት ቀጠሮ ተይዞ ስልጠናው በተማሪው መሰላቸት እና ጉርምርምታ 9 ሰአት ጀምሮ 10.30 ተበትኗል።
ህወሓት ብአዴንም፣ ኦህዴድም፣ ኢህአዴግም ሆኖ ሁሉም የሚጠይቀውን ጥያቄ ይመልሳል፡፡
አዛዡም ናዛዡም ህወሓት ነው:: Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
ከአመታት በፊት የገዥው ፓርቲ አባል ሳይሆን በመንግስት ስራ ላይ ተሰማርቶ ይሰራ ነበር፡፡ 1997 ዓ.ም በኋላ ግን በዚህ አቋሙ አልቀጠለም፡፡ ‹‹አንዴ ቅንጅት ሌላ ጊዜ ደግሞ ኦነግ እያሉ ስም ሲለጥፉብኝ ‹ከዚህ ሁሉ!› ብየ ኦህዴድን ተቀላቀልኩ›› ይላል ካድሬው ለነገረ ኢትዮጵያ፡፡ ከዚህ በኋላ ባሉት ጊዜያት ደመወዝና እድገት በእጥፍ ተጨምሮለታል፡፡ የትምህርት እድል ተሰጥቶታል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ኦህዴድም ሆነ ኢህአዴግ ህዝብ ላይ የሚፈጽሙትን በደል በቅርብ ርቀት ተገኝቶ ተከታትሏል፡፡
ካድሬው እንደሚለው ከእነ አባዱላና መሰል ፖለቲከኞች ውጭ የኦህዴድ ካድሬዎች በፓርቲያቸው እምነት የላቸውም፣ በህወሓት በደል በእጅጉ ተማርረዋል፡፡ የ‹‹ብአዴኖችም ከእኛ የሚለይ ነገር የለውም፡፡ ተመሳሳይ ነው፡፡›› ይላል ካድሬው፡፡
በበርካታ ጉዳዮች ‹‹ፓርቲዬ›› ከሚለው ኢህአዴግ እንደሚለይ ቢገልጽም በአንድ ጉዳይ ግን ይስማማማል፡፡ ‹‹ጥያቄ የሚያቀርብ ካድሬ አንድም ኦነግ አሊያም የድሮው ቅንጅት አካል የነበረ ፓርቲ ወይንም ትምክተኛ ተብሎ ስም ይሰጠዋል፡፡ ኦነግ ወይንም ‹‹ቅንጅትነት/ትምክተኝነት›› ጥያቄ ማንሳት ከሆነ የኦህዴድ ካድሬዎች ሲገለጡ ኦነጎች ናቸው፡፡ ብአዴኖቹ ደግሞ እንደዛው ቅንጅት/ትምክተኛ ናቸው ማለት ነው››፡፡ በዚህ ጉዳይ ካድሬው የድሮው ጠቅላይ ሚኒስትር ‹‹ኦህዴድ ሲገለጥ ኦነግ ነው!›› በሚለው ይስማማል፡፡
ካድሬው ለነገረ ኢትዮጵያ እንደገለጸው በተለይ የብአዴንና የኦህዴድ ካድሬዎች በህወሓት ጫና ከመቼውም በላይ ተማርረዋል፡፡ ‹‹አዛዡም ናዛዡም ህወሓት ነው፡፡ ትጠይቃለህ፡፡ ስም ይሰጥሃል፡፡›› የሚለው የኦህዴድ ካድሬ፤ የኦህዴድና የብአዴን ካድሬዎችም ሆነ ባለስልጣናት ይህ ነው የሚባል ተጽዕኖ እንደሌላቸው ከተሞክሮው ይመሰክራል፡፡ ‹‹ብአዴንና ኦህዴድ ይጠይቃሉ፡፡ ህወሓት ይመልሳል፡፡ የብአዴንና የኦህዴድ ባለስልጣናት ካድሬዎቹ የሚጠይቋቸውን ጥያቄዎች እንኳን በራሳቸው መመለስ አልቻሉም፡፡ ህወሓት ብአዴንም፣ ኦህዴድም፣ ኢህአዴግም ሆኖ ሁሉም የሚጠይቀውን ጥያቄ ይመልሳል፡፡ እንዲያው እድል ተሰጥቷቸው የሁለቱ ፓርቲዎች ፖለቲከኞች ቢመልሱ እንኳ የህወሓት ተራ ካድሬም ቢሆን የሆነ ነገር ያስተካክላል፡፡ ኦህዴድና ብአዴን ብቁ አለመሆናቸውን ለማሳየት የሚያደርገው ነው፡፡››
ካድሬውን ‹‹ኢህአዴግን ምን የሚያሰጋው ይመስልሃል?›› በሚል ከነገረ ኢትዮጵያ ለቀረበለት ጥያቄም የመጀመሪያው ያደረገው ፓርቲው ውስጥ ያለውን ክፍፍል ነው፡፡ ‹‹አብዛኛው የኢህአዴግ ካድሬ እንደ እኔ ፓርቲው ያደርስብኛል ካለው አደጋ ለመዳን አሊያም ለገንዘብ የተቀላቀለ ነው፡፡ አያምንበትም፡፡ ሁሉም ቀን ነው የሚጠብቀው፡፡ ወደ ህዝብ ሲቀርቡ በመካከላቸው ችግር እንደሌለ ያስመስላሉ እንጅ የኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች በመካከላቸው ከፍተኛ ቅራኔ አለ፡፡ ለምሳሌ ያህል በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ የተወሰደው እርምጃ የኦህዴድ ካድሬዎችን አስቆጥቷል፡፡ እስካሁን ይመለስላቸው አይመለስላቸው ባላውቅም በወቅቱ እነ አባዱላ ፓስፖርታቸውን እንደተቀሙ ሰምቻለሁ፡፡ ይህ አንድ ቀን የሚፈነዳ ይመስለኛል፡፡››
ሌላው ይላል ካድሬው ‹‹ህዝብ በፓርቲው እምነት እንደሌለው ሁላችንም እናውቃለን፡፡ ህዝብ ገንፍሎ የሚወጣ ይመስለኛል፡፡ በእርግጥ አሁን ህዝቡ ዝምታን መርጧል፡፡ በተለያዩ ጊዜያት ህዝብን ለማሳመን ወይንም ለማስተማር በሄድኩበት አጋጣሚ ከዝምታው በስተጀርባ ህዝብ ለፓርቲው ጥላቻ እንዳለው ለማየት ችያለሁ፡፡ በቅርቡ በተለያዩ የኦሮሚያ ዩኒቨርሲቲዎች ስልጠና የተሰጣቸው ተማሪዎች ሰነዱን አቃጥለው ስለ ነጻነት ዘምረዋል፣ ፓርቲው አብጠልጥለዋል፡፡ ይህ ሁሉ ሲደማመር አንድ ቀን ህዝብ ገንፍሎ የሚወጣ ይመስለኛል››
ባለፉት ሶስት ቀናት ከአፍሪቃ እና ከመካከለኛዉ ምሥራቅ ወደ አዉሮጳ ለመግባት ያቀዱ ቁጥራቸዉ ወደ 800 የሚጠጉ ተገን ጠያቂዎች ሜደተራንያን ባህር ሰጥመዉ ለህልፈት መዳረጋቸዉ ኢጣልያ ሮማ የሚገኘዉ ሀገራት አቀፍ የስደተኞች ድርጅት እንዲሁም የተመ የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ ይፋ ያደረጉት መግለጫ ያመለክታል።
ዜና 16.09.2014
ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ መንግሥት አልባ ሆና የቆየችዉ ሶማልያ፤ ዓለም አቀፍ እዉቅና ያለዉ መንግሥት ከመሰረተች ገና ሁለት ዓመትዋ ነዉ።
በበጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመዥንገር ዞን ጎደሬ ወረዳ ግጭት ተቀሰቀሰ።በግጭቱ የሞቱና ለስደት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርን ለማወቅ ፖሊስ ምርመራ እያካሄደ ነው።
በዛሬው የሙዚቃ ቃና ፕሮግራም የተመረጡ ዜማዎችን አና ሄኖክ ሰማ አግዜር ስለ Beyonce Knowels ያዘጋጀው አጠር ያል ዘገባ ተካትዋል።
የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በመጀመሪያው ተቃውሞ ካድሬዎች እርስ በእርስ ተጣሉ:: ዛሬ በተጀመረው የመምህራን ስልጠና አዲሱ የትግል ስልታችን ተግባራዊ ሆኖ ውጤቱን ከመጀመሪያው መታዘብ ችለናል:: ትላንት ከየኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ በተላለፈው የትግል ስልት አንድ መሰረት በቦሌ ክፍለ ከተማ ቦሌ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተሰበሰቡ መምህራን ምንም አይነት አስተያየት ከመስጠት በመቆጠባቸው ምክንያት […]
የአንድነት ፓርቲ ያለፈው አመት፣ የሚሊዮኖች ንቅናቄ በሚል መርህ በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች ሰላማዊ ሰልፎችን እንዳደረገ ይታወሳል። በየክልሉ ጠንካራ የአንድነት መዋቅሮች ተዘርግተዋል። በሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት እንዲሁም በሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት እንቅስቃሴዎች፣ ሁለት ጊዜ በደሴ፣ በባህር ዳር፣ በአዲስ አበባና በአዳማ/ናዝሬት፣ አንድ ጊዜ በጊዶሌ/ደራሼ ፣ በአርብ ምንጭ፣ በፍቼ፣ በጎንደር፣ በጂንካና በወላይታ ሶዶ ሰልፎች ተደርገዋል። በተጠሩት ሰልፎች ሕዝቡ ታላቅ ኢትዮጵያዊ […]
የዞንና የወረዳ አስተዳዳሪዎች ከነቤተሰቦቻቸው ተገደሉ በጋምቤላ ዞን በጎደሬ ወረዳ ነጋዴዎችና ሰፋሪዎች ከአካባቢው ተወላጅ የመዠንገር ጎሳ አባላት ጋር ተጋጩ። በግጭቱ ከ17 ሰባት በላይ ሰዎች ተገድለዋል። በግጭቱ የመዠንገር ዞን አስተዳዳሪና የጎደሬ ወረዳ ዳኛ ከነቤተሰቦቻቸው የግጭቱ ሰለባ መሆናቸው ታውቋል። ግጭቱን ለማብረድ የመከላከያ ሠራዊት የገባ ሲሆን፣ የጋምቤላ ክልል ልዩ ኃይል ግጭቱን ለማብረድ በጉዞ ላይ እንዳለ በተሰጠ መመሪያ እንዲመለስ ተደርጓል። […]
የዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ወደ ኤርትራ የሚደረግ ጉዞ ለአሜሪካ ዜጎች አደገኛ መሆኑን አስጠነቀቀ።
የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች ከኤርትራ መንግሥት የመውጫ ቪዛ ላያገኙ ስለሚችሉ ወደ ዚያች አገር ከመሄድ መታቀብ እንዳለባቸው ሚንስቴሩ በመግለጫው አስጠንቅቋል።
የኤርትራ መንግሥት የውጪ አገር ዜጎች በአገር ውስጥ በሚያደርጓቸው ጉዞዎች ላይ ገደብ መጣል መቀጠሉን መግለጫው አመልክቶ፤ እገዳውም ማንኛውም ነዋሪና አገር ጎብኚ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማቶችንም ጨምሮ፤ ከአሥመራ ከ25 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ለመውጣት ከፈለጉ ከአሥር ቀናት በፊት እንዲያመለክቱ የሚጠየቁ መሆናቸውን ገልጿል።
በአብዛኛው ፈቃድ የሚያስፈልገውም የቱሪስት መስህብ ለሆኑት ምፅዋና ከረን መሆኑም ታውቋል። ይሁንና ወደ ድንበር ቀረብ ያሉ ሌሎች አካባቢዎች እና ከዚህ ቀደም ዲፕሎማቶች…
ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ፣ ሕግ መንግስቱን በጣሰና የከፍተኛ ተቋማት ገለልተኛነትን በመጋፋት፣ ተቋማት የሚጠበቅባቸውን የሞያ ስልጠና ከመስጠት አልፈው ተራ የፕሮፖጋንዳ መንዢያ ቦታዎች እንዲሆኑ በማድረግ፣ የፖለቲክ ስልጠና በሚል፣ የተለያዩ ስብሰባዎችን በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች እየጠራ መሆኑ ይታወቃል። በስብሰባዎቹ ተማሪዎች ለባለስልጣናቱ የተለያዩ ጥያቄዎች በመጠየቅ፣ ስልጠናዎቹ እንደታሰበው አለመሄዳቸው በስፋት ተዘግቧል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተደረገው ስብሰባ፣ አገዛዙን ወክለው የመጡት አቶ ሬድዋን ሁሴን […]
«ቃልኪዳናችን ለቀጣዩ ትግላችን» በሚል መሪ መፈክር የአንድነት የወጣቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ መስከረም 11 ቀን 2007 ዓ.ም ከ9 ሰዓት ጀምሮ እስከ 12.00 ሰዓት የሚቆይ ልዩ ዝግጅት አጠናቆ ይገኛል፡፡ በዚህ ልዩ ስነስርዓት የህሊና እስረኞችን በማስመልከት የአደባባይ የሻማ ማብራት ዝግጅት እንደሚከናውን ቀደም ባሉት ቀናቶች በወጣቶቹ የተገለፀ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡ ይሄንን አስመልክቶ የከተማው ነዋሪዎች እና ደጋፊዎች በስፋት የሚታደሙበት እና […]
መስከረም ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ2007ዓ.ም ለሚደረገው ሃገራዊና ክልላዊ ምርጫ ህብረተሰቡ ለተለያዩ ተቀናቃኝ ፓርቲዎች ድምፁን እንዳይሰጥ ለማፈን በሚያስችል ሁኔታ በክልሉ የሚገኙ ሚሊሻዎች ልዩ ተልዕኮ እንደተሰጣቸው ተገለጸ የአማራ ብሄራዊ ክልል መንግስት ሚሊሽያ ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ መኳንንት መልካሙ ሰሞኑን ለታማኝ አመራሮች በሰጡት ድርጅታዊ መግለጫ ላይ በያዝነው ዓመት በሚካሄደው ምርጫ ህዝቡ የተለያየ ፅንፍ በመያዝ …
መስከረም ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሁለት ሳምንት በፊት በጠ/ሚንስትር ጽ/ቤት የሶማሊ ክልል መሪዎች፣ የደህንነት ሃላፊዎችና በክልሉ የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች በተገኙበት በተደረገው ግምገማ በፕሬዚዳንቱ አብዲ ሙሃመድ ላይ በርካታ ወንጀሎች ተዘርዝረው ከቀረቡ በሁዋላ ፣ ፕሬዚዳንቱን ከስልጣን ለማውረድ በሚፈልጉት የደህንነት ሹሙ አቶ ጌታቸው አሰፋና በክልሉ የመከላከያ ሹም ጄኔራል አብርሃ መካከል አለመግባባት ተፈጥሯል። ውሳኔ ለመስጠት የተቸገሩት …
መስከረም ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ጳጉሜ ወር የመከላከያ ሰራዊትን ጥለው የጠፉ ወታደሮች ለኢሳት እንደገለጹት፣ በጠጠናቀቀው አመት በርካታ ወታደሮች እየለቀቁ የተቃዋሚ ድርጀቶችን ከመልቀቅ ባሻገር ወደ ማሃል አገር እየሄዱ ኑሮአቸውን እየመሩ ነው። የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤት ትወስዳለህ ተብሎ ያለፍለጎቱ መከላከያን የተቀላቀለና ባለፈው ሳምንት መስሪያ ቤቱን በመልቀቅ የግል ኑሮውን ለመምራት የፈለገ ወታደር እርሱ በነበረበት የሁመራ …
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
ሊቢያ ጠረፍ አቅራቢያ እንደገና በሚያሰቅቅ ሁኔታ 250 ያህል ስደተኞች ሳይሰጥሙ እንዳልቀሩ ተነገረ። ከሊቢያ ባህር ኃይል በኩል እንደተገለጠው ከሆነ 250 ያህል አፍሪቃውያን ስደተኞችን ያሣፈረ ጀልባ ሰጥሟል። እስካሁን የ26 ሰዎችን ሕይወት ማትረፍ ተችሏል። የባህር ኃይሉ ቃልአቀባይ እንዳለው፣ የብዙ ሰዎች አስከሬን ባህር ላይ ሲንሳፈፍ ታይቷል።
የኩዌት የሀገር አስተዳደር ሚኒስቴር ኢትዮጵያውያን የኮንትራት የቤት ሰራተኞችን ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ ጥብቅ እገዳ መጣሉን ከኩዌት ዶሃ የሚሰራጩ መረጃዎች ይጥቁማሉ። ከዛሬ አንድ አመት ከመንፈቅ በፊት የሳውዲ አረቢያ መንግስት
የተመድ በመካከለኛዉ አፍሪቃ ሬፐብሊክ ዛሬ መስከረም 5 ቀን ይፋዊ ተልዕኮን ይጀምራል። በመካከለኛዉ አፍሪቃ ሬፐብሊክ ሰላም ለማምጣትና ሀገሪቱን የሚያስተዳድር መንግሥት ለመመስረት እንዲያስችል፤ የመንግሥታቱ ድርጅት ተልእኮ ለስድስት ወር ይዘልቃል መባሉ አያጠያያቂ ሆንዋል።
የአውሮጳ ሀገራት የአንደኛ ምድብ የእግር ኳስ ከለቦች ግጥሚያ፣ በሞሮኮ ማራኬሽ 2,9 ሚልዮን ዩኤስ ዶላር ለሽልማት የቀረበበት የክፍላተ ዓለም የአትሌቲክስ ውድድር፣ የአፍሪቃ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ዓመታዊ ስብሰባ በአዲስ አበባ እና የቅርጫት ኳስ በዛሬው የስፖርት ጥንቅር ተካተዋል።
በስዊድን ትናንት እሁድ በተካሄደዉ የምክር ቤት ምርጫ አዲስ የአስተዳደር ለወጥ የሚደረግበት ዉጤት ተመዘገበ። የስካንዲኒቪያዋን ሀገር ስዊድንን የሚያስተዳድር የነበረዉ የወግ አጥባቂዉ እና የለዘብተኛዉ ጥምር መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ፍሪድሪክ ራይንፌልድ ከስምንት ዓመት ሥልጣን በኋላ በምርጫዉ ተሸንፈዋል።
ብዙ ወራት ያስቆጠረው የዩክሬይን ውዝግብ አሁንም ገና እልባት አልተገኘለትም። ይኸው በምሥራቃዊ ዩክሬይን የቀጠለው ውዝግብ እንዲባባስ የምታደርግ ሩስያ ናት በሚል የሚወቅሰው እና የሚከሰው የአውሮጳ ኅብረት ከጥቂት
(ይህ ጽሑፍ የተጻፈው ግንቦት ውስጥ 2006 ዓ.ም ነው፤ ትቼው ከርሜ ሳበቃ አሁን ምን በል እንዳለኝ አላውቅም ደግሜ ቃኘሁትና ላክሁት፡፡) “እሳቸው በመጡና ድንጋይ በበሉ” አለች አሉ አንዷ የዳግም ዘማች ባለቤትና የቤት ሙሉ ልጆች እናት፡፡ በደርግ ጊዜ ነው፤ ወጣት-ሽማግሌ ባሏ ለዳግመኛ ሀገራዊ ወታደራዊ ግዳጅ ተጠርተው ሄደዋል፡፡ “አባታችን ናፈቀን” የሚሉ ብዙ ልጆች አሏት፡፡ ከልጆቿ ጋር የሚኖሩት በድህነትና በጠባብ […]
ከእምቢበል ወገኔ ሰሞኑን በተለያዩ በውጭ በሚገኙ የኢትዮጵያውያን የዜና ማሰራጫዎች፣ ድረገጾች፣ ብሎጎች፣ ፓልቶኮች፣ የማሕበራዊ መረብ መገናኛዎችና ሌሎችም ላይ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ የቆየው ጉዳይ ኤርትራ ውስጥ ይገኛሉ በተባሉ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች ላይ ሻቢያ ስለሚፈጽማቸው ወንጀሎችና አሻጥሮች እንዲሁም ግንቦት 7 ያለተደረገውን ተደረገ፤ ያልተፈጸመውን …
ካለፈው ነኀሴ 22 ጀምሮ ተቋርጦ የቆየው በተለያዩ የደቡብ ሱዳን ወገኖች መካከል ይካሄዳል የተባለ ድርድር ሰኞ – መስከረም 5/2007 ዓ.ም ባሕርዳር ላይ ይጀመራል ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡
SOUTH SUDAN, NEGOTIATIONS, Bahir Dar
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
ጊዜ ይከንፋል ፣ ትውልድ ያልፋል ፣ ትውልድ ይተካል። ሁሉም ሰው በዝች ዓለም በጤና፣ በሰላም፣ በተድላና ፍስሐ መኖር ይፈልጋል። ለራሱና ለሀገሩ ለሚገኝበት ማሕበረሰብ ፣ በጎ ነገር ፣ ሰላምና ብልጽግና ይመኛል። ምኞት አይከለከልምና ሰው ብዙ ሊመኝ ይችላል። እርግጥ የሚሣካና የማይሣካ የምኞት ዓይነት ይኖራል።
«አይ ኤስ» የተባለው አክራሪ ታጣቂ ቡድን ዳግም አንድ ምዕራባዊ ምርኮኛን ገድሎ ጭካኔ የተሞላበት ድርጊቱን በኢንተርኔት ይፋ ማድረጉ ተገለፀ።
የአዲስ አበባ አንድነት ወጣቶች ኮሚቴ፣ በአዲስ አበባ ለመስከረም 11 ቀን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ እየተዘጋጀ እንደሆነ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል። እንቅስቃሴው በዋናነት ፣ የአዲስ አበባን ህዝብ ለታሰሩ የፖለቲካ መሪዎች፣ ብሎገሮች፣ ጋዜጠኞች፣የሰባአዊ መብት ተሟጋቾች …ሶሊዳሪቲዉን በማሳየትና ሻማ በማብራት እስረኞች በማሰብ ላይ ያተኮረ እንደሚሆን አዘጋጆቹ ለአቡጊዳ ገልጸዋል። የአንድነት ፓርቲ ከዚህ በፊት የሚያደርጋቸው የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓቶች፣ በጽ/ቤት ብቻ እንደነበረ፣ የገለጽት […]
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ጀሀዲስቶችን ለማጥቃት ያወጡት እቅድ እና በሶማልያ ጽንፈኞች የተገደሉት አንድ የደህንነት ባለስልጣን